cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Bayrak muhafızları🇵🇸

ከየት እንደመጣን ለምን እንደመጣን ወዴት እንደምንሄድም ፈፅሞ አንዘነጋም መንገዱ የሚወስደን ወደ ታላቅነት ነው የአለም ስርአት እዛ ያደርሰናል መንገዱ የአላህን ቃል ወደ ማላቅ ይመራል

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
367
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 عوز
-2030 عوز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

🇵🇸🇵🇸🇵🇸 በደለኛን ይቅር ማለት ተበዳይን መበደል ነው። እስልምና ፍትሕን ሊያሰፍን እንጂ ፍትሕን ሊጠይቅ አልመጣም።🇸🇩🇸🇩 🇵🇸ሸሂድነት እስካሁን የኖርኩለት አላማየ ነው🇵🇸
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
በዛሬው እለት አጃንባ ኑር መስጂድ ፈርሷል 😭😭 በዛሬ እለት ሀያ አንደኛው መስጂዳችንን አፍርሰውብናል መንግስት ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለው ንቀት ዛሬ በግልፅ አሳይቶኛል ሸሂድ የሆኑትን ወንድሞቻችን ቀብረን ሳናበቃ ምን ያመጣሉ ብሎ ዛሬም ንቀቱን አሳይቷል ከመስጂድ ቆጠራ ወደ ጀነዛ ቆጠራ የቀየረው መንግስት ዛሬም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ያለውን ንቀቱን አልተው ብሏል እስከመቼ እንደሚቀጥል እምናየው ይሆናል  መጨረሻው ግን አያምርም 😭😭😭😭😭😭
نمایش همه...
«ትናንት አንዋር መስጅድ ዉስጥ ሰዉ ሁሉ ተጨንቆ ባለበት ወቅት ፈገግ እያለ ታጋቾቹን ፎቶ ሲያነሳ የነበረ ሰዉ ነበር። ልጁ በተደጋጋሚ ይህን ተግባር ሲፈጽም ተስተዉሏል። ያሳለፍነዉ ጁሙዓም እንዲህ ሲያደርግ ስለታዬ ነገሩ ያላማራቸዉ አንዳንድ ሰዎች አናግረዉት ፎቶዎቹን ያጠፉበት ቢሆንም መስጅዱ ዉስጥ ከነበሩ ሰዎች አሁን አፈሳ ጀምረዋል። ምናልባት ምንጩ የዚያ ልጅ ፎቶዎች ይሆናሉ። ስለዚህ አንዋር መስጅድም ሆነ ሌላ ቦታ ለመስገድ ስትንቀሳቀሱ እያስተዋላችሁ። አከባቢያችሁን በትኩረት እየቃኛችሁ። አጠገባችሁ ያለዉን ሰዉ ከዚህ በፊት የምታዉቁት ካልሆነ የመንግስት ቅጥረኛ፤ የሙስሊሙ ጠላት ሊሆን ስለሚችል ለምታወሩት ወሬ እየተጠነቀቃችሁ!
نمایش همه...
ያ አላህ! የግፈኛን እጅ ቁረጥ። የተገፋን ባሮችህን አግዝ። የተንኮለኛን ሴራ በራሱ ላይ አድርግ። አቅም ተስኖናልና አግዘን! #የአንዋር መስጂድ #ጭፍጨፋ ኡስታዝ ተውፊቅ በህሩ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የህይወት ወሳኝ ጥያቄዎች ከዚህ በታች ያሉት ጥያቄዎች መነሻ ሀሳቦች እንዲሆናችሁ ብዬ ነው ያቀረቡኩት እናንተ የራሳችሁን ጥያቄ መፍጠር ትችላላችሁ። 1.በህይወቴ ላሳካው የምፈልገው አላማ እና ራዕይ ምንድን ነው?? ከአምስት ወይም ከአስር አመት በኋላ ራሴን የት ማግኘት እፈልጋለሁ ?? 2.አሁን ያሉኝ ሕልሞች እና ግቦች ከጥቂት አመታት በፊት ከነበረው በጣም የተለዩ ናቸውን?  ከተለዩ ለምን? 3.አሁን ባለው ህይወቴ ከቀጠልኩ ከአምስት እና ከአስር አመት በኋላ ምን አይነት ህይወት ሊኖረኝ ይችላል?? 4.ለስኬት የሚያስፈልገው ፅኑ ፍላጎት ፣ ቁርጠኝንት እና ትጋት አለኝ ወይ፤ ከሌለኝ ለምን? 5.ህይወቴ ውስጥ ደስታ፣ ሰላም እና ፍቅር አለ ወይ? ከሌለኝ ለምን? 6.በህይወቴ የተሰጠኝ ፀጋ ፣ክህሎት ወይም ተሰጥዖ ምንድነው?? እንዴትስ ልጠቀምበት አስቤያለሁ?? 7.በምኖርበት ማህበረሰብ ውስጥ ምን አስተዋጽኦ አድርጌያለሁ? ከዚህ በኋላስ ምን ለማድረግ አስቤያለሁ? 8.መጥፎ ልማዶች(ሱስ) አለብኝ ወይ?? እንዴት ነፃ መሆን እችላለሁኝ?
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ዛሬ ከሰሞኑ የተፈፀመ አንድ አስተማሪ ታሪክ አነበብኩ ነገሩ አንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር የሆነው ፕሮፌሰሩ ሁሉንም ተማሪዎች ከታች በምስሉ በምታዩት መልክ ፊኛ እየነፉ ስማቸውን እንዲፅፉበት አደረጉ።ቀጥሎ ሁሉም ፊኛዎች ወደ አዳራሽ ተለቅቀው እያንዳንዱ ተማሪ የየራሱን ስም(ፊኛ) እንዲፈልግ ታዘዘ።5 ደቂቃ ተሰጣቸው ምንም ያህል በችኮላ ቢፈልጉም ማንምየራሱን ፊኛ ማግኘት አልቻለም ጊዜውም አለቀ። ፕሮፌሰሩ ቆይቶ ደግሞ ተጨማሪ 5 ደቂቃዎች በመስጠት ሁሉም ተማሪ ያገኘውን የሌላ ሰው ፊኛ ለባለቤቱ እንዲሰጥ  አደረገ። አስገራሚ ውጤት ታየ ተማሪው በሙሉ እየተጠራራ አንዱ ለሌላው እያቀበለ 5 ደቂቃው ሳይገባደድ ሁሉም የየራሱን ፊኛ ተቀበለ።ፕሮፌሰር ነገሩን ከሕይወት ልምድ ጋር ያቆራኘበት አግባብ ነው ያስደሰተኝ። "አያችሁ የናንተ ደስታና የልብ መሻትም እንደ ፊኛው ናቸው።የራሳችንን ደስታ(ፊኛ) ብቻ ባሳደድን ቁጥር ልናገኘው አንችልም ወይም እስክናገኘው ይቆያል።ይልቅዬ ለሰዎች ደስታ ፍላጎት ባሳየን በተባበርን መጠን ለራሳችንንም ደስታን በቀላሉ እንጎፀፋለን"
نمایش همه...
የአዲስ አበባ መጅሊስ መግለጫ‼ ======================== (የአዲስ አበባ መጅሊስ በዛሬው ዕለት በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ አካባቢ በተፈጸመው አስነዋሪና አረመኔያዊ ድርጊት ይህን መግለጫ አውጥቷል።) || ✍ «በወቅታዊ ጉዳይ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ። መብቱን በሰላማዊ መንገድ ለመጠየቅ በወጣ ህዝብ ሙስሊም ላይ የተወሰደው እርምጃ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ፣ ኢ-ፍትሃዊና ኢ-ዲሞክራሲያዊ በመሆኑ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያወግዛል። በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በሸገር ሲቲ የመስጅድ ፈረሳ እንዲቆምና የፈረሱትም በአስቸኳይ መተኪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በጉዳዩ ዙሪያ የሚመለከታቸው አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ ለሚመለከተው አካል ለማሳወቅ የተሞከረ ሲሆን የመስጅድ ፈረሳው ባለመቆሙ ህዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን በዛሬው እለት  በአደባባይ ድምፁን በሰላማዊ መንገድ  አሰምቷል። ይህንንም ሰላማዊ የመብት ጥያቄ ተከትሎ በታላቁ አንዋር መስጅድ የፀጥታ አካል  በወሰዱት ኢ-ህገ መንግስታዊ እና ኢ ሰብአዊ እርምጃ የሰው ህይወት አልፏል፣ ብዙሃን ቆስለዋል። በመሆኑም ይህንን አስከፊ ጥቃት የፈፀሙ እና ያስፈፀሙ የጸጥታ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ አጥብቀን እንጠይቃለን ። በቀጣይም የሚመለከተው አካል በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ እየተከናወነ ያለውን ድርጊት እንዲያስቆምና ወደ ውይይት በመምጣት ሾር ነቀል እርምትና እርምጃ ተጠናክሮ እንዲተገበር አጥብቀን እንጠይቃለን። የኃይማኖት ጉዳይ እና የእምነት ተቋማት ጉዳይ ሁሌም ቢሆን በስክነት መታየት ሲገባው፤ ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በእምነት በተቋማቱ ጉዳይ ሲከተሉት የነበረውን  አካሄድ እንደ ተሞክሮ ከመውሰድ ይልቅ በዚህ አካሄድ የተሰራው አስነዋሪ ተግባር የሀገራችንን ብሎም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ እየጣለ  ይገኛል። በሸገር ከተማ  መስጅድን በተመለከተ እየተከናወነ ያለው ድርጊት፣ ኃላፊነት የጎደለው፣የህዝበ ሙስሊሙን ክብር ያዋረደ፣ ሀገራችን ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ ያላገናዘበ፣ የመንግስት የለውጥ ሪፎርምን ወደ ኋላ የሚመልስ በመሆኑ ጉዳዩ እንደ ሀገር ሊታሰብበት ይገባል። በዛሬውም እለት በመስጅድ ፈረሳ ሳቢያ በሰላማዊ መንገድ መብቱን ለመጠየቅ በወጣው  ህዝበ ሙስሊም ላይ በተወሰደው ኢ-ህገ መንግስታዊ እርምጃ ህይወታቸው áˆ‹áˆˆá‰ አላህ (ሹ.ወ) ጀነትን እንዲወፍቃቸው፣ ለመላው ህዝበ ሙስሊም መፅናናትን እንመኛለን። የከተማችንም ህዝበ ሙስሊሙ በቀጣይ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንዲከታተል አደራ እንላለን። ግንቦት 18/2015Âť @Strong_iman
نمایش همه...
00:18
Video unavailableShow in Telegram
1.97 MB
ሸገር ከተማ መስጂዶችንና ሙስሊሞችን የሚያጸዳ ከሆነ፣  ለሙስሊሞች «ፈተና» እንጂ «የኩራት ምንጭ» ፈጽሞ ሊሆን አይችልም! 🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌🕌 መንግስት ሀገርን የሚያስተዳድረው በዜጎች ስም ዜጎችን በመወከል መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው። ይህ ባይሆን ኖሮ የመንግስት ባለስልጣናት የሚባሉት በጠቅላላ እንደኛው ተርታ ዜጋና፣ ከእያንዳንዳችን የተለየ  ምንም መብትም ስልጣን ሊኖራቸው አይገባም ነበር። ሀገር የጋራ መሆኑ ካልተካደ በቀር የሀገር ሀብትና በሀገር ውስጥ ያሉ እድሎች በጠቅላላ የጋራ ናቸው። ይህ ሆኖ ሳለ በመላ ሀገራችን ከተሞች ማስተር ፕላን ሲዘጋጅ ዘወትር ለፕላን አዘጋጆቹ ብቻ ሳይሆን ለፖለቲካ አመራሮቹ ጭምር መስጂድ ብቻ ተለይቶ ትዝ የማይላቸው እስከመቼ ነው? ሕዝበ ሙስሊሙ እንደዜጋና መስጂዶች በሀገሪቱ በሚዘጋጁ ማስተር ፕላኖች ላይ  ሆነ ተብለው እየተረሱ፣ የሙስሊሞች ጥያቄዎች መስጂድና ሂጃብ ብቻ ላይ ታጥረው እንዲቀሩ የማድረግ፣ በውጤቱም ዘወትር የሕዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች እነዚሁ ብቻ እንዲመስሉ  በማድረግ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴዎቹ በአቀበት የተሞላ እንዲሆን የማድረግ ስልት መሆኑ ግልጽ ነው። እነዚህ መሠረታዊ መብቶች የሆኑ ጉዳዮች፣ ጥያቄዎች  ሳይጠየቁም በፊት «በማስተር ፕላኑ መሠረት እዚህ ጋር መስጂድ ያሳያል» እየተባለ ሊመለሱ ይገባቸው የነበሩ፣ አልያም  ከተጠየቁም በቀላሉ ሊመለሱ የሚገባቸው ጥያቄዎች ነበሩ። ሆኖም በመላ ሀገሪቱ ሙስሊሞች መስጊድን በልመና፣ ወይም መሬት በገንዘባቸው እየገዙ ለመስገጃነት በማዋል፣ ባስ ሲልም በትግልና በደም [የመስጂድ ይዞታን ለማስከበር በሚደረግ ትግል በጸጥታ አካላት ሙስሊሞች የሚገደሉበት አጋጣሚ በርካታ ነው] የመጎናጸፍ ጉዳይ ካልቆመ በቀር፣ በሀገራችን የሙስሊሞች መብት ተከበረ ማለት አይቻልም። አንዳንድ ወገኖች መስጂዶች እየፈረሱ ያሉት «ሕገ-ወጥ ስለሆኑ ነው» ይሉናል። ይገርማል! እነኚህንና መሰሎቻቸውን የምንጠይቀው በሀገራችን «ሕጋዊ» የሚባሉት መስጂዶች የትኛቹ እንደሆኑ እንዲነግሩን ነው። አዲስ አበባን ጨምሮ መስጂዶች ለአስርት ዓመታት ሲሰገድባቸው ቢቆይም፣ ካርታ የሚያገኙት በስንት ጥረትና መንከራተት መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ሀቅ ነው። ከንጉሠ  ዘመን ጀምሮ የኖሩት ታላቁ አንዋር መስጂድና ኑር (በኒን ሰፈር)  መስጂድን ጨምሮ ሌሎችም በአዲስ አበባ የሚገኙ ጥንታዊ መስጂዶች ካርታ ያገኙት አቶ አርከበ እቁባይ ከንቲባ በኾኑበት በ1990ዎቹ ነበር። ሆኖም አንዋር መስጂድ የተሠራው በጣሊያን ዘመን ሲሆን፣ ኑር መስጂድ ግን ከጣሊያን ወረራ በፊት ነበር በአባቶቻችን የተገነባው። እነዚህ መስጂዶች በህዝበ ሙስሊሙ ያላሰለሰ ትግል ተሰርተው፣ ለዘመናት እየተሰገደባቸው ቢቆዩም፣ ሕጋዊ ካርታ ያገኙት ግን ከበርካታ አስርት ዓመታት እንግልት በኃላ ነበር። በበርካታ ከተሞች በሕዝብ ስም ስልጣን ላይ ያሉ አስተዳደሮች በሚያስተዳድሩት ከተማና ዜጎች በሚኖሩበት አከባቢ ማስተር ፕላኑ ሆነ ብሎ መስጂዶች እንዳይኖሩት ማድረጋቸው ሳያሳፍራቸውና ሳያሸማቅቃቸው፣ የአከባቢው ሕዝበ ሙስሊም በነጻ ሊሰጠው ይገባ የነበረውን የመስጂድ ይዞታ ከግለሰቦች ሳንቲም አሰባስቦ ለመግዛት ሲገደድ ነው የኖረው። ሆኖም ይህንንም ይዞታውን ጭምር «ለመስጊድነት አልተፈቀም፣ ሕገ-ወጥ ነው!» ብለው ሲያፈርሱ በተደጋጋሚ ጊዜ ታይቷል። የሚያሳዝነው ከብዙ ደጅ መጥናትና ዉትወታ በኋላም በሕጋዊ መንገድ ተብሎ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ከሌሎች እጅግ ያነሰ መሬት፣ ማለትም ለአንዱ በካሬ ለሌላው በሔክታር ተለክቶ፣ አድልዎ የተሞላበት አሰራር አሁንም ድረስ መቀጠሉ አሳዛኝ ነው። ይህንና መሰል  እኩይ አድሎ የተሞላበት አካሄድና አሠራር መጅሊስና ሕዝበ ሙስሊሙ በጋራ በሚያደርጉት የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ትግል ውጪ ሊለወጥ አይችልም። «ሕገ-ወጥ» ያሉዋቸው መስጂዶች ዛሬ በአንድ ጀምበር ተሰርተው ያደሩ ሳይሆኑ፣ ይልቁንም ሕዝብም መንግስትም እያወቁ ለዓመታት ለአካባቢያቸው ሕዝበ ሙስሊም ግልጋሎት ሲሰጡ የቆዩ ናቸው። ሌላው ቢቀር በአዲስ መልክና በአዲስ ዕቅድ  «ሸገር ከተማ» የሚል አዲስ የከተሞች ግንባታ ስለታቀደ እና በከተማው አዲስ ፕላን መሰረት ስፍራው ለመስጊድ ሳይሆን ለሌላ ጉዳይ ተይዞም ከሆነ፣ ፕላኑን ለመጂድ መገንቢያም ምቹ እንዲሆን ማድረግ እንጂ መስጂዶችን ድንገት ተነስቶ፣ ምንም ምክክር ሳያደርጉ በጅምላ ማፍረስ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም። የሸገር ከተማ አስተዳደር «በአዲሱ ፕላን መሰረት ለመስጂድ የተመደበው ስፍራ ይህ ነው» እያለ ተለዋጭ መሬት እያቀረበ፣ በውይይትና በስምምነት  በአዲሱ የከተሞች ግንባታ ውስጥ መስጂድ እንዲሰራ በማድረግ ጉዳዮችን መቋጨት እንኳ አልፈለገም። ከዚያ ይልቅ በተግባር ያደረጉት ለሃይማኖቱና ለሙስሊሞች ቅንጣት ታክል ክብር ሳያሳዩ መስጂዶችን በጅምላ ወደ ማፍረስ ነው የገቡት። ይህ ሁኔታ ሲታይና በተግባርም በሸገር ከተማ በርካታ መስጂዶችን በጅምላ ለማፍረስ የሚደረገው አሳዛኝ እንቅስቃሴ ሲታይ፣ ጉዳዩ የሕጋዊነት ጥያቄ ሳይሆን ከሸገር ከተማ መስጂድንና ሙስሊሞችን የማጽዳት [አብዛኛው ቤቱ እየፈረሰበት ያለው ሙስሊሙ መሆኑን ከግምት በማስገባት]  የአሻጥር እርምጃ አስመስሏል። ይኼን ማሳካት ፈጽሞውኑ በኢትዮጵያ ምድር ከእንግዲህ የማይታሰብና፣ የሸገር ከተማም መስጂድና ሙስሊሞችን ለማጽዳት ቆርጦ ከቀጠለ፣ ከተማው ለሀገሪቱ ግማሽ ለሆነው ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ «ችግር» እንጂ «የኩራት ምንጭ» ፈጽሞ ሊሆን አይችልም! ©አህመዲን ጀበል
نمایش همه...
የዝምታ ሃይል (The power of silence) ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ የሰዎች ወሬ 80%ው "ሓሜት" እንደሆነ ያውቃሉ። ካላወቁ ቀኑን ሙሉ ያወሩትን ወሬ መለሾ ብለው ይፈትሹት። በየትኛውም እምነት...ሓሜት ፈፅሞ የተከለከለ  ነው። ከሞራል አንፃርም ሲታይ መከልከሉ አምክኗዊ ነው። ፈጣሪ ማውራት እንችል ዘንድ ምላስና ሁለት ከናፍር ከሰጠን በኋላ ወሬያችን የተገነባበትን (80%) #ሓሜት የመከልከሉ ጥበብ ምን ይሆን ???  ዝርዝሩን ለሃይማኖቶች ልተወውና...የራሴን ምልከታ ላስቀምጥ። ሰዎች ከሃሜት እንዲርቁ ከተፈለገ፤ በሌላ አገላለፅ #ዝምታን እንዲያበዙ ተፈልጓል ማለት ነው፤ ምክኒያቱም ከእርሶ አጠቃላይ ወሬ ላይ ሃሜት ቢነሳ ምንም የሚቀርዎት ነገር ቢኖር...በቀጥታ ስለሚመለከትዎት ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ያደረጉት ንግግር ብቻ ነው። ማውራት ስትጀምር ማሰብ ታቆማለህ። ምላስ ከወሬ ዛዛታ ጋብ ሲል አዕምሮ ሚያስብበት ፋታ ያገኛል። ቀስ በቀስ የምታስበውን ነገር መቆጣጠር ስትጀምር ደግሞ ከፍታህ የሚሆነው #ሰው'ነት ነው። ማሰብ ግብአት ይፈልጋል። ግብአቶቹንም የምታገኛቸው #ከንባብ ነው። ቀና ትልና ሰማያትን ታነባለህ፣ የሰዎችን አይንና አፍንጫ ታነባለህ....ተፈጥሮን ታነባለህ። በተጨማሪም መፃህፍትን በማንበብ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተከስተው ሰዎችን ካስደመሙ ታላላቅ ማንነቶች (great personalities) ጋር ታወጋለህ፣ ሃሳብ ትሰርቃለህ። አዎ!...ዝምታ ወርቅ ሳይሆን የሰዎች ተፈጥሮ ነው። እርሶ የሚታወቁት በወሬኛነትዎ ከሆነ፣ ሃሜተኛ ነዎት ማለት ነው። እንዲሁም ከተፈጥሮ እጅግ ርቀዋል ማለት ነው። የማሰብ፣የማሰላሰለ፣የመመሰጥ አቅምዎ በጣም ደካማ ነው ማለት ነው። ጉዳዩ የዚህን ያክል ከባድ ስለሆነ ራስዎን ይፈትሹ።                           ✍ ዌሻፕት
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.