fa
Feedback
ኦርቶዶክስ መዝሙር(Ortodox Mezmur)

ኦርቶዶክስ መዝሙር(Ortodox Mezmur)

رفتن به کانال در Telegram

በእንግድነቴ አገር ሥርዐትህ መዝሙር ሆነችኝ።መዝ-118:54 ሸር በማድረግ ተባበሩን👇👇👇 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

نمایش بیشتر
7 407
مشترکین
-824 ساعت
-317 روز
-2730 روز
آرشیو پست ها
+5
አርጋኖን_የእመቤታችን_ምስጋናዘሠሉስ_ማክሰኞ_0.m4a40.17 MB

መጸለይ ባንችል ቢያንስ ብቻችንን ስንሆን እናድምጥ https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

መርቆሬዎስ  የችግሬ ደራሽ መርቆሬዎስ /2/ የችግሬ ደራሽ ና በፈረስ እንባዬን ልታብስ ፈጥነህ ድረስ ባስልዮስ ጎርጎሪወቀስ ሰምሯል ልመናቸው ስዕሉ ዘለለ ታምራት አያችሁ እናንተን የረዳ መጥቶ በፈረስ ዛሬም ለኛ ይድረስ ይምጣ መርቆሬዎስ ዑልያኖስ ተገድሏል ሃይማኖት ይስፋፋል ብሎ መሰከረ መርቆርዮስ ሃያል ገፀ ከላባቱ ባህርይ ቀየሩ እርሱን ለማገልገል ከእግሩ ስር አደሩ ትካዜ ሀዘኔ ይርቃል ጭንቀቴ መርቆርዮስ ሲመጣ ሲገባ ከቤቴ በፀሊም ፈረሱ እየገሰገሰ መርቆሬዎስ ወዳጄ ስጠራው ደረሰ ስቃዩን ሊያረዝም ዳኪዎስ ወደደ ከጨለማ እስር ቤት ታስሮ ተወሰደ በጋለ ሹል ብረት መርቆሬዎስ ተወጋ ስሙ ተሰየመ ከሰማዕት ጋ አልፈራም መከራ አልፈራም ችግር መፍቅሬ አብ ካለ ያኘሎፓዴር ቂሳርያ እስር ቤት መርቆሬዎስ ታሰረ ወህኒ ቤቱ በራ እግዚአብሔር ከበረ                መዝሙር ዘማሪ ዲ/ን ታዴዎስ ግርማ https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

መጸለይ ባንችል ቢያንስ ብቻችንን ስንሆን እናድምጥ

ጊዮርጊስ    ሰማዕተ እየሱስ የእውነት ምስክር ሕያው ነው በሰማይ ብፁዕ ነው በምድር ድራጎንን በጦር ወግቶ ገደለና ከሞት አፍ አዳነኝ ጊዮርጊስ ደረሰና/2/ የሀዘን ማዕበል እንዳያንገላታኝ ተዓምር ሰሪው ሰማዕት ፈጥኖ አረጋጋኝ በእግዚአብሔር ጣዕም በፍቅሩ ተጠምዷል ይህን ዓለም ንቆ በክብር አጊጧል ኦ ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ንፋስ ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ አድናት አገሬን ከገጠማት ትካዝ እርሱን ለምጠራው ሲመሽም ሲነጋ ዋስ ጠበቃዬ ነው በነፍስም በሥጋ ድንቅን የሚፈጽም ኃያል ሰማዕት ነውገበዝ በቅድመ እግዚአብሔር ለእኔ የሚቆመው ኦ ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ንፋስ ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ አድናት አገሬን ከገጠማት ትካዝ የምስጋናን አውታር የታጠቀ ሰማዕት ስሙን ተሸክሞ የታመነ እስከ ሞት ሙታን የሚያስነሳ ስልጣን ተቀብሏል በአባቱ መንግስት እንደ ፀሐይ ደምቋል ኦ ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥነህ የምትደርስ ከአውሎ ንፋስ ስምህ የተጠራ የኢትዮጵያ ገበዝ አድናት አገሬን ከገጠማት ትካዝ                 መዝሙር ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ👇👇 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

4_5776090049380662344.mp37.59 MB

ምልክቴ ነሽ

ወሶበ ርእዩ ወነጸሩ ዘንተ ተአምረ ወመንክረ ዘተገብረ በኃይለ መስቀሉ ለክርስቶስ እግዚእ ንጉሠ ስብሐት አይሁድ እኩያን ወከሀድያን ወመናፍቃን ተመልኡ መዐተ ወቁጥዓ ወቅንአተ ሰይጣናዌ   ትርጉሙም      የክብር ባለቤት በሆነ በጌታ በክርስቶስ መስቀል ኃይል የተደረገውን ድንቅ ተአምር ባዩ በተመለከቱ ጊዜ ተጠራጣሪዎችና ከሀድያን ክፉዎች አይሁድ ሰይጣናዊ ቅናትን ቁጣና ብስጭትን ተመሉ     ድርሳነ መስቀል ዘመስከረም     በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን     እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ አደረስን      መስከረም ፲፯(17) በዓለ መስቀል ዕፅ መስቀል ዕሌኒ ንግሥት ቅዱስ ኪራኮስ አረጋዊ አው ወብጽዕት ወታዖግንስጣ ሮማዊት ቅዱስ መቃርስ ሊቀ ጳጳስ       ዘነግህ ምስባክ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ ከመ ያምስጡ እም ገጸ ቀስት ወይድኀኑ ፍቁራኒከ          ትርጉም ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው ወዳጆችህ እንዲድኑ        መዝ ፶፱-፬              59   4           ወንጌል ዮሐ ም ፫ ቁ ፲፬-፳፪           3     14   22         የቅዳሴ ምንባባት ፩ ጢሞ ም ፭ ቁ ፱-፲፮ ያዕቆብ ም ፫ ቁ ፲፩-ፍ.ም ግብ.ሐዋ ም ፭ ቁ ፳፮-፴፫         ምስባክ ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁኮ ከመ ያምስሑ እም ገጸ ቀስት ወይድኀኑ ፍቁራኒከ          ትርጉም ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው ወዳጆችህ እንዲድኑ        መዝ ፶፱-፬              59   4        ወንጌል ማቴ ፰ ቁ ፲፮-፳፰       8      16  28      ምስባክ ወረከብናሁ ውስተ ፆመ ገዳም ንበውዕ እንከሰ ውስተ አብያቲሁ ለእግዚአብሔር ወንሰግድ ውስተ መካን ኃበ ቆመ እግረ እግዚእነ          ትርጉም በዱር ውስጥ አገኘነው ወደ ድንኳኖች እንገባለን እግሮቹ በሚቆሙበት ስፍራ እንሰግዳለን        መዝ ፻፴፩-፮               131  6       ወንጌል ዮሐ ም ፲፱ ቁ ፳፭-፳፰           19     25   28       ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ " የፍቅር ጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ኀሊናም ይመታል፤ነፋስም ትንቀጠቀጣለች ሥጋም ይደክማል "     ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ               ም ፩ ቁ ፶፯                   1     57 በዓሉ በዓለ ድኀነት በዓለ ምህረት በዓለ ብርሃን ያድርግልን ቸሩ አምላክ ዘላለም ሥላሴ በቸርነቱ ይማረን ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅ ፍቅሯን ጣዕሟ በልባችን ታሳድርብን ከዕፀ መስቀሉ በረከት ይክፈልን በዕፀ መስቀል ይባረክን በዓል ተከተሎ ከሚመጣ መቅሠፍት አምላክ ቅዱሳን ይሰውረን ይጠብቅን በቅዱሳን ፀሎት ይማረን ከቀዳሚ ሰማዕት ከሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ በረከቱ ይደርብን ቤተክርስቲያን ቅድስት በረከት ይጠብቅልን ድርሳነ መስቀል መልክእ መስቀል ውዳሴ መስቀል ድርሳነ ሰንበት ገድለ ሰማዕታት የተቀበለ ዘላለም ሥላሴ የኛንም ፆም ፀሎት ምህላ ምሥጋና ምጽዋት በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ለቅዱስ ኤፍሬም ሶርያም ለቅዱስ ያሬድ ማኀሌታዊ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ለቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት ለቅዱስ ጎርጎርዮስ ነባቤ መለኮት ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ ለቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ለቅዱስ ዮሐንስ ዘደማስቆ ለአቡነ ሃብተማርያም ለአባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ለአባ መብዓፅዮን ለአባ ኪሮስ ለአቡነ ሀቢብ ለቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ለአፄ ዘርዓያዕቆብ ለአፄ ዳዊት ለአፄ ናዖድ ለአፄ ልብነድንግል ለአፄ ይምሐርነ ክርስቶስ ለአፄ አብርሃ ወአጽብሃ ለቅዱስ ጊጋር መስፍነ ሶርያም የተለመነች እመ አምላክ ለኛም በቸርነት ትለመነን ሁላችንም ለንስሐ ሞት ያብቃን ለቅዱስ ስጋው ክቡር ደሙ ያብቃን መልካም የመስቀል በዓል ይሁንላችሁ ለሃገራችን ለቤተክርስቲያን እንፀልይ                     ምስባክ  ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥ https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

መስቀል ብርሃን ኧኸ መስቀል ብርሃን ኧኸ ለኩሉ ዓለም/2/ ኧኸ መሰረተ መሰረተ ቤተክርስቲያን/2/ መስቀል ኃይላችን ነዉ መስቀል መጽናኛችን መስቀል የነፍሳችን መድኃኒት ሚጠብቀን ከክፉ ከጠላት ኧኸ መሰረተ መሰረተ ቤተክርስቲያን/2/ መስቀል አይሁድ ቢክዱትም መስቀል እኛ እናምነዋለን መስቀል ያመነውም እኛ በመስቀሉ ከደዌ ድነናል ኧኸ መሰረተ መሰረተ ቤተክርስቲያን/2/ መስቀል ለብዙ ዘመናት መስቀል ሲኖር ተሰውሮ መስቀል ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን ሆነ አልቀረም ተቀብሮ ኧኸ መሰረተ መሰረተ ቤተክርስቲያን/2/ መስቀል የመዳን አርማ ነው መስቀል አዳኝ የዋለበት መስቀል ከጠላት አገዛዝ ከዲያቢሎስ ነፃ የወጣንበት ኧኸ መሰረተ መሰረተ ቤተክርስቲያን/2/ መስቀል ለብዙ ዘመናት መስቀል ሲኖር ተሰውሮ መስቀል ለዓለሙ ሁሉ ብርሃን ሆነ አልቀረም ተቀብሮ ኧኸ መሰረተ መሰረተ ቤተክርስቲያን/2/             መዝሙር ዘማሪ ዲያቆን አድማሱ ዘሪሁን ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

እሰይ እልል በሉ እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2) እሰይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ (2) የጥል ግድግዳ አበባ የፈረሰበት አበባ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር  አበባ የታረቀበት አበባ የእግዚአብሔር ልጅ አበባ    የነገሰበት አበባ የሞት አበጋዝ  አበባ       የወደቀበት አበባ አይሁድ በቅናት አበባ           መስቀሉን ቀብረው አበባ ቢከድኑት እንኳን አበባ በቆሻሻቸው አበባ ጌታን መቃወም አበባ ስለማይችሉ አበባ ይኸው ተገኘ አበባ ወጣ መስቀሉ አበባ ደጉ ኪራኮስ   አበባ       ሽማግሌው  አበባ እሌኒን መራ አበባ በደመራው አበባ ጌታ በእርሱ ላይ አበባ በመሰቀሉ አበባ ጭሱ ሰገደ አበባ ወደ መስቀሉ አበባ       የእምነት ምልክት አበባ        መስቀል ነውና  አበባ ተራራው ሜዳ  አበባ ሆነ እንደገና አበባ እንደተነሳ አበባ ጌታ እንደቃሉ  አበባ ከጉድጓድ ወጣ አበባ ዕፀ መስቀሉ አበባ  እኛም በመስቀል አበባ እንመካለን  አበባ በእግዚአብሔር ጥበብ አበባ መቼ እናፍራለን አበባ ሞኝነት እንኳን አበባ ቢሆን ለዓለም አበባ ኃይል ጸወን ነው አበባ ለዘለዓለም አበባ ግድግዳው ፈርሷል  አበባ የልዩነቱ አበባ                              ምድርና ሰማይ አበባ                     ሆኑ እንደ ጥንቱ  አበባ                    ነፍስና ስጋ አበባ                        በእርሱ ታርቀዋል አበባ                 ሕዝብና አሕዛብ አበባ                    ወንድም ሆነዋል አበባ                             መዝሙር   ዘማሪ ዲ/ን አበበ ታዬ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ👇👇 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

ግሩማን መላዕክት ግሩማን መላዕክት የምትተጉ ለምሕረት ኧኸ ለሠው ድህነት ከልዑል ዘንድ ለምኑልን ቸርነቱን እንዲያደርግልን(2) እስራኤልን በጉዞአቸው (2) የመራሃቸው ሚካኤል ነህ ጠባቂአቸው ማዕበሉን ያሻገርካቸው ያበሰርካት ለድንግል (2) ኧኸ የሕይወት ቃል መልዕክተኛው ኧኸ ለልዑል መልአከ ኃይል ገብርኤል እናቶችን በጭንቃቸው (2) ኧኸ የምትረዳቸው ሩፋኤል ነህ ጠባቂአቸው በምጥ ጊዜ አዋላጃቸው ሡራፌል ወኪሩቤል አፍኒን ወራጉኤል ኧኸ ወሳቁኤል በልዑል ፊት የምትቆሙ ምልጃችሁን ሥለ እኛ አሰሙ። 👉ሼር https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

⚡️ብርሃን ወጣ ብርሃን ወጣ ከመስቀሉ የሚያንጸባርቅ፣ የአምላክ እና የሰው ልጆች እውነተኛ እርቅ፣ ደስ ይበለን በትንሣኤው ብርሃን፣ እልል እንበል በአንድነት ሆነን፣ ተነሣልን መድኃኒታችን።   ከፊት ለፊት በመሣሉ የመስቀሉ ነገር የሚወደው ሐዋርያ የወንጌል መምህር ዮሐንስም ስቅለቱን በማየቱ አለቀሰ እስከ ዕለተ ሞቱ ቢያሠቅቀው ሞቱ ግርፋቱ ሞኝነት ነው ለሚጠፉት መሰናከያቸው በዓለም ጥበብ ለሚኖሩት እውነት ተስኗቸው ለጠቢብ ሰው በመንፈስ ለሚኖረው የመዳን ቀንድ እውነተኛ አርማ ነው ከገሃነም እሳት የሚያድን ነው       እስከ መሞት ላልተለየው ቅዱስ ሐዋርያ ለዮሐንስ ለወንጌል ሰው የፍቅር ባለሞያ ምስጋናችን በምድር ይድረሰው እንድናለን በሰጠን ምሳሌው ሰዎች ሁሉ እንከተለው          መዝሙር በሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

ለማስታወስ ያክል
ለማስታወስ ያክል

ወረት የሌለው ወረት የሌለው መውደድ ወረት የሌለው ፍቅር አንተ ጋር ብቻ ነው ያለው እግዚአብሔር /2/ ዘመን የማይዘው ጊዜ የማይገድበው ያንተ ፍቅር ብቻ ቀን በቀን አዲስ ነው ከዴማስ ጋር ስሄድ ትቼው የአንተን መንገድ ከቶ መች ቀነሰ ለእኔ ያለህ መውደድ በአመጽ ብጠፋም ከመንጋህ መካከል ይመሻል ይነጋል እኔን ስትከተል እንደወጣ ይቅር ብለህ መቼ ተውከኝ ሴኬም ድረስ ወርደህ ልጅህን ፈለከኝ በዝናዬም ዘመን ባለጸጋ እያለሁ ቤቴ በወዳጆች ቀን በቀን ሙሉ ነው እንደ ጤዛ ሲረግፍ ሃብትና ንብረቴ ያላንተ ማን ነበር በፈርሰው ቤቴ የታመንኩባቸው ወዳጆች ሲከዱኝ ሕመሜ ስር ሆነው ደጋግመው ሲወጉኝ ላንተ ጊዜ ባጣም ለኔ ጊዜ አለህ ገፋህ ክፉ ቀኔን ከኔ ጋራ አብረህ                 መዝሙር      ዘማሪ ዲ/ን አቤል መክብብ

መሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ይነገራል ዘመን የሚዋጅ አለን ምስጋና መድሀኔዓለም ስመ ገናና/2/ እልፍ አእላፍ መላእክት ቢቆሙ ካንተ ፊት አያርፉም ይተጋሉ ስሉስ ቅዱስ እያሉ ያለና የሚኖር ያለና የሚኖር ሊቃናት ይጮሀሉ በጉ ድል ነሳህ እያሉ የወርቅ ፅናን የያዙ ምስጋናህን አበዙ ያለና የሚኖር  /2/ አንተ ነህ እግዚአብሔር በደምህ የታተሙ ሀይልህን ተሸከሙ የቅኔ ዑደት ሆነ  ክብርህ በአለም ገነነ: ያለና የሚኖር  /2/ አንተ ነህ እግዚአብሔር በዙፋንህ ስር ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ከታመነው ምስክር አዲስ ውዳሴ መዝሙር ያለና የሚኖር  /2/ አንተ ነህ እግዚአብሔር             መዝሙር ዘማሪ ገ/ዩሀንስ ገ/ፃዲቅ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21

መሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል ክብርህም በምድር ይነገራል ዘመን የሚዋጅ አለን ምስጋና መድሀኔዓለም ስመ ገናና/2/ እልፍ አእላፍ መላእክት ቢቆሙ ካንተ ፊት አያርፉም ይተጋሉ ስሉስ ቅዱስ እያሉ ያለና የሚኖር ያለና የሚኖር ሊቃናት ይጮሀሉ በጉ ድል ነሳህ እያሉ የወርቅ ፅናን የያዙ ምስጋናህን አበዙ ያለና የሚኖር  /2/ አንተ ነህ እግዚአብሔር በደምህ የታተሙ ሀይልህን ተሸከሙ የቅኔ ዑደት ሆነ  ክብርህ በአለም ገነነ: ያለና የሚኖር  /2/ አንተ ነህ እግዚአብሔር በዙፋንህ ስር ካሉት ከሰባቱ መናፍስት ከታመነው ምስክር አዲስ ውዳሴ መዝሙር ያለና የሚኖር  /2/ አንተ ነህ እግዚአብሔር             መዝሙር ዘማሪ ገ/ዩሀንስ ገ/ፃዲቅ ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያጋሩ

ለመላው ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ እንኳን ለአዲስ አመት ለዘመነ ማርቆስ ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን በዓሉ የሰላም እና የፍቅር ይሁንልን ! መጪው አመት የስኬት እንዲሁም የሀሴ
  ለመላው ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ  እንኳን ለአዲስ አመት ለዘመነ ማርቆስ ዘመን መለወጫ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን     በዓሉ የሰላም እና የፍቅር ይሁንልን ! መጪው አመት የስኬት እንዲሁም የሀሴት ይሁንልን !  ከምንም በላይ ሀገራችንን ሰላም ያርግልን ህዝቦቿን ከክፉ ነገር  ይጠብቅልን መልካም አዲስ አመት  ይሁንላችሁ  ይሁንልን

ምን ብትወደኝነው ምን ብትወደኝ ነው ምን ብታስበኝ አዲስ ዘመንን ቀን ያሳየኸኝ ኦ አምላኬ ዘመንን ካየሁ ከተሻገርኩኝ ኦ ጌታዬ እዘምራለሁ ስቡህ እያልኩኝ/2/ ጠዋትም የለኝ ካንተ በቀር ማለዳዬ ነህ ማምሻዬም አንተ አልሻገርም አንተ ካልፈቀድህ ማዕበል ወጀቡን አሳልፈህ ጨለማውን አብርተህ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/              አዝ አልፍ እንድትሆን አንተ የባረካት ከመሬት ወድቃ ትላንትናዬን ወዜን ባርከኸው ለዚህ ብበቃ ባጌጠችው የምድር መሀል ሆኜ እቀኛለሁ ስለአዳኜ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/               አዝ ፍሬ ፈልገህ መጣህ ወደኔ በብርሀን ጸዳል      ፀሐይ አውጥተህ ልትባርከው ጌታ ፈቅደሀል ያንተ ወንዞች ውሃ ከተሞሉ ተራራዎችም ምስጋናህን ያመጣሉ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/              አዝ ማለፍ በክንድህ አዲስ ዘመንን ላንተ መዋጀት ግዛው ዘመኔን ውረስ አምላኬ የኔን ማንነት አዝማናቱ ስራህን እያሳየ ልሁንልህ ከዓለም የተለየ በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/              አዝ ቀንን ብቆጥር ዘመን ባሰላ ካልተለወጥኩኝ ከጸጋህ ዙፋን በዕምነት ቀርቤ ካልተፈወስኩኝ ምን ሊረባኝ ካንተ ጋር ካላረጀሁ ያለቃልህ በዘመን እንዲያው ባውጀው በአዲስ ዘመን ጌታዬ ስራኝና ላገልግልህ በዜማዬ እንደገና/2/ ዘማሪ👉በአቤል መክብብ https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21