fa
Feedback
LEARN TECH ||ethiopia ®

LEARN TECH ||ethiopia ®

رفتن به کانال در Telegram

We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share

نمایش بیشتر
1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
ሰበዝ ቁ.2 ልትሉት የምትችሉት መጸሐፍ ከች ብሏል!! 16 አጫጭር ታሪኮችን ይተርክልናል... ምን ተብላችኋል መሰላችሁ.. #ዶክተር_ዓለማየሁ_ዋሴ "ይህ 'ችቦ' በሚል ርዕስ የቀረበው ስድስተኛ መጽሐፌ
ሰበዝ ቁ.2 ልትሉት የምትችሉት መጸሐፍ ከች ብሏል!! 16 አጫጭር ታሪኮችን ይተርክልናል... ምን ተብላችኋል መሰላችሁ.. #ዶክተር_ዓለማየሁ_ዋሴ "ይህ 'ችቦ' በሚል ርዕስ የቀረበው ስድስተኛ መጽሐፌ ቀደም ሲል 'ሰበዝ' ከታተመው መጸሐፌ በቅርፅም በይዘትም ተመሳሳይ ሲሆን ከሰበዝ የሚቀጥል ታሪክ ግን የለውም"። 'ችቦ' ማለት ቀጫጭን እንጨቶች በአንድ ላይ ታስረው ብርሃን እንዲሰጡ ወይም ደመራ ለመለኮስ የሚዘጋጅ ማለት ነው። አንዳንዶቹ እንጨቶች ለብቻቸው የሚነዱ ቢሆንም አንድ ላይ ታስረው ሲቀጣጠሉ ግን ትልቅ ብርሃን ከመሆን አልፈው ትልቅ ዳመራን ማቀጣጠል ይችላሉ። እውነተኛ ገጠመኞቹን ተንተርሰው የቀረቡት አጫጭር ተረኮች/ታሪኮች እያነበባችሁ... ለመግዛት @noahbookdelivery 📚 @abyssinianwisdom

የደመቁ ገፆች .  .  .   . ሩሲያዊው ደራሲ ፊዮዶር ዶስተቭስኪ በህይወት ው ስጥ  "በምን?" ከማለት ይልቅ "ስለምን" እንደምትከብድ "Brother karamazov " የተሰኘ መፅሃፍ እንዲህ ይላል... "...የሰው ልጅ ነባሬያዊ  ምስጢር መኖር ብቻ አይደለም። የሚኖርለት ነገር ማግኘትንም ያካትታል። የተደላደላ የህይወት ግንዛቤ በሌለበት ሁኔታ የሰው ልጅ ለመኖር ስምምነት አያሳም። በምድር ላይ ከመቆየት ይልቅ እራሱን ማውደም ይመርጣል ።"   [ The scret of of man's being is not only to live, but to have something to live for, without a stable conception of the object of life, man would not consent to go on living and would rather destroy himself than remain on earth...] "በምን እንኖራለን?" አካላዊ ህልውና ላይ ሲመሰረት  "ለምን እንኖራለን" ግን የነፍስ ጥያቄ ነው። አካላዊ የህልውና ጥያቄ መልሱ ምን ቢከብድም እንደነፍ ስ ፈትሮ አይዝም። ተሸንጋይ ነው። ተታላይና ታጋሽ ነው። በቀን ሶስቴ መብላት ባንችል ወደ ሁለት፣ ከዚያ በቀን አንዴ ወደ መመገብ ወርደናል። በቀን አንዴ ከመብላት አሽቆልቁለን "በቀን ግማሼ" እና "በቀን ሩቤ" ውስጥ ብንወድቅም አካል በፍግምግሞሽ እንደምትቀጥል ከኛ የቀረበ ምስክር አይኖርም። ~  ~  ~  ~  ~  ~  ~  ~ አለማየሁ ገላጋይ (መለያየት ሞት ነው) @abyssinianwisdom

እስከ ነጋማ መጠበቅ የለብህም፤ማፍቀር እኮ ወንጀል አይደለም።ዝም ማለት ነው ወንጀል፤ምንም አለማለት ነው ወንጀል፤እያፈቀሩ እንዳላፈቀሩ መሆን ነው ወንጀል።አፍቅሩ በዝምታ መታሰር ግን የልብ ቁስል ነው።ማፍቀር ግን ወንጀል አይደለም። አዎ ስታፈቅር ስዕተት ነው ብለህ ታስባለህ፤ለመናገር ትፈራለህ፤ከራስህ ጋር ትጣላለህ።በጣም ይጨንቅሀል፤ከዛ ምን ማድረግ እንዳለብህ ባለማወቅ ውስጥ ግራ ትጋባለህ። አንድ ነገር ልንገርህ ጓደኛዬ? ፍቅርን ከራስህ ጋር እያቆየክ፤ፍቅርህን በውስጥህ እየደበክ፤ማፍቀርህን ሳትናገር እሷን ሌትም ቀንም እያሰብክ በፍቅር አውሎንፋስ እንድትሰቃይብኝ አልፈልግም።አንተ ካነገርካት እኔ እነግራታለው የሚል የድፍረት ነበልባል ከልብህ አልፎ መላው አካልህ ላይ ተትረፍርፎ እንዲመጣ ያለመድከም ፀልያለው፤ይሄም ካሎነልኝ ሄጄ እነግራታለው።ምክንያቱም ያ በልብህ ውስጥ ያለው ፍቅር ወደ ጥልቅ ቁስል ተቀይሮ ወደእኔ ገዝፎ እንዳይመጣ ሰጋለሁኝና..ይሄን ስልህ ደግሞ selfish እንዳትለኝ!ልልክ የፈለኩት በጣም ታመህብኝ እንዳታሳምመኝ በጣም ቆስለህብኝ እንዳታቆሳስለኝ በእሷ ተስፋ ቆረጠክ፤ራስህን አተክ እንዳንተጣጣ እነግራታለሁኝ፤የመጣብኝ ይምጣ...     ✍️በእምነት አለማየሁ(በእምኒ)              @Abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

✍ከስህተት መማር    እዚህ ምድር ላይ ሥህተት ያልሰራ የሰው ፍጡር የለም ለምን ቢባል ሰው በአፈጣጠሩ ዕለት ዕለት አዲስ ነገር ፍለጋ የሚማስን ፍጥረት በመሆኑ ነው። የሰው መሳሳቱ ትክክለኛው መንገድ ላይ አለመሆኑን የሚያሳይ እንጂ አለመቻሉን አይደለም ስለዚህ ለምን በስህተታችን ቁጭት ዕድሜያችንን እናባክናለን ይልቁንስ ትክክለኛውን መንገድ በመፈለግ ላይ መትጋቱ ትክክለኛና አስፈላጊ ውሳኔ ነው።   ሞክረን ነገሮች አልሳካ ሲሉን ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን የሚገባን አካሄዳችንን ማስተዋል ነው ወሳኙ ቁም ነገር እናም በውድቀትህ ማፈርም ሆነ መሸማቀቅ የለብህም ምክንያቱም ያልሞከረ አይሳሳትምና  ይልሃል ዕውቁ ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን። @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

6ትናንሽ ታሪኮች ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣   1  በአንድ ወቅት በአንድር መንደር የሚኖሩ ሰዎች ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት ፀሎት ሊያደርጉ ወሰኑ፡፡ፀሎቱ በሚያደርጉበት ቀን ሁሉም የመንደሩ ሰዎች ተሰባሰቡ፣አንድ ትንሽ ልጅ ብቻ ዣንጥላ ይዙ ተገኘ፡፡ (ይህ እምነት ይባላል፡፡) ፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 2  ህጻን ልጅህን ወደላይ እየወረወርህ ስታጫውታት በደስታ ትፍነከነካች እንጂ አታለቅስም ፡፡ምክንያቱም መልሰህ እንደምትቀልባት ታውቃለችና!! ይህም እርግጠኝንት ይባላል፡፡ ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 3  በእያንዳንዱ ምሽት ወደ አልጋችን ስንሄድ በነገው ማለዳ በህይወት እንደምንቆይ ምንም ዓይነት ማረጋገጫ ባይኖረንም አላርም(የማንቂያ ደወል) ሞልተን እንተኛለን!! ይህም ተስፋ ይባላል፡፡ ፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 4 ወደ ፊት ምን እንደምንሆን (እንደሚሆን)እውቀት ሳይኖረን ታላላቅ እቅዶችን እንነድፋለን!!! ይህ ደሞ በራስ *,መተማማን ይባላል፡፡** ፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣ 5 ዓለም ላይ የሚወርደውን መከራና ስቃይ እናያለን ይሁን እንጂ አሁንም እንጋባለን ይህም ፍቅር ይባላል፡፡ ፣፣፣፣፣፣ 6 አንድ ሽማግሌ በለመበሰው ቲሸርት ላይ እንዲህ የምትል አንዲት ጉሩም ዐረፍተ ነገር ተጽፋለች “እኔ የስድሳ ኣመት ሽማግሌ አይደለሁም ፣የአርባ አራት ኣመታት የሕይወት ልምድ ያለኝ የአስራ ስድሰት ኣመት ወጣት እንጂ” ይህ ለራሳቸእን ያለንን አመለካከት ያሳያል፡፡ ፣፣፣፣ መልካም ምሽት ይሁንላችሁ!! እምንት ፣እርግጠኝነት ፣ተስፋ ፣በራስ መተማማን ፣ ፍቅርና ለራሳችሁ ጥሩ አመለካካት ሳይለያችሁ ኑሩ !!! @abyssinianwisdom

ችግርህን ለማንም አትንገር ምክንያቱም ከነገርካቸው ውስጥ 20% ስላንተ አይጨንቃቸውም 80% ደግሞ አንተ ችግር ውስጥ መሆንህ ያስደስታቸዋል። @abyssinianwisdom

የዓለማየሁ ዋሴ " ችቦ " የተሰኘው አዲስ መጽሐፉ ለንባብ በቃ :: ዓለማየሁ ዋሴ እመጓ ዝጎራ መርበብት ሰበዝ ሚተራሊዮን በተሰኙት መጻሕፍቱ ይታወቃል :: 📚 @abyssinianwisdom
የዓለማየሁ ዋሴ " ችቦ " የተሰኘው አዲስ መጽሐፉ ለንባብ በቃ :: ዓለማየሁ ዋሴ እመጓ ዝጎራ መርበብት ሰበዝ ሚተራሊዮን በተሰኙት መጻሕፍቱ ይታወቃል :: 📚 @abyssinianwisdom

👉 የተማሪው ጉዞ ከ"ሀ" እስከ "ሆ" 👈 ሀ- ሀ ብሎ ጀምሮ~የትምህርትን ህይወት~                ከዜሮ ተነስቶ ሁ- ሁሉን በሚገባ~በአእምሮው ይዞ~                 ከልቡ ተረድቶ ሂ- ሂሳብ ኬሚስትሪን~ጠንቅቆ በመማር~                መስፈርቱን አሟልቶ ሃ- ሃሳቡን ሊያሳካ~ራሱንም ሊቀይር~                 በደንብ ተሰናድቶ ሄ- ሄዶ እንደገባ~በትልቁ ተቋም~                ሁሉን ነገር ትቶ ህ-ህዝብን የማገልገል~ ሀገርን የመጥቀም~                አላማውን ረስቶ ሆ- ሆ ብሎ ያምፃል~በረባ ባረባው~                አላዋቂ ሰምቶ። ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ By begitimenawga ✍️ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

" ከእብዶች መሀል የተገኘ ጤነኛ ከእብዶቹ በላይ ይታዘንለታል ። " ስህተታችን የሚጀምረው ጓደኛዬ አይደል እህቴ አይደለች ባሌ እኮ ነው በደንብ አውቀዋለው በደንብ አውቃታለው ብለን የማወቅን ልኬት መጎናፀፋችን ነው ። የሰው ልጅ አንብበን ጨረስን ስንለው ያላነበብነው እልፍ አእላፍ ምዕራፍ ምናገኝበት ሁሌ አዲስ የሆነ ፍጥረት ነው።  ይሄን ደግሞ የተገፉ የተረሱ እና አታስፈልጉም ተብለው ጥግ የተጣሉትን ሰዎችን ጠይቅ።  ስለተሳሳትክ ብቻ አትገፋም ። ልክነትን ተላብሰህ በስህተተኞች መነፅር ጥራትህን በእድፋቸው አንፀባርቀውት ገለል በል ልትባል ትችላለህ። እብደት እኮ ትርጓሜው እንደያለህብት ቦታ ነው ። ከእብዶች መንደር ጤነኛ ሆነህ ብትገኝ ከእብዶቹ በላይ ይታዘንልሀል ፣ አረ እንደውም " ወይ ሲያሳዝን " ብለው ከንፈራቸውን ይመጠብሀል ። @abyssinianwisdom

" ከእብዶች መሀል የተገኘ ጤነኛ ከእብዶቹ በላይ ይታዘንለታል ። " (ካሊድ አቅሉ ) ስህተታችን የሚጀምረው ጓደኛዬ አይደል እህቴ አይደለች ባሌ እኮ ነው በደንብ አውቀዋለው በደንብ አውቃታለው ብለን የማወቅን ልኬት መጎናፀፋችን ነው ። የሰው ልጅ አንብበን ጨረስን ስንለው ያላነበብነው እልፍ አእላፍ ምዕራፍ ምናገኝበት ሁሌ አዲስ የሆነ ፍጥረት ነው።  ይሄን ደግሞ የተገፉ የተረሱ እና አታስፈልጉም ተብለው ጥግ የተጣሉትን ሰዎችን ጠይቅ።  ስለተሳሳትክ ብቻ አትገፋም ። ልክነትን ተላብሰህ በስህተተኞች መነፅር ጥራትህን በእድፋቸው አንፀባርቀውት ገለል በል ልትባል ትችላለህ። እብደት እኮ ትርጓሜው እንደያለህብት ቦታ ነው ። ከእብዶች መንደር ጤነኛ ሆነህ ብትገኝ ከእብዶቹ በላይ ይታዘንልሀል ፣ አረ እንደውም " ወይ ሲያሳዝን " ብለው ከንፈራቸውን ይመጠብሀል ። @abyssinianwisdom

🟡ከፍ ያለ ቦታ ላይ ስትሆን ኩራት (PRIDE) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ኩራት አንተ የደረስክበት የስኬት ደረጃ ላይ ያልደረሱ ሰዎችን በንቀት እንድትመለከት ያደርግሃል፡፡ 🔴 ታችኛው ክፍል ላይ ስትሆን ፣ ምሬት (BITTERNESS) የሚባለውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ምሬት ቅናት እንዲሰማህ እና አንተ ያልተሳካልህ በሌሎች ሰዎች ምክንያት እንደሆነ እንድታስብ ያደርግሃል፡፡ 🟡 ወደ ላይኛው መንገድ ስትጓዝ ስግብግብነት (GREED) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ፡፡ ስግብግብነት ትዕግሥት ያሳጣሃል እናም እንድትሰርቅ ወይም አቋራጮችን እንድትፈልግ ያደርግሃል። 🔵ወደ ታች በምትወርድበት ጊዜ ፣ ተስፋ መቁረጥ (DESPAIR) ተብሎ የሚጠራውን ጭራቅ ተጠንቀቅ ፡፡ ተስፋ መቁረጥ፣ ሁሉም ነገር ተጠናቋል ብለህ እንድታስብ ሊያደርግህ ይችላል።                      ✍ኔልሰን ማንዴላ 👇join our channel👇        🫧@abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት
አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ አየህ አንፖል ተቃጠለ ተብሎ ቤት አይቀየርም፡፡ አንፖል ተቃጥሏል ብሎ ቤት የሚቀይር ሞኝ ነው፡፡ አንተም አንዱ የህይወቴ ጉዳይ አልተሳካም ብለህ ራስህን አታጥፋ፡፡ ይልቅስ አምፖልህን ቀይር ችግርህን ተጋፈጠው፡፡ ጭንቀትህን አስጨንቀው፡፡ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል "ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ " አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ታሪክህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ብቻ ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው✍         የምን ተስፋ መቁረጥ.......✍ ✍ጋሽ ስብሀት ገ/እግዝያብሄር 📚@abyssinianwisdom

#የማንዴላ_ምርጥ_አባባሎች 🔴  “መቼም አልሸነፍም። ወይ አሸንፋለሁ ወይም እማራለሁ።” 🔴 "ድፍረት ማለት የፍርሀት አለመኖር ሳይሆን በፍርሀት ላይ ድል መቀዳጀት እንደሆነ ተረድቻለሁ፡ ጎበዝ ሰው ማለት ፍርሃት የማይሰማው ሳይሆን ያንን ፍርሃት የሚያሸንፍ ነው።" 🔴” አሸናፊ...ተስፋ የማይቆርጥ ህልምኛ ነው።” 🔴 "በሕይወት ውስጥ የሚቆጠርልን እኛ መኖራችን ብቻ ሳይሆን፣ በሌሎች ህይወት ላይ ያደረግነው ለውጥ ነው” 🔴"ትምህርት ዓለምን ለመለወጥ ሊጠቀሙበት የሚችሉት በጣም ኃይለኛ መሣሪያ ነው።”    🔴”አንድ ትልቅ ኮረብታ ከወጣ በኋላ አንድ ስዉ ሊያውቅ የሚችለው ብዙ ተጨማሪ ኮረብታዎች መኖራቸውን ብቻ ነው።"            🔴 "በስኬቴ አትዳኙኝ፣ ወድቄ  በተነሳሁት ልክ ዳኙኝ ።" 🔴 "ሁሉም ሰው ራሱን ከሰጠና ለሚያደርገው ነገር ከፍተኛ ፍቅር ካለው፣ ከሁኔታዋች በላይ በመነሳት ስኬትን ሊቀዳጅ ይችላል።" 🔴"እስኪደረግ ድረስ ሁልጊዜ የማይቻል ይመስላል።"                🔴 "የተሻለችን ዓለም ለሚኖሩባት ሁሉ መፍጠር በእጅህ ላይ ነው ያለው።"                                            @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

መነሻውን በቅጡ ያላየ ተጓዥ .  .  .  .  አስራ አንድ ሰዓት ገደማ ነው ። ፀሐይዋ እያሸለበች ምሽቱ ለመምጣት ሽር ጉድ እያለ ነው ። ጎርጊስን ተሻግሬ ቆሜ አማትሪ የስድስት ኪሎን መንገድ እቃኛለው ።  ስልኬን አ ውጥቼ " የት ደረሽ?"  ለማለት ስሰናዳ ዜብራውን ስትሻገር ከርቀት አየዋት ጎሮሮዬን እየጠረኩ ሞቅ ያለ አቀባበል ላደርግ ተሰናዳው ። ውብ ቃል ለማውጣት የተሰናዳው አፌ መቅረብዋን ሲያይ የመጣለትን አሻገረ " እንኳን ደህና መጡ የተከበሩ " በፈገግታ እጆቼን ዘርግቼ አንገትዋ ስር ገባው ባትወጡ የሚል የቤተ መቅደስ እጣን ለዛ ያለው ውብ ከርቤ አወደኝ ። ጠረኑን አፍንጫዬ ላይ አስቀርቼ በቀስታ ተመለስኩ ። የቸርችልን መንገድ ቁልቁል ተያይዘነዋል ዝግ ባለ እርምጃ ከወክ ትንሽ ባነሰ ሀይል ። መሬት መሬቱን እያየች ቃል ሳታወጣ እግሯን ወደፊት ታዛለች ። ለአንድ አመት ሙሉ በተግባር ስገልፅላት የነበረውን ፍቅሬን ዛሬ በቃል ላፈነዳው ቀጠሮ ይዥ ነው ከቤት የወጣሁት ። ተግባር ያላበሰረው ፍቅር ንግግር ይገልጠዋል ? አላውቀውም ብቻ  ዛሬ ፍቅሬን ነፍስ አውጥቶ ለማሳየት አፍ መንደር ልከርም ነው ።  " በጣም ውድ የሆነን ነገር በተግባር ግለፀው " ይላል ስሙን የዘነጋሁት ደራሲ ግን ውድ ብዬ በተግባር ብገልፀው ከገለባ የቀለለባት መሰለኝ ለዛም ብቸኛ ነፃ አውጪ ንግግርን አድርጊ ውሰድኩት ። ከቸርችል ጫፍ የጀመረው ፍቅርን አስውቦ ካመጣጡ የማስረዳት ሂደት ብሔራዊ ቲያትር ጋር ሲደርስ ዘረገፍኩት ። " አፈቅርሻለው " ጮክ ብላ ያልኳትን ደግመች እጆችዋን አጣምራ ወደኔ ዞራ ።   " አፈቅርሻለው ለማለት ነው ሁለት መፅሀፍ ሚወጣው ንግግር ያሰማህኝ ? " ንግግርዋ ውስጥ ማፍቀርን የማቅለልን ሰልችተኝነት ይታይባታል ። ገና በጠዋቱ ለምን አልነገርከኝም ነው ቁጭትዋ ፤ በሃሳቤ ፈረስ ሳሽከረክራት ቆይቼ ወደ ማምሻው ላይ ማፍቀሪን ዘረገፍኩላት ። እሷ ይሄንንማ ማለዳ ላይ በነገርከኝ ብላ ከፍትዋታል ።  ወራጆቹን እያሳዩ ሄደው ማብቂያው ላይ ምንጩን ማሳየት ነገሩን ከስሩ ለመረዳት መንገድ አይከፍትም ? መነሻውን በቅጡ ያላየ መንገደኛ እንዴትስ ስለመድረሻው ብስራት ማቀንቀን ይችላል ?                        *    *    *                   @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

📘የመሻገር ሲቃ ✍ያዕቆብ ብርሃኑ "ፍቅሬ አበባዬ ሙሽራዬ ሆይ... ከዘለዓለም ጫፍ ጠራሁሽ። ከሞት መንጋጋ አስጣልኩሽ። የሕይወትንም ውኃ አጠጣሁሽ። ከሞት ጽኑ ቀንበር ነጻ አወጣሽኝ። በትንፋሽ አክናፍ እልመዓለምን አስቃኘሽኝ። በሕይወት መዝገብም አስጻፍሽኝ።ፍቅር እንደ ማህሌት ነው።እንደ ሱባዔ...እንደ ጦም ጠሎት።ፍቅሬ አበባዬ የገነት ወፌ ሆይ...ነይ ፍቅርን እናፍቅረው።በዋሊያና በውርንጫ ዓይነት መዋደድ እንዋደድ...ፍቅሬ አበባዬ ሙሽራዬ ሆይ...አንቺ በመቅበዝበዜ መሀል የተጣልሽ ምጥን የፈገግታ ቅኔ ነሽ... 📚 @abyssinianwisdom

ሁሉም ወዳጅ እኮ ደስታህን አይፈልግም! ደስታህን እንዲሁም የደስታህን ምንጭ እንድትቀንስ ካደረገኽ ወዳጅነቱን መመርመር አስፈላጊ ነው!ሰው ካለደስታው ሕይወቱ ብርሐን የለሽ ናትና!!!           @abyssinianwisdom

መልካም የእናቶች ቀን ።
መልካም የእናቶች ቀን ።

📘ዛምራ ✍ይስማዕከ ወርቁ ብራሶል አስቀድሞ በእርዳታ ድርጅቶች እጅ ኢትዮጵያን ሲሰልል ነበር። ስለላ ማለት ለግል ጥቅሙ እንጂ ፣ ለሀገሩ ሩሲያ ጥቅም አይደለም። ብራሶል የሚያቀርበው የጠብመንጃ ሽያጭ ሲሆን ፣ እስካሁን በዞረበት ሀገር ሁሉ ለግሉ የሚሰልለው ማዕድናትን ነው።የብራሶል አመለካከት እንዲህ ነው። ዓለም ውስጥ ያሉ መንግሥታት በሙሉ ማፍያዎች ናቸው። በህዝብ የተመረጡ ወይም በህዝብ ሳይመረጡ የወጡ ህጋዊ ማፍያዎች። እኛ ከነዚህ የምንለየው ህጋዊ አለመሆናችን ብቻ ነው። ፖለቲካ በሚሉት የውሸት አብዮት ፣ ህዝቡን ስለማናታልል ነው።" ይላል ሁልጊዜም።  📚 @abyssinianwisdom

* “መፀሀፍን የሚያነብ ሰው በህይወት ውጣ ውረዱ አያማርርም። ሠዎች ለምን ጎዱኝ፣ ለምንስ አያስቡልኝም ብሎም ሌሎችን አይወቅስም። ከሌሎች ጋርም አይቀያየምም ምክንያቱም መፀሀፍ የሚያነብ ሰው ለራሱ ስ
* “መፀሀፍን የሚያነብ ሰው በህይወት ውጣ ውረዱ አያማርርም። ሠዎች ለምን ጎዱኝ፣ ለምንስ አያስቡልኝም ብሎም ሌሎችን አይወቅስም። ከሌሎች ጋርም አይቀያየምም ምክንያቱም መፀሀፍ የሚያነብ ሰው ለራሱ ስኬትና ደስተኛነት ራሱ ብቁ ነውና ከሌሎች ምንም ስለማይጠብቅ።”(ባሮው) * “ዛሬ ላይ ያለህ ማንነት የዛሬ አምስት አመት ከሚኖርህ ማንነት ጋር ፍፁም ለውጥ ሳይኖረው ተመሳሳይ ነው። ግን በነዚህ አመታቶች ውስጥ መፀሀፎችን ካነበብክ አዎ! ከአሁኑ ይልቅ የዛሬ አምስት አመት የተሻለ ማንነት ይኖርሃል።”               (ቻርሊጃንሥ) @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

በቃ ልመዱት !!! •  ሰዎች “አደርገዋለሁ” ብለው የገቡላችሁን ቃል ኪዳን ላይፈጽሙ ይችላሉ - ልመዱት! •  ዛሬ የሚወዷችሁና የሚያከብሯችሁ ሰዎች ነገ ሊጠሏችሁና ሊንቋችሁ ይችላሉ - ልመዱት! •  ዛሬ ምስኪን መስለው ለሕልውናቸው በእናንተ እርዳታ ላይ የተደገፉ ሰዎች ነገ ውለታ-ቢስ ሆነው ልታገኟቸው ትችላላችሁ - ልመዱት! •  ሰዎች የሆናችሁትን ማንነት ሳይሆን ያላችሁን ቁሳቁስ አይተው እንደቀረቧችሁ ልትደርሱበት ትችላላችሀ - ልመዱት! •  አንዳንድ ሰዎች በሰላሙ ጊዜ የሰሙትን ምስጢራችሁን ግንኙነታችሁ ሻከር ሲል ለወሬና እናንተንው ለማጥቃት ሊጠቀሙበት ይችላሉ - ልመዱት! እነዚህንና እነዚህን መሰል በማንኛውም ሕብረተሰብ መካከል የሚንጸባረቁ የሰዎች ባህሪያትን መልመድ ማለት፣ ሁል ጊዜ ከሰዎች የምንጠብቀውን ነገር እንደማናገኝ መገንዘብና ራስን ማዘጋጀት ማለት ነው፡፡ ከሰዎች የምንጠብቀውን መልካም ነገር ስናገኝ ደስ የመሰኘታችንንና ሰዎቹንም የማመስገናችን ልምምድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለማንኛውም አይነት ወጣ ያለ የሰዎች ሁኔታ ራስን ማዘጋጀትና ከሁኔታው ባሻገር አልፎ ለመሄድ የውስጥ ውሳኔን መወሰን እጅግ ጠቃሚ ልምምድ ነው፡፡  እንደሰው የመለዋወጥ ሁኔታ የሚለዋወጥ ሰባራ ማንነት እንደሌላችሁ ለራሳችሁ የምታስመሰክሩበት ቀን ይሁንላችሁ! ዶ/ር እዮብ ማሞ @abyssinianwisdom