LEARN TECH ||ethiopia ®
رفتن به کانال در Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
نمایش بیشتر1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
በአለማችን ላይ በጣም እየተነበቡ የሚገኙ 5 መጽሐፎች
📚1,The Holy Bible
📚2.The Holy Quran
📚3.Think and Grow Rich
📚4.The Da Vinci Code
📚5.The Power
https://t.me/abyssinianwisdom
"ሁሉን ነገር መፈለግ፣ ሁሉን መሻት፣ ያለገደብ ለመኖር ማሰብ የዚህ ዓለም ጣጣ፣ የድካም ምንጭ ነው። የምትጠቀምበትን ያክል ብቻ እወቅ፤ የሚያጠግብህን ያክል ብቻ ብላ፤ የሚያረካህን ያክል ብቻ ጠጣ፤ ሁሉን ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም ሁሉን ነገር ማግኘትም ዕዳ ይሆናል፡፡ ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም ሁሉን ማወቅ ደግሞ ሸክምም ይሆናል።''
📓 ዝጎራ
✍🏻 አለማየሁ ዋሴ
አሜሪካ ሲባል ብዙዎቻችን የምናውቀው በቀይ ምንጣፍ የሚመላለሱ ፊታቸውን በቀለምና በፓውደር የተቀባቡ ሞልቃቃ የፊልም ተዋንያን እና ዘፋኞችን ብቻ ይመስሉናል።ቁራጭ ጨርቅ ለብሰው እርቃናቸውን በቴሌቪዥን የሚታዩ እና ተጋቡ ተፋቱ የሚባልላቸው ብቻ ይመስሉናል አሜሪካውያን! እንደነዚህ አይነቶቹ አሜሪካ ቀሪውን አለም የምታደነዝዝባቸው ሞረፊን ናቸው።
አሜሪካ ግን አሜሪካ የሚያሰኟት ብልጭልጮች አይደሉም።በተዘጋ በር ውስጥ በትልቅ ፋብሪካ የብረት አረር የሚያነዳቸው፣በእያንዳንዱ ላብራቶሪ ውስጥ ኬሚካል የሚያቃጥላቸው በየጫካው በትል የሚበሉና ከአውሬ ጋር የሚታገሉ ፣ከምድር ወለል በታች መስኮት በሌለው ቢሮ ውስጥ 18 ሰአት የሚሰሩ ሳይንቲስቶች፣መሀንዲሶች ፣ባለሙያዎች ሀገር ናት አሜሪካ !
በየቀኑ የምትነግረን የምታሳየን ብልጭልጮችን እንጂ እንደዚ ለሙያ የተሰጡትን የሀገር ዋልታና ምሰሶ የሆኑትን ሳይንቲስቶች ተጋድሎ እና ምግባራቸውን ነግራን አታውቅም።
ከ ሰበዝ መፅሐፍ የተወሰደ ገፅ 77
አለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)
"ብልህ ሰው የትም ቢሆን መፍትሔ አያጣም!"⛏
በአንድ ከተማ የሚኖር አንድ በእድሜ የገፋ ሰው ነበር፡፡ በጓሮው በሚገኘውን ማሳ ቆፍሮ ድንች መትከል ፈልጎ እርጅና ተጫጭኖታልና አቅሙ አልፈቀደለትም፡፡ ሊረዳው የሚችለው ብቸኛ ልጁ ደሞ እስር ቤት ነው የሚገኘው፡፡ እናም አባት ለልጅ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ፃፈ፡፡
፡
"ውዱ ልጄ ምንም ጥሩ ስሜት አየተሰማኝ አይደለም፤ ምክንያቱም የድንቹን ማሳ መቆፈር አልቻልኩም፡፡ አለመቆፈሬን አልወደድኩትም፤ ምክንያቱም እናተህ አትክልት በጣም ነበር የምትወደው፡፡ አንተ እስር ቤት ባትሆን አውቃለሁ ትቆፍርልኝ ነበር ፤ አባትህ"
፡
በቀጣዩ ቀን አባት አጠር ያለ ፁሁፍ ደረሳቸው፡፡ "በፈጣሪ ስም ይዤካለው አባ ጓሮውን እንዳትቆፍረው፤ ሽጉጡን የቀበርኩት እዚያ ነው"
፡
ከሰዓታት በኀላ በደርዘን የሚቆጠሩ የFBI መርማሪዎችና ፖሊሶች የሽማግሊውን ጓሮ በሙሉ በቁፋሮ ምስቅልቅሉን አወጡት፤ ነገር ግን ምንም ሽጉጥ እዛ አልነበረም፡፡
፡
አባት በጣም ግራ በመጋባት አጠር አድርገው ለልጃቸው ምን እንደተፈጠረ እና ቀጣይ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ፃፉለት፡፡🤔
፡
ልጅ "አሁን ድንችህን ትከል አባ፤ ከዚህ ሁኜ ላደርግልህ የምችለው ነገር ቢኖር ይህን ብቻ ነው" ብሎ ፃፈላቸው፡፡😁
ያለንበት ነባራዊ ሁናቴ እኛን ሊወስነን አይገባም!
ዶ/ር ምህረት ደበበ ! https://t.me/abyssinianwisdom
ድንቅም አደል?
እስቲ ሰው ሞልቶ ባገሩ
ተትረፍርፎ በየበሩ
እያንዳንዱ በየግሉ
እንደዘበናይ እድሉ
ተገንጥሎ ለበኩሉ
ለየፊናው ለየቅሉ
ከነፍስ ወከፍ መደበሩ
አንድ ራሱን መሰወሩ
ለብቻው መነጋገሩ
ከጥላው መመካከሩ
በነፍስ ወከፍ መደበሩ
ከህልሙ መመካከሩ
ብቸኝነት ውጦት ሁሉ
ለፍሬም ባይሆን ለቃሉ
የተስፋን ችቦ መላሱ
ለውንም ባይሆን ላመሉ
እንደዘበናይ እድሉ
በምኞት ሱስ መዋለሉ
"ከዘመድ ከወዳጅ ጠለል"
ከስንቱ 'መዐት' መካከል
ለየብቻው በመገንጠል
በህልም አለም ለመንጠልጠል
ተደባብቆ ሲብሰለሰል
ጉድም አደል? ድንቅም አደል?
እሳት ወይ አበባ
ሎሬት ፀጋየ ገ/መድህን
https://t.me/abyssinianwisdom
