fa
Feedback
LEARN TECH ||ethiopia ®

LEARN TECH ||ethiopia ®

رفتن به کانال در Telegram

We are dedicated to provide tech tips and other tech related information. #join and #share

نمایش بیشتر
1 495
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-107 روز
-5530 روز
آرشیو پست ها
❤️ሁለት ልብ❤️ ❤️+❤️=❤️❤️ ክፍል 7 ""የውልክ አሁን ምንም ማውራት አልፈልግን plzz አንዴ ብቻ ክርስቲ ወደ ዶርም ጥላኝ ሄዳለች .... " እናት plzz ..ምን አልክ እናት የት የምታቃትን.... ያንተ ሄዋን እናት ብለክ የምጠራትማ ሞታለች ከየት እንደመጣ ባላውቅም እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ . "" "".እሺ ግን ሁሉንም ላስረዳሽ ግዚ ስጭኝ .....አታልቅሺ ከባድ እራስ ምታት እንዳለብሽ አውቃለው ..... እረ ታውቃለክ እንግዳውን አንተ ነክ ህመሜ ስለምንም ማውራት አልፈልግም ያለፈ እና የሞተ ነገር ነው እያልኩ የእጆቼ መራውጭት እና ሳሚ ከቆሙበት ይመለከቱ ነበር ውደላይ ድምፅ ተሰማኝ ቀና ስል ክርስቲ በመስኮት...እእእ ስትል ሰማዋት..... እሺ ሌላው ቢቀር ጓደኞችሽ ፊት እንኳን ጥሩ ፊት አሳይኝ እሺ ግን ባንድ ነገር እንስማማ.... Ok... """ከእኔ ጥሩ ፊት እንድታይ ስለእኔ እና ስላንተ ለማም ትንፍሽ እንዳትል ያስማማሀል ........ . ...."እእእ ግን እንዴት ።.. እሺ ተስማምቻለው። እኔ ዶርሜ ገብቼ ስሜቴን መቆጣጠር አቃተኝ ያሁላ ውንዬ ባንዴ ጠፋ በቃ ሄዋን ዝም በይ .....እንዴት አድርጌ አንዴ ባገኛው እና ለምን እንደተወኝ ለመጠየቅ እፈልግ ነበር አሁን ግን ....አንደበት አጣው ....... ""በማግስቱ ከክላስ እንደውጣን የምንቀመጥበት ቦታ አመራን... ብዙም ሳይቆይ የሳሚ ስልክ ጠራ እእእ አቤል ሲል እኔ ደነገጥኩ እኔ ብቻ ሳይሆን ክርስቲንም .....መጣው እያለ ተነስቶ ሄደ .....አሮን ማታ ስልክ ተለዋውጠው ነበር አለ እኔ ፍርሀት ያዘኝ ...ሳሚዬ ቢሰማ የሚሆነውን ....omg ፈጣሪ አውጣኝ ..... ይዞት መጣ በተባባልነው መሰረት ሁሉንም በሆዴ አድርጌ መሳቅ ጀመርኩ. " አሮን ስለ ፍቅር ታሪክ ማውራት ጀመረ ...ናቲ ሲጠየቅ እውነት ለመናገር ክፍስቲ የመጀመርያዬ ነች ....ተራው ሳሚ ጋር ደረሰ እኔም ለመስማት እግሩን ዘርግቶ ተኝቼ ነበር ብድግ ስል አቤት ለውሬ በክሽ ተኝ......የፍቅር ሒውት ኖሮኝ አያውቅም አለ ..... አይን አይኔን እያየ .....ተራው ክርስቲ ጋር ...ከት ብላ ሳቀች..... እንዴ አላት ናቲ አይ ሳስበው ስለሚያስቀኝ ነው .. :""በይ ተናገሪ አብረን እንሳቅ እኔ ፍቅር ሳይሆን የዓይን ፍቅር ነበር እውነት ካላየሁት ማደር አልችልም ክፍል የሚገባው ሰኞ .ህሮብ ..ሀርብ ነው ግን ሌላ ክፍል ሄጄም ቢሆን አየው ነበር አቤት የሱ ክፍለጊዜ ሰዓቶ ታጥርብኝ ነበር።....እነዛ ቀናቶች ውብ ሆኜ ነው ትምህርት ቤት የምመጣው ....አንድም ቀን ዞር ብሎ አይቶኝ አያውቅም እድሜው ገነ ልጅ ነው.. ......ናቲ አስቸኩሎት ማነው....ምንድነው..... .. ....ክርስቲ ዝምታ ሰፈነ ካስተማሪዬ ነበር....ሁላችንንም አሳቀን ግን ፍቅር ነው እኔ ጋር ደረሰ ይቅርታ እለፉኝ ...ሳሚ አይቻልም አለ ......ክርስቲ አዎ ይለፋት....ወደ አቤል ተዘዋወረ "በረጅሙ ተነፈሰ በጣም ከራሴ በላይ የምውዳት የማፈቅራት አለች ግን በራሴ ጥፋት አጣዋት ታቃላቹ የመጀመሪያዬ ነች መርሳት አቃተኝ ናቲ እዚ ጋር አቤል ድንግልናህም የሰጠካት አለው በአባባሉ ሳኩኝ ሁሉም ሳቁበት አዎ ወይ ጥያቄ እና መልስ ... ድንግልናዬን የሰጠዋትም የሰጠችኝም ከራሷ በላይ ነው። """:የምትውደኝ እኔ ግን በራሴ ችግር ከፊቼ ወደ አዲስ ገባው ሳልነግራት ...በጋጣሚ ሳገኛት....እያለ እንባው ከአይኑ እኔ ላለቅስ ትንሽ ነው የቀረኝ ....ክርስቲ እንዴ በቃ ከዚ ውጡ ሳሚ ለምን አናስታርቅክህም በተለይ ሄዋን ለዚ ነገር አንደኛ ነች .......ናቲ ሰሞኑን ፈተነ እንዳለ ታቃላቹ..... ....... " አዎ ከንግዲ ማንም ስለፍቅር ...ሌላም ነገር ማንሳት የለብንም የመጣንበት እናሳከ የሚስማማ ብላ እጃን ዘረጋች ማንም ሳይቀድመኝ እኔ ተስማምቻለው ብዬ ዘረጋው .....ሁላችንም ተስማማን ለኔ ትልቅ እረፍት ነው ።.. .ሳሚ ስልኩን ነካካ ውድያው ለኔ ሚሴጅ ገባልኝ..... መልስ.....ጨነቀኝ . እኔም መልሼ 😷😷 ከፈተና በኃላ ተባለ እኮ❤️ መላስኩለት ከላኩ በኃላ ግን ለምን ልብ ቅርፅ ላኩለት ውድያው ፊቱ በደስታ ተሞላ ...ዶርም አመራን... ክርስቲ ይቅርታ አንድ ነገር ልጠይቅሽ ...:እሺ ምን ነበር......"" እንዴት ከቤት ውተሽ ልታድሪ ቻልሽ ....አየሽ እኔ ስለምውደው የዳንስ ክበብ በገባሁበት ውቅት ለጉብኝት ደብረዘይት ባብጋያ ጉዞ ነበረን በርግጥ ደርሶ መልስ ነው ግን ከአቤል ጋር መደር ስለምፈልግ እናቴን እንደምን ብዬ አስፈቅጄ አደርኩ አቤልም ባብጋያ ሆቴል ይዞ ይጠብቀብ ነበር እኔ ከክበብ አብሬ ካሳለፍን ከዛ አመሻሽ ላይ ተመለሱ እኔ ውደ አቤል ጋር ያቺ ለሊት እኔ አቤልም አይተን የማነውቀው አለም ውስጥ ገባን .... .....እኔ ምልሽ ሄዋንዬ አንቺ ና ሳሚ ፍቅረኞት ነው የምመስሉኝ ነበር እውነት የምትሆኑን .....ብቻ ታስታውሻለሽ እኔ ከናቲ አንቺ ከሳሚ ጋር ....omg አንቺ ዝበይ .....hhhhh ምነው እውነቴ ነው አታያቸውም እንዴ የግቢ ተማሪዎችን ስንቱ ነው በሳሚ ቁንጅና በፍቅር ጠብ ያሉት ........""ሆይ ገና ጉድ ታወሪለሽ ..።...."በማግስቱ ቀኑን አብረን ውሀ ስንራጭ ውለን አመሻሽ ላይ ተመልሰን ወደ ፊቼ .. ..... """ ይገርማል ..በጣም ስለፍቅር ሒውቴ ከምፅፈው ዲያሪ በስተቀር ለማንም ተንፍሼ አላውቅም ለእናቴም.........ufff ሰሞኑን ፈተና ስለሆንን ውሏችን ላይብረሪ ነው። አቤልም ምንም ነገር አንስቶ አያውቅም ።....ያው ከፈተና በኃላ ሳሚዬም መልሴን አቤልም በግልፅ እንደምነውራ ተስፋ አድርገዋል ።.. ...."የሳሚን የፍቅር ጥያቄ ለማንም አልተነፈስኩም ከኔ ካንቺ እንዳይውጣ ስላለ ... ሀርብ ፈተና ጨርሰን የተለመደው ቦታ ቁጭ ብለን ለምን እሁድ ውጣ አንልም አለ አቤል wow ምርጥ ሀሳብ ናቲ ተከተለ ሁላችንም ተስማማን የት ደብረዘይት አዳር....አለ አቤል ደነገጥኩ ክርስቲ ቶሎ ፊቴን ስታይ ሌላ ቦታ ሌላ ከማውራቱ በፊት እኔ እዛ አይመቸኝም አልውደውም እያልኩ መነጫነጭ እንዴ ለምን በቃ እዚሁ ሀዋሳ ሀይቅ....ሳሚ...ለምን.... ክፊል 8 ይቀጥላል........ እስኪ ደስ እንድለኝ አብሮነታችሁን በ Share አሳዩኝ https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

❤️ሁለት ልብ ❤️❤️ ❤️+❤️=❤️ ክፍል 6 ፍቅረኛ እንዳለው ዳግም ፊቼ እንደማይመለስ....ብቻ ክርስቲዬ ማንነቴን ነው አሳልፌ የሰጠሁት ከሱ ሌላ ውንድ አላውቅም ።..።.ግን እንደቀልድ የተጀመረ ፍቅር ነው ሁለታችን ሳናውቅ የፍቅር ውጥመድ ውስጥ የገባነው...... ።......"እስቲ ላንብበው ደብዳቤዎቹ ተመችተውኛል...... አቤልዬ ለጤናህ እንዴት ሰንብተሀል? እኔማ አምላኬ በሰጠኝ እስትንፋስ ቢመርም ቢጣፍጥም፣ቢከፋም ቢለማም፣ ከኑሮ ጋራ እየታገልኩ ይመስገነዉ አለሁ፡፡ ይሄንን ቀፋፊ የዝባዝንኬ አለም ለአፍታም ቢሆን የሚያስረሳኝ ከአንተ ጋር ያሳለፍኳቸዉ እነዛ ወርቀ ትዝታዎቼ ናቸዉ፤ትዝታ ባይኖር የሰዉ ልጅ ህይወት ልክ እንደደፈረሰ ደራሽ ዉሃ እዚህም እዚያም እያለ የያዘዉን ይዞ ይነጉድ ነበር፡፡ እስኪ ለዛሬ ትዝታዎቼን ላስታዉስህ…ትዝ ይልሀል በጨጎጊት ሌሊት አንድ ላይ ተቃቅፈን ያወራነዉ ፣የተጨዋወትነዉ…የተሳሳቅነዉ…. አንተ ---ማሬ እኔ---ወዬ አንተ---እኔና አንቺ ከ 40 አመት በኋላ ምን የምንሆን ይመስልሻል? እኔ---ዛሬ ደግሞ ምን አይነት ጥያቄ ነዉ የምትጠይቀኝ? አንተ---መልሽልኝ.. እኔ--- ሰማይ ቤት የምንሆን ይመስለኛል አንተ --. አይ… እዚሁ ምድር ላይ ነን ብለሽ አስቢና የትና ምን ዕያረግን እንደሆነ መገመተ አትችይም? እኔ---ኦኬ! እርጅት እርጅትጅት ብለን…ይህን የያዝኩትን ዋለላ እጆችህን እቅፍቅፍ አድርጌ እሹሩሩ ስልትለኝ…ጥርሶችህ በሙሉ እርጅና ተጭኗቸዉ ስለሚወለልቁ ወላቃ እያልኩ ሳበሽቅህ…ደግሞ ሙቅና ሾርባዉን ሳጠጣህ… አንተ ---ሂጂ!መቼ ነዉ ገን አንቺ ና ሙቅ ስምምነታቸሁን የመታፈርሱት… እኔ ግን ምን እንደሚሰማኝ ታዉቃለሽ? እኔ-- አስኪ ንገረኝ… አንተ--- እም… ልክ እንዳሁኑ ያኔም እንዲሁ የምንሆን ይመስለኛል…ግን የዛኔ መዋደዳቸን በዘመናት ብዛት ጎልምሶ፣ተዉቦ፣የዛሬዉ ፍቅራችን የምር መሆኑ ለጠላቶቻን መርዶ፣ለወዳጆቻችን የምስራች አይነት የሚሆንበት የትልቅነትና ልዩ የሆነ የእርጅና ወራት… ውዴ ያ ሁሉ ቀረና እርጅናውን ሞቱም ዘገዮና እኛው ተለያየን ታውቃለህ እኔ እንዳንተ ማስመሰል አልቻም አስተምረኝ ውዴ ይጠቅማል እንዴ? ማስመሰል እንዴት? አቤልዬ ..ያኔ ...ትዝ ይልሀል ውዴ ተረጋግቼ ሳወራህ አንተም አይን አይኔን እያየህ ያወራንባቸው ጊዚያት ትዝ ይልሀል ውዴ ላልከዳህ ላትከዳኝ የተማማልንባቸው እነዚያ ቀናት ሁልጊዜ እንደምትወደኝና እንደምወድህ ብነግርህም ...ብትነግረኝም የዛች ቀን ልውውጣችን ግን እስከመቼም አልረሳትም ትዝ ይልሀል ውዴ ዘወትር ከንፈርህ ከከንፈሬ ሳይገናኝ ተለያይተን አናውቅም ነበር ነገር ግን የዛች ቀን የሳምከኝ እስከመቼም አልረሳትም እውነቴን ነው የምልህ አብረን ሳለን የፍቅር ልውውጣችን ሚዛን ሳይደፋ ቀርቶ ሳይሆን የመጨረሻዋን እለት ግን ሊተካልኝ አልቻለም ለኔ ልዩ ቀን ነበረች በልቤ ፅፊያታለሁ አንተን ንጉሴን ማውጣት አልቻልኩም እስከመጨረሻው አፈቅርሀለሁ አውቃለሁ ውዴ ቃልህን አጥፈሀል ፣ ቃልህን በልተሀል ፣ በሌላም ተክትህኛል እኔ ግን አይደለም መተካት በሙሉ አይኔ ያየሁት ወንድ እንኳን የለም ግን ለምን ውዴ? ለማን ትተህኝ? ካንተ ውጪ ሰው እንደማለምድ እያወክ ግን ለምን ውዴ? እባክህ አንተን ያስቻለህን ታውቃለህ ለኔም ላክልኝ እኔኮ አንተን መርሳት ማለት ጣቴን እንደመቁረጥ ከባድ ነው ይህንንም ጠንቅቀህ ታውቃለህ ብቻ ...ውዴ ባለህበት ሰላም ሁን! ግን አንድ ነገር ቃል ግባልኝ አይንህን እንዳይ ፍቀልኝ አንዴ ብቻ ?? አቤልዬ አንተ እኮ ግን ሌባ ነህ ግን ይሁን አይንክ ማየት እፈልጋለው ታማኝነቴን እንድያይልኝ. ፍቅር እንድፈራ እንዳልይዝ አደረከኝ😘 እንዴ ሄዋንዬ .ይሄ ሲደርሰው ምን .....ምን አላሽ......በመሀል ስልኬ ጠራ ሳሚ ነው።...አንቺ አናግሪው......ክርስቲ አንስታ ሀይ ሰላም ናት አታስቡ ።......እእእ የት እያለች በመስኮቱ ውደታች ታያለች እሺ መጣን ...ስልኩን ዘግታ እኔ ምንሆነሻል እኔ አልሄድም .... ...."""ሄዋንዬ ምንም አታስቢ መላ አለኝ ይቀየማሉ ...እያለች ከተቀመጥኩበት እጄን ጎትታ አስነሳችኝ .።..እንባዬን ጠርጋ አቀፈችኝ ክርስቲ ጥሩ ልጅ ናት ።...አንድ ሀሳብ ቀለለልኝ። ነገሮች ለክርስቲ ቀላል ይሆኑላታል.... ......ከነሳሚ ጋር አቤልም ነበር ፈጠን ብላ አቤል ኤለመንተሪ ስትማሩ ስትል ደነገጥኩ....እስፖርት ሜዳ ገፍትረካት ከዛ ተጣላቹ...በሉ አሁን ይቅር በላት አቤል የኔን ማልቀስ ስላየ አዎ ሄዋንዬ እስከ ዛሬ ቂም ይዘሽብኛለሽ እያለ ተጠግቶኝ አቀፈኝ ያ የማውቀው ለስት ዘመነት የናፈቁኝ ክርስቲ በፈጠረችው አቀፍኩት ከላይ እስከታች ውረረኝ .።.።.ሳሚ አይ ሄዋን ለዚ ነው እንደዛ የሆንሽው ሁሉም ሳቁ ..።. በቃ ትንሽ ስላመመኝ ልተኛ እነሱም እሺ ብለው ዞር ብለው ሂድ እኛም ውደ ዶርም ዞርን ልክ ከመቅሰፍት ሂዋን አንዴ ብቻሽን ላውራሽ......አቤል ነበር ..... ክፊል 7 ይቀጥላል...... Share Share Share https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

❤️ሁለት ልብ ❤️ ክፍል 5 ሰኞ ክፍል ስገባ ሳሚ በሀሳብ ጭልጥ ብሎል ናቲ እና አሮን ብቻ ነዉ ያሉት ሳሚ የለም ማለት ይቻላል። ሁለቱም ዝም ብለዉ ይተያያሉ። "አሮን ሳሚ በሰላም ነዉ እንደዚ?" አልኩ ሁለቱንም እያየሁ። " አረ ሳሚ በጣም ቀዝቅዞብኛል ፈገግታ ጨዋታው ከትላንት ጀምሮ ጠፍቶል ምን የሚሉት ነው ሳሚሻ እያልኩ ....ተጠጋሁት ምን አለኝ የተሰጠንን አሳይመንት መስራት ጀመርን። አሮን ድንገት ውደ ውጭ ተመልክቶ አቤል እያለ መጣራት ክርስቲ ተናዳ ቆይ አንተ የማታውቀው ሰው ናፈቀኝ ....hhhh ባገሬ ልጅ እማ ቀልድ የለም ብሎ ውጣ ....ውሬአቸው ይሰማን ነበር አይገርምም አንድ ግቢ ሆነ ይሄን ወር ሙሉ ሳንተያይ .....ናቲ እንዴ ማን ነው ይሄን ያልክ ...ብዙም ሳይቆይ ይዞት መጣ እኔ ከአቀረቀርኩበት ቀና አላልኩም ጓደኖቼን ተዋውቃቸው ብሎ ሁሉንም ከተዋውቀ በኃላ ሂዋን ትባላለች ያሀገራችን ልጅ ናት እኔ አይኔን የሸፈነውን ፀጉሬን ውደላይ እያረኩ ቀና ስል omg አቤል ...ሄዋን ከተቀመጥኩበት ብድግ ....ቀጭ ሰራው የዘረጋውን እጅ ሳየው አፌን በእጄ አድርጌ ውደ ዶርሜ እሮጥኩ ሂዋን የሚል ድምፅ እና የግር ኮቴ ይሰማኝ ጀመር ዞር ስል ሳሚ ና ክርስቲ .. ሳሚ ሳየው ፍጥነት ጀመርኩ......ዶርሜ ገብቼ ሰው እንዳባረረው በሩን ዘግቼ እዛው መረት ላይ ሆኜ እንዴት ልሆን ይችላል እኮ እንዴት " .ብዘም ሳይቆይ በሩ ተንኳኳ ...ሄዋን ክፈቺልኝ ......።። ምንድነው የሆንሽው ትተዋውቃላቹ ንገሪኝ አታልቅሺ ....ታሪኩ ብዙ ነው ከየት ልጀምርልሽ .... ።......"የት ተዋውቃቹ....ከዚ ጀምሪ.... ፍቅረኛዬ ነበር አንድ ትምርት ቤት እየተማር ነው ያደግነው።.. ታውቂያለሽ በልጅነት ልቤ ውስጥ የነገሰው እሱ ብቻ ነው ከ7ተኛ ክፍል 9 ድረስ አንድ ላይ ነበርን ድንገት ሁለተኛ ሴሚስተር ከትምርትቤት ቀረ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያልኩ ስጠብቅ ያመት አልቆ 10ክፍል ደረስኩ አሁንም ልቤ አቤልን በተስፋ ይጠብቃል አንድ ቀን የነሱን መኪና ከ አ.አ.ወደ ፊቼ የሚሰራ ሹፊር ጉረቤታችን ነው ሰላም በልልኝ አልኩት ማታ ላይ ደብዳቤ ደረሰኝ ቆይ ላሳይሽ ከቦርሳይ የማትውጣው ..... ይሄው .... ....💌📥 ሄዋንዬ በጣም ይቅርታ ቤተሰብ ናቸው ይዘውኝ የሄድት...ጌታዬ ከሰጠኝ ነገሮች አንቺ ልዩ ነሽ ። ስለፍቅር በሰማው ቁጥር አንቺነህሽ ውስጤን ይማርከዋል ፦በደስታ ና በሀዘኔ ሁሉ አስብሻለሁ። የሚያቃጥል የውስጥ እሳት ሆንሽብኝ ሒወቴ አንቺን መርሳት ፈጽሞ አልቻልኩም። እንድታፈቅርኝ እንድታስቢኝ ላስገድድሽ አልችልም ብቻ ብቻ አንድ ነገር የማስቸግርሽ ላንቺ ያለኝ ስሜት ምን ያህል ጥልቅ እንደሆነ እንድታውቂልኝ ነው። ልቤ ውስጥ ስለተቀረፅሽ ካንቺ ውጪ ሌላ ማሰብ ምንኛ ብንራራቅም ፈጽሞ ልረሳሽ አልችልም ሒወቴ ጥሩ ጓደኞች ምርጥ ቤተሰብና እንቺን የመሰለ ማር አፍቃሪ ስለሰጠኝ አምላኬን አመሰግነዋለው እውድሻለው..። ከዛስ .....ከዛማ እኔ መልሼ ።..... 📩📃 አቤልዬ. እውነት እንደምትውደኝ አውቃለው እኔ ትመጣለክ እያልኩ በር በሩን አያለው ዛሬ ልዬ ስለሆነ ሰው እያሰብኩ ነበር በህይውቴ ሁሉ ከጎኔ ስለሆንክ አመሰግናለሁ በሂውት እስካለሁ እውድሀለሁ። አቤልዬ አንድ የምወደው ማንነት አለ ይህ ማንነት ከልቤ ና ከአይኔ ሳይጠፋ እስከ ህይወቴ ፍጽሜ ይኖራል እርሱም ምርጥ ፍቅረኛ የሆነው ያንተው ልብ ነው። ግን ተራርቆ ፍቅር እስከመቼ ...?ጠረንህ እንዛ ማር ማር የሚሉ ከናፍሮችህ ናፍቆኛል በእንባዬ መላው አካልክን ላበስብሰው በዛ በሚያስደነግጠው ቅላፄህ እቅፍ አድርገህ አባብለኝ እሹሩሩ ሆዴ እሹሩሩ በለኝ ..አቤልዬ ስላንተ እያምሰብኩኝ ቀኑን ሙሉ ፈገግ ስል ነበር ናፍቀኸኛል በዛ በጭጋግ ጨለማ ውክ እያደረግን አብረኸኝ እያለክ ለምን ልቤ ፍርሀት ፍርሀት ይለዋል.?እጆቼስ ለምን የሚንቀጠቀጡ ይመስልሀል ሌላ ነገር እኮ አይደለም የፍቅርህ ውጥመድ ውስጥ ገብቼ ተሰቃየው በፍፁም ትቼክ አልኖርም ልሄድ ነው እንኳን ሳትለኝ ብትሄድም የኔ ፍቅር ያው ነው አልተለውጠም ያለንበት ችግር ከባድ ውስብስብ ቢሆንም ሁሌም እውድሀለው ❤️ ይሄ ደርሷት ዝምታ መረጠ ሰዓታት ቀነት ተተክተው ድፍን 2ወር ሞላው ትምርቴን መማር አቃተኝ እማስበው አቤልን ብቻ ነበር ።...........ባለሹፊሩ ለሰው ሲያውራ ሰማው........ ክፊል 6 ይቀጥላል .... https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

"እናት የቤተሰቦቿ ዶክተር ናት" እናቶቻችን ከማጥባት ጀምሮ ምግብ ስንበላ ምንም ዓይነት ንግግርም ሆነ ሌላ ጉዳይ ጣልቃ እንዳናስገባ ይመክሩናል።በተጨማሪም የጎረስነው ምግብ በደንብ አኝከን ሳንውጥ እጃችንን ወደ መሶብ እንዳንልክ ያግዱናል።ዉስጣችንን በማዳመጥ ካገሣን በኃላ መጥገባችን ስለሚያመለክት እንደበቃን አውቀን እንድንነሣ ይነግሩናል።ይህ በእውነቱ ከሳይንሱ ያልወጣ ሐቅ ነው።ለጨጓራ በሽታ ዋና መንስኤውም ከተሠጡት ቤተሰባዊ መመሪያዎች ሲወጣ ብቻ ነው። በ19ኛው ክ/ዘመን አንድ እንግሊዛዊ የስነ አመጋገብ ተመራማሪ " የስው ልጅ መቃብሩን የሚቆፍረው በጥርሱ ነው" ብለው ነበር።አልተሣሣቱም ማንኛውም በሽታ የሚመጣው በአመጋገብ ባህላችን ላይ በሚጨመሩ አዳዲስ ልማዶች ነው ። እንግዲህ አመጋገባችን እንዴት መሆን አለበት የሚል ጥያቄ በሁላችን ዘንድ ያለ ይመስለኛል፤ ከዚህ በታች ባለው መሠረት ማንም ሰው ከተጠቀመ የጨጓራ በሽታ አያጋጥመውም። 1የምንበላው ሁሉ በአፋችን ውስጥ እስኪሟሟ ድረስ መታኘክ አለበት፣ወደ ጨጓራችን ሲወርድ ምንም ጠጣር ነገር ባይኖርው ጥሩ ነው ። 2 ጨጓራ የገባውን ለማብላላት የሚያስችለው ሙቀቱን በመጠበቅ ከተወለድንባት ቀን ጀምሮ እስከ እለተሞታችን ድረስ ከልብ እና ከሳንባ ባልተናነሰ ደረጃ ይሠራል ።ስለዚህ የጨጓራ ሥራ ተዛባ ማለት ሁሉም ነገር ተበላሸ ማለት ነው ።እዚህ ላይ ማሰብ ያለብን ነገር ጨጓራ ማዋኃኃጃ እንጂ የማጠራቀሚያ አለመሆኑን ነው። ስለዚህ:- ጨጓራ አምጣ ሳይለን መመገብ የለብንም። የሚበቃንን ያህል ከተመገብን በኋላ ጨጓራችን በመኴማተር ምግቡን በሚያገላብጥበት ጊዜ ያገሳናል በዚህ ወቅት አንድ ጉርሻ እንኳን መጨመር የለብንም። ከጠገብን በኃላ ከውኃ በቀር ለ5 ሰዓታት ምንም ዓይነት ምግብ በአፋችን ማስገባት የለብንም።ምግብ ለመብላት በምንዘጋጅበት ጊዜ ከ15 ደቂቃ በፊት 1ብርጭቆ ውኃ ብንጠጣ ጥሩ ነው። ከ የጤና ምስጢራዊ ቁልፍ መጽሐፍ ገጽ 192-193 የተውስደ አዘጋጅ:-ዶ/ር ፒተር ጀይ.ዲ.አዳሞ ትርጉም:-ዮናስ ተዛረ https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

❤️ሁለት ልብ❤️ ክፍል 4 ድንገት ስልኩ ጠራ ሁለታችንንም አስደነገጠን ግን ምን ሆኜ ነው ሆይ ... "ሄዋንዬ ይሄን ይመስል ነበር እንዴት አየሽው " "እንዴ ከመቼ ጀምሮ ነው እንደዚ ገጣሚ የሆንክልኝ ጉንጩን እንደመሳም እያልኩ" የደስታ ስሜት ሲሰማው ፊቱላይ ይታያል ግን ሳሚሻ እንዴዚ የተገጠመላት ለማነው? "በቅርቡ እነግርሻለው" እሺ ዶርም ደርሰን ቻው ተባብለን ተለያየን ግን ይናት ይሁን ለማን ይሆን ማብሰልሰል ጀመርኩ።...።. እለተ እሁድ ናቲ በጣም እንደፈለገኝ ነገሩን ከዶርም አስጠራኝ እዛ የተለመደው ባታ ሄድኩ አንተ አናታም ምን ሆነክ ነው እንደዚ በግር በፈረስ የምፈልገኝ "ሄዋንዬ ጉድ ሆኜ ልሻለው በርግጥ ግን አሁን ብቻ ሳይሆን በፊትም አልነገርኩሽም እንጂ ትመቸኝ ነበር " "እእእእ አንተ ደሞ ማንም አፈቀርክ " "አይን አይኔን እያየ በተቆራረጠ ድምፅ ክ..ር..ስ...ቲ....ን አለ ውስጤ በደስታ ፈነጠቀች። እሷ ምን ያልክል እንደምታፈቅር ባውኩ እያሉ በሆዴ እና እኔ ምን ላድርግልህ አልኩ እንደ መኮሰተር እያልኩ" "እናማ ያው ጓደኛሽ አይደለች አናግሪልኝ እኔ ስለምፈራት ነው.. ." "ዌል እንግዴ ብዬ ትንሽ ጉራ ልጀምር ስል ..." "ተናደደ እኔን እንደማባረር አለ " ምን አለሁሉም ሰው ከሚውደውና ከሚያፈቅረው ሰው ጋር ቢገጣጠም ግን ሒውት እንደዚ ናት አንዳንዴ ሁለቱም ተፋቅረው ....በሌላው ደሞ ለውለታ ሲባል ......ብቻ ብዙ ነገር አለ .....እኔ አለው አይደል ..... ውስጤ በደስታ ተሞልታ ወደ ዶርሜ ተመለስኩ ልክ ስገባ ክርስቲ በደረቶ ተኝታ የፍቅር ሙዚቃ ከዘፈኑጋር ትዘፍናለች" "ስልኬን አይጥቼ ልዬ ቀን የሚለውን ዘፈን እብሬው እየዘለልኩ ማበድ ጀመርኩ።" በኔ ሁኔታ ክርስቲ ና ሀናን ተገርመው ያዮኛል "ስልኬን ተቀብለችኝ ምን ተገኛ "በጣም ደስ ብሎኛል ..." "ሄዋን ደሞ አበዛሽው በጭንቀት ልሞት ነው.. ......እእእእ... "ና....ቲ.... ካፊ ላይ ተቀብላ "እእእእ ...ናቲ.. "እንዴ ደስ ይላል ዛሬ ስል ክርስቲ ብመታኝ ደስ ባላት ናቲ ምን ሆነ "ናቲ ለአንቺ...... "እእእ ለኔ "እንዴ ተረጋግያ የምን መጣደፍ ነው የምጣድ እያለ የእንቅብ ተንቀጠቀጠ አሉ" ውሬውን ትታ በኔ አባባል መሳቅ ጀመሩ።"" እሺ ባለተረቶ ናቲ ለኔ "የፍቅር ጥያቄ አቀረበ .......መጮ ጀመረች ዘልዬ አፏን እንደመያዝ አልኩ.... "እንዴ ይሄን ደስታ በዚህ አያበቃም እሁድ አይደል እንበላ"? በሀሳቡ ተስማምተን። ውደ ፀጉር ቤት አመራን ሰዓቱ አንድ ተኩል አካባቢ ከግቢ ውጣን ወደ ሸንበረሮ አቀናን በጣም ደስ የሚል ቤት ነው። ጥግ ባታ ተቀመጥን የሰው ብዛት ዳንሱ ሙዚቃው ሌላ አለም ውስጥ አስገባን ሁለት ልጆች ውደኛ መተው አስነሱን እኛም መደሰት ስለምንፈልግ ተነስተን መደነስ ጀመርን። ማን ይችላል አይችልም የሚባልበት አይነት አይደለም በመሀል ሙዚቃው ተቀየረ እኛም እንዳማረብን ውደቦታችን "ደስ የሚል የፍቅረኛሞች ሙዚቃ ሁሉም ፍቅረኛውን ይዞ መውዛውዝ ጀምረዋ እኛ ባላየ አንገታችንን ደፍተን የቀረበልንን መጠጥ በሙዚቃ ማውራረድ ......ባለንበት አቅጣጫ ለሁለታችንም የእጅ መዳፍ ተዘረጋልን በመደንገጥ ቀና ስንል "ናቲ ና ሳሚ" ናቲ በክርስቲ ሳሚ በኔ በኩል ምንም ሳንተነፍስ ተነሳን እጆቹን ውገቤ ላይ እኔ በአፅፋው አንገቱላይ አሳረፍኩ መውዛውዝ ግን እንዴት መጡ?በውስጤ ማሰብ ማሰላሰል ......"ሳሚዬ ዛሬ ደስ ብሎኛል" አልኩት "ምን ተገኛ" አይኖቹን ሰበር እያደረገ እያየኝ "አታያቸውም ሁለት የሚዋደድ ዛሬ ደሞ ፍቅር አንድ አድርጓቸው" "እእእእ ደስ ይላል "ትንፋሽ እንደማውጣት " ግን እንዴት መጣቹ..? "እስቲ ዝም በይ "ብሎ የቀኝ እጄን በእጁ ይዞ ልብ ላይ አንገቴን ውደ አንገቱ ስር የማላውቀው ስሜት ተሰማኝ ""ጠረኑ ሁሉም ነገር ልቡ በጣም ትመታለች አንገቴን ጥንቀት በተሞላው ትንፋሽ እሞቀው ወደ ጆሮዬ ጠጋ "ሄዋንዬ ምን አለ እንደዚ እንዳለን ቢነጋ?" ብሎ እንደመጣ ሲል ከጥፍሬ እስከፀጉሬ ነዘረኝ ..... ዘፈኑ አልቆ ተቀምጥን አሁን እና ናቲ በግልፅ ፍቅረኛሞች እንደሆኑ ታውቆል ሰዓቱን ስናይ በጣም ሄዶል ዘበኛውን ናቲ ትንሽ ሸጎጥ ስለማረግለት ወደ ግቢ አመራን ዶርም ልገባ ስል" ሄዋን"አለ ሳሚ ውይ ብዬ ስዞር ለብቻሽ እይው ብሎ 💌 እንዴ ቅድም አንገቴን ስለሳመኝ ይቅርታ ሊጠይቀኝነው? አልጋዬ ላይ ውጥቼ ፓስታው ላይ "በሰለጠነበት ዘመን ደብዳቤ በቀረበት እኔ ግን ድፍረት አጣው ለዛ ነው በዚች ብጫቂ ውረቀት ላይ ልነግርሽ የፈለኩት "ፖስጣው በፍጥነት ከፈትኩት """ "ሄዋንዬ በርግጥ ከኔ ይሄንን አጠብቂም።ግን ተፈጥሮ ነው ሄዋንዬ ግን ታውቂያለሽ ሴት ልጅ ለአይኔ ነው የምጠላው ብበቀል ሁላ ደስ ባለኝ እንደዚ እንድሆን ያደረገኝ አስተዳደጌ ነው። እናቴ 5አመቴ ሞተች ከዛ እንጀራ እናት ላይ ለመውደቅ ተገደድኩ የማታሰራኝ ስራ የለም ከትምርቴ እያስቀረችኝ ፓንት ሳይቀር ነው የምታሳጥበኝ ልጆቾ እየተከፈለ ይማራሉ እኔ የመንግስት ልጆቹ ሴቶች ስለነበሩ እንደሰው አያዩኝም። በቀን አንዴ ምግብ የምበላው በገዛ ቤቴ ስቃዬን ነበር ያሳዩኝ ለዛም ሴት እርኩስ ናት ብዬ መቅረብ የተውኩት ግን ካንቺ ጋር የማሳልፋትን ጊዜ ለካ አንድ አይደሉም ሄዋንዬ የምነግርሽ አዝነሽልኝ የኔ እንድትሆኝ ሳይሆን ለኔ የፍቅር ስሜት ካላሽ ነው እንድ እውነታ ልንገርሽ ፈፅሞ አንቼን አጥቼ መኖር አላስብም ከልቤ ነው የምውድሽ የማፈቅርሽ ትምርቴን መማር አልቻልኩም ለኔ የተፈጠርሽ ሄዋኔ ነሽ💋❤️🙏 .. ክፈል 5 ይቀጥላል........ https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

ሁለት ልብ 2❤️❤️ ትረካ አቀራረብ ምን ይመስሎታል??
Anonymous voting

❤️ሁለት ልብ❤️ ክፍል 3 በቅናት እርር እላለው ........ ባነጋገሮ ስስቅ "ምነው ሳቅሽ " አይ ምንም እንደዚ ልብሽ ውስጥ የገባው ማነው? በተቆራረጠ ድምፅ " ና....ቲ.... ነው። ሄዋንዬ "በእናትሽ እንዳትነግሪው" አለችኝ ከየት መጣየማይባል ዘበኛችን እስራችን ደርሶ ውደ ክፍላቹ አገብም በዚ ሰአት ምንድነው? እኛም ልንገባ ብላነው ወደ ዶርማችን አመራን "ክርስቲ የሸገር ልጅ ናት" ህሮብ ቀን ፈተና ተፈትነን ከጀለሶቼ ጋር የምንቀመጥበት ቦታ ሄድን ዛሬ ክርስቲን ላስተዋውቃት ነው መንገድ ላይ አሮን ና ናቲ አጠገባችን ደረሱብን ሰላም ብለውን እንደማለፍ ሲሉ "እንዴ ምንነው? አሮን "ከሰው ጋር ነሽ ብለን ነው ሚስጢር የባቄላ ......ጨርሽው አለ። እየሳቀ "በሉ ሁሌ ሶስት ለአንድ ነበር አሁን ደሞ ሁለት ለሶስት እመራለሁ" ናቲ ውድያው ገብቶታል woww welcome" እያላ ውደ ክርስቲ መጠጋት ጀመረ "ናቲ እባላለው ይሄ አሮን ያ ደሞ ሳሚ ወደ ባታው ላይ እየጠቆመ። ግን ወደኛ ስገቢ መስፈርት አለው? "እኔ አስደነገጠኝ የምን መስፈርት? "እስቲ ዝም በይ ማን ጠየቀሽ ለሷ ነው ።..... ሁሉንም ተዋውቃ ልክ እንደቆየን ጓደኛሞች መሳቅ ማውራት ጀመረች ከሰው ጋር ቶሎ ስለምትግባባ አልከበዳትም ። "አሮን ና ናቲ በፈተነው መከራከር ጀመሩ። አቤት የነሱ ክርክር እንዴት ደስ እንደሚል በዛ ሰዓት ክርስቲ "በአይኖ ሰረቅ እያደረገ ናቲን ታየዋለች" ድንገት እኔ ክርስቲ አይን ተገጣጠመ ሁለታችን ለሳቅ ቅርብ ነን። ክት በለን ስንስቅ ደንግጠው ሳሚም ገርሞት እናዛም ከሚከራከሩበት ዝምታ ሰፈነ አንዴ እኔን እሷን አይናቸው ማማተር ጀመረ ። አሮን "ምንድነው? " " እንዴ እራበኛ በማለት ወሬ አስቀየስኩ...... የተለመደው ቤት ሄደን ዛሬ ሁለት ሴት ሶስት ውንድ ሆነናል መጎራረሳችንን ጀመርን ልክ እንደጨረስን አሮን ግቢ መሄድ አለብኝ አለ። እኛ ትኩስ ነገር ለመውሰድ ውደካፊ አመራን እኔ ሳሚ ከኃላ ናቲ ክርስቲ ከፊ ሰዓቱ 10:30ስለሆነ ብዙም ፀሀይ የለም ሊዊ ካፊ ገብተን ስንጫውት ሳናስበው 11:30ሆና እኔ ልሄድ እንደሆነ ስናግራቸው ክርስቲ "ከዘ የሞቀ ጨዋታ ላይ" ሳሚን አስነስቼ እንዲሸኛኝ አደረኩ ዶርም ገብቼ ድንገት ስልኬ ጠራ "ምን ነበር "አልኩ እንደመኮሳተር ሳሚ ነበር "አብረን እንድንሄድ ነው በር ላይ እጠብቅሻለው "ከዶርም እንደውጣው እየጠበቀኝ ነበር "ዛሬ እንዴት ውደዚ መራክ " "መቼም እኛ ሰዎች ስንባል ስንቸገር ነው ውደ አምላካችን የምናዘውትረው"አለ እየተነፈሰ እኮ እንደ አንተ አይነቱ ነው እየሳኩበት ግን እንደዚ ለምን አለ? ስንመለስ የምነግርሽ ነገር አለ ብሎኝ በውንድ መግቢያ ሄደ ስንመለስ ማታ ስለናበር ወክ ማድረግ ጀመርን። እእእ በላ ንገረኝ ምንድነው? ሳሚ "ተረጋጊያ ግጥም ላነብልሽ ነው " ሳኩበት ....እንዴ ከመቼ ጀምሮ ነው ግጥም....መግጠም ... .......እእእ። እሺ ልስማዋ? #እኔ_ምን_አውቃለው እኔ ምን አውቃለው ሳይሽ ደስ ይለኛል ስላንቺ አስባለው አመመኝ ደከመኝ አጣው መድኃኒት ፍቅርሽ አስጨነቀን እንደልብ ውጋት መውደዴ ከሆነ እኔ አንቺን ማየቱ ልቤ ከተሰማው የፍቅር ግለቱ ገረመኝ እራሴን ሳየው ሁኔታዬን ውዳንቺ እያደላ እቢ አለኝ ተው ብለው ነጋ ጠባ አንቺን ነው የማስበው ልቤ ተቆልፎ ያስባል ለብቻው ግን ግን የምውዳት ልጅ ያቻትና መክፈቻው . ......""ሂዋን...ምን ሆንሽ ....አይኔ። ..።።።። ቆይ ላውጣልሽ ተጠጋኝ በጣም ተጠጋጋ.......አውጥቶልኝ ......... ይቀጥላል....... https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

❤️ሁለት ልብ ❤️ ክፍል 2 እረ ማሚ አስጨነቅሽኝ "ሄዋንዬ ድስ ብሎኛል አባትሽም ፀበል ገብቶል ውዶ አይደለም ልጄ እንደዛ የሆነው መቼም ዘንድሮ ሰው ለሰው ሰላም የማይመኝለት ዘመን ነው አሁንማ ያሁላ ቀርቶል እህትሽም ሁሉንም ተረድታው ብቻ ሁሉም እየተስተካከለ ነው አታስቢ ልጄ በርችልኝ ታናሽሽም ከትምርትቤቱ አንደኛ ውታ ተሸልማለች ለማንኛውም በርትተሽ ተማሪ " እሽ ማም by . . በአቅራብያዬ ካለው ቤተክርስቲያን ሄጄ የበፊቱ ሰላማችን ስለተመለሰልኝ አመስግኜ ስመለስ ዶርም ልገባ ስል ተደውለልኝ ሳሚ ነው። "ምን ፈለክ ድመቴ" አልኩ ስልኩን አንስቼ "መቼም ድመት አይጥ እንደሚፈል ታውቂዋለሽ የኔ አይጥ "ቆይ የት ሆነክ ነው እንደዚ የምታዝገኝ . "ባክሽ ሊዊ ካፊ ነኝ ለምን አትመጭም ምርጥ ለአየሩ የሚስማማ ትኩስ ነገር ልጋብዝሽ "እሺ ቆይ ነጠላዬን ላስቀምጥ መጣው ተገኝቶ ነው አልኩ እየሳኩበት" . "እንዳገቢ ባላሽበት ፊትሽን አዙረሽ ነይ ምን ታፍራለሽ እንዴ" አለ ከግቢ ወጥቼ "ሊዊ ካፊ" ጉዞ ቀጠልኩ ሳሚ ከካፊው በረንዳ ላይ ቁጭ ብሏል አጠገብ እደደረስኩ "አንቺ ከየትነው የምትመጭው ከሀገርሽ ነው እዴ ደሞ ሲያምርብሽ ነጠላሽ እማሆይ መስለሽልኛል" አለ እየሳቀ አስተናጋጁን ጠርቱት ልምዴን ስለሚያውቀው ማኪያቱ አዘዘልኝ "ሳሚዬ በቃ አታጠናም አይደል " " በትልቁ እየተነፋሰ እነሱ ላይቡሪራ ናቸው እኔ ደግሞ .....እዚ አላውቅም ምን እንደሆንኩ "ውይ አንተ ማውቅ ካልቻልክ መቼስ ፍቅር ምናምን ያዘኝ እዳትለኝ?እየሳኩበት "የሆንሽ አይጥ ነገር እኔ አሁን ፍቅር ያዘኝ አልኩ" "እውነቴነው እደዚ ስሜትክን ማወቅ እስኪያቅትክ ድረስ ትምህርት አስጠልቶክ ሰው ለፈተና እያጠና አንተ ደግሞ የሊዊ ካፌ ትኩስ ነገሮችን ታጠናለክ" በጣም እየሳቀ "ሂጂ የሆንሽ እቡዱ ነይ ትንሽ ወክ እናዱርገን እንመለሳለን" ብሎኝ ቀዱሞ ተነሳ እጄን ዘርጋ ሰአት ሳይ "አንዱ ሰአት ተኩል ሆኑል ሁሉም ጥዱጥዱ ሆነው ወክ በማዱረግ ላይ ናቸው እኔና ሳሚ በትንሽ ደቂቃ ዝምታ ሰፈነ ሳሚ አዩናቹን ሰረቅ እያደረገ "ሄዋንዬ እስቲ እነዛ ልብ የሚያጥላሉ ልብ ወለዶችሽ አንዱን ንገሪኝ" "እዴ ሠአቱን አይተከዋል ወደ ጊቢ መግባት አለብን ሌላቀን ሰፊ ጊዜ ወስደን" "እሺ አንዱ ሙዚቃ ዝፋኝልኝ "እሱ ያስማማናል ጭር ያለ ቦታ ስንደርስ "ታዲያ ከዳንስሽ ጋር ዳንስ ክበብ ትሰራ አልነበር "መዱረሱ አይቀር ደረስን ሙዚቃ ከፍቼ በማያስደንሰው መደነስ ጀመርኩ። በመሀል ስልኬ ጠራ አሮን ና ናቲ ናቸው አንስቼ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ሳደርግ "የት አባሽ ጠፍተሽ ነው ላያብረራ የለሽም ዶርምም ስንጠያቅ የለችም ውይ አለሁ እንዴ እውነታቸው ነው የለሁም እኮ አላኩ .... "ደግሞ ያአ አዝግ ጉደኛሽ የት እዳለ ታውቂያለሽ " "እእእእ ስሜቱ የተረበሸው ጓደኛችንን ያሄው እኔን እያዛገኝ ነው "የት ናቹ " "ግቢ እዛው የተለመደው " በቃ መጣን" ሳሚ የዛሬው አስተያየቱ ግራ አጋባኝ እዴ ምን አባሆነክ ነው እደዚ የምታየኝ ገራመሽኝ እኔ የተረበሸውን ስሜቴን እንዲታስተውኝ ስፈልግ ጭራሽ በማያስደንሰው ዘፋን በአስቴር ፍቅር ፍቅር ይዞኛል እያልሽ ማባባስሽ.... "ያው ስሜትህ ከዚህ አይዘልም በማለት ነው" እየተጨቃጨቅን እያለ እነ አሮን መጡ. "ሄዋንዬ ይህን ዳንስ ተያይዘሽዋል "ባክ አንዱ ድቡር ስላለ ፍታ እንዲል ነበር" ናቲ "እናንተ ነገ እኳ ፊዚክስ እፈትናለው እንዳለ ታውቃላችሁ" "እንደመደንገጥ ብዬበሉ በሉ ልግባና ትንሽ ላጥና ቻው ብዬ ልለያቸው ስል ከት ብለው ሳቁ" . "ሳቃቸውን ሳይጨርሱ ምን ያስቃል ስል" " "ናቲ አይ ከመቼ ጀምሮ ነው እኛ ዶርም ሳናደርስሽ መሄድ የጀመርሽው ያውም በማታ" በናቲ አነጋገር የደበርው ሳሚ መሳቅ ጀመር." እኔን በመሀል አድርገውኝ ጉዞ ቀጠልን እኛ የባጡን የቆጡን ስናወራ ስሚዬ ግን ዝምታ መርጧል "እጄን በጅ አሾልኬ እንዳይወጣ ጥብቅ አድርጎ ይዞኛል: " ዶርሜ አካባቢ ልንደርስ ስንል ሳሚ ስልክ ላውራ ብሎ ወደኅላ ተመለሰ አሮንና ናቲ ተሰነባብተው መሄድ ጀመሩ። ሳሚ by ሄዋንዬ ብሎ በጅ ምልክት ሰጠኝ"🤚 "ሳሚ እንደዚህ ግን ነገ ያገናኘናል ብዬ ወደ ዶርም ልገባ ስል" "ሄዋን" የሚል ድምጽ ሰማው አቤት ብዬ ዞር ስል ክርስቲ ናት "ክርስቲ ማለት አብራኝ አንድ ዶርም ና እንድ ክፍል ነው የምንማረው "ሄዋንዬ"ፍልጌሽ ነበር አሁን ማውራት እንችላለን። እሺ በሰላም ነው ከበር ላይ ተመልሰን የዶርማችንን መውጫና መውርጃ ደርጃ ላይ ቁጭ አልን. እሺ ክርስቲ ምን አጋጠመሽ "ምን መሰለሽ ሄዋንዬ አንቺ ትርጂኝ አለሽ ብዬ አስባለው" በረጅሙ እንደ መተንፍስ እያለች" . "በመጀመሪያ ጥሩ ጎደኛሞች እንድንሆን እፍልጋለው ቀጥዬ ደሞ ከጎደኛሽ ፍቅር ይዞኛል" " ደነገጥኩ የኔ መደንገጥ ፊቴ ላይ አይታ ምነው ሄዋን ያጠፍሁት ነገር አለ" . ክርስቲዬ እንደውም የሴት ጎደኛ የለኝም አገኘው ግን ከማን ነው ፍቅር የያዘሽ" " ክርስቲ ላይ ዝምታ ሰፈነ እንዴ ምን ነው አሁን እኮ ጎደኛሞች ሆነናል ንገሪኝ." "ታውቂያለሽ ሄዋንዬ ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ካላየሁት መዋል ማደር አልችልም አንዳንዴ ካንቺ ጋር ስትላፉ ሳይ ይቀጥላል..... https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

ሁለት ልብ ❤️+❤️=2❤️ ክፍል 1 . . ከልጅነቴ ጀምሮ ቤት ዉስጥ ሰላም ፍቅር እያየሁ ነዉ ያደግኩት። የሆነ ጊዜ ላይ ደስታና ፍቅሩ ጭቅጭቅ ወደ ፀብ ተተካ ! አባቴ መስከር ጀመረ። እናቴ ደግሞ የአባቴ ስካር ስላማረራት ትናገረው ነበር። በርግጥ እናቴ የሱ ነገር ሆኖባት እንጂ ጭቅጭቅ አትውድም በዚ የተነሳ ይደባደባሉ ሳይደበድባት ነግቶ አይመሽም። እኔና እህቴም ድብድቡን ክፍላችን መሽገን በጭላንጭል እየተመለከትን አደግን። ፀባቸዉ ገና ሲጀመር እንባዬ ከአይኖቼ ዱብ ዱብ እያለ ክፍሌ ተደብቄ አያለሁ። ሁሌም ሰላም የለኝም። አንዳንዴ የአባቴ ተግባር እኔን ራሱ በጣም ያበሳጨኝ ነበር። እንግዳ በሚመጣበት ጊዜ አመትባል በሆነበት ውቅት አባቴ ያለው መጠጥ ቤት ነው። እንደዚ ከመሆኑ በፊት የሚያስቀና ቤተሰብ ነበርን አባቴ ለእኛ ያለው ክብር ደስ ስለሚል ጓደኞቼ ይቀኑብኝ ነበር። እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ እና ነገሮችን ላቅ ባለ እይታ ማገናዘብ ስጀምር እናቴ የጭቅጭቁን መናሻ ምን እንደ ነበር? አባቴ ለምን እንደዚ እንደሆነ ጠየኳት የአባቴ ሁኔታ ምን ያህል መጥፎ እንደሆነ ስለተረዳሁት የእናቴ መናደድ ሲያንሳት ነዉ ወደሚል ድምዳሜ ደረስኩ። ምንም አባቴ ቢሆንም በፍፁም ለእኛ አርዐያ መሆን እንደማትችል ተረዳሁ። ።እኔ እና ታናሽ እህቴ ታዲያ እህቴ አባቴን በሚላት ነገር ለእናቴ መጥፎ አስተሳሰብ እንዲኖራት አድርጎል የሚጠጣበት ምክንያት ያልሆነውን እየነገራት ለማሚ ፍቅር እንዳይኖራት ባደረገ ቁጥር እቤት ሰላም እየራቀ መጣ አባቴን ምን ያህል አሳፋሪ ድርጊት እያደረገ "ሴት ውደ አባቷ ሆነ እንዴ ሲለኝ ይቺ አባባል የእናትሽ ቢጤ ነሽ ብትል ይቀልሀል እያልኩ። ምክሬን አልቀበልም በፍፁም አልተቀበለኝም። አባቴ ይህም አልበቃ ብሎት በየመጠጥ ቤቱ ስሟን ማጥፋት ጀመረ። ሚስጥሯን መደበቅ እና የጎደለውን መሙላት ሲገባው ያልሆነችውን የሆነችውን ማውራት ጀመረ ። እቤት ውስጥ መናናቅ ሁሉንም ነገር በየግል ውሳኔ መውሰን ተጀመረ የቤተሰቡ መሰረት ተናጋ!ከምንም በላይ የሚገርመኝ የእናቴ ትግስት ፅና ነው .... ለምን አትፈታውን? እኔ ብሆን እንደሷ ይሄን ያክል ጊዜ የምታገስ አይመስለኝም። . እድሜዬ ከፍ ብሎ የአስራሁለተኛ ክፍል ተማሪ ስሆን ቤት መግባት የሚባል ነገር አስጠላኝ። ጠዋት ከቤት እውጣለው በሰበብ አስባቡ ማታ አምሽቼ እገባለሁ ማታ ወደ ቤት ስመለስ ልክ ወደ ሀዘን ቤት የምገባ ይመስለኛል። ወደ ቤት ላለመመለስ ስል ቀኑን በተቻለኝ መጠን ራሴን በተለያዩ ነገሮች ቢዚ በማድረግ አሳልፋለሁ። ከተውሰና ጊዜ በኃላ ከቤተሰቤ የተነጠኩትን ያጣሁትን ፍቅር ከክበቦች ለማግኛት ወደ አርት ውዳለበት አቀናው ብዙዎቹ ጓደኞቼ ቤታቸዉ ዉስጥ ያላቸዉ ሰላም እና የቤተሰብ ፍቅር ምን ያህል ትልቅ ፀጋ እንደሆነ አይረዱትም። "ከሰፈር ስድብና አሽሙር ችዬ ሁሉንም በፍቅር ሳያቸው " ሲመለከቱ በጥንካሬዬ ይገረማሉ። እኔ ከእዚ የገባሁት ያንን ጭቅጭቅ አለመስማት መሸሸጊያዬ ነው። ቤተሰብ የሁሉም ነገር መሰረት ነዉ። መልካም ባልሆነ ቤተሰብ ዉስጥ ያደገ ልጅ መጥፎ ቢሆን አይገርምም። ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ የምሳተፍባቸው ክበቦች እና የዳንስ ምሽት ለጊዜዉ ከሀዘናን ጭንቀቴን ከማስረሳት በቀር እዚ ሙያ ውስጥ የመቀጠል ሀሳብ እንዳሌለኝ አውቃለው። . እድሜዬ 22 ሲሆን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተመድቤ ፊዚክስ ዲፓርትመንት መማር ጀመርኩ። ሀዋሳ በጣም ዉብ ከተማ ነች። መንገዶቿ በአረንጓዴ ልማት ያጌጡ እና ፅዱ ናቸዉ ። ከፊቼ ጋር ሲነፃፀር የማይገነኝ ነዉ። ሀዋሳ ከዚ በፊት እኔ አባቴ እናቴ እህቴ ሆነን ለጉብኝት መጥቼባት ነበር ግን ታይታ የማትጥገብ ነች። የላንጋኖ ሀይቅ ታይቶ አይጠገብም ... ብቻ ሁሉም ነገሮ ደስ ይላል። በአንድነት የሰፈሩባት ለምለም ምድር ናት። ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግቢዉም እንደ ከተማዋ አረንጓዴ ነዉ። ዩኒቨርስቲ መግባት ልክ እንደኔ ባልታሰበ ሰዓት ሰላሞን ለተነጠቀ ሰላም ከሌለዉ ቤተሰብ ለመጣ ሰዉ ትልቅ እረፍት ያለዉ ቦታ ነዉ። ትምህርት ተጀምሮ ጥቂት ወራት እንደተማርን ከክፍል ተማሪዎች ጋር መግባባት ጀመርኩ። ውራቶች የፈጀብኝ እኔ ቶሎ ስለማልግባባ ነው። አይን አፋር ቢጢ ነኝ። ሲጀመር ግቢው ውስጥ ያሉ ልጆች ቅልብን ይስባሉ የሴቶች አለባበስ የውንዶች ቁመና እረ ስንቱን.........።..።."" ያንን ቤት ማስታውስ አልችልም ... ሳሚ ፣ ናቲ እና አሮን ጓደኞቼ ሆኑ እኔ ምንም አይን አፋር ነገር ብሆንም ግን ከተግባባን በኃላ ለቀቀኝ። ከእህቴ ልጅ እቤት በተፈጠረው ነገር መልካም ቅርርብ ስላልነበረኝ የወንድምነትን የህትነትን ሁለቱንም ፍቅርን ከነሱ ለማግኘት ብዬ በደንብ ቀረብኳቸዉ። ሳሚ ን ረጋ ብዙም ወሬ የማይውድ ቀይ ድሬ ልጅ ነው። ከአሮን ጋር ያንድ ሀገር ልጆች ነን ከፊቼ ነው የመጣው ። . ናቲ የሀዋሳ ልጅ ነው እድል ሆኖ ባገሩ ደረሰው ...... ቀስ እያልን እየተላመድን መጣን ከመላመድም አልፎ ምግብ አብረን እየተጎራረብን ስንበላ ፍቅራችን ያስቀና ጀመር ። ማናችንም ተነጣጥለን በልተን አናውቅም በፆታ እኔ ብቻ ሴት ነበርኩ። አመሻሽ ላይ ከጓደኞቼ ተለይቼ ውደ ላይብረሪ ለመግባት ስል ማሚ ደውለችልኝ ሰላምታ ከተለዋውጥን በኃላ አባቴ እንዴት ነው ስላት ድምፆ እራቀብኝ ዝምታ ሰፈነ..... . ይቀጥላል...... https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

🌹🌹🌹🌹ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች 🌹🌹 ከዛሬ የካቲት 26 ከቀኑ 6:00 ጀምረን በተከታታይ ልብ አንጠልጣይ የሆነ ሁለት ልብ 2❤️❤️ የተባለዉን ትረካ በጥበብ🇪🇹 ዘአቢሲንያ🇪🇹 ቴሌግራም ቻናል እንጀምራለን. 📕ርእስ :ሁለት ልብ (2❤️+❤️) 📕የክፍል ብዛት :14 ክፍል ብቻ እስከዝያዉ ቻናላችንን በመቀላቀል ሙሉ ትረካዉን ይከታተሉ . ለመቀላቀል ከታች ያለዉን ሊንክ ነክተዉ join ማለት....2❤️❤️ 2❤️❤️ https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

🔰 ርዕስ: "ሁቱትሲ" 🔰 ደራሲ: ኢማኪዩል ኢሊባጊዛ 🔰 ተርጓሚ፡መዘምር ግርማ 🔰 የመጽሐፉ ይዘት: እውነተኛ ታሪክ 🔰 የገጽ ብዛት: 237 @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

ሁቱትሲ፣_ከሩዋንዳው_የዘር_ማጥፋት_የተረፈች_ወጣት.pdf0.20 KB

ያለ ፀፀት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ❗️ "📚 የሚስጢር ሙዳይ ሁን እንጂ ፤ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን❗️ 📚 ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸው ና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር ፤ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን❗️ 📚 ለ እውቀት ትጋ ፤ በከፊል በተረዳኸው ነገር ራስህን እንደ አዋቂ አትቁጠር ፤ በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል። 📚 ስራ ስትሰራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይ ብሰራ የሚጠቀመው ሌላ ነው በሚል ተስፋ ቢስ ሁነህ ሳይሆን ፤ ዘላለም እንደምትኖር ያህል ሁነህ በመትጋት ነው ፤ ትጋት ጥሩ ነው ፤ ችኮላ ግን ውጤት አያመጣም ፤ በችኮላ መስራት ና በፍጥነት መስራት የተለያዩ ናቸው። 📚 ርኩሰት የ ዕውቀት ና የስልጣኔ መገለጫ አይደለምና ፤ ማንነትን ና ሰብአዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ እናድርግ❗️ 📚 እናም በየእለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን❗️ያለ ፀፀት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ። ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ፤ ልክ እንደገና ህይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና የመወለድ ዕድል ቢኖርህ ፤ ደግመህ የምትኖረውን ና ለማከናወን የምትመርጠውን አይነት ህይወት ለመኖር ሞክር❗️" ከ ዶክተር አለማየሁ ዋሴ እሸቴ ፤ ዝጎራ መፅሐፍ የተወሰደ። 📌 መልካም ቀን❗️ https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

ይህን ያውቃሉ በፖርቹጋል ውስጥ የእግርኳስ ተጫዋቹን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀውልት ሰርተው የሚያመልኩ ሰዎች አሉ። ሌሎችንም ለማግኘት ይቀላቀሉ https://t.me/abyssinianwisdom https:/
ይህን ያውቃሉ በፖርቹጋል ውስጥ የእግርኳስ ተጫዋቹን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሀውልት ሰርተው የሚያመልኩ ሰዎች አሉ። ሌሎችንም ለማግኘት ይቀላቀሉ https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

🌟የምኒልክ ተስፉዉ እግዚአብሔር ነዉ። @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom
🌟የምኒልክ ተስፉዉ እግዚአብሔር ነዉ። @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom @abyssinianwisdom

እንኳን ለ127ኛው የ_#አድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ @abyssinianwisdom
እንኳን ለ127ኛው የ_#አድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ @abyssinianwisdom

እንደምነህ እግዜር ፣ ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ዳዊትስ ደህና ነው? ዛሬም ይዘምራል ? ዛሬም ይፎክራል? ሰላም ናት ጠጠሩ ፣ ሰላም ናት ወንጭፉ? እዛስ አቅል ገዛ ፣ ጎልያድ ተራራው ፣ ጎልያድ ግዙፉ? ።።። እልፍ አእላፍ ጎልያድ ፣ ከቦን ሲደነፋ ወንጭፉን ጠቅልሎ ፣ ምነው ዳዊት ጠፋ? ብለህ ጠይቅልን። ።።።። 👉 ከአሌክስ አብርሃም ግጥም ላይ የተቆነጠረ ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

👏👏የግእዝ ቁጥሮች በአኀዝና በፊደል!! ====================== 0. - አልቦ 1. ፩ አሐዱ 2. ፪ ክልኤቱ 3. ፫ ሠለስቱ 4. ፬ አርባዕቱ 5. ፭ ሐምስቱ 6. ፮ ስድስቱ 7. ፯ ስብዓቱ 8. ፰ ስመንቱ 9. ፱ ተሰዓቱ 10. ፲ አሠርቱ 11. ፲፩ አሠርቱ ወአሐዱ 12. ፲፪ አሠርቱ ወክልኤቱ 13. ፲፫ አሠርቱ ወሠለስቱ 14. ፲፬ አሠርቱ ወአርባዕቱ 15. ፲፭ አሠርቱ ወሐምስቱ 16. ፲፮ አሠርቱ ወስድስቱ 17. ፲፯ አሠርቱ ወሰብዓቱ 18. ፲፰ አሠርቱ ወስመንቱ 19. ፲፱ አሠርቱ ወተሰዓቱ 20. ፳ እስራ 21. ፳፩ እስራ ወአሐዱ 22. ፳፪ እስራ ወክልኤቱ 23. ፳፫ እስራ ወሠለስቱ 24. ፳፬ እስራ ወአርባዕቱ 25. ፳፭ እስራ ወሐምስቱ 26. ፳፮ እስራ ወስድስቱ 27. ፳፯ እስራ ወሰብዓቱ 28. ፳፰ እስራ ወሰመንቱ 29. ፳፱ እስራ ወተሰዓቱ 30. ፴ ሠላሳ 31. ፴፩ ሠላሳ ወአሐዱ 32. ፴፪ ሠላሳ ወክልኤቱ 33. ፴፫ ሠላሳ ወሠለስቱ 34. ፴፬ ሠላሳ ወአርባዕቱ 35. ፴፭ ሠላሳ ወሐምስቱ 36. ፴፮ ሠላሳ ወስድስቱ 37. ፴፯ ሠላሳ ወሰብዓቱ 38. ፴፰ ሠላሳ ወሰመንቱ 39. ፴፱ ሠላሳ ወተሰዓቱ 40. ፵ አርብዓ 50. ፶ ሃምሳ 60. ፷ ስድሳ 70. ፸ ሰብዓ 80. ፹ ሰማንያ 90. ፺ ተሰዓ 100. ፻ ምዕት 101. ፻፩ ምዕት ወአሐዱ 102. ፻፪ ምዕት ወክልኤቱ 103. ፻፫ ምዕት ወሠለስቱ 104. ፻፬ ምዕት ወአርባዕቱ 105. ፻፭ መዕት ወሐምስቱ 106. ፻፮ ምዕት ወስድስቱ 107. ፻፯ ምዕት ወሰብዓቱ 108. ፻፰ ምዕት ወስመንቱ 109. ፻፱ ምዕት ወተሰዓቱ 110. ፻፲ ምዕት ወአሠርቱ 111. ፻፲ወ፩ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 112. ፻፲ወ፪ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 113. ፻፲ወ፫ ምዕት አሠርቱ ወሠለስቱ 114. ፻፲ወ፬ ምዕት አሠርቱ ወአርባዕቱ 115. ፻፲ወ፭ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 116. ፻፲ወ፮ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 117. ፻፲ወ፯ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 118. ፻፲ወ፰ ምዕት አሠርቱ ወስመንቱ 119. ፻፲ወ፱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 120. ፻፳ ምዕት ወእስራ 130. ፻፴ ምዕት ወሠላሳ 140. ፻፵ ምዕት ወአርብዓ 150. ፻፶ ምዕት ወሃምሳ 160. ፻፷ ምዕት ወስድሳ 170. ፻፸ ምዕት ወሰብዓ 180. ፻፹ ምዕት ወሰማንያ 190. ፻፺ ምዕት ወተሰዓ 200. ፪፻ ክልኤቱ ምዕት 201. ፪፻ወ፩ ክልኤቱ ምዕት ወአሐዱ 202. ፪፻ወ፪ ክልኤቱ ምዕት ወክልኤቱ 203. ፪፻ወ፫ ክልኤቱ ምዕት ወሠለስቱ 204. ፪፻ወ፬ ክልኤቱ ምዕት ወአርባዕቱ 205. ፪፻ወ፭ ክልኤቱ ምዕት ወሐምስቱ 206. ፪፻ወ፮ ክልኤቱ ምዕት ወስድስቱ 207. ፪፻ወ፯ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓቱ 208. ፪፻ወ፰ ክለኤቱ ምዕት ወስመንቱ 209. ፪፻ወ፱ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓቱ 210. ፪፻ወ፲ ክልኤቱ ምዕት ወአሠርቱ 211. ፪፻፲ወ፩ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአሐዱ 212. ፪፻፲ወ፪ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወክልኤቱ 213. ፪፻፲ወ፫ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሠልስቱ 214. ፪፻፲ወ፬ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወአርባቱ 215. ፪፻፲ወ፭ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሐምስቱ 216. ፪፻፲ወ፮ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወስድስቱ 217. ፪፻፲ወ፯ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰብዓቱ 218. ፪፻፲ወ፰ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወሰመንቱ 219. ፪፻፲ወ፱ ክልኤቱ ምዕት አሠርቱ ወተሰዓቱ 220. ፪፻፳ ክልኤቱ ምዕት ወእስራ 230. ፪፻፴ ክልኤቱ ምሪዕት ወሠላሳ 240. ፪፻፵ ክልኤቱ ምዕት ወአርብዓ 250. ፪፻፶ ክልኤቱ ምዕት ወሃምሳ 260. ፪፻፷ ክልኤቱ ምዕት ወስድሳ 270. ፪፻፸ ክልኤቱ ምዕት ወሰብዓ 280. ፪፻፹ ክልኤቱ ምዕት ወሰማንያ 290. ፪፻፺ ክልኤቱ ምዕት ወተሰዓ 300. ፫፻ ሠለስቱ ምዕት 400. ፬፻ አርባዕቱ ምዕት 500. ፭፻ ሐምስቱ ምዕት 600. ፮፻ ስድስቱ ምዕት 700. ፯፻ ስብዓቱ ምዕት 800. ፰፻ ስመንቱ ምዕት 900. ፱፻ ተሰዓቱ ምዕት 1000. ፲፻ አሠርቱ ምዕት 2000. ፳፻ እስራ ምዕት 3000. ፴፻ ሠላሳ ምዕት 4000. ፵፻ አርብዓ ምዕት 5000. ፶፻ ሃምሳ ምዕት 6000. ፷፻ ሳድስ ምዕት 7000. ፸፻ ሰብዓ ምዕት 8000. ፹፻ ሰማንያ ምዕት 9000. ፺፻ ተሰዓ ምዕት 10,000. ፻፻ እልፍ 20,000. ፪፻፻ ክልኤቱ እልፍ 30,000. ፫፻፻ ሠለስቱ እልፍ 40,000. ፬፻፻ አርባዕቱ እልፍ 50,000. ፭፻፻ ሐምስቱ እልፍ 60,000. ፮፻፻ ስድስቱ እልፍ 70,000. ፯፻፻ ሰብዓቱ እልፍ 80,000. ፰፻፻ ስመንቱ እልፍ 90,000. ፱፻፻ ተሰዓቱ እልፍ 100,000. ፲፻፻ አሠርቱ እልፍ 200,000. ፳፻፻ እስራ እልፍ 300,000. ፴፻፻ ሠላሳ እልፍ 400,000. ፵፻፻ አርብዓ እልፍ 500,000. ፶፻፻ ሃምሳ እልፍ 600,000. ፷፻፻ ስድሳ እልፍ 700,000. ፸፻፻ ሰብዓ እልፍ 800,000. ፹፻፻ ሰማንያ እልፍ 900,000 ፺፻፻ ተሰዓ እልፍ 1,000,000 ፻፻፻ አእላፋት 10,000,000 ፲፻፻፻ ትእልፊት 100,000,000. ፻፻፻፻ ትልፊታት 1,000,000,000. ፲፻፻፻፻ ምእልፊት https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

ከሀገሩ ውጪ ላሉ ጭቁኖች የተፋለመው ኢትዮጵያዊው አፄ ካሌብ 👉በ 5ኛው ክ/ዘመን ኢትዮጵያን ንጉሥ አፄ ካሌብ በሚአስተዳድሩበት ዘመን በዓረብ አገራት የሚኖሩትን የክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ አይሁዳውያኑ በፋርስ ድጋፍ አማካኝነት በመጨፍጨፍ፣ በማሰቃየትና በመጨቆን አላኖር አሏቸው። በአሁን አጠራር የመን አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦችን ንጉሥ ፊንሐስ ክፋኛ መከራቸውን አበዛው ፤ በአንድ ቀን ብቻ 20,000 ክርስቲያኖችን እንዳስፈጀ ብዙዎች ፅፈዋል። በዚህ ጊዜም ቶማስ የተባለ ጳጳስ ከየመን አምልጦ ወደ አክሱም በመምጣት ለአክሱም ንጉሥ ካሌብ የተፈፀመውን ግፍ ሁላ አብራራ። አፄ ካሌብም ሁኔታውን እንደሰማ ለዘመቻ ዝግጅት ጀመረ። ከዝግጅቱ በኋላም 72 ታላላቅ መርከቦችና 70,000 የሚሆኑ ሰራዊት ይዞ ጉዞ ጀመረ። በቦታው እንደደረሰም ውጊያው መርከብ ላይ እንዳሉ በጦር በቀስትና መርከቦቻቸው ተጠጋግተው በጨበጣ ለጥቂት ጊዜ ሲካሄድ ቆይቶ ፍልሚአው ወደየብስ ተቀይሮ በሁለቱም ወገን ብዙ ሰራዊት ካለቀ በኋላ ድሉ የአፄ ካሌብ ሆነና አይሁዳውያኑ ሲበታትኑ ንጉሥ ፊንሐስም ሸሸ። ከዚያም አፄ ካሌብ ወደ የመን ከተማ ወደ ዛፋር ሔዶ የከተማውን ጠባቂዎች አሸንፎ ከተማውን ያዘ። አፄ ካሌብና ንጉሥ ፊንሐስም ፊት ለፊት ተገናኝተው በጨበጣ ፈረሶቻቸው ላይ ሆነው ሲዋጉ ካሌብ ፊንሐስን ወግቶ ከፈረሱ ላይ በመጣል ወደ ባህር ገፍትሮ ወርውሮ በመገድል ድል አረገው። ከዚህ በኋላ የሸሹትና የተደበቁት ክርስቲያኖች ወደየመንደራቸው ተመለሱ። የፈረሱትንና ያረጁትን ቤተክርስቲያኖች ራሳቸው አፄ ካሌብ እየቆፈሩ በማሰራት ጥቂት ጊዜ በየመን ተቀመጡ። በየመን ህዝብ ፍላጎትም መሰረትም አርያት የተባለውን ሰው ንጉስ አርጎ ሾሞላቸው በየአመቱም ለአክሱም ቤተ መንግስት እንዲገብሩ ትዕዛዝ ሰጠ። በዚህም የየመን ህዝብ ከካሌብ ጀምሮ ለ100 ዓመታት በመገበር ቀጥለው የነበር ሲሆን ከዚያ በኋላ ግን ፋርሶች መጥተው የመንን በመቆጣጠር ቤተክርስቲያናትን አፍርሰው የጣኦት ቤተ መቅደሶችን ገነብተዋል። ረሱለላሂ ነብዩ መሐመድ መጥተው ፋርሶችን አሸንፈው የጣኦት ቤተ መቅደስ በማስፈረስ መስጊድ እስካአስገነቡበት 630 ዓ.ም ፋርሶቹ በየመን ቆይተዋል። እንግዲህ አፄ ካሌብ የአክሱምን ስልጣኔ ከማሳደጋቸው ባለፈ ከሀገራቸው ውጪ ላሉ ጭቁኖች በመፋለም ነፃነትን ያጎናፅፋ መሪ በመሆናቸው በአረቦችና በቆስጠንጢኒያ የገነኑ ንጉሥ ናቸው። ዛሬ ድረስ የሮም ቤተክርስቲያን ከሠማዕታቱ ጋር ቆጥራ በየዓመቱ የአፄ ካሌብን በዓል ኦክቶበር 27 ቀን ታከብራለች። https://t.me/abyssinianwisdom https://t.me/abyssinianwisdom

እመጓ.pdf19.46 MB