fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

️ፈለገ ጥበብ Photography (ፈለገ ጥበብ ፎቶ ማህደር ዘፈለገ ጥበብ ሚዲያ)

️ፈለገ ጥበብ Photography (ፈለገ ጥበብ ፎቶ ማህደር ዘፈለገ ጥበብ ሚዲያ)

رفتن به کانال در Telegram

እንኳን ወደ ፈለገ ጥበብ ሚዲያ የ 🅿🅷🅾🆃🅾🅶🆁🅰🅿🅷 ቻናላችን በደህና መጣቹ። ✔️በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤትም ይሁን በተለያዩ ደብራት የሚነሱ ፎቶግራፎችን በዚህ የፈለገ ጥበብ የፎቶ ማህደር ላይ ያኙታል። መልካም ጊዜ 📸📷📹💽

نمایش بیشتر
733
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
በ2016 ዓ.ም የደብረዘይት ደብረመዊዕ ቅዱስ ሚካኤል ወደብረ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል አብያተክርስቲያናት ስብከተ ወንጌል ከደብሩ ሰንበት ት/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ለ3ወራ ሲያስተምሯቸው የነበሩትን የክረምት ኮርስ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት በቅዱስ ሚካኤል ወርሀዊ ጉባኤ ላይ ያስመረቀ ሲሆን በመርሀግብሩላይም ታላላቅ ሰባኪያነ ወንጌል ፤ መዘምራን እና አባቶች የተካፈሉ ሲሆን በኮርሱ ላይም ለተሳተፍ ተማሪዎች የሰርተፍኬን መስጠት መርሀግብር እና በ3ቱም ዙሮች ላይ ከ1 እስከ 3 ለወጡ ተማሪዎች የስጦታ መርሀግብር የነበረ ሲሆን ላስተማሩ መምህራንም ከተማሪዎች ስጦታ በማበርጀት በአበርክተዋል። እንደዚህ አይነት መርሀግብሮች ይበሉ ይቀጥሉ በማለት የፈለገ ጥበብ የመረጃ ሚዲያ እና ህዝብ ህንኙነት ክፍል በማለት ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። መልካም የአገልግሎት ጊዜ መስከረም 12/2016 ዓ.ም #ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ የፈለገ ጥበብ የዲጂታል ሚዲያን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ🙏🙏🙏 👉ዩቲዩብ (Youtube) 👉ቲክቶክ (Tiktok) 👉ኢኒስታግራም (Instagram) 👉ፌስቡክ (Facebook) 👉ቴሌግራም (Telegram)

በ2017 ዓ.ም የአዳዲስ አባላት ቅበላ ተደረገ። በመርሀግብሩላይም የትምህርተወንጌል ፣መዝሙር፣የኪነ ጥበብ ፣የፀበል ፃዲቅ መርሀግብር የተካሄደ ሲሆን በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ምክትል ሰብሳቢ ወጣት ተሾመ ዳባ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት እና የሰንበት ት/ቤቱ ህገ ደንብ በጥቂቱ የአንድ አባል መብትና ግዴታን በተመለከተ አጭር መክዕክት ያስተላለፈ ሲሆን በመጨረሻም የሰንበት ት/ቤቱ አባላት ክትትል እና ግንኙነት ክፍል ሰብሳቢ በሆነው አቶ ተሸመ ደስታ በቀጣይ የገብትን አባላት በመመዝገብ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ በጥቂቱ በመግለፅ መርሀግብሩ በፀሎት ተዘግትዋል። በተያያዘ በ2017 ዓ.ም የአዳዲስ አባላትም ይሆን የነባር አባላት የትምህርት በመስከረም 19 በሰንበት ትምህርት ቤቱ በሁሉም መርሀግብሮች ( በህፃናት እና ወጣቶች) የሚጀምር ሲሆን የህፃናት (ከቅድመ መደበኛ እስከ 4ኛ ክፍል አዳዲስ አባላትን ጨምሮ) እሁድ ከጠዋቱ 3:30 እስከ 6:00 ትምህርታቸው የሚሰጥ ሲሆን የወጣቶች (ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል አዳዲስ አባላትን ጨምሮ) ከ ቀኑ 7:00 - 10:00 ሰዓት የሚሰጥ ይሆናል። አዳዲስ ወደ ሰንበት ት/ቤቱ የተቀላቀላችሁ አባላት እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን በዛሬው መርሀግብር ላይ ያልተሳተፋችሁ ነገር ግን መማር የምትፈልጉ ምዕመናል መስከረም 19 ለመማር በመምጣት በዚያውም ምዝገባውን ማካሄድ አደንደምትችሉ በደስታ እንገልፃለን። መስከረም 12/2017 ዓ.ም #ፈለገ_ጥበብ_ሰንበት_ትምህርት_ቤት #ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ የፈለገ ጥበብ የዲጂታል ሚዲያን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ🙏🙏🙏 👉ዩቲዩብ (Youtube) 👉ቲክቶክ (Tiktok) 👉ኢኒስታግራም (Instagram) 👉ፌስቡክ (Facebook) 👉ቴሌግራም (Telegram)

በ2016 ዓ.ም በፈለገ ጥበብ ሰንበት ትምህርት ቤት ህፃናት ክፍል እና ትምህርት እና ስልጠና ክፍል ለተከታታይ 3ወራት ለ2017 ዓ.ም በአለማዊ የትምህርት ዙሪያ ተማሪዎችን ብቁ እና ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለማድረግ ሲያስተምራቸው የቆዩ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት የማጠቃለያ መርሀግብሩን ያደረገ ሲሆን በመርሀግብሩላይም ላስተማሩ መምህራን የምስጋና ሰርተፍኬት እና ከየክፍሉ ከ1እስከ 3ኛ ለወጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ይህ የጥናት እና የትምህርት መርሀግብር ከመንፈሳዊ ትምህርት ጎን ለጎን ከህፃናት ወላጆች ጋር በመወያየት በበጋ ወቅትም ለማስቀጠል ስራ ላይ እንደሚገኝ ክፍሉ አሳውቅዋል። በዚህ መርሀግብር ላይ ሲሳተፍ የነበሩ ተማሪዎች ከ4ኛ እስከ 10 ኛ ክፍል ተማሪዎች መሆናቸውን ክፍሉ የገለፀ ሲሆን እንደዚህ ያሉ መርሀግብሮች ይበሉ ይቀጥሉ በማለት አስተያየታችንን እንገልፃለን ። መልካም የትምህርት ዘመን መስከረም 12/2017 ዓ.ም ደብረዘይት /ቢሾፍቱ #ፈለገ_ጥበብ_ሚዲያ የፈለገ ጥበብ የዲጂታል ሚዲያን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ🙏🙏🙏 👉ዩቲዩብ (Youtube) 👉ቲክቶክ (Tiktok) 👉ኢኒስታግራም (Instagram) 👉ፌስቡክ (Facebook) 👉ቴሌግራም (Telegram)