fa
Feedback
ግጥም

ግጥም

رفتن به کانال در Telegram

በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor

نمایش بیشتر
4 828
مشترکین
+824 ساعت
+657 روز
+21630 روز
آرشیو پست ها
የዝምታ ቅኔን መፍታት ሲሳናቸው ዝም ያለ ፈሪ ነው ማለት ቀለላቸው ከብዙ ዋይታ ከልፍ አላፍ ጋጋታ ብቻውን ያስፈራል ቅኔ ነው ዝምታ።

ዛሬ አንዷን አናድጃት ምን ብትለኝ ጥሩ ነው ፡ እስኪ ቂጤን አቀብለኝ የምትል ሚስት ይስጥህ አላለችኝም እግዞ

ማዘር👵ምጣድ ልትገዛ ሄዳ 2500 ብር ሲሏት . . ምንድነው አንዱን ጋግሬ ሌላውን Copy ነው እንዴ ማደርገው?🤔። አይ ማዘሯ 💋❤️

ቀልድ ያስፈልጋል?

አንገቴ ጎንበስ በል ይለፍ ይኼ ግዜ ለሁሉም መልስ አለው ለዛሬው ትካዜ ነገ ሌላ ቀን ነው ዛሬን አይወክልም ሀዘን መከራውም በዚህ አይቀጥልም ቅዝምዝሙ ይለፍ ገንበስ ልበልና ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ነውና

#ሸማኔ_የለንም ጥበበኛ ጠፍቶ በጥበበኛ ሀገር አስማምቶ አሻጋሪ በእውነተኛ ፍቅር ፈታይ ሳይቸግረን ድርና ማግ ሞልቶ ሸማኔ የለንም ሀገር ሰሪ አስማምቶ

ሰላም 🕊

#አልተኛም_ከእንግዲህ በህልም ዓለም መጥተሽ በሁኔ ከማጣሽ አትምጪ ልንገርሽ ድሮም ስቃዬ ነሽ ስተኛ አይሻለለሁ ስነቃ አጣሻለሁ አንቺ የጠዋት ጤዛ መጥተሽ መሄድ በዛ በህልሜ እየመጣሽ መንገዴን ከምስት አልተኛም ከእንግዲህ አንቺን ላለማየት። ♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

ቤተሰብ ዛሬ የፍቅር ግጥም ይለቀቅ?

በመንጋ በመንጋ ሆናችሁ ስትሄዱ አደራ በሞቴ እኔን አትውሰዱ። የጅምላ ፍረጃ ወንዝ ላያሻግር ህልሜን ልኑርበት እያልኩ ሀገር ሀገር።

👋

ይነጋል ያልነው ቀን መልሶ ጨለመ ይሻለዋል ያልነው ይብሱን ታመመ ማንጋጠጥ ይሻላል ለሰማዩ ጌታ የምድሩስ ተክኗል በውሸት እስክስታ ሀገር ታማ ታማ መድሀኒቷ ጠፍቶ እህ እህ ነው ዛሬም ሁሉም ሰው ተከፍቶ ♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

ቤተሰብ ናፍቃችሁኛል እንዴት ናችሁ?

ከሀይማኖት በላይ እምነት ስጠኝና ጌታዬ ሰው ልሁን ልነሳ እንደገና። የስናፍጭ ታህል ቅንጣት እምነት ቢኖር ተራራው መከራ በተናደ ነበር። ♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

ተናገር ጎዳናው ተናገር መንገዱ እየረመረሙህ ስንቶች በአንተ ሄዱ? ♡ ㅤ     ❍ㅤ         ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢʰᵃʳᵉ

የፍትሕ ሚዛኑ በገንዘብ ተለካ በብሔር ተፈጭቶ በዘር ዛር ተቦካ ከንግዲህስ ደሃ ፍርድ የለም ዘንድሮ ብትለምደው ይሻላል ተበድለህ ኑሮ

አላችሁ?

"#እኔም_ልቤን_ልስጥሽ" ከልብሽ ከሆነ በፍቅር ተመርጠሽ እኔነቴን እንኪ እራሴንም ልስጥሽ ለንዋይ ከሆነ ለገንዘብ አምልኮ ልብሽ ልብ ሳይል በጥቅም ተማርኮ ከእኔ ድሃ ጎጆ ከእኔ ምስኪን መንደር ገንዘብን አምልኮ አይኖርም መከበር ልብ እንጂ ቀለቡ ፍቅር እንጂ መጠጡ ዙፋኑን አይለቅም በጥቅም ለመጡ!!! ቀለቡ ፍቅር ነው ያሳደገኝ መንደር አንቺ ትብሽ አንተ ሰክኖ መነጋገር ስለዚህ ልንገርሽ ቢገባሽ ባይገባሽ ፍቅርን ይዘሽ ግቢ እኔም ልቤን ልስጥሽ

የፍቅር ግጥም ይለቀቅ የምትሉ ❤️ ንኩ

❤️ዙፋኑ ልብ ነው❤️ ልብ ካልታሰረ በፍቅር ሰንሰለት በጣቶቻቸው ላይ ቢሰካ ቀለበት ይወልቃል ሲላላ የፍቅር ማገሩ ዙፋኑ ልብ ነው ዋናው ቁምነገሩ #GOOD_NIGHT_I_LOVE_YOU_ALL