ኦርቶዶክስ መዝሙር(Ortodox Mezmur)
رفتن به کانال در Telegram
በእንግድነቴ አገር ሥርዐትህ መዝሙር ሆነችኝ።መዝ-118:54 ሸር በማድረግ ተባበሩን👇👇👇 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21
نمایش بیشتر7 107
مشترکین
+1524 ساعت
+357 روز
+10830 روز
آرشیو پست ها
ዐረገች በስብሐት
ዐረገች በስብሐት ዐረገች በእልልታ
በስብሐት በእልልታ
አረገች አረገች በእልልታ
የጻድቃን እመቤት የኃጥአን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
የማይታበለው እንዲፈጸም ቃሉ
ብታርፍም እመ አምላክ ቤዛዊተ ኩሉ
ዐረገች ተነስታ ድንግል የኛ እናት
እልል በሉላት እልል በሉላት
ሰማያት ተደንቀው በአዲሲቷ ሰማይ
ያልቻሉትን ጌታ ወስናው ብትታይ
ሊቀበሏት ወጡ በሀሴት በሙሉ
ነዪ ነዪ እያሉ ነዪ ነዪ እያሉ
ዘመኗን በሙሉ ስለ ልጇ አልቅሳ
የመከራ ሰይፍን አሳልፋ ነፍሷ
በቀኙ ልትቆም ንግሥት እየተባለች
ይኸው ዐርጋለች ይኸው ዐርጋለች
በሐዋርያት አበው ትምሕርት የጸናችሁ
የልጇ ምሥክር ከዘሯ የቀራችሁ
ከሞት ተነሥታለች ቅድስት እናታችሁ
እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አላችሁ
እጅሽ በዳሰሰው በነካው ሰበን
እንደ ባረክሻቸው ሐዋርያቱን
ማርያም ማርያም ስንል ደጅሽ ላይ ቆመን
እኛንም ባርኪን እኛንም ባርኪን
መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አማን ኡርጌሳ
✅ Join NEAR Mobile referral campaign and receive $NPRO today. Download https://nearmobile.app on Android or iOS for free and use this referral code to earn some $NPRO now! 👇
AD0VEC
#ቡሄ
ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል፡፡
#ጅራፍ
በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡
የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል፡፡
#ችቦ
ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡
የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና ፡፡
#ሙልሙል
በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም፡፡
ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ፡፡
በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡
ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡
አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡
አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው፡፡ ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።
ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበረካታ ዓመታት ሲወርድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው፡፡ በተለይ ወጣቱ ክፍል ይህንን አውቀን ተረድተን ለቀሪው ትውልድ ማስተላለፋ እንችል ዘንድ ከክፉ ጠላት ከሰይጣን ፈተና፣ በሽታ ከመሳሰሉት ችግሮች ለመዳን ወደ ተራራዋ ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሸሽ ከክፉ ነገሮች ሁሉ ማምለጥ ይቻላል፡፡
በቤተ ክርስቲያን ጥላ ሥር የሚጠለሉ ሁሉ ዕድሜያቸው ይረዝማል፡፡ አስተዋዮችም ይሆናሉ ሁሉን ማየትና የሚጠቅማቸውን መምረጥ ይችላሉ በሥነ-ምግባር የታነፁ አገርንና ወገንን የሚጠቅሙ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን በመጠጋት ከክፉ ሁሉ የሚያመልጡ ይሆናሉ ለዚህም የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
ነሐሴ 7 ጽንስታ ለእግዝእትነ
አያቶቿ ቴክታ በጥሪያ ይባላሉ ብዙ የወንድ ባሪያ የሴት ባሪያ የቀንድ ከብት፣ የጋማ ከብት የነበራቸው ባለጸጐች ነበሩ ከወርቁ ብዛት የተነሣ እንደ ቀለበት አንደ አምባር እያሰሩ ከበሬው ከላሙ ቀንድ እያደረጉ ይህን ያህል የወርቅ ቀንድ ይህን ያህል የብር ቀንድ አለን ይሉ ነበር::
አንድ ቀን ቴክታ ከቤተ መዛግብት ገብቶ ወርቁ ብሩ ተዝረክርኮ አይቶ በጥሪቃ ሀብታችን ብዙ ንብረታችን ብዙ ነገር ግን የወለድነው ያሳደግነው ልጅ የለንም ለማን ይሆናል አላት ፡፡
እግዚአብሔር እንጂ ከኔ ባይሰጥህ ከሌላ ይሰጥህ ይሆናል አግብተህ አትወልድምን አለቸው ሕያው እግዚአብሔርን አላደረገውም አላት በዚህ ጊዜ አዘኑ ሌሊት በሕልሟ እንቦሳ ከበረታቸው ስትወጣ እንቦሳይቱ እንበሳ እየወለደች እስከ ስድስት ስትደርስ ስድስተኛይቱ ጨረቃን ጨረቃ ፀሐይን ስትወልድ አይታ እንዲህ ያለ ሕልም አለምሁ አለችው ።
ከመተርጉመ ሕልም ሄደው ቢጠይቁ ደግ ልጅ ትወልዳላችሁ ጨረቃይቱ ከፍጡራን በላይ የምትሆን ልጅ ትወልዳላችሁ የፀሐይ ነገር ግን አልተገለጸልኝም እንደ ነቢይ እንደ ንጉሥ ያለ ይሆናል አላቸው ።
ጊዜ ይተርጉመው ብለውት ሄዱ ከዚህ በኋላ ጸነሰች ወለደች ስሟን ረከብኩ ስዕለትየ ስትል ሄኤሜን አለቻት ሄኤሜን ዴርዴን፣ ዴርዴ ቶናን፣ ቶና ሲካርን፣ ሲካር ሄርሜላን፣ ሄርሜላ ሐናን ወለደች ።
ሐናም ልጅ አጥታ ስታዝን ትኖር ነበር ዘማዊት ጎረቤት አለቻት አንድ ቀን ሐና ልብሴ ቆሽሿል እንጂ አምላኬን ለምኚው እመለስ ነበር አለች ልብስማ የኔ ልብስ ሣጥን መልቶ ተርፎ የለምን አንዱን ለብሰሽ አትሄጅምን አለቻት ።
ያንቺ ልብስ በአስበ ዝሙት የተሰበሰበ ነው ንፁሐ ባሕርይ ጌታ ንፁሕ ነገር ይወዳልና ይህን ለብሼ ብለምነው አይሰማኝም ብዬ ነዋ አለቻት ሐና እኔስ ጌታ ስለምን ልጅ ነሣት እያልኩ ሳዝንልሽ እኖር ነበር ። ለካስ በዚህ ክፋትሽ ነው እንደ ድንጊያ አጠጥሮ እንደ ግንድ ገትሮ ያስቀረሽ አለቻት ። በዚህ አዝናለች ፡፡
ሊቀ ካህናቱ ሮቤል ይባላል ብዙ ተባዙ ያለውን ያስቀረባችሁ ርጉማን ብትሆኑ አይደለምን መባችሁን አልቀበልም አላቸው ሁለተኛም ወላድያን የሚመገቡት ተረፈ መስዋዕት ነበረ ያን ከልክሏቸው እያዘኑ ተመለሱ ።
ሲመለሱም ከዛፍ ጥላ ሥር አረፋ ሐና አእዋፍ ከልጆቻቸው ጋር ሲጫወቱ አይታ አእዋፍን ከባሕርያቸው እንዲራቡ ዕጽዋትን እንዲያፈሩ ስታደርግ ሐና ባሪያህን በምን ነገር ልጅ ነሳሀት በውኑ ተፈጥሮዬ ከደንጊያ ነውን ብላ አዘነች ።
ከቤት ሲደርሱ ወንድ ልጅ ብንወልድ እርፍ ይዞ ተክል ተክሎ ይርዳን አንልም ለቤተ እግዚአብሔር ምንጣፍ አንጣፊ መጋረጃ ጋራጅ ይሆናል እንጂ ሴትም ብንወልድ እንጨት ሰብራ ውኃ ቀድታ ትርዳን አንልም መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ቤተ እግዚአብሔር ታገልግል እንጂ ብለው ብፅዓት ገብተዋል
ሐምሌ 30 እሷ ለርሱ ግምጃ ሲያስታጥቁት መቋሚያው አፍርታ ፍጥረት ፍሬዋን ሲመገቡ እሱ ለእሷ ነጭ ርግብ ሰባቱን ሰማያት ሰንጥቃ መጥታ በቀኝ ጆሮዋ ገብታ በማኅፀንዋ ስታድር ሕልም አለሙ ።
ሄደው ለመፈክረ ሕልም ነገሩት የከበረች ልጅ ትወልዳላችሁ አላቸው የማይመስላቸው ቢሆን ጊዜ ይፍታው እንጂ አንተስ አልፈታህውም ብለውት ተመለሱ ።
ዓለም ሳይፈጠር አስቀድሞ በሕሊና አምላክ ታስባ ትኖር የነበረች እመቤታችን የተነገረላት ትንቢት ሊፈጸም የአባት የእናቷ ራዕይ ሊተረጐም ጌታ የፈቀደበት ጊዜ ሲደርስ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል መጥቶ ኢያቄምን ሚስትህ ሐና ትጸንሳለች ደግ ልጅም ትወልዳለች አለው ።
ዝሙት ይሆንብናል ብለው ምንጣፍ ለይተው ይኖሩ ነበር ፈቃዱስ ከሆነ ብለው በአንድ ምንጣፍ አድረዋል እመቤታችን በዚሁ ሌሊት ተፀንሳለች ።

subscribers to boost the channel using this link: https://t.me/OrtoMezmur21?boost. As your channel receives more boosts, it will level up – with each level unlocking additional benefits.
✝️ድንግል ትንሳኤሽን
ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ
ገብተናል ሱባዔ በአንድነት በመንፈስ
ለእኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት
አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነ ምህረት (፪)
ሞትን የረገጠ ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው
ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው
የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል
ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል
ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር
ለምን ተስወረን የትንሳኤሽ ምስጢር
በራችንን ዘግተን በፀሎት ወድቀናል
ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል
መዝሙረኛ አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል
ሞትን የማያይ ስው ማን አለ ብሎናል
ይህ እውነት በዘመን አንቺ ላይ ቢደርስም
በሞት ተሽንፏል መቃብር አይኖርም
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል
ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን
ስለ ሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን
እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት
ድንግል አሳስቢልን ኪዳነ ምህረት
ሞትማ በሞት ተሽንፏል
በአንቺ ላይ እንዴት ኃይል ያገኛል
መዝሙር
🎙በሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴድሮስ ዮሴፍ
"እነሆ በፆማችሁ ቀን..."
ኢሳ ፶፰ ፥ ፩-፲
👋 You own a popular channel – @OrtoMezmur21. Now you can customize its appearance so that your channel will stand out among others.
These features are exclusive and require your channel to reach a specific level to access them. Just ask your subscribers to boost the channel using this link: https://t.me/OrtoMezmur21?boost. As your channel receives more boosts, it will level up – with each level unlocking additional benefits.
Also, you can host a 🎁 giveaway in your channel, gifting Telegram Premium to random subscribers. Each gifted subscription will add 4 boosts to your channel. The giveaway feature has just been upgraded – now offering a longer duration, options to include additional prizes, and a public list of winners.
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 