fa
Feedback
LEARN TECH ||ethiopia ®

LEARN TECH ||ethiopia ®

رفتن به کانال در Telegram

We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share

نمایش بیشتر
1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
📍ዕርቃንህን_እንደመጣህ_ዕርቃንህን ትሔዳለህ:: ,,,,,,ደካማ ሆነህ እንደመጣህ ደካማ ሆነህ ትሔዳለህ:: ያለ ገንዘብና ያለ ንብረት መጥተሃል ያለ ገንዘብና ያለ ንብረት ትሔዳለህ:: ለመጀመሪያ ጊዜ ሰውነትህን ያጠበህ ሌላ ሰው ነበር ለመጨረሻ ጊዜም ሌላ ሰው ያጥብሃል:: ,,,,,,,ሕይወት እንዲህ ናት:: ስለዚህ ብዙ ክፋት ማብዛት ምን ይጠቅማል? የበዛ ቅናት : የበዛ ግፍ : የበዛ ራስን መወደድና የበዛ ትዕቢት ምን ይጠቅማል? ባዶ እጃችንን ለምንሔደው ለምን እንዲህ እንሆናለን? በምድር ያለን ጊዜ በጣም ጥቂት ነውና በማይጠቅም ነገር አናባክነው:: 🌹_ሰናይ ሰንበት

ትውልድና ዘመን ❤️ፍቅር በዋጋ ሴክስ በነፃ የሆነበት አሳፋሪ ትውልድ ❤️ድንግልናን ከማስወሰድ በላይ ስልክን መሰረቅ በጣም የሚያስቆጭበት ትውልድ ❤️I Phone መያዝ ተምሮ ከመመረቅ በላይ የሚደሰትበት ትውልድ ❤️ሴቶች ከHIV ይልቅ እርግዝናን የፈሩበት አስነዋሪ ትውልድ ❤️እውነት ተዳፍኖ ውሸትና ክህደት እውነት መስሎ የታየበት አስፀያፊ ዘመን ❤️ህዝቡ ከፈጣሪ ይልቅ አሸባሪ ፣ ገዳይና ሌባን የሚፈራበት አስቀያሚ ዘመን ❤️ገንዘብ ከቤተሰብና ከጓደኛ በላይ የተወደደበት ርካሽ ትውልድ ❤️በፍቅረኛ ላይ ሌላ ካልደረቡ "ፋራ" ተብሎ ሰውን የሚሳደቡበት ትውልድ ❤️ሰው ሞልቶ ተርፎ ብቻን እንዲኖሩ ያስገደደ አሳዛኝ ዘመን ❤️ለፍቅር መታመን ፣ ለፍቅር መሰደድ ፣ ለፍቅር መሰቃየትና መሞት እንደ ሞባይል game የተቆጠረበት ቅስም ሰባሪ ትውልድ ❤️ባልና ሚስት የማይተማመኑበት መሽቶ ላይነጋ የጨለመ ዘመን ❤️ወንዶች ሱሪን ዝቅ አድርጎ መታጠቅ ስልጣኔ መስሏቸው ለሰይጣን የሰገዱበት የተረገመ ትውልድ ❤️ሴቶች እምብርትንና ጡትን በአደባባይ እንደ ከተማ ህንፃ እዩኝ እዩኝ እያሉ ለዲያቢሎስ የተማረኩበት ትውልድ ❤️አለባበስ ታይቶ የሰውን ማንነት በአብረቅራቂ ነገርና በአይን ብቻ የሚገምትበት ትውልድ ❤️ወደ ፈጣሪ ቦታ ስኬድ ስልክና ኤርፎን ይዞ የሚሄድ ትውልድ ... . .... ምን ትላላችሁ እስኪ ኮሜንት ላይ ሃሳባችሁን አስቀምጡ 👇👇👇👇👇 @abyssinianwisdom

ትውልድና ዘመን ❤️ፍቅር በዋጋ ሴክስ በነፃ የሆነበት አሳፋሪ ትውልድ ❤️ድንግልናን ከማስወሰድ በላይ ስልክን መሰረቅ በጣም የሚያስቆጭበት ትውልድ ❤️I Phone መያዝ ተምሮ ከመመረቅ በላይ የሚደሰትበት ትውልድ ❤️ሴቶች ከHIV ይልቅ እርግዝናን የፈሩበት አስነዋሪ ትውልድ ❤️እውነት ተዳፍኖ ውሸትና ክህደት እውነት መስሎ የታየበት አስፀያፊ ዘመን ❤️ህዝቡ ከፈጣሪ ይልቅ አሸባሪ ፣ ገዳይና ሌባን የሚፈራበት አስቀያሚ ዘመን ❤️ገንዘብ ከቤተሰብና ከጓደኛ በላይ የተወደደበት ርካሽ ትውልድ ❤️በፍቅረኛ ላይ ሌላ ካልደረቡ "ፋራ" ተብሎ ሰውን የሚሳደቡበት ትውልድ ❤️ሰው ሞልቶ ተርፎ ብቻን እንዲኖሩ ያስገደደ አሳዛኝ ዘመን ❤️ለፍቅር መታመን ፣ ለፍቅር መሰደድ ፣ ለፍቅር መሰቃየትና መሞት እንደ ሞባይል game የተቆጠረበት ቅስም ሰባሪ ትውልድ ❤️ባልና ሚስት የማይተማመኑበት መሽቶ ላይነጋ የጨለመ ዘመን ❤️ወንዶች ሱሪን ዝቅ አድርጎ መታጠቅ ስልጣኔ መስሏቸው ለሰይጣን የሰገዱበት የተረገመ ትውልድ ❤️ሴቶች እምብርትንና ጡትን በአደባባይ እንደ ከተማ ህንፃ እዩኝ እዩኝ እያሉ ለዲያቢሎስ የተማረኩበት ትውልድ ❤️አለባበስ ታይቶ የሰውን ማንነት በአብረቅራቂ ነገርና በአይን ብቻ የሚገምትበት ትውልድ ❤️ወደ ፈጣሪ ቦታ ስኬድ ስልክና ኤርፎን ይዞ የሚሄድ ትውልድ ... . .... ምን ትላላችሁ ጋይሶች እስኪ ኮሜንት ላይ ሃሳባችሁን አስቀምጡ 👇👇👇👇👇 @abyssinianwisdom

ሰዎች ፍቅር እውር ነው ይላሉ። እንዲህም የሚሉት የፍቅርን ትርጓሜ ስላላወቁ ነው። እኔ ግን እላችኋለሁ ፍቅር ብቻ ነው አይን ያለው። ከፍቅር ውጪ ሌላው በሙሉ እውር ነው።                                                   ✍️ኦሾ

እስኪ ዛሬ የሚገርም ትዕግስትና ለማመን በሚደንቅ ሁኔታ ተስፋ ስለማይቆርጠው ሰው ልንገራችሁ... 🎯 በ21 አመቱ ንግድ ለመስራት ሞክሮ ከሰረ ! 🎯 በ22 አመቱ ከህግ ትምህርት ቤት ተባረረ ! 🎯
እስኪ ዛሬ የሚገርም ትዕግስትና ለማመን በሚደንቅ ሁኔታ ተስፋ ስለማይቆርጠው ሰው ልንገራችሁ... 🎯 በ21 አመቱ ንግድ ለመስራት ሞክሮ ከሰረ ! 🎯 በ22 አመቱ ከህግ ትምህርት ቤት ተባረረ ! 🎯 በ24 አመቱ በድጋሚ ንግድ ሊሰራ ሞክሮ ከሰረ ! 🎯 በ26 አመቱ በጣም የሚያፈቅራት የልጅነት ፍቅረኛውን በሞት አጣ ! 🎯 በ34 አመቱ ለምክር ቤት ተወዳድሮ ሳይሳካለት ቀረ ! 🎯 በ45 አመቱ ለሴናተርነት ተወዳድሮ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ ! 🎯 ተስፋ ሳይቆርጥ በ47 አመቱ ለምክትል ፕሬዝዳንትነት ተወዳደረ አሁንም ሳይሳካለት ቀረ ! 🎯 በ49 አመቱ በድጋሚ ለሴናተርነት ተወዳድሮ በድጋሚ ሳይሳካለት ቀረ ! በመጨረሻ ግን በ52 አመቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት መሆን ቻለ ! ይሄንን ሰው ብዙዎቻችን እናውቀዋለን አብረሃም ሊንከን ይባላል ! አለማችን ካየቻቸው ታላላቅ መሪዎች አንዱ እና ዋነኛው ነው ታላቅ የፅናት ተምሳሌትም ነው ! እስቲ ለዚህ ሰው ያላችሁን ክብር ምን ያህል ነው ? 👏 ሰለ አስትሮኖሚ ብቻ የሚወራበተን ቻናል ለመቀላቀል👇👇👇👇 @abyssinianwisdom

🦅 ከንስር ልንማራቸው የሚገቡ ሰባቱ የአዕምሮ ለዋጭ ባህሪያት 🦅 1⃣ #ንስሮች_ብቻቸውን_በታላቅ_ከፍታ_ይበራሉ ንስሮች ከእርግቦች፣ ከድንቢጦች ወይም ከትናንሽ የወፍ ዝርያዎች ጋር አብረው አይበሩም። 📝 ትርጉም:- ጠባብ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ራቅ። ከአቅምህ በታች እንድትበር ያደርጉሀል። ንስሮች ሲበሩ ሊታዩ የሚችሉት ከንስር ጋር ነው። በአካባቢህ እንዲሆኑ የምትፈቅድላቸው ሰዎች ለአንተ ማንነት መለያዎች ናቸው። ጥሩ ጓደኞችን አጥብቀህ ያዝ። 2⃣ #ንስሮች_ታላቅ_የማየት_ችሎታ_አላቸው። ከአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ሆነው አንድን ነገር በአትኩሮት መመልከት ይችላሉ። የተመለከቱትንም እንቅፋት ቢኖር እንኳ እስከሚያገኙት ድረስ አትኩሮታቸውን አይለውጡም። 📝 ትርጉም፡-  በህይወትህ የራስህን አላማ ያዝ። እንቅፋቶች ቢኖሩም ከአለምከው ነገር ፍንክች አትበል። 3⃣ #ንስሮች_ፍርሀት_የለሽ_ናቸው። ንስሮች በሚያድኑት ታዳኝ ጥንካሬ እና ግዝፈት አይበገሩም። ታዳኛቸውን ለማሸነፍ ወይንም ግዛታቸውን ለማስመለስ ሁልጊዜም ይፋለማሉ። 📝 ትርጉም፡- የገጠመህ ችግር ምንም ያህል ትልቅ ወይንም አዳጋች ቢሆን ተስፋ አትቁረት። ይልቁንም ተጋፈጠው። ስኬታማ ሰዎች የማይፈሩ ናቸው። ችግሮቻቸውንም በቀጥታ የሚጋፈጡ ናቸው። 4⃣ ንስሮች_ግትር_ናቸው። ንስሮች ማዕበልን ይወዳሉ። ዳመናዎች ሲሰበሰቡ ንስሮች በደስታ ይሞላሉ። የማዕበሉንም ንፋስ በመጠቀም ወደ ከፍታ ይወጣሉ። ሀይለኛ ንፋስም ካለ ከዳመና በላይ እንዲያወጣቸው ይጠቀሙበታል።  ከዳመና በላይ መሆንም ለክንፋ እረፍትን ይሰጠዋል። ሌሎቹ አዕዋፋት ግን እራሳቸውን በቅርንጫፎች እና በዛፎች ደብቀው ይቆያሉ። 📝 ትርጉም፡- ስኬታማ ሰዎች በሚገጥማቸው ማዕበል በፍርሀት ከመዋት ይልቅ  ማዕበሉን ለትርፋማነታቸው ይጠቀሙበታል። 5⃣ #ንስሮች_የሞቱ_ነገሮችን_አይመገቡም። ራሳቸው ያልገደሉትን ካልሆነ ሞቶ የተገኘን ነገር አይመገቡም። 📝 ትርጉም፡- ባለፉ ስኬትህ ደስተኛ ሆነህ አትርጋ ይልቁንም አዳዲስ ወሰኖችን ለመግዛት እራስህን አዘጋጅ። ያለፈውን ነገር ቦታው አስቀምጠው። ቦታውም ኋላ ነውና። 6⃣ ንስሮች_እራሳቸውን_ያሰለጥናሉ ንስሮች ላባቸውንና የሚኖሩበት ጎጆ የተሰራበትን ሳር ያስወግዷቸዋል። ምክንያቱም አዳዲሶቹ ጫጩቶች ለመብረር የሚያደርጉትን ጥረት አዳጋች ለማድረግ ብለው። ጫጩቶቹም በሚኖሩበት ጎጆ ውስጥ መቆየት ሊቋቋሙት የማችሉት ደረጃ ላይ ሲደርስ መብረር ይጀምራሉ። 📝 ትርጉም፡- የምቹነት ቦታህን (Comfort Zone) ለቀህ ውጣ። ምክንያቱም በዚያ እድገት የለምና። 7⃣ #ንስሮች_ህያውነትን_ይተገብሩታል። ንስሮች በሚያረጁበት ሰዓት ላባቸው በጣም ደካማ ይሆንና የሚፈልጉት ቦታ በሚፈልጉት ፍጥነት መሄድ ያዳግታቸዋል። ይህም ሞቱን የሚያፈጥን ስለሆነ ራቅ ብሎ 🗻 ተራራ ላይ ይወጣና ደካማ ላባዎቹን ይነቅላቸዋል። መንቁረንና ጥፍሩን ሙሉ በሙሉ ራቁቱን እስከሚሆን ድረስ ከአለቶች ጋር እያጋጨ ይሰባብራቸዋል። ከከፍተኛ ህመም በኋላም ድብቅ ስፍራ በመሄድ ላባው፣ ጥፍሩ እና መንቁሩ እንደአዲስ እስከሚበቅሉ በዚው ይቆያል። ከዛም ከዚህ በፊት ያልወጣውን ትልቅ ርቀት መጓዝ ይጀምራል። 📝 ትርጉም፡- ምንም ያህል ከባድ ቢሆን ከዚህ በኋላ በህይወትህ ለውጥን የማያመጣልህን ወይንም የሚያቃጥሉህን መጥፎ ልማዶች አስወግዳቸው ምክንያቱም ውድቀትህን ያፋጥኑታልና።

By all means marry. If you get a good wife, you'll be happy. If you get a bad one, you'll become a philosopher. በምንም መንገድ ቢሆን በትዳር ተሳሰሩ።  ጥሩ ሚስት ካገኘህ ደስተኛ ትሆናለህ፣  መጥፎ ሚስት ካገኘህ ደግሞ ፈላስፋ ትሆናለህ።                           ሶቅራጠስ

አንቺን እንዲሰጠኝ አንቺን እንዲሰጠኝ ፈጣሪን ለመንኩኝ አንቺን እንዲሰጠኝ በፀሎት በረታሁ ሱባኤም ገባሁኝ አንቺን እንዲሰጠኝ ግሸን ሄጄ ጠየኩ ዝቋላም አለቀስኩ ዋልድባ አልቀረኝ ኢቲሣም ረገጥኩ አንቺን እንዲሰጠኝ ፆም መፆም ጀመርኩኝ ቅዳሴም ለመድኩኝ አንቺን እንዲሰጠኝ ጌታዬን ለመንኩት ግን በዚህ ሂደት ውስጥ.... አንቺን ረስቼ ፈጣሪን ወደድኩት🥰               @henila31 ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

የተመለከተህ ሁሉ መሳቀቅን ከፈጠረብህ ከጊዜያት በኋላ ለሰው ያለህ እይታ እንደ ድመትና አይጥ ይሆንብሃል።

አንዳንድ ሰዎች ምክንያት እየፈለጉብህ ከሆነ እዳይደክሙ በቶሎ መሻታቸውን ስጣቸው! ልቡ መሔድ ያሰበን እጁን ብትይዘው ታግለህ አታስቀረውም!!!

ዛሬን ወስን ! የነገ ህይወታችን ስኬት ሚስጥሩ ያለው ዛሬ ላይ ነው እዚህች ቀን ላይ ዛሬያችን ነገን መስሪያ መሳሪያችን ነው ዛሬ ላይ የምናጠፋውም የምናለማውም ነገን ይወስንልናል ! ቆንጆ አርብን ተመኘን 🙏

''...እኔ የምመኘው ዛሬ አርጄ ነገ ልታረድ፤ ዛሬ ቀምቼ ነገ ልቀማ የሚለዉ የልበደንዳናነት እምነት ተወግዶ እንዲሁም ዛሬ እንደተጠቃሁ ነገ ማጥቃት አለብኝ የሚለዉ የተጠቁት ሰዎች የመበቀል ስሜት ተወግዶ  ታላቅ እርቅና ሰላም ወርዶ የነገዋ ዓለማችን ለሁሉም መልካምና ሰላማዊ ኑሮ እንድትሰጥ ነዉ።...'' ~~ ፠ ''በፍጹም አልወለድም'' አልሁ ጮኽ ብዬ ነገሩ ግራ ሆነባት ወዲያና ወዲህ ፊቷን እያዞረች ሰው እንዳለ ማየት ጀመረች። ወይ ግሩም! ሰይጣን ጠራኝ ልበል? አለች። አዬ ደግሞ የምን ሰይጣን ?  እኔ ነኝ አልወለድም"  ያልኳት ወደ ሆዷ አንገቷን ዝቅ አደረገችና " አንተ ማን ነህ? አለች በታላቅ ፍርሀትና ጭንቀት። እንግዳው ነገር የተሰራው ሆዷ ውስጥ ሆነና የምታመልጥበት ዘዴ ባይኖራት እንጂ በዚህ ጊዜ ልቧ እስኪፈርስ ብትሮጥ በወደደች " እኔ በሆድሽ ውስጥ ያለሁት ልጅ ነኝ" አልኳት...           አልወለድም                                           ከአቤ ጉቤኛ @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ ቤተሰብ ! DV 2025 መሙላት ተጀምሯል ፣ ከዚህ በፊት DV 2024 እኛ በሞላነው 13 ሰዎች እድለኛ ሁነዋል። 💐💐💐 በዘንድሮውም እኛን ባካል ማግኘት ሳይጠበቅ በአስተማማኝ ሁኔታ እንሞላላችኋለን ። ሞልተን confirmation number መልሰን ለእናንተ እንልካለን ። የሚያስፈልጉ ፦ 1 ዲጂታል ጉርድ ፎቶ ግራፍ 2  ትክክለኛ አድራሻ /የትውልድ ቦታ ዞን ከተማ ። 3 ሙሉ ስም ከነ አያት በ እንግሊዘኛ 4  የትምህርት ደረጃ 5  ስልክ ቁጥር 6 ኢሜል / ግዴታ አደለም  በውስጥ ላኩልን  👉 @kohal_g        ስልክ 0972789826

በጊዜያዊ መፍትሔ የተነሳ ዘላቂው መፍትሔ ላይ መቀዝቀዛችን ቋሚ ጤናማነታችን እንዲጠፋብን ሆኗል።

በአፍላ የፍቅር ዘመን የማይሆኑት የለም።መሮጥ-መሯሯጥ፥መምታት-መማታት፥መሳቅ-መሳሳቅ፥መብረር-ማባረር፥አረ ስንቱ!የሁለቱም ወገን ድርጊት በወጉ ለፍቅር፥ለደስታ ስለሆነ ለክፉ አሳልፎ አይሰጥም፤በመካከሉም ለቀልድ ተብሎ የሚወረወር ጠጠር አናት ፈርክሶ ሲያደማ መታየቱ ከፋ እንጅ! የ27 ዓመቷ ዩጎዝላቪያዊት ሚላንካና የ32 ዓመቱ ጉብል ኢሊጃ ተፈቃቅረው ከተጋቡ መንፈቅ አልሞላቸውም።አቶ ባል አንዳንድ ጊዜ ድንገተኛና ያልታሰበ ድርጊት እየፈፀመ ሚስቱን ያስደነግጣል፥"ውቃቢ ያስርቃል"፤ያስቃል።በአራዳው ቋንቋ ይኮምካታል እንደ ማለት ነው።ሚስትም እንደዚሁ። አቶ ኢሊጃ ባለቤቱን እቤት ትቶ ለስራ ይወጣና በዚያው ከአንድ ጓደኛው ቤት ይሄዳል።ሲመለስ ከዚያው ከጓደኛው ቤት የተዋሰውን ሙሉ ማስክ በማጥለቅ ወደቤቱ ያመራል።ከደጁ ደርሶ በር ሲያንኳኳ ሚስት በመስተዋቱ የታያት ባሏ ሳይሆን እጅግ አስፈሪ ልብስ የለበሰ ሰው ይሆናል።ታዲያ ባልዋ በአጋጣሚ ክፉ ቀን ሲገጥማት ራስዋን ለማዳንና ከአደጋ ለመከላከል ትችል ዘንድ የጠመንጃ አተኳኮስ አስተምሯት እንደነበር ማስክ አጥልቆ የመጣውን ሰው ስታይ  ትዝ ይላታል። ወይዘሮ ሚላንካ ወዲያው ወደመኝታ ክፍሏ ትገባና የባሏን አውቶማቲክ ጠመንጃ ከቁምሳጥን አውጥታ የሚያብለጨለጩ ጥይቶቹን በማቃም አቀባብላ ወደበሩ ተጠጋች።በሩ ባለመስታወት ስለነበር ወይዘሮዋ ጠመንጃዋን ደግና ሰውየው ከአከባቢው እንዲሄድ ምልክት ታሳየዋለች።ያ ሞቱ የቀረበ ባል ግን ሚስቱ ላይ የቀለደ መስሎት እምቢታ በማሳየት እዚያው ይገተራል።ፊትዋን ብታኮሳትር፥እጇን ብታወራጭ ሰውየው ፍንክች ሳይል ይቀራል። ወይዘሮ ሚላንካ የመጨረሻውን ርምጃ በመውሰድ ቃታ ስባ ተኩስ ከፈተች።የጥይት መዓት የተርከፈከፈበት ያ "ምስኪን " ባልዋ ከደጃፉ ላይ ተደፋ።ወዲያው ሟች በአንቡላንስ-ገዳይ በፖሊስ ታጀቡ። ሆስፒታል ተደርሶ የሟች ማስክ ሲገለጥ ቆማ ትመለከት የነበረችው ወይዘሮ ሚላንካ እራስዋን ይዛ እዬዬዋን ታቀልጠው ጀመር።በነገሩ ግራ የተጋቡት ፖሊሶችና ሐኪሞች ሚላንካን ዘወር አድርገው ሁኔታውን ማጣራት ሲጀምሩ ሟች ባል፥ገዳይ ደግሞ ሚስት መሆናቸውን ይረዳሉ።በሚስቱ እጅ የውሸት ሳይሆን የእውነቱን ሞት የተቀበለው ኢሊጃ በማግስቱ ሲቀበር ሴቲቱ ግን ማረፊያ ቤት ገባች።"ወንጀለኛም ሃዘንተኛም" መሆኗ ነው እንግዲ።ያለቦታው የሚሆን ቀልድ ለዚህ አበቃ።"ቀልድና.....ቤት ያጠፋል" እንዲሉ።

ተስፋ_መቁረጥ_ከየት_ይመጣል ? ___ ብዙ ጊዜ ሰዎች በተለያዩ ሁኔታዎች ሁነው ተስፋ የለኝም ፣ ተስፋዬ ተሟጧል ፣ የመሳሰሉትን ቃላት በቀን ተቀን ሕይወታቸው ይጠቀማሉ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ ወደ ግባችን / ፍላጎቶቻችን እንዳንደርስ የሚያረገን ባህሪ ነው ፡፡ በሕይወቱ ብዙ ጊዜ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ወደግቡ/እቅዱ የመድረሱ እድል በጣም አነስተኛ ነው ፡፡ ወደ ጠቃሚ የሕይወት ግባችን አለመድረስ ደግሞ ድብርት ፣ ጭንቀት ፣ ፍርሃት ፣ የበደለኝነት ስሜት ያመጣብናል ፡፡ ሳይኮሎጂ ችግር የመፍቻ ዋና መንገዱ የችግሩን ምክንያት መረዳት እንደሆነ ያትታል ፡፡ስለሆነም የተስፋ መቁረጥ ዋና ዋና ምክንያቶች እንመለከታለን፡፡ ___ 1.Environmental Factor (አካባቢያዊ ምክንያት) በአካባቢያችን ያሉ የተለያዩ ሁኔታዎችና ገጠመኞች ፍላጎቶቻችንንና እቅዳችንን እንዳናሳካ ይከለክሉናል ፡፡ ለምሳሌ ፦ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ማድረግ የምንፈልገውን ነገሮች " አትችለውም ፣ ይከብድሀል ፣ ከዚህ በፊት አልተሞከረም ፣ ሰው ምን ይልሀል" በማለት ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ ፡፡ በተጨማሪ ደግሞ ያደግንበት ባህል ፣ የምንኖርበት አካባቢ ለማድረግ ያቀድነውን ነገር እንዳናሳካ በራሱ ሊይዘን ይችላል ፡፡ ይሄ በሕይወታችን ተስፋ መቁረጥን ያስከትላል ፡፡ 2.Personal inadequency Factor (ግላዊ ብቃት/ክህሎት ማጠር ) ይህ ደግሞ ፍላጎቶቻችንን እንዳናደርግ የሚገድበን አለመሙላት (ብቃት አልባነት) ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድን እቃ በጣም ወደነው ለመግዛት ስንፈልግ ከተወደደብንና ያለን ገንዘብ አነስተኛ ከሆነ ተስፋ ቆርጠን ላንገዛ እንችላለን ፡፡ እዚህ ጋር ነገሩን ለመግዛት በቂ ገንዘብ አለመኖር የራሳችን የሆነ ጉድለት ይሆናል፡፡ ሌላው አንድን ነገር ለመስራት አስበን የግል ችሎታ / ብቃት/ ክህሎት ሲያንሰን እሱ " በቃ አልችልም " በማለት ተስፋ ለመቁረጥ መንስኤ ይሆነናል ፡፡ 3. Conflict of interest ( የፍላጎት ግጭት ) የመጨረሻው የግላዊ ፍላጎቶች/ ግቦች እርስ በእርስ ሲፃረሩ ተስፋ ሊያስቆርጠን ይችላል ፡፡ ተስፋ መቁረጡ የሚመጣዎ ሁለቱንም ግቦቻችንን ልናሳካ ባለመቻላችን ነው ፡፡ አንዱን ግብ ብናሳካ ራሱ ሌላውን ስላላሳካን የመወላወል ተስፋ የመቁረጥ ( የማዘን ) ስሜት ይሰማናል፡፡ ከነዚህ ሶስቱ ዎና ዎና ምክንያቶች እግጅ በጣም ብዙ ሰው የሚያጋጥመው የመጨረሻው (.Conflict of Motives / የፍላጎት ግጭት ) እንደሆነ ሳይኮሎጂ ይጠቁማል፡፡ __ እነዚህ Conflict of motives ( የፍላጎት ግጭት ) ደግሞ በ አራት ይከፈላሉ ፡፡ __ ሀ. Approach - Approach Conflict (ፍላጎት ፥ ፍላጎት ግጭት) ይህ ግጭት ሁለት ነገሮችን በእኩል ፈልገን ነገር ግን መምረጥ የምንችለው አንዱን ብቻ ሲሆን ማለት ነው ፡፡ ለምሳሌ :- ተማሪዎች ዩኒቨርስቲ ከገቡ በኅላ Department ሲመርጡ ብዙ ተማሪዎች በሁለት ወይም ከዛ በላይ በሆኑ የdepartment ምርጫዎች ይወጠራሉ ነገር ግን መምረጥ የሚችሉት የወደዱትን ሁሉ ሳይሆን አንዱን ብቻ ስለሚሆን ግጭት ውስጥ ይገባሉ ፡፡ ሌላው ገበያ ሂደን ሁለት ሱሪዎች በጣም ወደናቸው ነገር ግን መግዛት የምንችለው አንዱን ብቻ ከሆነ ይህ አይነት ግጭት ከራሳችን ጋር ይገጥመናል፡፡ ለ. Avoidance - Avoidance Conflict (የማስወገድ ፥ የማስወገድ ግጭት) ይህ ደግሞ ከሁለት የማንፈልጋቸው ነገሮች የግድ አንዱን መምረጥ ግድ ሲለን ነው ፡፡ ለምሳሌ ፦ ልጃችን በሰዎች ታግቶ ብር ካልከፈላችሁ ይገደላል ቢሉን ፤ እዚህ ጋር ልጁ እንዲሞትም አንፈልግም ለአጋቾቹ ብር መክፈልም አንፈልግም ፡፡ ግን አንዱን መምረጥ ግድ ይለናል ፡፡ ሌላ ምሳሌ ፦ ሐ. Approach - Avoidance Conflict (የፍላጎትና ማስወገድ ግጭት) ይህ ደግሞ በአንድ ግብ ላይ የፍላጎትም የማስወገድም ስሜት ሲሰማን ነው ፡፡ መ. Multiple Approach - Avoidance Conflict (ብዙ የፍላጎት ማስወገድ ግጭት) ይህ ሁላችንም በሕይወት ቆይታችን የሚያጋጥመን የለት ተለት ግጭት ነው ፡፡ እያንዳንዱ የሚገጥመን ነገር #ብዙ_አወንታዊና_አሉታዊ ነገሮች ይይዝና እሱን #መምረጥና #አለመምረጥ ችግር ይሆናል ፡፡ ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው መልኩን ፣ ገቢውን ወደን ፀባዩ አመለካከቱ ካላማረን ይሆነኛል አይሆነኝም ብለን ከራሳችን እንጋጫለን ፡፡ሌላው አንድን ስራ ስንሰራ በዉስጡ ያሉ የተለያዩ ጥሩና መጥፎ ነገሮች ስገፉን ሲስቡን እንደዚህ አይነት ግጭት ውስጥ እንገባለን ፡፡ ፠፠__፠፠ ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛 በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 @abyssinianwisdom ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል ! ቸር ሰንብቱ! ፠፠__፠፠ የሳምንት ሰው ይበለን!

#5ቱ_መልካም_ቃላት ትናንት፣ የዛሬ አመት ወይም የዛሬ አስር አመት ምንም ይከሰት ምን ዛሬ ላይ  እንደ አዲስ ቀንህን መጀመር ትችላለህ። እያንዳንዱ ንጋት ከትናንትናህ የምትሻልበት አዲስ እድል ነው፤ አዲስ ታሪክ የምትጽፍበት፣ የጎደለ ብርጭቆህን የምትሞላበት ነው። እያንዳንዱን ቀንህን አለምን ለመቆጣጠር አስበህ ጀምር፤ አምስት መልካም ቃላትን ምረጥና ለራስህ ደጋግመህ ንገረው። የኔ አምስቱ መልካም ቃላት እነዚህ ናቸው፦ 🤗 በራሴ እተማመናለሁ 💎 ዋጋ አለኝ ✅ ለውጥ እያመጣሁ ነው 👑 ስኬታማ ነኝ 💕 ተወዳጅ ነኝ እናንተስ አዲሱን ቀናችሁን እንዴት ለመጀመር አስባችኋል? Join our channel @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

200 ብር አሁን ተቀበልኩ 🎁 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ ! 📌አንድ ሰው ሲጋብዙ 3 ብር ይሰራሉ ። 📌100% የተረጋገጠ (የሚከፍል ) ነው:: 📌በtelebirr ነው የምትቀበሉት :: 🎁 ይጋብዙ እና ገንዘብ ይስሩ ! - አንድ ሰው ሲጋብዙ 3 ብር ይሰራሉ ። 🔰 መጋበዣ ሊንክ : https://t.me/Share251_Inviting_Bot?start=OTgZT ✅ ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና በቴሌብር ይቀበሉ ። ⚠️ NB : FAKE REFERRAL & MULTI ACCOUNT USERS NO PAYMENT !!! ✅ ዛሬውኑ ጀምሮ ገንዘብ ያካማቹ እና በቴሌብር ይቀበሉ ።