LEARN TECH ||ethiopia ®
رفتن به کانال در Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
نمایش بیشتر1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
በሂወቴ አንድም ቀን ፊቱ ጭፍግግ ኮስተር የሚል ፣ ያልገባውን አልገባኝም ፣ትክክል ካልመሰልኩት ትክክል አይደለህም እያለ የሚሞግት እና የሚገስፀኝ ሙሉ ስሜን ካለይሉኝታ ሳያቆላምጥ የሚጠራኝ ኑሮዬን አክብዶት አያቅም ።
ሳስቀይመው እንደተቀየመ የሚያሳየኝ ቅር ያለውን የሚያንፀባርቅ። አወዳዱ እኔ ጋ ከሚያገኘው ጥቅም ጋ ብቻ የማያጣብቅ ሰው ልብ ውስጥ ፍስስ የሚል በቀላሉ የማይቆም ሃዘን አፍልቆብኝ የሚያቅበትን ግዜ አላስታውስም ።
ይልቁንስ
ቅልስልስ የሚሉ ። የሚያገኙት ጥቅም ያለ ከመሰላቸው የሚንሿከኩ ፣ እንደ ውሃ በተቀመጡበት ቦታ ቅርፅ የሚቀያየሩ ።
ከፊት እና ከጀርባ አቋም የሚቀያየሩ ። ፊት ለፊት ባልወደዱት ባልገባቸው ጉዳይ የማይወያዩ ልምጥምጥ ግለሰቦች እሾሃቸው የቱ ጋ እንዳለ ስለማይታይ የምድርን ቆይታ ከሆነው በላይ ብርቱ ሰልፍ ያደርጉታል ።
የሆነው ሆኖ
ቅልስልስ ልምጥምጥ አስመሳይ ሰዎች ዘግይተው ሲጠሉ ኮስተር ክችች ግትር የሚሉት እውነተኛ ሰዎች ዘግይተው ይወደዳሉ ።
የሆነው ሆኖ
እኔ እና ልቤ ግን በዙርያችን የተኮለኮሉ ውብ ነብሶች ላይ እንመሰጣለን❤🙏
©
🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼 🌼🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼🌼
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼
🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼 🌼 🌼 🌼🌼🌼
🌼 🥀 🌼 🌼 🌼 🌼 🌼
🌼🌼🌼 🌼🌼🌼 🌼 🌼🌼🌼
🌻🌻💐💐💐🌻🌻🌻🌻
🌻🌺 እንኳን 🌺🌻
🌻🌹 አደረሳችሁ 🌹🌻
🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼
🌼happy new year🌼
🌼2016🌼
እንኳን ለ2016 የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም በፍቅር በአንድነት አደረሳችሁ... አዲሱ ዘመን የሰላም የፍቅር ያድርግልን...
መልካም አዲስ አመት
አፍሪካ ለአፍሪካውያን የቀብር ቦታ ብቻ ናት!
የራሺያ ፕሬዘዳንት ቪላድሚር ፑቲን ከተናገሩት:-
አንድ አፍሪካዊ ሃብታም ሲሆን ..
*ገንዘቡን የሚያስቀምጠው በስዊዝ ባንክ ነው!
*ለህክምና የሚሄደው ፈረንሳይ ነው!
*ኢንቨስት የሚያደርገው ጀርመን ውስጥ ነው!
*ዕቃ የሚገዛው ዱባይ ነው
*የሚጠቀመው ቻይና ነው
*ለፀሎት የሚሄደው ሮም እና መካ ነው
*ልጆቹ የሚማሩት አውሮፓ ነው
* ለቱሪዝም ጉብኝት የሚሄደው አሜሪካ እና ካናዳ ነው
❗️ሲሞት ግን የሚቀበረው በእናት ሃገሩ አፍሪካ ውስጥ ነው።
አፍሪካ ለአፍሪካውያን የቀብር ስፍራ ብቻ እንጂ ሌላ አይደለችም
የመቃብር ቦታ ደግሞ እንዴት ያድጋል?
ሲል ይጠይቃል?
@abyssinianwisdom
♦️♦️♦️ጳጉሜን ♦️♦️♦️
ጳጉሜን የሚለው ስያሜዋ ግን “ሄፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ መሆኑን አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ተነግሯል፡፡ “ኤፓጉሜኔ” ማለት ጭማሪ ማለት ነው፡፡ በግእዝ ቋንቋችን ተውሳክ ማለት ነው፡፡ ተውሳክ ማለት ተጨማሪ ማለት ነው፡፡ “ወሰከ - ጨመረ” ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ (ምንጭ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ገጽ ፱፻፭)፡፡ ምዕራባዊያኑ ጳጉሜን ተጨማሪ ቀን አድርገዋታል፡፡ እኛ ግን የወር ተጨማሪ አድርገናታል፡፡ በጽርዕ ኤፓጉሜኔ ትባል እንጂ ሊቃውንት ግን ተረፍ ይሏታል፡፡ ጳጒሜን የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የአዲሱ ዓመት መንደርደሪያ ዕለት እንደሆነች የክርስቶስ ልደትም የዓመተ ፍዳ ማቆሚያ የዓመተ ምሕረት መጀመሪያ በመሆኑ ዕለታቸው ራሱ በተመሳሳይ ቀን ተቀምሮ ይውላል፡፡
የጳጉሜን ወር ‹‹የምሕረት ወር›› ስለመባሏ፡-
ኢትዮጵያ በዓለም ብቸኛዋ የ፲፫ ወራት ጸጋ ባለቤት ስትሆን የጳጉሜን ወርም በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምሕረት ወር ተብሎ ይታመናል። በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ጸሎት የሚያደርግበት ዕለተ ምጽአት የሚታሰብበት የምሕረት ወር መሆኑን ታስተምራለች፡፡ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት መሠረት ምእመናኑ በጳጉሜን ጸበል በመጠመቅ ድኅነት በማግኘታቸው የምሕረት ወር መሆኑን ምእመናን ያብራራሉ፡፡
የጳጉሜን ወር በጸሎት በንስሓ ተወስነን ወደ አዲሱ ዓመት የምንሸጋገርባት ድልድይ ናት፡፡ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር የፈቀደላቸው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ጸሎት በመጸለይ ጸበል በመጠመቅ ያስቧታል፡፡
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ካሉት ሁለት የፈቃድ አጽዋማት መካከል አንዱ በዚህ በጳጉሜን ወር የምንጾመው ሲሆን መሠረት የሚደረገውም ጾመ ዮዲት ነው፡፡ የዮዲት ጾም የሚባለውም እርሷ ስለ ጾመችው ነው፡፡ ይህን መሠረት አድርገው ሕዝቡ ሳይቀር “ጳጉሜን ዕድሜ ትሰጠናለች፤ በኋላም ታድነናለች” ብለው ጾም ይጾሙባታል፡፡ (ምንጭ-ቅዱስ መልከ ጸዴቅ ድርሳን)፤ በሀገራችንም ንግሥት ዘውዲቱ እና ምኒልክ የጾም ሥርዐት ይፈጽሙባት ነበር፡፡ ሌሎችም ሽማግሌዎችና ባልቴቶች አክብረው ይጾሙባታል፡፡ የጳጉሜንን አቆጣጠር አንዱ ከቀን ጋራ ሲደርገው፣ ሌለኛው ደግሞ ከወር ጋራ ቢያደርገውም በሁሉም አቆጣጠር ውስጥ ሕያዊት ሆና መገኘቷ የታወቀ ነው፡፡
የዐውደ ዓመት መሸጋገሪያ ናት፡፡
ይህም ጳጉሜን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ መሸጋገሪያ ናት፡፡ ጳጉሜን የዓመቱ መጨረሻ ወር ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜ አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ ናት፡፡ ስለሆነም አዲሱ ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የልማት፣ የመተሳሰብ ዘመን እንዲሆንልን በጾምና በጸሎት ማሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
ነገረ ምጽ አት የሚታሰብባት ናት፡፡
የጳጉሜን ወር የነገረ ምጽአት የሚታሰብባት ስትሆን ምጽአት ማለት የጌታን መምጣት የሚያስረዳ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን የጌታን ምጽአት በዓመት ሁለት ጊዜ ታስታውሳለች፤ ይኸውም በጳጉሜን ወርና በጌታ ጾም እኩሌታ (በደብረ ዘይት) ነው። ቅዱስ ዳዊት ”እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል፤ ዝም አይልም፤ እሳት በፊቱ ይነዳል፤” እንዲል፤(መዝሙረ ዳዊት ፵፱ ፣ ፪-፬)፡፡ ይህ ስለ ነገረ ምጽአት ያስረዳል፡፡
ይህም ጳጉሜን ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት፣ ከክረምት ወቅት ወደ ጸደይ ወቅት መሸጋገሪያ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ከጊዜያዊው ወደ ዘላለማዊ፣ ከምድራዊ ወደ ሰማያዊ፣ ከዚህ ዓለም ወደ ወዲያኛው መሸጋገሪያ ናትና ነው፡፡ ጳጉሜን የክረምቱ ማብቂያ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም በመጨረሻው ዘመን መከራ የሚበዛበት የዚህ ዓለም ማብቂያ ናት፡፡ ወርኃ ጳጉሜን አዲሱን ዓመት ለመቀበል የዝግጅት ጊዜ እንደሆነች ሁሉ ምጽአትም ጻድቃን አዲሲቷን ምድር (መንግሥተ ሰማያትን) ለመውረስ ተዘጋጅተው “ኑ የአባቴ ብሩካን ዓለም ሳይፈጠር የተዘጋጀላችሁን የእግዚአብሔር መንግሥት ውረሱ” የሚባሉባት ቀን ናት፡፡ የጌታ አመጣጥ ሳይታሰብ ነውና በተሰጠን ጸጋ ቅዱስ አምላካችንን እያመሰገንን ተዘጋጅተን እንድንጠብቀው። የድንግል ማርያም ልጅ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይርዳን።
ቀጣዩ ዘመንም ቃሉን ፈጽመን መልካም ፍሬ የምናፈራበት ዓመት ይሁንልን፤ አሜን !!!
©️ከፈለኝ ዘለለው
የኢራን ንጉሥ በምስራቅ ካሉ ጠቢባን አንዱን ማግኘት እንደሚፈልግ ጠቅሶ አገሩን እንዲጎበኝ ግብዣ ላከለት።
ጠቢቡም በተባለለት ጊዜ ኢራን ደረሰና ወደ ቤተመንግሥቱ በክብር ሲገባ እዚያ የተቀመጡ ስድስት ነገሥታት አንድ መስለው ለመለየት አስቸግረው። በዚህ ሁኔታ በመገኘቱ ተደነቀ። ሁሉም የንጉሥ ልብስ ለብሰው፤ አንድ አይነት ይመስሉ ነበር።
"አንተ ትክክለኛ ጠቢብ ከሆንህ እውነተኛው ንጉስ ማን እንሆደነ ተናገር"የሚል ድምጽ፤ ጠቢቡ ሰው ከኋላው ተሰማው በዚህ ቅጽበት በልበ ሙሉነት ወደ ንጉሡ ቀርቦ ሰገደ።
ይሄኔ፤ ንጉሡ በማፈር "ግን እንዴት ለየኸኝ?" አለ። ጠቢቡም ፈገግ አለና "አምሳያ ነገሥታትህ በሙሉ አንተን ይመለከቱ ነበር። አንተ ግን በቀጥታ ወደ ፊት ታያለህ።
"ተራ ሰዎች የንጉሥ ልብስ ለብሰው እንኳ ሁል ጊዜም ቢሆን ትዕዛዝ እና ድጋፍ ለማግኘት ንጉሣቸውን ይመለከታሉ። በዚህ ለየውህ ንጉሥ ሆይ አለ።"
ንጉሡም በቤቱ ሾመው... ስጦታም አበረከተለት።
•••
ለራሳችን ዋና ንጉሥ የምንሆነው መቼ ነው?
•••
**እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ**
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አንድ ሀብታም ሰው ልጁን ከመጥፎ ልማዶቹ እንዲያርቀው አንድ ሽማግሌ ምሁርን በአስተማሪነት ቀጠረ።
ከዚያም ምሁሩ ከወጣቱ ጋር በአትክልቱ ስፍራ ለመንሸራሸር ወረዱ። ምሁሩ በድንገት ቆሞ ልጁ እዚያ የሚያድግ አንድ ትንሽ ተክል እንዲያመጣ ጠየቀው። ወጣቱ ተክሉን በአውራ ጣቱ እና በጣቱ መካከል ይዞ አወጣው። ከዚያም አዛውንቱ ከቅድሙ ትንሽ የሚበልጥ ተክል እንዲያመጣ ጠየቁት። ወጣቱ አጥብቆ ጎትቶ ተክሉን ነቀለው። ከዚያ አዛውንቱ ወደ አንድ ቁጥቋጦ እየጠቆሙ “አሁን ያንን አምጣ” አሉት። ልጁ ለማውጣት ሁሉንም ኃይሉን መጠቀም ነበረበት። በዚህም እየደከመው መጣ።
ከዚያም አዛውንቱ ወደ ቋጥኙ እያመለክቱ “አሁን ይህንን ፈንቅል” አሉት። ወጣቱ ግንዱን ይዞ ለማውጣት ሞከረ። ግን አቃተው። ጥረቱን ቀጠለ ግን ከበደው ይሄኔ “አልችልም” አለ።
ጠቢቡም "መጥፎ ልምዶችም እንዲሁ ናቸው ፤ትንሽ ሲሆኑ ለመተው ቀላል ነው፤ ግን ስር ሲይዙ ሊነቀሉ አይችሉም አሉት" ከአዛውንቱ ጋር የነበረው ክፍለ ጊዜ የልጁን ሕይወት ለውጦታል።
ሞራል- መጥፎ ልማዶች በውስጣችሁ እስኪያድጉ አትጠብቁ ፣ በሚቆጣጠሩበት ጊዜ በለጋነት ይጣሏቸው ፣ አለዚያ ይጥሏችኃል።
***
የተዋችሁት መጥፎ ልምድ አለ? ንገሩን
***
እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ
ንበብ ለንባብ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ወዳጄ ሆይ.... ሞኝ አትሁን! ፍቅር፣ ወሲብ፣ ምናምን ቀድሞ የተዘጋጀ ቀመር የለውም። የምክንያትና የሎጂክ ጣጣም አያውቅ።ድንገት ብቅ ይላል፣ሀሴት አዝንቦልህ መልሶ ይሰወራል። እንደገና ትናፍቀዋለህ። ይህንን የተፈጥሮ ህግ እንኳንስ አንተ የፍቅር አማልክት ሊለውጡት አይችሉም።
📓 የሱፍ አበባ
✍️ ሀብታሙ አለባቸው
📚 @abyssinianwisdom
ፓስተሩ ኃጢያተኛ በረገጠው መሬት አልራመድም አለ🙉❗
የሐይማኖቶች እብደት እንደቀጠለ ነው።
በጊቱራይ፣ ኬንያ የሪቫይቫል ቤተ ክርስቲያንን ጆን ምዋንጊን የተባለ ፓስተር "የእግዚአብሔር አገልጋይ በኃጢአተኛ መሬት ላይ መሄድ ስለማይችል ሬንጅ ሮቨር 2023 ሞዴል እስኪገዙለት ድረስ ሁል ጊዜ ጉባኤው ተሸክመውኝ ይሄዳሉ " በማለት መሬት ሳይነካው በዚህ መልኩ እየተገለገለ ነው።
የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች ለሕዝቡ አገልጋይ መሆን ሲገባቸው ህዝቡን እንዲህ ላለ ኃላ ቀርነት ዳርገውታል።
👉ለትክክለኛ እና ሚዛናዊ መረጃዎች ቻናላችንን join በማለት ተከታተሉ👇👇
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
መቼና እንዴት እንደሆነ ባላውቅም ደንታቢሶች ሆነናል።ሰቆቃን ለምደናል፣ቁስል አይሰቀጥጠንም፣ረሃብ ትኩረታችንን አይስብም፤ዓይናችንን ጨፍነን መራመድ ለምደናል።ይሄ ባይሆን በዚህ ሆስፒታል ኮሪደሮች ላይ ምንም እንዳልተፈጠረ መራመድ እንዴት ይቻለን ነበረ? ሞት እና መከራን ከፊታችን እያየን በፈገግታ ማለፍ እንዴት ልንለምድ ቻልን?ወይ ተስፋ ቆርጠናል አሊያም ግዴለሽነት ጠፍንጎ ይዞናል።
📓 አለመኖር
✍️ ዳዊት ወንድምአገኝ
📚@abyssinianwisdom
👀 እስቲ አንድ ጊዜ ሁላችሁም ከቻናላችን ስር ያለው #Button_ምን_እንደሚል ተመልከቱ።
❌ #Unmute የሚል ከሆነ አንድ ጊዜ #ተጫኑት_ከዛ_Mute_ላይ_ይሆናል ማለት ነው።
✅ #Mute_የሚል_ከሆነ_ግን_ምንም አትንኩት።
👨💻 በየጊዜው አሪፍ ና አስገራሚ እውነታዎች መረጃዎችን ስንለቅ ቶሎ ቶሎ Notification ለናንተ ይደርሳችኋል #UNMUTE_ከሆነ_ግን_ምንለቀው_መረጃ ለናንተ አይደርሳቹም ስለዚ አንዴ #MUTE አርጉት👍
@abyssinianwisdom
#በግ_ነህ?
በሐምሌ 2005 ዓም አንድ ግራ አጋቢ ሁነት በቱርክ አገር ውስጥ ተከሰተ።
በተራራ ዳር ተሰማርተው የነበሩ 1500 በጎች ያለምንም ምክንያት ራሳቸውን ከ15 ሜትር ገደል ላይ ፈጠፈጡ። ከእነርሱም ውስጥ 450 በጎች መሬቱ ላይ ቀጥታ በማረፋቸው ሲሞቱ፣ የቀሩት 1050 በጎች ግን ከእነሱ በፊት የዘለሉት በጎች እንደ ለስላሳ የትራስ ምንጣፍ ሆነዋቸው ተርፈዋል። በጎቹ የ26 የተለያዩ ቤተሰቦች ነበሩ፤ እረኞች ቁርስ ለመብላት እንዲያመቻቸው መንጋውን አምጥተው ከኮረብታ ላይ አሰማሩት።
ከመንጋው ውስጥም አንድ በግ አስቀድሞ ዘለለ፣ እናም ሌሎችም በደመነፍስ የመጀመርያውን በግ ተከትለው ራሳቸውን ወደ ገደል መልቀቅ ጀመሩ። እረኞቹ ይህንን እብደት ሊያስቆሙ አልቻሉምና የሚሆነውን በድንጋጤ መመልከት ጀመሩ።
የአእምሮህን ኢነርጂ ለመጠቀም የመጀመሪያው እርምጃ የሚሆነው ሌሎችን በጭፍን አለመከተል ነው። አእምሮህን ልክ እንደ ኩራዝ አስበውና የሌሎችን ሃሳብ የምትጠብቅ ከሆነ፣ ልክ በንፋስ ውስጥ እንዳለ ኩራዝ ትሆናለህ። እነሱ በሚፈልጉበት አቅጣጫ እየሳቡም፣ ይህን አድርግ፣ ይህን የማድረግ አቅም የለህም እያሉ ወደ ገደል ይጥሉሃል።
"ይህን ለማድረግ አስቢያለሁ" ባልክ ቅጽበት፣ ህጸጽን እያወጡ ያሽመደምዱሃል። በትንሹ የለኮስካትንም ተስፋ እፍ ብለው ያጠፉብሃል። እናም ከዚህ ሰዎችን የመከተል ሰንሰለት ተላቀቅ፣ የራስህን የስኬት መንገድም አብጅ!
ተወዳጁ #የአእምሮ_ኢነርጂ መጽሐፍ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
👓አንብቡት በተለይ የሰው ምክር ሰምታችሁ ትዳራችሁን የምትበትኑ🙏
እኔና ባሌ አራት አመታትን በፍቅር ኖረናል ፣ በትዳር ደግሞ 4 አመታትን ፣ ትዳርና ፍቅር የተለያየ ነው እያልኩ አይደለም እኔና ባሌ ከትዳር በኋላ ጥሩ የፍቅር ህይወት አልነበረንም ፣ ለዛ ነው ባሌ በጣም ዝምተኛ ነው ፣ ምንም ነገር አጥፍቼ ብሆን አይቶ ዝም ይላል ፣ ስለዚህ የበላይነት ይሰማኝ ጀመር ጓደኞቼም ጀግና እንደሆንኩ መሰከሩ ታዲያ ኩራቴ የበለጠ ጨመረ ።ለባሌ ምንም አይነት ክብር መስጠት አቆምኩ የትም ውዬ ማታ ላይ እመጣለሁ ባሌ በጣም ተናዶ እንኳን ዝም ይላል ። ታዲያ አንድ ቀን አምሽቼ ወደ ቤት ስመጣ በጣም ተናዶ ቆይ ለምን ለትዳርሽ ክብር አይኖርሽም የድሮ ፍቅራችን ወዴት ሄደ አለኝ እኔ ንቄ ገፍቼ ልገባ ስል በጥፊ መታኝ ። ለመጀመሪያ ጊዜ በጥፊ መታኝ ፣ ለመጀመርያ ጊዜ በኔ ላይ በር ቆልፎ እሱ ቤት አደረ ። ጥዋት ላይ ቤተሰቦቼ መጥተው ፖሊስ አምጥተው እሱን እስር ቤት ወሰዱት ።
ከዛም ከእስር ቤት አስወጥቼ የፊቺ ጥያቄ አቀረብኩ ፣ ሁሉም ሰው ትክክል ነሽ አሉ ፣ ጓደኞቼም ጥሩ አደረግሽ የት አባቱ አሉኝ ። ከዛ እሱም በሀዘን ተሞልቶ ድርሻዬን ሰጥቶ ብቻውን ተቀመጠ ። ከሁለት ዓመት በኋላ እሱ ሌላ ሚስት አግብቶ ልጆች ወልዶ ጥሩ ህይወት እየኖረ ነው ። የኔ ህይወት ግን ተበላሸ ። ትላንት ትክክል ነሽ ያሉት ሁሉ ዛሬ ትክክል አይደለሽም አሉኝ ። ትላንት የት አባቱ ወንድ የት ጠፍቶ ያሉት እነሱ ለእራሳቸው ጥሩ ህይወት እየኖሩ ነው ፣ እኔ ግን ብቻዬን ቀረሁ ፣ ትላንት ከአንቺ ጋር ነን ያሉት ሁሉ ዛሬ ከኔ ጋር የሉም ።
እህቶቼ ሴት ልጅ በተፈጥሮ ጠቢቡ ናት የተበላሸ ትዳር ማስተካከል ትችላለች ። ስለዚህ በትዳራችሁ ባልሽ ሞኝ ቢሆን እንኳን አንቺ ትዳርሽን ማስተካከል ትችያለሽ በትዳር መቀልድ ግን ትልቅ አለማውቅ ነው ። ከምንም በላይ ለትዳራችሁ ክብር ስጡ ፣ ትዳር የሴት ልጅ ውበት ነው ። በትዳራችሁ መካከል ለሚገባ ሰው እሱ ሰው መልካም አይደለም ስለዚህ ከእንደዚህ አይነት ሰው እራቁ ምክሩንም አትስሙ.!!!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አለማችን ላይ ስለ ስኬት ፍልስፍና ከተጻፉ መጻሕፍት ውስጥ ቁጥር አንድ እንደሆነ የሚነገርለት የ ‘Think and Grow Rich’ ደራሲ ናፖሊዮን ሂል ለስኬት የሚያበቁ ድንቅ መርሆዎችን በመጽሃፉ አስፍሯል። ከነዚህም ውስጥ አንዱ ‘እራስን ማሳመን-Auto Suggestion’ ሲሆን አእምሮአችን እውነት ብሎ የሚቀበለው ነገር ደግመን ደጋግመን የምንመግበውን እንደሆነ ይነግረናል።
እዚህ ላይ ይህንን በደንብ የሚያስረዳ አንድ ታሪክ ይነግረናል።
ታሪኩ እንዲህ ነው:
<<ሁለት ውሾች የነበሩት አንድ ሰው ነበር። አዘውትሮ እነዚህን ውሾች አደባባይ እየወሰደ እንዲደባደቡ ያደርግ ነበር።
ታዲያ ተመልካቾቹ የትኛው ውሻ በእለቱ እንደሚያሸንፍ ሲጠይቁት “በደንብ የምመግበው ውሻ ነው” ሲል መለሰላቸው። >>
☞ሁላችንም ውስጥ ሁለት ዉሾች አሉ:-
✔ የመልካም እና የክፋት፤
✔ የልማት እና የጥፋት፤
✔ የእውቀት እና የድንቁርና፤
✔ የውድቀት እና የድል ውሾች።
የበላይ ሆኖ የሚመራን ውሻ ዘወትር የምንመግበው ነው።
ለዚህ ነው ናፖሊዮን ሂል “አውቶ ሰጀሽን”ወይም ለራስ መልካም ነገሮችን ደጋግሞ በመንገር አይምሮዋችንን ወደፈለግነው መንገድ መምራት እንደምንችል የሚነግረን።
@abyssinianwisdom
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
እንኳን ደስ አለን!
ኢትዮጵያ ❤
🥇ጉዳፍ - ወርቅ
🥈ለተሰንበት - ብር
🥉እጅጋየሁ - ነሃስ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ጢቅ አድርጎ ብዙ ተሳፋሪ የያዘ ተክሲ ፦
ደባሪ ሙዚቃ በሚንኮሻኮሽ ስፒከር ዘፈን ተከፍቷል ፣ አፉ ውስጥ ጫት የያዘ እየጮኸ የሚያወራ ረዳት ፣
የሚጨቃጨቁ ነበልባል ድምፅ ያላቸው ነጠላ ያጣፉ ሁለት እንስቶች
እሰይ ዛሬ ሰፈር አይውሉም የሚባልላቸው አይነት ይመስላሉ
አንዴ እዚ አንዴ እዛ ግር እያለ አቋም የማይዝ ተሳፋሪ እያጉረመረመ አሮጌ ታኪሲ ውስጥ ተጠቅጥቋል ።
መሪ መያዙን ያልገባው የሚመስል ስሜታዊ ሹፌር ችግር ፈጠረ የሚለውን ሁሉ "ካልተመቻቹ ውረዱ! " እያለ ያስፈራራል ።ረዳቱንም አለቃው እንደሆነ እየሰደበው ያስታውሰዋል ።
ብዙ ቦርጭ በሆዱ የያዘ ትራፊክ ትርፍ መጠቅጠቃችን እያየ እንዳላየ ሆነ።
ልቤ ተጨነቀ ።
ቀልቤን በመስኮቱ አሻግሬ እያየው ከውስጥ ያለውን ጭቅጭቅ፣ ስድድብ፣ ዘግናኝ ሙዚቃ እና መታጨቃችንን ፊት ለመንሳት እየሞከርኩ ነው ።
በታክሲው መስኮት ወደውጪ ስመለከት
በክራንች ታግዘው የሚጓዙ ወጣቶች ። የሚለምኑ አዛውንቶች ፣ ማስቲሽ የሚስቡ ህፃናት ሃሳብ ውስጥ ጭልጥ ብሎ የሚጓዝ መንገደኛ ።
ውጪው እንደውስጡ ይደብራል !
መንገዱ በመኪና ስለተጨናነቀ የተሳፈርኩበት ታኪሲ ይጎተታል ።ወደ ታክሲው ውስጥ ቀልቤንም አንገቴንም ከተትኩ ።
አጠገቤ አንዲት ቆንጆ ልጅ ተቀምጣለች ። ስልክክ ያለ አፍንጫዋ ስር ደማቅ ጥቁር ጥንጥ ነጠብ አለባት ።አንገቷ እርዝም ያለ ነው ። ከንፈሯ እስራስ ቀለም ሊፒስቲክ ተቀብታለች። ደስ አለቺኝ ። ቆዳዋ ጥርት ያለ ነው ።
ላዋራት እጅግ ፈለኩ ። ጫጫታው አላስጀንጀን ይላል ።
ሆድ ባሰኝ ፦
ድንገት አምባረኩኝ ፦
ሹፌር.... ዘፈኑን ቀንሰው አልኩት ቀነሰው ።
ወደ ነገረኛ ሴቶቹ ዞሬ እናንተ ምንድን ነው የምትጨቃጨቁት በጠበጣችሁን እኮ!! ረዳቱን አንተ ደሞ ምንድነው እምጮኸው አልኩት ።
ድንገተኛ ድምፅ ስላወጣሁ ሁሉም ሰሙኝ ግን አፍታ አልቆዩም ።
ሁለቱ ነገረኛ ሴቶቹ አምባረቁብኝ ለካ እኔ ስናገራቸው እነሱም ዝምታ ውስጥ ነበሩ
ሹፌሩ ረዳቱ ተሳፋሪው አንድ ላይ ስድብ ርግማን ግሳፄ ምክር ዛቻ አወረዱብኝ ።
ቆንጇዋ ጠይሞ ልጅ ወደጆሮዬ መጥታ አንሾካሸከች;
" አንተ ውጪ ውጪ ስታይ ታክሲ ውስጥ የነበረው ሁኔታ እና ሁካታ ተቀያይሮ ነበር አለቺኝ ።
ኤጭ አንዳንድ ሁኔታ ለትግል አይመችም !
ሁሉም ሲረባረቡብኝ የምሄድበት ሳጣ ወደ መስኮቱን ዳግም አንገቴን ቀልብሼ በሆዴ እየተራገምኩ ጎዳናው ላይ አፈጠጥኩ።
ከቅድሙ የበለጠ ደመነብኝ ። እነሱ ብቻ የሚያቁት እውነት ያላቸው ሰዎች አሰ..ብ አድርጌ አሳዘኑኝ
ድንገት የጠይሟ ልጅ ውለታ ታወሰኝ
ላዋራት አንገቴን ወደ እሷ ሳዞር
ወራጅ ...ማስለጠኛው ጋ ... አዎ እዚ ጋ አለች እና ወረደች
ተከትያት ወረድኩ ።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ከርስቲያን ምዕመናን እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱ ለተገለጸበት ለደብረ ለታቦር(ብሄ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
በዓሉ ልባችን እንደ ልብሱ ነጭ የሚሆንበት ፤ አእምሯችን እንደ ብርሃኑ የሚበራበት እንድሆን እንመኛለን።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
#ሁላችሁም_ተጋብዛችኋል። (በነጻ)
-----
ልዩ መርሐግብር:- ከደራስያን እና ገጣሚያን ጋር የጨዋታ ቆይታ
የዕለቱ እንግዳ:-
ደራሲ እና ገጣሚ ዮሐንስ ሀብተ ማርያም
ተጋባዥ:
ገጣሚ ረድኤት ተረፈ
ደራሲ እና ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም
ገጣሚ ሰለሞን ሳህል
የተመረጠው መጽሐፍ:- ፍቅር
ሰው
ማህሌት
የመርሐግብሩ አሰናጅ:- ዋልያ መጻሕፍት::
ቦታ:- አራት ኪሎ: ከቱሪስት ሆቴል ጀርባ: ኢክላስ ህንጻ ዋልያ መጻሕፍት::
ቀን:- ቅዳሜ: ነሐሴ 13 2015:: ከሰዓት በኋላ ከ10:00 እስከ 12:30 ድረስ::
@abyssinianwisdom
#ሞክሩት_ይሰራል_አትሸወዱ
በድጋሚ 200 ብር telebirr አካውንቴ ገባ ::
🎁 አንድ ሰው ሲጋብዙ 1 ብር ይሰራሉ ።
🔰 መጋበዣ ሊንክ :
https://t.me/hulepay_official_bot?start=r00701804811
👆👆ለ ካርድ ይሆናችኋል ይሰራል
1 ሰው ስጋብዙ 1 ብር ያገኛሉ minimum withdrawal 10 birr
Fast invite for fast money
