LEARN TECH ||ethiopia ®
رفتن به کانال در Telegram
We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share
نمایش بیشتر1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
በጃፓን ይማር የነበረ አንድ አፍሪካዊ ወጣት በአንድ ወቅት በፌስቡክ ገጹ ላይ እንዲህ ሲል ጽፏል።
በጃፓን ባለ፣ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንግዳ ነበርኩ፣ እና እኔ በምኖርበት ሆቴል መዋኛ ገንዳ ውስጥ እያለሁ፣ ገንዳው ውስጥ ከእኔ በቀር ማንም አልነበረም፣ ውሃው ስር ሽንቴ አመለጠኝ፣ እናም ድንገት... ውሃው ወደ ሮዝ ተለወጠ።
አላርም (ማንቂያው) ጮኸ ወዲያው ሰራተኞቹ መጥተው ከገንዳው ውስጥ አወጡኝ። ከዚያም ውሃውን ባዶ እንደሚያደርጉት እና ገንዳውን እንደሚያጸዱ ነገሩኝ። የሆቴሉን አስፈላጊ ህግና ደንብ እንደጣስኩም ነገሩኝ።
ከዚያ በኋላ ጠሩኝና እንግዳ ተቀባይዋ ፓስፖርቴን ሰጠችኝና ከሆቴሉ እንድወጣ ጠየቀችኝ።
ከሆቴሉ ወጥቼ ሌላ አማራጭ ፈለግሁ፣ እና ሆቴል በገባሁ ቁጥር እንግዳ ተቀባዩ ፓስፖርቴን እያየ “ይቅርታ፣ አንተ ነህ…. አህ… እና ስላልተቀበልንህ ይቅርታ ጠይየቀኝ… ሌሎች ሆቴሎችም ስሄድ ተመሳሳይ ነው… በየትኛውም ሆቴል እንዳርፍ ስለተከለከልኩ ወደ ኤምባሲው ሄድኩ።
ኤምባሲዬ የመዋኛ ገንዳ የሌለው ሆቴል እንድይዝ መከሩኝ...ከጃፓን ስወጣ የፓስፖርት ሹሟ ፓስፖርቴን ስታረጋግጥ ‹ ትምህርቱን እንደተማርክ ተስፋ አደርጋለሁ› አለችኝ።
ማጠቃለያ፡- ሁሉም ጃፓናዊ ሽንቴን በመዋኛ ገንዳ ውስጥ እንደሸናሁ ያውቅ ነበር፣ እኔ የመጣሁባት አፍሪካዊት ሀገሬ ላይ ግን እስካሁን ድረስ መንግስታችን ከመንግስት ግምጃ ቤት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የሰረቀ ማን እንደሆነ አያውቅም።
#ምንጭ:Tales Of Africa
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
Repost from LEARN TECH ||ethiopia ®
ወድ የቻናላችን ቤተሰቦች አድስ የተከፈተውን ጉሩፓችን ይቀላቀሉ
https://t.me/abyssinian_wisdom
ፍቅር የያዘው ሀብታም የፃፈው ግጥም
"አመጣለሁ " ብለሽ ፣ ከቀጠርሽኝ ቦታ
እድሜ እንደ "ቅፅበት" ፣ ዘመን እንደ "አፍታ"
ቆሜ ስጠብቅሽ ፣ ሳላገኝሽ ያልፋል
ስትቀሪ ጊዜ...
ዘላለሜ ባክኖ ፣ ናፍቆትሽ ይገዝፋል፡፡"
ምናምን እያለ...
በቃል አሳምሮ ፣ የሚፅፍ ብሶቱን
የደሀ ግጥም ነው ፣ ልንገርሽ እውነቱን ።
.............................................
አናልሽ የኔ ውብ...
ደሀ "ውድ" ያለውን ፣
"ርካሽ ነው" ብሎ ፣ ሀብታም እየገዛው
ለምን ይመስልሻል...
"ውዴ" የሚለው ቃል ፣ ግጥም ላይ የበዛው?
እውነቱን ልንገርሽ...
ደሀ አፍቃሪ ነው ፣
ግጥምን እየፃፈ ፣ "ውዴ"ን ያጠነዛው ።
............................... ..... .......
እናልሽ የኔ ውብ ...
በፍቅርሽ ተቃጥላ ፣ ነፍሴ ብትቀልጥም
ቆሜ ስጠብቅሽ....
እድሜዬ አያልፍም ፣ ዘመኔ አያመልጥም
ባለሽበት ቦታ ...
"ሳልቀጥርሽ ላግኝሽ" ፣ ሚል ነው የኔ ግጥም።
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
፧፠፨፠፧ አዎ! እሱጋ ያመኛል! - አድኃኖም ምትኩ ፧፠፨፠፧
....
ጋሼ ገዘፍ ያለ መካከለኛ ቁመት የነበረው ፣ ፂማም ፀጉሩን የሚያጎፍር አፍሮ ነው ።
በሽራፊ ሰከንድ ያየው ሰው እርጋታውን የፂሙን ያህል መታየት የሚችልበት ነበር። ቤታችን ኮርነር ጋ ያለው መጽሐፍ የተደረደረበት መደርደርያ አጠገብ ባለው ጠረንጴቤዛና ወንበር ላይ ተቀምጦ ብዙ ጊዜ ያነባል፤ አንዳንዴም ይጽፋል።
"አታቲዬ ጋሺዬ ምንድን ነው የሚያጠናው? ይማራል እንዴ? "
ፈገግ ትልና “ጋሼ እኮ ጸሐፊ ነው።” ፊት ለፊት ከድርድር መጽሐፍት ጎን የተከማቹትን ጋዜጦች እየጠቆመችኝ...
“እነዛ ጋዜጦች ላይ ይጽፋል ፤ “ያኛው ሦስተኛው መደርደርያ ላይ ለብቻው የተቀመጠው መጽሐፍትእኮ የእሱ ሥራዎች ናቸው።” ትለኛለች
"ያ ሁሉ ...?"
“አራት ናቸው እኮ ፤ ሦስት ሦስት ቅጂ ተደርጎ ስለተቀመጠ ነው።”
"ግን እኮ አንዱ ራሱ ወፍራም አይደል እንዴ?"
ስስ የተሰሰተ የሚያበረታታ ፈገግታ በጠይም ፊቷ ላይ አርብባ
“በእርግጥ አዎ!”
”ግን መጻፍ እና ማንበብ ይገናኛል እንዴ?”
”በደንብ እንጂ!
ጎበዝ አንባቢ ያልሆነ ጎበዝ ጸሐፊ አይሆንም። ምናብ ብቻውን ሩቅ አያራምድም ፤ ቁንፅል ያደርጋል።”
ዝም ብዬ ያልሺው አልገባኝም ፣ አብራሪልኝ ተማፅኖ በሚመስል ሳያት
“ይኼውልሽ እድሌ በምትሠሪው ሥራ ታዋቂ ፣ ጎበዝ ፣ ዝነኛ ለመሆን ሥራው ከሚያስፈልገው ትጋት በላይ ካልኖረሽ በሥራው ላይ ከተሰማሩት የበለጠ ማማ ላይ አትወጪም ፤ ስመጥር መሆን አይቻልሽም።”
።
።
።
አታቲ ስትሰማው ትቆይ እና "ፓ አንተ እኮ ምድር ባትመጣ ታጎላለህ" ትለዋለች።
አንዳንዴ ደግሞ ሲያነብላት ታጨበጭብለታለች ወይም ታቅፈዋለች ፤ አንብቦላት ያልተደመመችበት ቀንን አላስታውስም
እጅግ አልፎ አልፎ ጽሑፍ ካነበበላት በኋላ ይሟገታሉ ፤ በእርጋታ ይሰማት... ይሰማት እና ያብራራላታል።
ትሰማዋለች ፤ ሙግታቸው የጎበዝ አስተማሪና የጎበዝ ተማሪ ወይም ደግሞ የሆነ የሚዋደዱ የታናሽ እና የታላቅ አይነት ነው ፤ ያኔ የሙግታቸው እና የውይይታቸው ኮንተንት (ፍሬ ነገር) አይገባኝም ነበር ፤ ሁኔታቸው ብቻ እንጂ ከእነሱ ጋ መኖር ያስለመደኝ ነገር ቢኖር ረጅም ሰዓት መስማትና ያልገባኝን ነገር ለመረዳት ስል በትህትና መጠየቅን ነው።
አታቲዬ ጋሼ ከሞተብን በኋላ በቀስታ አረቄ ውስጥ ተመሸገች።
ትንሽ ቀማምሳ እቤት ትመጣና
“እድሌ” ትለኛለች
"ወይ አታቲዬ"
“በጣም ጎበዝ ፣ በጣም ተንከባካቢ ፣ በጣም ጀግና እና ታታሪ እንዳታገቢ እሺ .... ድንገት ካጣሺው ትዝታው እና እጦቱ አያራምድሽም።”
"እሺ አታቲዬ"
“እድሌ ..”
"አቤት አታቲዬ”
“ስታገቢ ተራ ፣ ከሰው የተለየ ጉብዝና ያላየው ፤ ኖርማል ፣ የትም የሚገኝ ፣ የትም ያለ ፣ ከብዙ ሰው የማይለይ ፣ መርህ እና ግብ ያልታጨቀበት አግቢ እሺ ብታጪው እንኳን ማንነትሽ አይናድም... እሺ እድሌ”
"እሺ. .. እሺ. . አታትዬ"
።
።
።
አጀንዳውን እንደዘበት ስከፍተው እንዲህ የሚል ጽሑፍ አገኘው ...
‘ምድር ከሰጠችኝ ገፀ በረከት እሷ ዋነኛዋ ነች።
ምድር ላይ መቆየት ካማረኝ የሚያምረኝ በእሷ ምክንያት ነው ፤ የህይወት ተጋድሎዬን ያህል ነው ትርጉም የምትሰጠኝ ፤ በዚህ በዝባዥ ስርዓት ፣ በእዚህ አምባገነን ስርዓት ፤ ሕዝብ ከቁጥር በቀር ትርጉም በማይሰጠው ይህን በዝባዥ አገዛዝ እታገለው ዘንድ እሷ የምትሰጠኝ ተስፋ እና ፍቅር ግዙፍ ነው።
‘Socialism እና Karl Marx’ እንደማይነጣጠሉ ሁሉ የኖረኝ ክብር እና ዝና ከእሷ ከሚስቴ ጋር ሊነጣጠል እና ካለ እሷ የሚቻል አልነበረም ፤ አይኔን አይታ የምትታዘዘኝ እና የምታዝንልኝ የእኩለ ለሊት ብርሃኔ እሷ ናት።
እሷ ጠይም የደስታ መግቢያ በሬ ናት ። እሷ ሳትኖረኝ ምንስ ቢኖረኝ ምን ያደርግልኛል !? ስንት ቀን እሱን ያየ ፤ ከእሱ ጋ የቆመ እንደሎጥ ሚስጥ የጨው ሃውልት ይሆናል ተብሎ ታውጆ እንኳን ምን ቢመጣ ካላንተ ስሆን ከሚሰማኝ አይበልጥም ብላ አብራኝ ነበረች ፤ ስንቴስ መቀመቅ ሲያወርዱኝ ከእሷ በቀር ማን አብሮኝ ቆመ ?!
እሷ የነፍስ ምግብ ፀዳሌ ናት።
ምንም ብሆን ፤ ምንም ባጣ የማይደንቀኝ ልበ ደንዳና እንደሆንኩ ያለፍኩበት ጨለማ ይመሰክራል እሷ ብቻ ከእኔ ጋ ትሁንልኝ እንጂ። እሷ ከቀደመችብኝ ያን እለት ነው ኩራባቸው መንፈሱ የሚታወከው ፤ እሷ ካለችማ ኩራባቸው ልቡ ላይ ሃሴት እንደተመላለሰ የተሰፈረለትን ዘመን ይጨርሳል ....
እሷ የልቤ ብርሃን ናት።
ግፍን እቋቋም ዘንድ የተቸረችኝ ጫንቃዬ ናት ፤ በንፅህና ከእውነት ጋ እንድቆም ፣ አቋሜ እንዳይሸረሸር ፣ መንገዴን ፣ አቋሜን በፍቅር ከመንገዴ እንዳልሰናከል በትልቁ አቅም ሆናኛለች።
በጠላት፣ በአሰናካይ ፣ በቀለብተኛ ተከብቤ ሳለሁ እንዳላፈገፍግ የምታበረታኝ የደስታዬ ፍላፃ መዓዙን የአላማዬ ያህል ነው የምወዳት ......’ይላል
።
።
።
ሌላ ገጽ ገለጥኩ…
‘“I will not quit until I make my dreams come true.” እንደምን ድምፅ ለመሆን መጥቼ ዝም እላለሁ ፤ በዜጎች መሃል ግጭትን የሚቸረችር አገዛዝ ፤ የማንነታችንን ግንብ የሚሸረሸር ትርክት የሚያንሸረሽሩ ቀለብተኞች ባሉበት ፤ ግፍ ባራኪ ፣ ሞራል አልባ አሸከር ፣ ፈሪ ፣ መርህ አልባ አለቅላቂ ልሂቃን በተሰባሰቡበት ምድር ተገኝቼ እስክሞት ዝም አልልም ደሞስ ላለመሞት አልመጣሁ ይግደሉኝ እንጂ መቼም እንደማልደለል እኔም ፣ መዓዙም ፣ እነሱም ያውቃሉ።
እኔ ኩራባቸው ይልማ አገር እንድታብብ ከማለም በቀር ፤ መነሻ አልባ ትርክት ከማጋለጥ በቀር አንድም ስውር ህልም እና ግብ ኖሮኝ እንደማያውቅ የልቤን እውነት የምታውቀው መዓዚ ህያው አምላኬ ምስክር ነው እንጂ’ማ ስንቴ በስልጣን ሊደልሉኝ ታከውኝ የለ ፤ እንጂ’ማ በጉቦ ሊጥሉኝስ አላሴሩም ፤ እኔ ኩራባቸው ሳንቲም ግድ የሚሰጠኝ መስሏቸው .. ሃሃሃሃሃ የሚታገሉትን ኩራባቸውን አያውቁትም እኮ።’
ሌላ ገጽ ገለጥኩ ...........
፧፠፨፠፧ # Adhanom Mitiku -
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ዝናብ ባይኖር እንኳን ችግኝ ትከሉ
በሰው ደም እና እንባ አይቀርም መብቀሉ
በላይ በቀለ ወያ
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ወንጀለኛዋና ሐዘንተኛዋ
በአፍላ የፍቅር ዘመን የማይሆኑት የለም።መሮጥ-መሯሯጥ፥መምታት-መማታት፥መሳቅ-መሳሳቅ፥መብረር-ማባረር፥አረ ስንቱ!የሁለቱም ወገን ድርጊት በወጉ ለፍቅር፥ለደስታ ስለሆነ ለክፉ አሳልፎ አይሰጥም፤በመካከሉም ለቀልድ ተብሎ የሚወረወር ጠጠር አናት ፈርክሶ ሲያደማ መታየቱ ከፋ እንጅ!
የ27 ዓመቷ ዩጎዝላቪያዊት ሚላንካና የ32 ዓመቱ ጉብል ኢሊጃ ተፈቃቅረው ከተጋቡ መንፈቅ አልሞላቸውም።አቶ ባል አንዳንድ ጊዜ ድንገተኛና ያልታሰበ ድርጊት እየፈፀመ ሚስቱን ያስደነግጣል፥"ውቃቢ ያስርቃል"፤ያስቃል።በአራዳው ቋንቋ ይኮምካታል እንደ ማለት ነው።ሚስትም እንደዚሁ።
አቶ ኢሊጃ ባለቤቱን እቤት ትቶ ለስራ ይወጣና በዚያው ከአንድ ጓደኛው ቤት ይሄዳል።ሲመለስ ከዚያው ከጓደኛው ቤት የተዋሰውን ሙሉ ማስክ በማጥለቅ ወደቤቱ ያመራል።ከደጁ ደርሶ በር ሲያንኳኳ ሚስት በመስተዋቱ የታያት ባሏ ሳይሆን እጅግ አስፈሪ ልብስ የለበሰ ሰው ይሆናል።ታዲያ ባልዋ በአጋጣሚ ክፉ ቀን ሲገጥማት ራስዋን ለማዳንና ከአደጋ ለመከላከል ትችል ዘንድ የጠመንጃ አተኳኮስ አስተምሯት እንደነበር ማስክ አጥልቆ የመጣውን ሰው ስታይ ትዝ ይላታል።
ወይዘሮ ሚላንካ ወዲያው ወደመኝታ ክፍሏ ትገባና የባሏን አውቶማቲክ ጠመንጃ ከቁምሳጥን አውጥታ የሚያብለጨለጩ ጥይቶቹን በማቃም አቀባብላ ወደበሩ ተጠጋች።በሩ ባለመስታወት ስለነበር ወይዘሮዋ ጠመንጃዋን ደግና ሰውየው ከአከባቢው እንዲሄድ ምልክት ታሳየዋለች።ያ ሞቱ የቀረበ ባል ግን ሚስቱ ላይ የቀለደ መስሎት እምቢታ በማሳየት እዚያው ይገተራል።ፊትዋን ብታኮሳትር፥እጇን ብታወራጭ ሰውየው ፍንክች ሳይል ይቀራል።
ወይዘሮ ሚላንካ የመጨረሻውን ርምጃ በመውሰድ ቃታ ስባ ተኩስ ከፈተች።የጥይት መዓት የተርከፈከፈበት ያ "ምስኪን " ባልዋ ከደጃፉ ላይ ተደፋ።ወዲያው ሟች በአንቡላንስ-ገዳይ በፖሊስ ታጀቡ። ሆስፒታል ተደርሶ የሟች ማስክ ሲገለጥ ቆማ ትመለከት የነበረችው ወይዘሮ ሚላንካ እራስዋን ይዛ እዬዬዋን ታቀልጠው ጀመር።በነገሩ ግራ የተጋቡት ፖሊሶችና ሐኪሞች ሚላንካን ዘወር አድርገው ሁኔታውን ማጣራት ሲጀምሩ ሟች ባል፥ገዳይ ደግሞ ሚስት መሆናቸውን ይረዳሉ።በሚስቱ እጅ የውሸት ሳይሆን የእውነቱን ሞት የተቀበለው ኢሊጃ በማግስቱ ሲቀበር ሴቲቱ ግን ማረፊያ ቤት ገባች።"ወንጀለኛም ሃዘንተኛም" መሆኗ ነው እንግዲ።ያለቦታው የሚሆን ቀልድ ለዚህ አበቃ።"ቀልድና.....ቤት ያጠፋል" እንዲሉ።
📚 @abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
""""ንገሯት ለእናቴ""""
ልጄ ልጄ ስትል ስሜን ስታዎሳ፣
ልሂድ አይኗን ልየው.....
ልጠይቃት ብላ እግሯን ስታነሳ፣
እዳትመጪ በሏት ብትላችሁ እሽ፣
ልጅሽን ለማዬት እግርሽን አታንሽ፣
በቁሟ ሙታለች ብትችይ አታስታውሻት፣
ከነመፈጠሯ ከመኖሯም እርሻት፣
በሏት.....
አደራ ንገሯት አጥብቃችሁ ሞቴን፣
ብትናፍቀኝም.....
ላያታ አልፈልግም እንዲህ ሆኜ እናቴን፣
ወይም እዲህ በሏት ብላለች አትምጪ፣
ልጅሽ ክዳሻለች በቃ እርምሽን አውጪ፣
ወልደሽ አሳድገሽ ልጦርሽ ሲገባ፣
እናቷን ከሀዲ ሆነች የማትረባ፣
በሉልኝ ብታምን፣
አልባሷ ቡትቶ ስራዋ ምናምን፣
ይቅርና ለናቷ ያልሆነች ለነብሷ፣
እርኩስ.... የረከሰች.....
ለሁሉ ከፍ የሚል ወለቂ ቀሚሷ፣
እንኳንስ ሊኖሯት ልጆችና ትዳር፣
ቤት የላት መጠጊያ አዳሯ መንገድ ዳር፣
ንገሯት ለናቴ ኑሮዬን ትረዳ፣
አትሆንም ለዘመድ አጠቅምም ለባዳ፣
ድሮ የምታቂው በልጅነት አለም፣
ያ የሚያምረው መልኳ ገፅታዋ የለም፣
በውስጥሽ ያለውን የልጅነት ምስሏን፣
አጥፊ ተያት እርሻት አታስታውሻት እሷን፣
በሏት......
አይ.... አይ.... አትበሏት.....
ይቅር አትንገሯት እውነታውን ለእማ፣
የሚጨክን አንጀት ይህን እየሰማ፣
ጆሮ ዳባ የሚል አካል ስለሌላት፣
በቃ እደውም ተዋት፣
እሽ አትልም ትምጣ፣
ልቀበላት እና አይታኝ እርሟን ታውጣ።
✍❤️✍❤️✍❤️
ኤዶምገነት ፃፈችው
@Edom_Ge
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ለሞተ ወንድ የሚዳሩ ሴቶች
የደቡብ ኦሞሸ ክራሞቴ'
ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ "ያልተቀበልናቸው" በሚለው መፅሐፉ '
* * *
በደቡብ ኦሞ አከባቢ ካሉ ህዝቦች መካከል በናዎች ፥ ፀማዮች እና ኤርቦሬዎች ከሌላው ህዝብ የተለየ ልማድ አላቸው፥ ልማዳቸው ከእውነት ይልቅ አእምሮ ወለድ ለሆነ ምናባዊ ፈጠራ የቀረበ ይመስላል። ልብ-ወለዳዊ አልያም ተረት እንጂ መሬት ላይ ያለ የገሃድ አለም ልምምድ መስሎ አይታይም።
አንድ ወንድ ተወልዶ ሚስት ሳያገባ ቢሞት ለሟቹ ሚስት ይዳርለታል። ሟች እንደህያው ተቆጥሮ ከአከባቢው ሴቶች መካከል ሚስት የምትሆነው ትመለመላለች። ለሚስትነት ለተመረጠችው ሴት በባህሉ መሰረት ሽምግልና ይላካል።
ሟች ገና የተወለደ ጨቅላ አሊያም ለአቅመ አዳም የደረሰ ወጣት ሊሆን ይችላል። እድሜው ለውጥ አይፈጥርም። ዋናው ቁም ነገር ትዳር አለመመስረቱ ነው።
ወንድ ልጅ ሳያገባ እንዲሞት አይፈለግም። ትዳር አለመመስረት አይበረታታም። ድንገት ቤተሰብ ሳይመሰርት ይህችን አለም ትቶ ቢሰናበት ለሙት መንፈሱ ሚስት ትታጫለች።
ሟችን በመወከል የቅርብ ቤተሰቡ ለተመረጠችው ሴት ቤተሰቦች ሽምግልና ይልካሉ። "ልጃችሁን ለሞተው ልጃችን ዳሩልን" ብለው ይጠይቃሉ። የልጅቷም ቤተሰቦችም በወጉ መሰረት ልጃቸውን ሊድሩ ይስማማሉ።
ሰርግ ይደገሳል። ሟች ሙሽራ በሌለበት የሞቀ ድግስ ይደረጋል። ሙሽሪትም በይፋ የሟች ሚስት መሆኗ ይረጋገጣል።
ሴቷ የሚስትነት ወግ ጠብቃ መኖር ትጀምራለች። በተዘጋጀላት መኖሪያ የሴትነትን ሃላፊነቷን እየተወጣች ኑሮዋን ትገፋለች።
በተዘጋጀላት ቤት የሟች ሚስት ሆና በምትኖርበት ጊዜ እንግዳ የማስተናገድ ሃላፊነት ይጠብቃታል።
እንግዳው የሟች ወንድም ወይም የቅርብ ዘመድ ነው። በምሽት ወቅት ማንነቱ እንዳይታወቅ ተጠንቅቆ በጨለማ ወደ ሴቷ መኖሪያ ይገባል። የእንግዳው መምጫ ምክኒያት ምን እንደሆነ ስለምታውቅ ጭኗን ከፍታ ራሷን ትሰጠዋለች። ባህል ነውና ከሟች ዘመድ መካከል አንዱ እንደሚሆን ከሚገመተው ሰው ጋር ወሲብ ትፈፅማለች።
'አይሆንም' ማለት አይፈቀድላትም። ሰውዬውን አልፈልግም ለማለት የምትችለው በአንድ ልዩ ሁኔታ ብቻ ነው። ሰውዬው ሲመጣ አስቸጋሪ አመል ካየችበት 'ሂድልኝ' ብላ ልታበረው ስልጣን አላት። ነገር ግን በሱ ምትክ ሌላ ወንድ ሲመጣ ልታስተናግደው ትገደዳለች።
በዚህ መንገድ አብራው ከምትተኛው ወንድ ፅንስ የሚፈጠር ሲሆን የተወለደው ልጅ ህጋዊ አባት ተደርጎ የሚቆጠረው ሟች ነው። የተኛት ወንድ ለሚወለደው ልጅ እንደ አባት አይቆጠርም፥ ሴቲቱን እንደ ባል አይንከባከባትም፥ አንዳች ሃላፊነት አይኖርባት፥። ምሽት ሲሆን በስውር ወደቤቷ እየመጣ ይገናኛታል። ሴቷ ይሄን ሁሉ በፈቃዷ እንድትከውን ባህል ያስገድዳታል።
የሴቲቱ ሚስትነት ለሞተ ሰው ነው። ለተወለደው ልጅ አባት ተደርጎ የሚቆጠረውም ሟች ነው። "የማን ልጅ ነው?" ቢባል "የሟች ልጅ" ይባላል
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አንድ ጊዜ በጣም ስኬታማ የሆነች ሴት ሚስጥሯን እንድታካፍለኝ ጠየኳት።
ፈገግብላ እንዲህ አለችኝ...
"እኔ ስኬታማ መሆን የጀመርኩት ትናንሽ ትግሎችን ለትናንሽ ታጋዮች መተው ስጀምር ነው።
ሀሜተኛ የሆኑብኝን መጣላት አቁሜያለሁ...
ከጠላቶቼ ጋር መጣላት አቁሜያለሁ...
ትኩረት ለማግኘት መታገል አቁሜያለሁ...
ሰዎች ስለእኔ የሚጠብቁትን ነገር ለማሟላት መታገል አቁሜያለሁ...
ሁሉንም ሰው ለማስደሰት መታገሌን አቁሜያለሁ...
ስለኔ ትክክል እንዳልሆኑ ለማሳየት ትግሌን አቆምኩ...
እንደዚህ አይነት ሙግቶችን ሌላ ጠብ ስለሌላቸው ተውኩት...
እናም ለራዕዬ፣ ለህልሜ፣ ለሀሳቤ እና ለዕጣፈንታዬ መታገል ጀመርኩ።
አንዳንድ ግጥሚያዎች ጊዜህን አይመጥኑም.....
የምትታገልለትን ነገር በጥበብ ምረጥ!"
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
**ማንኛውንም
አላማ እንዴት
ማሳካት
ይቻላል?**
___
1:-ስለምትፈልገው በትክክል መወሰን
2:-እቅዶችህን በወረቀት ላይ አስፍር
3፦ዋጋ ለመክፈል አታመንታ
4፦ግልጽ እቅድ ንደፍ
5፦ በእቅድህ መሠረት ወደ ተግባር ግባ
6፦ በየቀኑ የሆነ ነገር ስራ
7:- እጅ አትስጥ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ከመፅሐፈ ... " ችቦ "
ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ (ዶ/ር)
" ..... ስንት ሰው አስቦና አቅዶ ስንቱን አፈናቀለ ። ዘላለም የምንኖር ይመስል ስንቶችን ካደጉበትና ከኖሩበት ቀዬ ገፋን ። በጎሳ ፖለቲካ ሽፋን ስንቶቹ ያፈሩትን ጥሪት ተቀምተው ተፈናቀሉ ። ስንቶች በማያጠረቃ ኢንቨስትመንት ሰበብ ተገፉ ። መቻቻል አቃተን ፤ መታገስ እየተሳነን ስንቶቹን አፈናቀልን ። ስንቶቹን በምሬት እንዳይኖሩ መሞትን እንዲመኙ አደረግን ። እኛ እራሳችን ለስደት የሰው በር እያንኳኮን ስኔቱን ለስደት አበቃነው ። የእውነት ዘመን ፣ የፈጣሪ ፍርድ ስትመጣ ይህንን የሕሊና እዳ ፣ የሞራል ጥያቄ ማን ይመልሰው ይሆን ? .... "
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
📘ዴርቶጋዳ
✍ይስማዕከ ወርቁ
አንዲት ጠብታ ዝናብ ለ አንድ ጉንዳን ውቅያኖስ ብትሆንም ብዙ ጉንዳኖች አንድ ላይ ከተያያዙ ግን ውቅያኖስ መሻገር ይችላሉ።
📚 @abyssinianwisdom
ከ "ሀ" እስከ "ሃ"
ወንበርን የያዙት ~ ጉዳይ ተቀብለው
ጉዳይ ሚያስጨርሱ
ይመስሉኝ ነበረ ~ ፊደል በስርዓት
ቆጥረው የጨረሱ
ዳሩግን ወዲህ ነው~መማር ተምረዋል
ሙሉውን ባይሆንም~ጥቂት ግን ቆጥረዋል
አዎ ሰምቻለው
እንደውም አቃለው
ከፊደል ገበታ ~ መጀመሪያ መስመር
ከ ''ሀ'' እስከ "ሃ'' ድረስ ~ ቆጥረው እንደነበር
እና እኚ ሰዎች
ሆነው ሰራተኞች
ሲያስፈፅሙ ጉዳይ
አንድ ነገር አለ ~ ሁልጊዜ የማይቀር
ሁልጊዜ የሚታይ
ምንድነው ካላችሁኝ~ የጥያቄው መልሱ
ናቸው እና እነሱ
"ሀ" ብለው ጀምረው "ሃ"~ ላይ እንደቀሩ
እዚህ የደረሱ
ጉዳይ አይፈፅሙም ~ "ሃ" ባለ አፋቸው
ጉርሻ ካልጎረሱ::
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
➱@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
#በአእምሮህ_መታደስ_ተለወጥ!
ከመጽሐፍት ሁሉ እጅግ ትልቁ የሚባለው መጽሐፍ፤ “ሰው በልቡ እንዳሰበ እንዲሁ ነውና” ይላል፡፡
አሁን የምናስበው፣ ለረጅም ጊዜ እያሰብን የነበረው፣ ወደፊት የምናስበው ነገር ምን እንደምንሆን እና የምንኖርበትን አለም በትክክል ይወስናል።
ሁልጊዜም የምንሆነውን የሚወስነው የምናስበው ነገር ነው።
አስተሳሰባችንን ስንቀይር፣ ዓለማችንን እንለውጣለን። አስተሳሰባችንን በትክክል ስንለውጥ፣ ሁሉም ነገር ወደ ውስጣዊ ሰላም፣ ደስታና ግላዊ ኃይል ይለወጣል፡፡
ታላቁ መጽሐፍ፣ በአእምሮአችሁ መታደስ ተለወጡ። (ሮሜ 12÷2) ይላል፡፡ ከዚህ የበለጠ ጥበብ ያለበት ነገር ፈጽሞ አልተነገረም።
ይህ ማለት በአስተሳሰባችን መንፈሳዊ እድሳት ራሳችንን፣ የምንኖርበትን አለም፣ የቤታችንንና የንግዳችንን ሁኔታ እንዲሁም መላ ህይወታችንን መለወጥ እንችላለን ማለት ነዉ::
ምንጭ:- ሶሉሽንሰሚናር
መልካም ቀን
@abyssinianwisdom
@Abyssinianwisdom
ከሄድኩኝ በኋላ.......
.
.
በየጥጋጥጉ በየመሸታዉ ቤት፤
በየሰርጣ ሰርጡ ሰዉ ባገኘኝበት፤
ለአላፊ አግዳሚው መንደሬዉ በሙሉ፤
ፍቅር መኮብለሏን ትነግራለህ አሉ፣
አይታክትህ መቼም.........
በር በሩን ስታይ ዉለህ ማመሻሸት፤
እንቅልፍ የራቀዉን አይንህን ማሻሸት።
ባታዉቅልኝ እንጂ........
ጀርባዬን ሰጥቼህ መንገዴን ስቀጥል፤
ልብህን ቃኘሁት ህመም ሲያቀጣጥል።
ከሄድኩኝ በኋላ ልቤ ከኔ ርቃ፤
ፀፀት ለገሰችኝ ከእንባ ጋር መርቃ።
ሚዛኔን እየሳትኩ ምስቅልቅሌ ወጥቶ፤
ትዝታህ አመመኝ አቅሜን አሳጥቶ።
እንጃልኝ መዉደዴ......
አይኔን በጨዉ ዉሃ ልጠበዉ መሰለኝ፤
ጉዳትህን ሽሮ ከእቅፍህ ቢያኖረኝ፤
ፀፀቴን አጣጥቦ አንተን ቢያሳየኝ።
........................................
ተፃፈ፦በኤደን ታደሰ
@ediwub
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
➡The Troxler fading illusion ይባላል አንድ ጊዜ ሙሉ ትኩረታቹን መሀል ላይ ያለው ምልክት ላይ አድርጉና ለ 10 ሰከንድ ተመልከቱት
ካስተዋላቹ ሌላው ቦታ ወደ ነጭ ቀለም እየተቀየረ ነው አይደለ ካልተቀየረ ትኩረት አልሰጣቹም ማለት ነው ።
➡ይህም የሚሆነው አይምሯችን ራሱን ላለማድከም ካተኮርነው ቦታ ውጪ ያለውን እንደ አካባቢው ቀለም ስለሚለውጠው ነው
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
ሳትፈልግ ይፈልጉሃል ፤ መፈለግ ስትጀምር ታጣቸዋለህ! ያኔ ትርፉ ቁጭት በማጣትህ ሳይሆን ለምን መፈለግ ጀምርኩ ፤ ባለሁበት ለምን አልጸናውም በሚል!!!
አቡ
@abyssinianwisdom
ዓሳ አጥማጁ
© Bekirstos kassa
ዓሣ አጥማጅ ገና ሳይነጋ በጠዋቱ ወደ ባህር ዳርቻ ሄደ ነገር ግን ይህ ሰው የደረሰበት ሰዓት ጨለማ ነበር...
በወቅቱም ለማጥመድ ሥራው ስላልተመቸው እስኪነጋ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ጀመረ ። እናም በጭለማው ውስጥ ከባህር ዳርቻውም አጠገብ በድንጋይ ጠጠሮች የተሞላ ጆንያ አጋጠመው፡፡
ዓሳ አጥማጁም ከጆንያው ውስጥ ያለውን አንድ ጠጠር አውጥቶ ወደባህሩ ሲወረውረው እንቦጭጭጭጭ የሚል ድምፅ ሰማ፡፡
...ይህም ድምፅ ስላስደሰተው ወድያውኑ ሌሎች ጠጠሮችን በየተራ እየወረወረ እንቦጭ እንቦጭ እያደረገ እየተደሰተ መወርወሩን ቀጠለ...
ይህ ዓሣ አጥማጅ በጆንያ ውስጥ የነበሩትን ጠጠሮች ወርውሮ አንዲት ጠጠር ብቻ ስትቀረው ነጋ ወዲያው የብርሃን ወገግታ መምጣቱን አስተዋለ፡፡
አጥማጁም የያዘውን ጠጠር ለመወርወር ከመቀመጫው ብድግ ሲል በእጁ የያዘውን ጠጠር አብረቀረበት... #አንፀባረቀበት ዓሳ አጥማጁ ድንገዩን በደንብ አገላብጦ ተመለከተ ደነገጠ። በድንጋጤም ውስጥ ሆኖ ሲያስተውለው ጠጠር ሳይሆን አልማዝ መሆኑን ተረዳ፡፡
ዓሣ አጥማጁም በንዴት ሲቃ ተናነቀው ምከንያቱም እስኪነጋ ድረስ ሲወረውር የነበረው ጆንያ ሙሉ ጠጠር ሳይሆን አልማዝ መሆኑን አስተዋለ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇
🙏ብዙ ሰዎች በህይወታቸው እንዲህ ናቸው፡፡ በእጃቸው ያለው ጊዜ አልማዝ መሆኑን ሳይረዱ እንቦጭ እንቦጭ የሚል ድምጽ ለመሰማት ሲሉ ውድ ጊዜያቸውን እና እድሜያቸውን በእንቅልፍ፣ በፊልም፣ በማህበራዊ ድህረ-ገጽ ፌስቡክ ቴሌግራም ቲክቶክ ላይ፣ በወሬና በጥል፣ በፑል ቤት በመጠጥ በክርክር እና በብስጭት ወደ ጥልቁ እና ወደ ማይመልሰው ባህር ይወረውሩታል።
፧
መክሰር እንዲህ ነው ልጅኘት ጅልነት እያልን የምንቆጭበት ዘመን ይመጣል፡፡ የአሁን ችግራችን የትናንት ስህተቶቻችን ጥርቅም ነው፡፡ እንደ አሳ አጥማጁ ከጊዜዊ እርካታ ይልቅ ዘላቂ ደስታ ብንመኝ ይሻል ነበር::
እድሜና መላጣነት ሲሄድ አይታወቅም በተሰጠን ጊዜ ልንሰራው የሚገባውን እንስራ፡፡
፧
👍 ጥቂቶች ደግሞ እንደ ዓሣ አጥማጁ በመጨረሻ ሰዓት ጊዜያቸው አልማዝ እንደሆነ ሲረዱ አብዛኞቹ ግን ጊዜ ምንም እንዳልሆነ ሳያውቁ በዚያው ያበቃል፡፡😭😭😭
የሰው ልጅ በምድር ላይ የተሰጠው ጊዜ ውስን መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው፡፡ ይህንንም ውስን ጊዜ በወቅቱና በሰዓቱ ካልተጠቀመበት እድሉ ላይመለስ ይወሰድበታል፡፡ ማንም ምንም ቢለፋ ቢያለቅስ ቢፀፀት ተመልሶ አያገኘውም፡፡ ይልቁንም በጊዜው የዘራውን መልካም ይሁን ክፉ በጊዜው ያጭዳል፡፡
ደህና እደሩ
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
አንድ ባለስልጣን አማኑኤል ሆስፒታልን እየጎበኙ አንድ በሽተኛ ያጋጥማቸውና ጠጋ ብለው
ወደዚህ እንዴት ልትመጣ ቻልክ ማለቴ የህመምህ መንስኤ ምንድነው?' ብለው ይጠይቁታል ።
በሽተኛውም መለሰ...
' ጌታዬ ይሄ ሁሉ መዓት የወረደብኝ አንዲት መናጢ ሴት ሳገባነው።
ይሀውሎት አንዲት አግብታ የፈታችና ቆንጆ ሴት ልጅ ያለቻት ወይዘሮ አገባለው።
እናም ይህቺ ቆንጆ ልጅ የእንጀራ ልጄ ሆነች ማለት ነው።
ከዛ አባቴ አንድ ቀን ሊጎበኘን ይመጣል። በዚህች ቆንጆ ልጅ ፍቅር ይከንፍና በግድ ያገባታል።
ስለዚህ የእንጀራ ልጄ የእንጀራ እናቴ ሆነች ማለት ነው። ባለቤቴም ለኔ አንድ ወንድ ልጅ ትወልድልኛለች።
በመሆኑም የኔ ልጅ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ ለአባቴ ደግሞ ዋርሳ ሆነ ማለት ነው ምክንያቱም አባቴ የእንጀራ ልጄን አግብቷልና።
እና እንደነገርኩህ የእንጀራ ልጄ አባቴን ስታገባ እሷ በመጀመሪያ የእንጀራ እናቴ ሆነች በኋላ ላይ ደግሞ ወንዱ ልጄ ለእንጀራ እናቴ ወንድም ስለሆነ እርሱ ደግሞ በተዘዋዋሪ አጎቴ ሆኖ እርፍ!
ሚስቴ ደግሞ የእንጀራ እናቴ እናት ስለሆነች የእንጀራ አያቴ ሆና እርፍ!
የእንጀራ እናቴ የእንጀራ ልጄ መሆኗን አትርሳ። እንዲሁም የራሴ የገዛ ሚስቴም የእንጀራ ልጅ ልጅ መሆኔንም አትዘንጋ። ይሄ ሁሉ ሲሆን እኔን የገረመኝ የእንጀራ አያቴን ስላገባሁ ለሚስቴ የእንጀራ የልጅ ልጇ እና ባሏ ብቻ ሳልሆን የራሴም አያት መሆኔ ነው።
ወደዚህ ወደ አማኑኤል ሆስፒታል አብጄ የመጣሁበት ምክንያቴም ይሄው ነው!!'😭
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
@abyssinianwisdom
