cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ ስብከት | ORTHODOX SIBKET

በዚህ ቻናል የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶችን በሥርዓተ ቤተከርስቲያን ለማነጽ ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው የስነልቦና ማማከር ከፈለጉ በ @binigirmachew ላይ ያናግሩን

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
16 336
مشترکین
-924 ساعت
-67 روز
+6830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ቅዱስ ሲኖዶሰ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ለመነኮሳት ምህላ አወጀ ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡"
نمایش همه...
27🙏 10👍 9
አዲስ አበባ ወጌት ብቻ ነው የብርሃናተ ዓለም ጴጥርስ እና ጳውሎስ ቤተክርስቲያን ያለው መሄድ ለምትፈልጉ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
📚81ዱ መጽሐፍ ቅዱስ በአዲስ አበባ ለሚገኙ ምእመናን ማድረስ ጀምረናል አሁን ላይ የተረከብነው ጥቂት በመሆኑ በ 0970908094 ላይ በመደወል ማዘዝ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ። 🔔ለቻናላችን አባላት ታላቅ ቅናሽ ተደርጓል 📯 ⛪️ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍ📚
نمایش همه...
📥በቴሌግራም ለማዘዝ🧧
የፍለጋ ማብቂያ “በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን ።” ኤፌ. 2 ፡ 6-7 ። የሚመጡ ዘመናት አሉ ። የሚመጡ ዘመናት ሲል ሁለት ጉልህ ነገሮችን ይገልጣል፡- የመጀመሪያው ትንሣኤ ልቡና አግኝተን በእምነት በምግባር የምንኖርበት እስከ ዕለተ ሞታችን ያለው ጊዜ ነው ። ትንሣኤ ልቡና ማለት አማኝ በድኅነት ጸጋ የሚከብርበት ፣ ክርስቶስን የማግኘት ጥልቅ ትርጉም ነው ። እምነትም ለማይታየው እግዚአብሔር የምንሰጠው ምላሽ ሲሆን ምግባር ደግሞ ለሚታየው ዓለም ተማጽኖ የሚታይ ሥራ የምንሠራበት ነው ። ይህ ዓለም በማይነገር መቃተት ከክርስቲያኖች የሚታይ ምግባር እየፈለገ ነው ። ፍቅርን ተርበው ያሉ በነጻ የሚወዳቸው ፣ በጎነታቸውን አጉልቶ ክፋታቸውን አሳንሶ የሚቀርባቸው እየፈለጉ ነው ። የቸርነት እጆችን ብናገኝ ወራሪ ሁኖ የመጣብንን ረሀብ ድል እንነሣው ነበር እያሉ የሚከጅሉ አያሌ ወገኖች አሉ ። የቅን ፍርድን ብናገኝ ሞት ሕይወት ይሆንልን ነበር በማለት ፍትሕን የተጠሙ ወገኖች በዝተዋል ። ክርስቲያኖች ከማይታየው እግዚአብሔር ጋር ስላላቸው የእምነት ግንኙነት መተንተን አንችልም ። ጸሎታቸውን ፣ ንስሐቸውን እነርሱ ያውቁታል ። ለተጨነቀው ዓለም ግን እየሰጡ ያለውን ምላሽ ሁሉም ሊናገረው የሚችለው ነው ። እንኳን ለጠፋው ዓለም ይቅርና እርስ በርስ የሚዋደዱ ክርስቲያኖችን እያጣን ነው ። አረማውያን ሌላውን ለማጥቃት የቡድን ፍቅር ፣ ዘረኞች እነርሱ ብቻ ለመኖር የጎሠኝነት ጽዋ በሚጠጡበት ዘመን ክርስቲያኖች ወይ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያገናኝ ንጹሕ ፍቅር ፣ ወይ ከመደምሰስ የሚያድን የቡድን ፍቅር አጥተው ይኖራሉ ። ቅዳሴ ላይ ጉቦ የሚቀባበሉ ፣ በፖሊስ ላለመታየት አምልኮውን የተዳፈሩ ፣ መላእክትን የዘነጉ ብዙ አማንያን አሉ ። ሁለት ትዳር ይዘው በክሬ አትምጡብኝ እያሉ የሚተዉኑ አያሌ ናቸው ። ከቤተ ክርስቲያን መልስ መንደሩን በነገር የሚያቃጥሉ ቍጥር የላቸውም ። በኢየሱስ ስም እያሉ ሰውን ሲያስለቅሱ የሚውሉ በየቢሮው የተሰገሰጉት ባለጭምብሎች ፣ ደጉን ክርስቶስ ዓለም እንዲጠላው እያደረጉ ነው ። ክርስቲያን ነኝ ማለት ኢትዮጵያዊ ነኝ እንደ ማለት የዜግነት ስም ያደረጉት ብዙ ናቸው ። ጨካኝ ሁኖ ኢትዮጵያዊ መሆን ይችላል ፣ ሰው እያረዱና እያስቀሉ ክርስቲያን መሆን ግን አይቻልም ። ትንሣኤን ተነሥተን ብናከብር እግዚአብሔር ደስ ይለው ነበር ። የዓመት ፈቃድ የወጡ ጠጪዎችና አመንዝራዎች በበዓሉ ቀን ወደ ቀደመ ሥራቸው ይገባሉ ። በጥንቱ ዘመን ምዕራብና ምሥራቅ ተብሎ ክርስትናው በአቅጣጫ በተከፈለበት ጊዜ ክርስቲያን ወንድሙን ከአላውያንና ከአረማውያን ጋር ወግኖ ወግቶታል ። ወንድሙን ገድሎ ሲመለስ ግን አንተም ካድ ተብሎ በሰይፍ ሃይማኖቱን ጥሏል ። ባመንን ቀን በክርስቶስ ፍቅር አምነናል ፣ በመጨረሻው ቀንም ለሰዎች ያለን ፍቅር በስድስቱ ቃላተ ወንጌል ይዳኛል ። ትንሣኤ ልቡና የነፍስን መነጽር የሚወለውል ፣ ለበጎ ሥራ የሚያነቃቃ ፣ ሕይወት ባለው ግንኙነት የሞተውን ዓለም የሚታደግ ፣ የአድራሻ ለውጥ በማድረግ የቀደመ ኑሮን በጽድቅ ግብር የሚበቀል ነው ። ዘመኑና ተግባሩም እስከ ዕለተ ሞት ነው ። ከዕለተ ሞት በኋላ የበጎ ሥራ ሽልማት እንጂ የበጎ ሥራ ዕድል የለም ። የሚመጣው ዘመን ሁለተኛው ትንሣኤ ሥጋ አግኝተን ከክርስቶስ ጋር የምንኖርበት ነው ። የሚበዛው ዘመን ያለው ወደፊት ነው ። በዚህ ዓለም ያለው የትኛውም ዘመን ፣ እንደ ማቱሳላ የሺህ ዓመት ድንበር ብንነካም የሚመጡት ዘመናት ብዙ ናቸው ። በዚህ ዓለም ብንጎዳ በማያልፈው ዓለም እንጠቀማለን ። በዚህ ዓለም ተጠቅሞ በማያልፈው ዓለም መጎዳት ግን ከባድ ነው ። ዓለም ከንቱ ነው ስንል ደስታውም ኀዘኑም ኃላፊ ነው ማለታችን ነው ። ስለዚህ በደስታውም በጣም አለመደሰት ፣ በኀዘኑም በጣም አለማዘን ይገባል ፣ ከንቱ ነው የሚለው ቃልም ሚዛንና ልክ መስጫ ነው ። በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ያለው ቸርነት ብዙ ነው ። እግዚአብሔር አብ የእጁን ብቻ ሳይሆን ልጁን ሰጥቶ ዓለምን ያዳነበት ምሥጢር ረቂቅ ነው ። ልጁ ራሱም ስጦታ ነው ። ልጁ ራሱም ሰጪ ነው ። ቸርነት በዝቶልናል ። በዓለም ላይ ያሉ በቢሊየን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ቤተሰባችን ናቸው ። ይህ ቸርነቱን የሚገልጥ ነው ። በቤተ ክርስቲያንም የህልውና መጀመሪያ ይሆን ዘንድ ልጅነትን በጥምቀት ሕይወትን በሥጋ ወደሙ ሰጥቶናል ። በየዕለቱ የምናገኘው የቃሉ ገበታም ትልቅ በረከታችን ነው ። እግዚአብሔር የስጦታውን ብዛት አትረፍርፏል ። በእርሱ እውቀት ውስጥ ብቻ የተሰወረች ርስተ መንግሥተ ሰማያትንም ስናስብ የሆነልን ብዙ ነው ። አሁን በቤተ ክርስቲያን ያለው ጸጋ በረከት ቅምሻ ሲሆን በመንግሥተ ሰማያት የሚገለጠው ግን ከቃላት በላይ ነው ። በሰማይ ላይ የሚታየውን ውብ ቀስተ ደመና ወደ ታች ስበን በወጠርነው የሥዕል ሸራ ላይ ማተም እንደማይቻለን የመንግሥተ ሰማያትን ደስታ በዚህ ዓለም ማምጣትም መናገርም አይቻልም ። ይህን የመንግሥተ ሰማያት ደስታ ለመካፈል ሁለት ነገሮች ይቀድማሉ ። የመጀመሪያው ከክርስቶስ ጋር መነሣትና ከክርስቶስ ጋር መቀመጥ ነው ። ለመነሣት መሞት ያስፈልጋል ፤ ያልሞተ አይነሣምና ። ለመቀመጥም ከፍ ማለት ይጠይቃል ፣ ያላረገ በሰማያዊ ስፍራ አይቀመጥምና ። ከክርስቶስ ጋር መሞት በጥምቀት የምንገልጠው ትእምርት/ምልክት ሲሆን ዓለምን ክጃለሁ የምንልበት ምስክርነት ነው ። ለዓለም ሞቻለሁ በማለት ቀድሞ የምንኖርለትን ነገር መለወጥ ነው ። የቀድሞ የመጠጥ ወጪአችንን ፣ የዝሙት በጀታችንን ለስብከተ ወንጌል ማድረግ እርሱ መሞት ነው ። ከክርስቶስ ጋር መቀመጥም እርሱ ራስ ነውና ራስ ባለበት አካል ይኖራል ። ከክርስቶስ ጋር መዋሐድ በቀኙ መቀመጥ ነው ። መቀመጥ የሚለው ቃልም መደላደልና ማረፍን የሚያመለክት ነው ። ክርስቶስ የፍለጋ ሁሉ ማብቂያ ነውና ። በጥላህ አኑረን !
نمایش همه...
17👍 10🙏 6
“ጴጥሮስም፦ ንስሐ ግቡ፥ ኃጢአታችሁም ይሰረይ ዘንድ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ስጦታ ትቀበላላችሁ።” ሐዋርያት 2፥38
نمایش همه...
🙏 11👍 1
ዳዊትም ስለ እርሱ እንዲህ አለ:- እግዚአብሔርን ሁልጊዜ በፊቴ አየዋለሁ:እንዳልታወክ በቀኜ ነውና። ስለዚህ ልቤን ደስ አለው አንደበቴም ሐሤት አደረገ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋው አደረ። የሐዋርያት ም: 2፥25
نمایش همه...
24👍 3
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.