ኦርቶዶክስ መዝሙር(Ortodox Mezmur)
رفتن به کانال در Telegram
በእንግድነቴ አገር ሥርዐትህ መዝሙር ሆነችኝ።መዝ-118:54 ሸር በማድረግ ተባበሩን👇👇👇 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21 https://t.me/OrtoMezmur21
نمایش بیشتر7 414
مشترکین
-524 ساعت
-447 روز
-1730 روز
آرشیو پست ها
✞በምን ደስ ላሰኝህ ✞
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
ዓለምና መላው የአንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ የአንተው አይደለም ወይ(፪)
ኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ስሉስ ያሉህ
መላእክት በራማ የሚያመሰግኑህ
ድንቅ መካር ኃያል ኤልሻዳይ ነህና
ትቢያ ነኝ ምን ልስጥህ ምንስ አለኝና/፪/
ቅዱሱን መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ
ምን ይዤ ልምጣና ከአምላኬ ፊት ልስገድ
ወደላይ በሰማይ ወደታች በጥልቀት
አምላኬ የታለ የማትገኝበት
ጌታ ሆይ የታለ የማትገኝበት
በኪዳን በጸሎት ቅዳሴ ሰዓታት
አንተ የሰጠኸን የመንፈስ ቅዱስ ሐብት
መልሰን ወደ አንተ ብንሰጥ ምንድነው
ተወው ጉዳችንን ስስታችን ይኸው/፪/
ሐብት እና ንብረቴስ ጉልበቴስ ምንድነው
ጤናን የሰጠኸኝ ከአንተ በቀር ማንነየእኔ
በሰጠኸኝ እድሜ በሕይወት ዘመኔ
ከገላዬስ ቢሆን የትኛው ነው የእኔ
ከአካላቴስ ቢሆን የትኛው ነው የእ
_በምን_ደስ_ላሰኝህ_ዘማሪ_ዳግማዊ_ደርቤ_2018_የአእላፋት_ዝማሬ_መዝሙር_በጃን_ያሬድ_ኅብረ_ዝማሬ_የተዘመረ.MP412.05 MB
ጽዮን ሆይ እያልኩ
ጽዮን ሆይ እያልኩ እጠራሻለው
ቃሉን አፍርሼ ተራቁቻለው
ገባች ከአፌ በለሷን ቆረጥኩ
ወጣሁ ከገነት እያጎነበስኩ
አዝ-----
ከአምላኬ ይልቅ ሰማሁ ከሳሼን
በሐሰት መርቶ ናደብኝ ክብሬን
አውልቄ ጣልኩት የፀጋ ልብሴን
እርቃኔን ቀረሁ አፈርኩ እራሴን
የገነት ደጃፍ ቢዘጋም በሩ
አዩሽ አይኖቼ እያሻገሩ
ከንፁህ አካሌ ከዘሬ ቀርተሽ
ዳግም ከበርኩኝ ጌታዬን ወለድሽ
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
አልፎ ሌሊቱ ያለቀስኩበት/2/
አዝ-----
ከክብሬ ሐገር ወጣሁ ፈጥኜ
በደሌ ገፎኝ ራሴን ኮንኜ
ወደኔ መጣ ያ የሚወደኝ
ወዴት ነህ ልጄ አዳም እያለኝ
እንደምን ልየው እኔስ አፈርኩኝ
በከፋው ገድሌ ተሸማቀኩኝ
ሰይፍ አልያዘም ዛሬም ፍቅር ነው
ተስፋ የሰጠኝ ድንግል ከንቺን ነው
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
አልፎ ሌሊቱ ያለቀስኩበት/2/
አዝ-----
ጣቴ ቢቀሰር ወደ ሔዋኔ
በምክንያቶቼ አልዳንኩም እኔ
ትዕዛዙን ጥሼ ወጣሁ ከሀገሬ
ለፍቅር ሚዛን በቆመች ፍሬ
ጸጋ ከሞላው ከሕይወት ሀገር
ማን ይመልሰኝ ለማን ልናገር
አንቺን በተስፋ ተጠባበኩኝ
የገባልኝን ቃል እያሰብኩኝ
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
አልፎ ሌሊቱ ያለቀስኩበት/2/
አዝ-----
ትንቢቱ ደርሶ እስከሚፈጸም
ዓይኔ በተስፋ አልተከደነም
ናፈቀች ነፍሴ የአንቺን መወለድ
የዕዳ ፅህፈቴ እስከሚቀደድ
የእውነት ነው ቃሉ ጊዜው ደረሰ
ከአንቺ ተወልዶ ክሴ ፈረሰ
የሕይወት በሬን ቁልፍ አጊንቻለሁ
ባፈሰሰው ደም ተቀድሻለሁ
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
በልጅሽ ማኅተም ገባሁኝ ከገነት/2/
ጽዮን ሆይ እያልኩ
ጽዮን ሆይ እያልኩ እጠራሻለው
ቃሉን አፍርሼ ተራቁቻለው
ገባች ከአፌ በለሷን ቆረጥኩ
ወጣሁ ከገነት እያጎነበስኩ
አዝ-----
ከአምላኬ ይልቅ ሰማሁ ከሳሼን
በሐሰት መርቶ ናደብኝ ክብሬን
አውልቄ ጣልኩት የፀጋ ልብሴን
እርቃኔን ቀረሁ አፈርኩ እራሴን
የገነት ደጃፍ ቢዘጋም በሩ
አዩሽ አይኖቼ እያሻገሩ
ከንፁህ አካሌ ከዘሬ ቀርተሽ
ዳግም ከበርኩኝ ጌታዬን ወለድሽ
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
አልፎ ሌሊቱ ያለቀስኩበት/2/
አዝ-----
ከክብሬ ሐገር ወጣሁ ፈጥኜ
በደሌ ገፎኝ ራሴን ኮንኜ
ወደኔ መጣ ያ የሚወደኝ
ወዴት ነህ ልጄ አዳም እያለኝ
እንደምን ልየው እኔስ አፈርኩኝ
በከፋው ገድሌ ተሸማቀኩኝ
ሰይፍ አልያዘም ዛሬም ፍቅር ነው
ተስፋ የሰጠኝ ድንግል ከንቺን ነው
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
አልፎ ሌሊቱ ያለቀስኩበት/2/
አዝ-----
ጣቴ ቢቀሰር ወደ ሔዋኔ
በምክንያቶቼ አልዳንኩም እኔ
ትዕዛዙን ጥሼ ወጣሁ ከሀገሬ
ለፍቅር ሚዛን በቆመች ፍሬ
ጸጋ ከሞላው ከሕይወት ሀገር
ማን ይመልሰኝ ለማን ልናገር
አንቺን በተስፋ ተጠባበኩኝ
የገባልኝን ቃል እያሰብኩኝ
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
አልፎ ሌሊቱ ያለቀስኩበት/2/
አዝ-----
ትንቢቱ ደርሶ እስከሚፈጸም
ዓይኔ በተስፋ አልተከደነም
ናፈቀች ነፍሴ የአንቺን መወለድ
የዕዳ ፅህፈቴ እስከሚቀደድ
የእውነት ነው ቃሉ ጊዜው ደረሰ
ከአንቺ ተወልዶ ክሴ ፈረሰ
የሕይወት በሬን ቁልፍ አጊንቻለሁ
ባፈሰሰው ደም ተቀድሻለሁ
ማርያም ልበልሽ የተስፋ ስንቄ
አከብርሻለሁ ፊትሽ ወድቄ
በዘርሽ ወድቋል የሞት ሰንሰለት
በልጅሽ ማኅተም ገባሁኝ ከገነት/2/
✝️ ጾመ ነብያት ✝️
#ጾመ_ነቢያት (የገና ጾም) ከ"ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት" መካከል አንዱ ሲሆን “ጾመ ነቢያት” የተባለበት ምክንያት ነቢያት ስለጾሙት ነው፡፡
📌“ነቢያት የጾሙት ስለምንድን ነው?” ቢሉ ለአዳም የተሰጠውን “አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈጸም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ” የሚለውን የተስፋ ቃል በማሰብ ከሰማየ ሰማያት ይወርዳል፣ ከድንግል #ማርያም ይወለዳል፣ በሞቱም ሞት የተፈረደበትን የሰው ልጅ ነፃ ያወጣዋል ብለው ነው፡፡
📌“ይህንን ጾም የትኞቹ ነቢያት ናቸው የጾሙት?” ቢሉ ሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ 40 ቀን ጾሟል (ዘፀ 34፡27)፤ ነቢዩ ኤልያስም 40 ቀን ጾሟል (1ኛ ነገ 19፡1)፡፡ በተጨማሪም በተለያየ ዘመን የነበሩት ነቢዩ ዕዝራ፣ ነቢዩ ነህምያ፣ ነቢዩ ዳንኤል እንዲሁም ክቡር ዳዊት ጾመዋል፡፡
📌"ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ብለው ከጾሙ፤ እኛ እርሱ ወርዶ፣ ተወልዶ ተሰቅሎ ካዳነን በኋላ ያለን የሐዲስ ኪዳን ክርስትያኖች ስለምን የነቢያትን ጾም እንጾማለን?” ቢሉ እኛ የነቢያትን ጾም የምንጾመው እንደቀደሙት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያልን ሳይሆን የቀደሙት ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል እያሉ የጾሙትን በማሰብ በመጾማችን ድኅነተ ሥጋ፣ ድኅነተ ነፍስ፣ በረከተ ሥጋ፣ በረከተ ነፍስ እንድናገኝበት ነው፡፡”ጾመ ነቢያት (የገና ጾም) ከኅዳር 15 ጀምሮ እስከ ታኅሳስ 29 ቀን (በዘመነ ዮሐንስ እስከ ታኅሳስ 28 ቀን) ድረስ ለ44 ቀናት (በዘመነ ዮሐንስ ለ 43 ቀናት) ይጾማል፡፡ ከእነዚህም መካከል 40 ቀናት ጾመ ነቢያት፣ 3 ቀናት ጾመ አብርሃም ሶርያዊ ሲሆኑ የቀረው 1 ቀን ደግሞ የገሃድ ጾም ነው (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 15 ቁጥር 565፣ 567)፡፡ ጾመ ነቢያትን ከኅዳር 15 ጀምሮ ሳይጾሙ የልደትን ዋዜማ ብቻ መጾም የቤተክርስቲያን ሥርዓት አይደለም፡፡
➡️ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፦
✨፩. ጾመ አዳም
✨፪. ጾመ ነቢያት
✨፫. ጾመ ሐዋርያት
✨፬. ጾመ ማርያም
✨፭. ጾመ ፊልጶስ
✨፮. ጾመ ስብከት
✨፯. ጾመ ልደት
✨ጾመ አዳም፦ አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ ፥ ተክዞ ፤ አለቀሰ [እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ ፤ እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ] ፥ ጾመ፣ ጸለየ፡፡ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም #እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ ፣ በደጅህ ድኼ ፣ በዕፀ #መስቀል ተሰቅዬ፣ ሞቼ አድንሃለሁ፡፡" የሚል ነው፡፡ [ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ] ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ ፥ የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡
✨ጾመ ነቢያት፦ ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ፣ #ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች : ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም : ቅዱስ ሙሴ : ቅዱስ ኤልያስ ፣ ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: [ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬] ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ: #ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል:: ለሞትም አብቅቶታል::
✨ጾመ ሐዋርያት፦ ሐዋርያት "ትንሣኤ
#የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ለከሃዲያን/አርዮሶች መልስ ለመስጠት
1: ሥለ ሥላሴ
የእግዚአብሔር አንድነትና ሶስትነት:-
🔹ዘፍ 1:26 ዘፍ 3:22
🔹ዘፍ 11:18 ዘፍ 18:1-2
🔹ኢሳ 48:26
ማቴ 3:16-17
🔹ማቴ 28:19 ሉቃ 1:35
🔹ዮሐ 7:28-29
ዮሐ 14:25-26
🔹የሐ.ስራ 3:14 1ኛ ቆሮ 12:4-7
🔹2ኛ ቆሮ 13:14 ኤፌ 4:4-7
2: #የእመቤታችን ቅድስናዋ ፣ ክብሯ ፣ ድንግልናዋንና አማላጅነቷ:-
🔹መዝ 9:11 መዝ 13:10
🔹መዝ 44:9 መዝ 86:5
🔹መዝ 131:13 መዝ 44:2
🔹መኃ 4:12 ኢሳ 7:14
🔹ኢሳ 49:23 ኢሳ 60:14
🔹ማቴ 1:23 ሉቃ 1:28
🔹ሉቃ 1:42 ዮሐ 2:1-11
🔹ዮሐ 19:16 ሮሜ 11:26-27
🔹2ኛ ቆሮ 11:2 ራዕ 12:16
3: #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ፈራጅ እንጅ አማላጅ አይደለም፡-
🔹ዘፍ 3:22 1ኛ ሳሙ 16:1
🔹ኢሳ 9:6 ዳን 7:14
🔹ሆሴ 13:4 ዘካ 9:9-10
🔹ሚክ 5:2 ሉቃ 1:32-33
🔹ዮሐ 10:30 ሉቃ 2:12
🔹ዮሐ 14:7 ሮሜ 9:5
🔹ቆላ 2:9-10 ቲቶ 2:11-13
🔹ዕብ 1:3-4 ዕብ 1:10-11
🔹1ኛ ጴጥ 3:23 1ኛ ዮሐ 2:23
🔹ራእ 3:22 ራእ 22:12-13
4:#ስለታቦት እና ፅላት
🔹ዘፃ 24:12 ዘፃ 25:10
🔹ዘፃ 25:21 ዘፃ 26:34
🔹ዘፃ 31:18 ዘፃ 32:15
🔹ዘፃ 34:1 ዘፃ 34:28
🔹ዘፃ 37:1 ዘፃ 40:20
🔹መኃ 7:89 ኢያ 3:3
🔹ኢያ 7:6 2ኛ ቆሮ 6:16
5: #ሥለ_ፆም_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ማሥረጃ:-
🔹ዘፃ 34:28 ዘፃ 9:9
🔹ሳሙ 20:26 1ሳሙ 7:6
🔹1ሳሙ 31:13 2ኛ ሳሙ 1:12
🔹2ኛ ሳሙ12:16 ዕዝ 8:21
🔹ዕዝ 68:10 ዕዝ 108:24
🔹ኢሳ 48:3 ኤር 36:9
🔹ዳን 9:3 ዳን 20:2-3
🔹ኢዩኤ 2:14 ኢዩኤ 2:12
🔹ዩና 3:5 ማቴ 4:2
🔹ማቴ 6:16:18 ማቴ 9:14-15
🔹ማቴ 17:21 ማር 2:18
🔹ማር 9:29 ሉቃ 2:37
🔹ሉቃ 18:12 የሐ.ስራ 13:3 🔹የሐ.ስራ 14:23 2ኛ ቆሮ 11:17
6: #መስቀል_በመጽሐፍ ቅዲስ:-
🔹ማቴ 10:38 ማቴ 16:20
🔹ማር 8:34 የሐ.ስራ 5:30
🔹1ኛ ቆሮ 1:18 ገላ 3:13
🔹ገላ 6:13 ፊል 2:8
🔹ፊል 3:18
7: #ጥምቀትን_በተመለከተ:-
🔹ሕዝ 36:25 ማቴ 3:5-6
🔹ማቴ 26:19-20 ማር 1:4-5
🔹ማር 16:16 ሉቃ 3:21
🔹ዮሐ 3:5 ዮሐ 3:22
🔹ኤፌ 4:5 ገላ 3:26-27
🔹የሐዋ 19:4 የሐዋ 18:8
🔹የሐዋ 13:24 የሐዋ 10:47 🔹የሐዋ 9:18 1ኛ ቆሮ 1:16
🔹1ኛ ቆሮ 10 :2 1ኛ ቆሮ 12:13
8:#ስዕለትን_በተመለከተ:-
🔹ዘኁ 28:20 ዘኁ 21:2
🔹ዘፃ 23:21 መሳ 11:30
🔹መዝ 49:14 መዝ 75:11
🔹1ኛ ሳሙ 1:11 መክ 5:4-5
🔹ዮና 2:10 ናሆ 1:15
🔹የሐዋ 18:18
9: #ፃድቃን_ሠማዕታት ያማልዳሉ:-
🔹ዘፍ 18:17-18 ዘፍ 18:23:24
🔹ዘፍ 20:7 ዘፍ 33:3
🔹ዘፍ 42:6 1ኛ ሳሙ 28 :14
🔹2ኛ ሳሙ 1:2 2ኛ ነገ 1:13
🔹2ኛ ነገ 2:15 2ኛ ነገ 4:9
🔹2ኛ ነገ 4:32-35 መዝ 88:34
🔹ማቴ 18:18 ዮሐ 20:23
🔹የሐዋ 10:25 የሐዋ 16 :29
🔹1ቆሮ 6:1-2 ፊሊ 4:6
🔹1ኛጢሞ 5:17 ያዕ 5:14
🔹ራዕ 14:13
10: #መላዕክት_ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ይቆማሉ:-
🔹መዝ 148:2 ኢሳ 6:3
🔹ማቴ 4:12 ማቴ 18:10
🔹ማቴ 25:31 ማር 8:38
🔹ራእ 1:11 ሉቃ 1:19
11: #መላዕክት_ፀሎታችን ወደ እግዚአብሔር ያደርሳሉ:-
🔹ጦቢ 12:15 ሉቃ 15:10
🔹የሐዋ 10:4 እዩብ 25:3
🔹ኤር 33:22 ዳን 7:10
🔹ሄኖ 10:1 ራዕ 5:11
12:#ለመላዕክት_የአክብሮት ስግደት ይገባል:-
🔹ዘፍ 19:1 ማኅ 22:31
🔹ኢያ 5:14 ዳን 8:16-17
13:#መላዕክት አብሣሪያን ናቸው:-
🔹ዘፍ 16:11 ሉቃ 1:13
🔹ሉቃ 1:19 ሉቃ 1:30-31
🔹ሉቃ 2:10-11
14:#መላዕክት_በአደጋ_ጊዜ ፈጥነው ይደረሣሉ:-
🔹ዘፍ 22:11-12 መዝ 90:11-12
🔹ዳን 6:22 ዳን 10:13
🔹ማቴ 2:13 የሐዋ 5:19-20
🔹የሐዋ 12:7
15: #ፀበል_መርጨት ያስፈልጋል:-
🔹ዘኁ 19:20
10ቱ_መዓርጋተ_ቅዱሳን_10ሩ_የቅዱሳን_የቅድስና_ደረጃዎች_ትርጓሜና_ምስጢራት_#eotc_#mk_#Ethiopia.M4A29.38 MB
✝አምላከ_እስራኤል✝
አምላከ እስራኤል ክበርልኝ
በዘለዓለም ፍቅር የወደድከኝ
ክንድህ ዘወትር ያበረታኛል
እንዳንተ ያለ ከየት ይገኛል
ክብርህን ሳየው እጅግ እጠግባለሁ
በረከት ሆነህ ጓዳዬን ሞላኸው
የአምላኬ ስራ ሁሌም ይደንቀኛል
እንዳንተ ያለ ከወዴት ይገኛል
ውለታህ ብዙ ተነግሮ አያልቅም
ኃጢአተኛ ነው ብለህ ሰው አትንቅም
ጠላት ሊወግረኝ ድንጋይን ቢያነሳ
አንተ ሆንክልኝ ከባቴ አበሳ
በደልን ከድኖ ሞገስን የሚሰጥ
በተኩላ መሃል ልጆቹን የሚመርጥ
ማን እንደ ጌታ ርኅሩኅ አለና
እስኪ ለስሙ እናቅርብ ምስጋና
ምህረትህ በዝቷል ለእኔ ያደረከው
የኃጢአቴን ቅርፊት ከእኔ አስወገድከው
ላመስግን አንተን ባለውለታዬን
አትረፍርፎ ታል በረከት ጓዳዬን
ዘማሪ ዳግማዊ ደርቤ
https://t.me/OrtoMezmur21
https://t.me/OrtoMezmur21
https://t.me/OrtoMezmur21
