fa
Feedback
LEARN TECH ||ethiopia ®

LEARN TECH ||ethiopia ®

رفتن به کانال در Telegram

We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share

نمایش بیشتر
1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
የኦሾ_ትንታኔዎች_በፍቅር_እና_በንቃት_ዙርያ_.doc0.24 KB

እሳት_ወይ_አበባ፤_ሎሬት_ጸጋዬ_ገመድህን_የግጥም_መድብል.pdf1.13 MB

❓ምሁራን ስለ ጥያቄ(?) ምን አሉ...❓ ⁉️ " የትኛው ላንተ የተሻለ መሆኑን የሚያውቀው ያው ጥያቄውን ያመነጨው ልብህ ነው ። " /ሊዮ ቶልስቶይ/ ⁉️ " የምትጠይቃቸው ጥያቄዎች ትኩረትህን አስተሳሰብህን ስሜትህን እና ራስህን ይወስናሉ ። " / አንቶኒ ሮቢንስ / ⁉️ " ያላችሁን እምቅ ሃይል ካልጠየቃችሁ በስተቀር ይዛችሁት ነው የምትሞቱት ።" / ዶክተር ማይልስ ሙንሮ / ⁉️ " ብዙ በማውራት ወይም በመለፍለፍ የተማርኩት ምንም የለም ። በመጠየቅ ከጠየኩት በላይ ተምሬአለሁ ። " / ሉ ሆልትዝ / ⁉️ " የሰው ልጅ ሁሉ ራሱን መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ይህች አለም ተስማሚ ናት? ብሎ ነው ። " / አልበርት አንስታይን / ⁉️ " የሚጠይቅ ሰው ለ 5 ደቂቃ ጅል ይሆናል ፤ የማይጠይቅ ግን ዘላለሙን ጅል እንደሆነ ይቀራል ። " / ቻይና / 🗒 ምንጭ 📰 ንግሥት መጽሔት ቅጽ 15 ታህሳስ 2011 እትም 📰 ፨ ለተጨማሪ መረጃ ፦ የቻይና የተባለው ንግግር የፈላስፋው ኮንፊሽየስ እንደሆነ የሚናገሩ መጽሐፍትም አሉ ። https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

በደቡብ ኮሪያ የማሳጅ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ማየት የተሳናቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ! @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom
በደቡብ ኮሪያ የማሳጅ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት ማየት የተሳናቸው ሰዎች ብቻ ናቸው ! @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom

በዙሪያችን አራት አይነት ሰዎች አሉ። 1,የማያውቅ እና እንደማያውቅ የማያውቅ ፦እንዲህ አይነቱ ሰው ሞኝ ነውና አትከተለው። 2,የማያውቅ እና እንደማያውቅ የሚያውቅ፦እንዲህ አይነቱ ሰው ያልበሰለ ነውና
በዙሪያችን አራት አይነት ሰዎች አሉ። 1,የማያውቅ እና እንደማያውቅ የማያውቅ ፦እንዲህ አይነቱ ሰው ሞኝ ነውና አትከተለው። 2,የማያውቅ እና እንደማያውቅ የሚያውቅ፦እንዲህ አይነቱ ሰው ያልበሰለ ነውና አስተምረው። 3,የሚያውቅ እና እንደሚያውቅ የማያውቅ፦እንዲህ አይነቱ ሰው ያንቀላፋ ሀያል ነውና ቀስቅሰው። 4,የሚያውቅ እና እንደሚያውቅ የሚያውቅ፦እንዲህ አይነቱ ሰው መሪ ነውና ተከተለው። ወደ ማወቅና ያወቅነውንም በማወቅ ወደ መደላደል ለመዝለቅ በመጀመሪያ መሪ እንደሆንን ማመን አስፈላጊ ነው።የተፅኗችን ስፋት ይለያይ እንጂ በዚህ ምድር ላይ እንደመሪ ሌሎች የማያዩት ሰው የለም።ታላቅ ለታናሹ፣አባት ለልጁ፣አስተማሪ ለተማሪው፣በእድሜ የገፉ ለአፍላዎች......እያለ የአመራሩ ሃላፊነት ይቀጥላል። በመቀጠልም የተማሪነት ልቦናና በአመራር ለማደግ ፅኑ ፍላጎት የግድ ነው።መማር ያቆመ ሰው ማደግ ያቆመ ሰው ነው።ማደግ ያቆመ ሰው ደግሞ መኖር ያቆመ ሰው ነው።ይህ እንዳይሆን የተማሪነትን መንፈስ መያዝና ካለማቋረጥ አዳዲስ እይታዎችን ለማዳበር መጣጣር አስፈላጊ ነው። "መሪዎች በሂደት ወደ መሆን ይመጣሉ እንዲ መሪ ሆነው አይወለዱም። እንደማንኛውም ነገር በብርቱ ስራና ጥረት ወደ መሆን ይመጣሉ።" -Vince Lombardi #ኢዮብ_ማሞ #አመራርAtoz https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

"በዶ/ር ኢዮብ ማሞ የተጻፉ መጽሐፎችን ለጠየቃችሁኝ!" 📜1. አመራር A to Z 📜2. 25 የስኬት ቁልፎች 📜3. የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ 📜4. የስሜት ብልህነት 📜5. እይታ 📜6. ትኩረት �
"በዶ/ር ኢዮብ ማሞ የተጻፉ መጽሐፎችን ለጠየቃችሁኝ!" 📜1. አመራር A to Z 📜2. 25 የስኬት ቁልፎች 📜3. የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ 📜4. የስሜት ብልህነት 📜5. እይታ 📜6. ትኩረት 📜7. የማንነትህ መለኪያ 📜8. ሁለንተናዊ ብልጽግና 📜9. የትራንስፎርሜሽን አመራር 📜10. የአለማችን አስቸጋሪ ሰዎች 📜11. ራስን ማሸነፍ 📜12. የገንዘብ ነጻነት አምዶች 📜13. የሕይወት ጸጸት 📜14. ገዢው ስሜት 📜15. ምርጫና ውሳኔ 📜16. ግንኙነትና አለመግባባትን መፍታት 📜17. የጥበብ መንገድ 📜18. ሁለቱ ክህሎቶች 📜19. አመኔታ 📜20. የመገፋት ሕመም 📜21. የፍቅር ሕይወት 📜22. ጀምሮ መጨረስ https://t.me/abyssinianwisdom

ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ይባላል። የእመጓ፣ የዝጎራ መርበብት እና ሚተራሊዮን መፃሕፍት ደራሲ ነው። የሚኖረውን የሚያስተምር ብርቱ ሰው ነው። ስለሱ የሰማሁትን እውነታዎች ልንገራችሁ... ➊. በሚሰራበት መ
ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ ይባላል። የእመጓ፣ የዝጎራ መርበብት እና ሚተራሊዮን መፃሕፍት ደራሲ ነው። የሚኖረውን የሚያስተምር ብርቱ ሰው ነው። ስለሱ የሰማሁትን እውነታዎች ልንገራችሁ... ➊. በሚሰራበት መስሪያቤት <<ጠንካራ ስራ አስኪያጅ ስለሆንክ ደመወዝህን በእጥፍ አሳድገንልሀል>> ተብሎ በቦርድ የተወሰነለትን ደመወዝ አልቀበልም ብሎ በደብዳቤ መልሷል። ➋. ከአንድ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ውስጥ ለስራ ተወዳድሮ ካለፈ በኋላ፣ ደመወዙ ስለበዛ ቅጥሩን ሰርዞ ያውቃል(80,000 ብር)። ➌ ከወር የቤትና የራሱ ወጪ ውጪ ያለውን የባንክ ገንዘቡን በየወሩ ለነዳያንና ለገዳማት ይሰጣል። የዶክተር አለማየሁ መርህ ምን መሰላችሁ? የራሱንና የቤተሰቡን ኑሮ ስታንዳርድ አበጅቷል። "ቤት አለኝ" ይልህና፤ "የቤቴን አይነት ግን አትጠይቁኝ" ይልሀል። "መኪና አለኝ" ይልህና፣ "የመኪናዬን አይነት ግን አትጠይቁኝ" ይልሃል። "የምኖረው ከተማ ነው" ይልህና፣ "የት ከተማ ግን እንዳትለኝ" ይልሀል። ምክንያቱም ይላል "ከቤት በላይ ቤት፣ ከመኪና በላይ መኪና፣ ከከተማ በላይ ከተማ አለ፤ ከቀበቶ በላይ እንኳን ቀበቶ አለ፣ የቀበቶ ስራው ግን ሱሪ እንዳይወልቅ ማድረግ ነው።" ይላል። ባጠቃላይ ዶክተር አለማየሁ ምኞትን በጥልቅ ጉድጓድ ቆፍሮ የቀበረ፣ የገንዘብን አቅም ያሰነሰ ምርጥ ሰው ነው። ሲናገር እና ሲያስተምር ደግሞ አዝናኝ ነው። የፃፋቸው አስደማሚ መፃሕፍት የሱን ህይወት ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። ምንጭ፡- ማህበረ ኢትዮጵያ https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

ለአሸናፍነት መገዛት.pdf2.77 MB

📌አሸናፍዎች የተለየ ነገር አያደርጉም ነገሮችን በተለየ መንገድ ይከውናሉ እንጅ 📌ሰላም ቤተሰቦቻችን ዛሬ አንድ ምርጥ መጽሐፍ ይዜላችሁ መጥቻለሁ 📚ርዕስ፦ለአሸናፍነት መገዛት 📚ደራሲ ፦ሺቭ ኬራ
📌አሸናፍዎች የተለየ ነገር አያደርጉም ነገሮችን በተለየ መንገድ ይከውናሉ እንጅ 📌ሰላም ቤተሰቦቻችን ዛሬ አንድ ምርጥ መጽሐፍ ይዜላችሁ መጥቻለሁ 📚ርዕስ፦ለአሸናፍነት መገዛት 📚ደራሲ ፦ሺቭ ኬራ በመላው🌎 አለም በ8 ቋንቋዎች ተተርጉሞ ከ1000,000 በላይ ቅጂዎች በላይ የተሸጠ አንብቡት ።

📜ጥንታዊ ምሳሌያዊ ንግግሮችን የያዘ መጽሀፍ ።

ይህንን ያውቃሉ ⁉️ በኢንዶኔዥያ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት ጎሳዎች ተነጥለው የሚኖሩት የዳኒ ጎሳ ሴቶች ባሎቻቸው ሲሞቱ ለነሱ ያላቸውን ፍቅር ፣ ክብር እንዲሁም ሀዘን ለመግለጽ በሚል የእጆቻቸውን ጣቶች
ይህንን ያውቃሉ ⁉️ በኢንዶኔዥያ ግዛት ውስጥ ከሚገኙት ጎሳዎች ተነጥለው የሚኖሩት የዳኒ ጎሳ ሴቶች ባሎቻቸው ሲሞቱ ለነሱ ያላቸውን ፍቅር ፣ ክብር እንዲሁም ሀዘን ለመግለጽ በሚል የእጆቻቸውን ጣቶች ይቆርጡታል. https://t.me/abussinianwisdom

ርዕስ #ሚተራሊዮን ደራሲ #አለማየሁ_ዋሴ "እየውልህ! አንተ ለእምነትህ አዳሪ፣ፈጣሪን የምትፈራ ጥሩ ክርስቲያን ነህ።እኔም በአላህ ላይ ያለኝ ኢማና፣ለነበዩ ያለኝ ክብር እንደምታውቀው ጥልቅ ነው።ሁለታ
ርዕስ #ሚተራሊዮን ደራሲ #አለማየሁ_ዋሴ "እየውልህ! አንተ ለእምነትህ አዳሪ፣ፈጣሪን የምትፈራ ጥሩ ክርስቲያን ነህ።እኔም በአላህ ላይ ያለኝ ኢማና፣ለነበዩ ያለኝ ክብር እንደምታውቀው ጥልቅ ነው።ሁለታችንም በእውነትና በቅንነት ባመንበት እየተጓዝን ነው" አለና ፈገግ ብሎ "ብቻ ከሁለት አንዳችን መጨረሻ ላይ ስህተት ሆነን መገኘታችን አይቀርም።" ሲል ሁላችንም ሳቅን። "እና ምን አሰብክ? አለው ዶ/ር ክበረ በዓል "እኔ ትክክል ሆኜ ከአላህ ፊት ስቀርብና <ወደ ጀነት ግባ> ስባል አንተ ስህተተኛ ሆነህ <ወደ ጀሀነም ሂድ> ስትባል "ቸሩ አላህ ሆይ ኪብሩን ጀነት አብረህ ካላስገባህ ብቻዬን አልገባም" እላለሁ ወይም ደግሞ አንተ ትክክል ሆነክ ክርስቶስ ፊት ስትቀርብ "ወደ ጀነት ግባ፣ነቢል ወደ ጀሃነም ይሂድ" ሲባል "እሱንም ጀነት ካላስገባህ እኔንም ጀሃነም አስገባኝ" ትላለህ።በዚህ መልክ ሁለታችንም Safe እንሆናለን" አለው። ንግግሩ የዶ/ር ክብረ በዓልን ብቻ ሳይሆን የኔንም እንባ አስመጣው። ድንገት ክብረ በዓል ብድግ ብሎ ግንባሩን ሳመውና፦"አይዞህ! በተለያዩ መንገድ ብንጓዝም በቅንነት እስከሆነ ድረስ ፈጣሪ ፍርዱን አይነሳም አለው። እዛው እንደተቀመጥኩ ፍቅራቸውና ባልንጀርነታቸው ደንዳናውን ልቤን ብስክስኩን አወጣው።ከዚያ በኃላ የሚነጋገሩትን ብዙም አልሰማሁም።በዚች ምስጢራዊት ሀገር እንደዚህ ያሉ ልበ-ንፁሀን ሰዎች በመኖራቸው ነው ምንጮች የሚፈልቁበት፣ወንዞች የሚፈሱት፣በደረቅ ሰማይ ደመና ዝናብ አርግዞ ጠለ-ምህረት የሚዘንብ፣ሰማይ ያለምሶሶ የረጋው፣ምድር ያለካስማ የፀናችው" እያልኩ በእጅጉ የመፅናናት መንፈስ ውስጤን አረሰረሰኝ ከሚተራሊዮን መጽሐፍ @Abyssinianwisdom @Abyssinianwisdom

ይህ የምትመለከቱት ኢራናዊ ግለሰብ ለ65 አመታት ያክል ገላው ውሀ እና ሳሙና ነክቶት አያውቅም።ይህም የሆነበት ምክንያት ውሀ እና ሳሙና ያሳምሙኛል ብሎ ስለሚያስብ ነው ! በቀን 1ፓኮ ሲጋራም ያጨሳል
ይህ የምትመለከቱት ኢራናዊ ግለሰብ ለ65 አመታት ያክል ገላው ውሀ እና ሳሙና ነክቶት አያውቅም።ይህም የሆነበት ምክንያት ውሀ እና ሳሙና ያሳምሙኛል ብሎ ስለሚያስብ ነው ! በቀን 1ፓኮ ሲጋራም ያጨሳል ! በመጨረሻም በ94 አመቱ ህይወቱ ልታልፍ ችላለች ! https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

አምስቱ የዓለማችን ታላላቅ ላይብረሪዎች 🏢1,"ላይብረሪ ኦፍ ኮንግረስ" በአሜሪካ የሚገኝ ሲሆን በውስጡ 32 ሚልየን ጥራዞችን ይዟል። 🏢2,"ብሪቲሽ ላይብረሪ" በብሪታንያ የሚገኝ ሲሆን በውስጡ 29 ሚሊየን ጥራዞችን ይዟል። 🏢3,"የደች ላይብረሪ" በደች የሚገኝ ሲሆን በውስጡ 22 ሚሊየን ጥራዞችን ይዟል 🏢4,"የሩሲያ አካዳሚ ላይብረሪ" በሩሲያ የሚገኝ ሲሆን በውስጡ 20 ሚለየን ጥራዞችን ይዟል። 🏢5,"የካናዳ ብሔራዊ ላይብረሪ" በካናዳ የሚገኝ ሲሆን በውስጡ 20,000,000 ጥራዞችን ይዟል። https://t.me/abyssinianwisdom

የሚተራልዮን መጽሐፍ ደራሲ ማነው?
Anonymous voting

ሊታነቡት የሚገባ በdale carnegie የተጻፈ ምርጥ መጽሐፈ ነው። ርዕስ፦how to stop worrying and.. ... ዘውግ፦የስነ ልቦና https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

የአለማችን ትልቁ እና በርካታ ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ ህንድ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አባውራው "ዚዮና ቻን" ይባላል ...... 39 ሚስቶችና 94 ልጆች አሉት ! https://t.me/abyssinianwis
የአለማችን ትልቁ እና በርካታ ሰዎች ያሉበት ቤተሰብ ህንድ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን አባውራው "ዚዮና ቻን" ይባላል ...... 39 ሚስቶችና 94 ልጆች አሉት ! https://t.me/abyssinianwisdom

"እግዚአብሔር ሆይ ከወዳጆቼ ጠብቀኝ" አለማችን ካፈራቻቸዉ ስመ ጥርና ታላላቅ ሰዎች አንዱ የሮማው ጁሊየስ ቄሳር መሆኑ ይታወቃል።ጁሊየስ ቄሳር ብሩተስ የሚባል አንድ የልብ ወዳጅ ነበረው። መቼም የትኛውም ታላቅ ሰው ያለ ጠላት እንዲኖር የተፈቀደ አይመስልምና ጁልየስ ቄሳርም ጠላቶች ነበሩት።እኚህ ጠላቶቹ ጁሊየስን ለማጥፋት ሲሞክሩ ስውን በወዳጁ በኩል ማጥፋት ቀላል በመሆኑ የልብ ወዳጁ የብሩተስ ርዳታ አስፈለጋቸው። ስለዚህ ቄሳር የውድ ሀገራቸው የሮማ እድገት እንቅፋት መሆኑን አሳመኑትና ብሩተስ የሚያምነውን ወዳጁን ለሚወዳት አገሩ ሲል ለማጥፋት ተስማማ። ጠላቶቹ ከጀርባው ነገር ሲጎነጉኑና ካራ ሲስሉ ከርመው ከቀናት በአንዱ ታላቁ ጁሊየስን ተረባረቡበት። እርሱም በጥንካሬ ሊቋቋማቸው ጣረ።ሆኖም በዚህ መሀል ያ የልብ ወዳጁ ብሩተስ ጩቤውን መዝዞ ሲወጋው "አንተም ብሩተስ? በማለት መከላከሉን አቆመ።ከዚያም የህይወቱ ፍፃሜ ሆነ። ቄሳርን የገደለው የጠላቶቹ ብርታት ሳይሆን የወዳጁ ክህደት መሆኑን ማንም አይስትም።"አንተም ብሩተስ?" በሚለው ልብን ስርስሮ የሚገባ የመጨረሻ ንግግሩ ውስጥ ብዙ ነገር መኖሩ ግልጽ ነው ።ወዳጅ ሊገድላችሁ ጦር መሣሪያ ይዞ በራፋችሁ ላይ ቆሞ ብታዩት እንኳ ቤታችሁን እየጠበቀላችሁ ነው የሚመስላችሁ።ታዲያ "እግዚአብሔር ሆይ ከወዳጆቼ ጠብቀኝ ፤ጠላቶቼን እኔው ጠብቃቸዋለሁ" ቢባል ምኑ ላይ ነው ክፋቱ? ከያልተንኳኩ በሮች መፅሐፍ ገፅ 22 የተወሰደ ጳውሎስ ፈቃዱ ጥበብ🇪🇹 ዘአቢስንያ🇪🇹 እንኳን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ። የተለያዩ የልቦለድ መጽሐፍትን ና ሌሎች የፍልስፍና መጽሐፍ ለማግኘት view channl የሚለውን ነክተው ይቀላቀሉ። https://t.me/abyssinianwisdom

👉 አንድ ወንድ ግንኙነት ካደረገ በኋላ የሚለቀቀው የሴመን(የወንድ የዘር ፈሳሺ) መጠን 400 ሚሊዮን ስፐርም ሴል አለው ይላል ሳይንስ። ስለዚህ በዚህ ሎጂክ መሰረት በሴት ልጅ ማህፀን ውስጥ ያ መጠን ቦታ ቢያገኝ 400 ሚሊዮን ህፃናት ይፈጠራሉ! ይህ 400 ሚሊዮን የወንድ ፈሳሺ እንደጉድ ወደ ሴት ማህፀን እየሮጠ ከ300-500 ብቻ ነው በህይወት የሚተርፈው። 👉 ሌላውስ? በመንገድ ላይ በድካም ወይም በሽንፈት ይሞታል። እነዚህ ከ300-500 ናቸው። ይህም ኦቪውል ላይ መድረስ ችለዋል። አንደኛው ብቻ በጣም ጠንካራው ኦቪውሉን ያዳብራል ወይም ኦቪውል ውስጥ ይቀመጣል። ያ እድለኛ አንተ ወይም እኔ፣ ወይም ሁላችንም ነን፡፡ ይህንን ታላቅ ጦርነት አስበው ያውቃሉ? 1. ስትሮጥ "አይን፣ እጅ፣ እግር፣ ጭንቅላት አልነበረም፣ ሆኖም አሸንፈሃል። 2. ስትሮጥ ሰርተፍኬት አልነበረህም ጭንቅላት አልነበረህም ግን አሸንፈሃል። 3. ስትሮጥ ምንም ትምህርት አልነበረህም፣ ማንም የረዳህ የለም ግን አሸነፍክ። 4. ስትሮጥ መድረሻ ነበረህ በአንድ ጭንቅላት ስትሮጥ ያንን መዳረሻ አላማ አድርገህ በመጨረሻ አሸነፍክ። - ከዚያ በኋላ ብዙ ህፃናት በእናት ሆድ ውስጥ ጠፍተዋል። አንተ ግን አልሞትክም 9 ወር ሞላህ - ብዙ ህፃናት በወሊድ ጊዜ ይሞታሉ አንተ ግን ተርፈሃል - በህይወት በመጀመሪያዎቹ 5 አመታት ብዙ ህፃናት ይሞታሉ አሁንም በህይወት አለህ - ብዙ ህፃናት በምግብ እጥረት ምክንያት ይሞታሉ። ምንም አልሆንክም -ብዙዎች ይህን አለምን ትተው ሄደዋል፤ አንተ አሁንም አለህ። 👉 ዛሬ ደግሞ ...... የሆነ ነገር ሲፈጠር ትደነግጣለህ ትበሳጫለህ ግን ለምን? ለምን የተሸነፍክ ይመስልሃል? ለምን በራስ መተማመን አጣችሁ? አሁን ጓደኞች፣ እህት ወንድሞች፣ ሰርተፍኬት፣ ሁሉም ነገር አሉህ። እጅና እግር አለ፣ ትምህርት አለ፣ ለማቀድ ጭንቅላት አለ፣ የሚረዳ ሰው አለ፣ ሆኖም ተስፋ ቆርጠሃል። በህይወት የመጀመሪያ ቀን ተስፋ ሳትቆርጥ ስትቀር በ400 ሚልዮን ሴመን የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ያለምንም አጋዥ ብቻውን ውድድሩን በተከታታይ በመሮጥ አሸንፈሀል። 🙏 የሆነ ነገር ሲፈጠር ቶሎ ተስፋ አትቁረጥ! 🙏 https://t.me/abyssinianwisdom

_OceanofPDF.com_The_Alchemist.pdf1.05 MB