925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+47 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልእክት
የ7ኛው የታማኝ ግብር ከፋይ እውቅና ሥነሥርዓት ተሸላሚዎች እንኳን ደስ አላችሁ።
ባለፈው ዓመት የምታዋጡት ግብር ለጋራ እድገት እና ለሕዝባዊ ጠቀሜታ በሚውሉ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ እንደሚውል ቃል ገብተን ነበር። ዛሬ በከተማችን ኮሪደሮች የሚታየው ለውጥ ለዚያ ቃላችን ሕያው ምስክር ሆኖ ይታያል።
አስታውሱ፣ የዛሬ ጥረታችሁ የነገን ትውልድ የተሻለ መፃኢ እድል እየቀረፀ ነው። ሙስናን እና ሌብነትን ለማስወገድ በምናደርገው ጥረት ሥርዓቶቻችንን ማጠናከራችንን እንቀጥላለን።
ግብር ከፋዮችም በመሰል ጎጂ ተግባር የተሠማሩ ሰዎችን ባለመተባበር እንዲያግዙ አሳስባለሁ። በጋራ ግልጽ፣ ተጠያቂነት የሰፈነባት እና የበለጸገች ሀገር እንገነባለን።
መስከረም 27/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በአዲሱ የደመወዝ ጭማሪና አከፋፈልን አስመልክቶ በዛሬው እለት ውይይት ተደረገ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨
መንግስት የሰራተኛውን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ ብሎም የመንግስት አገልግሎት ለማቀላጠፍ የሚከፈለውን ደመወዝ ጭማሪ እያገኘ ለህብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳለበት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ ጽ/ቤት አስታወቀ።
የውይይት መድረኩን የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍሪስ ከማል እና አቶ አብድልዋሃብ ኸሊል የወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ በጋራ በመሆን መርተዋል።
በዚህ ወቅት አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያው ከመስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ በውይይት መድረኩ ይፋ ተደርጓል።
በመድረኩ ከአዲሱ የመግሥት ሰራተኞች ደሞወዝ ጭማሪ መጠንና በአበል አከፋፈል ዙርያ መመሪያ ተላልፈዋል።
መንግስት የደሞዝና የአበል ማስተካከያ የተደረገው የመክፈል አቅም ኖሮት ሳይሆን የመንግስት ሰራተኛውን የኑሮ ጫና ለመቀነስ ብሎም የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ትግበራ ለማቀላጠፍ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።
በመሆኑም የመንግስት ሰራተኛው ይህንን በውል ተገንዝቦ ተገልጋዩን ሳያጉላላ የመንግስት የስራ ሰዓት በማክበር በአግባቡ ማገልገል እንደለበት እና ሳይመር ያስተማረውን ህብረተሰብ በቅንነት በታማኝነት ማገልገል እንደሚገባው በመድረኩ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ውይይቱ የወረዳው የመንግስት ተቋማት የስራ ኃላፊዎች ጽ/ቤቶች ሀላፊዎች፣የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።
የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ ደርሷል- ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሁለቱ ምክር ቤቶች የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የባሕር በር ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነቱ እንደጨመረ ገልጸዋል።
በዚህም ኢትዮጵያ አስተማማኝ እና ዘላቂነት ያለው የባሕር በር የማግኘት ጉዳይ ከፍ ወዳለ ደረጃ እንደደረሰ ነው የገለጹት።
ይህም የሆነው ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን በፍትኀዊ መንገድ ማቅረቧ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቅቡልነት ማግኘት ተችሏል ነው ያሉት።
የውጭ ግንኙነት ማዕከል እና መሠረታዊ ማጠንጠኛው ብሔራዊ ጥቅም እና የዜጎች ክብር እንደሆነ ገልፀው፤ በዚህ መነሻነትም የኢትዮጵያ የጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በመደርጀት ላይ ይገኛል ብለዋል።(EBC)
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀሥላሴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዓመታዊ ሥራቸውን መጀመራቸውን አበሰሩ።
#EBC
መስከረም 25/2018 ዓ.ም
አዲስ ለሚወለዱ ህጻናት ለመጀመሪያ ጊዜ የጉበት በሽታ መከላከያ ክትባት እንደሚሰጥ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት የጉበት በሽታ ክትባት (Hep birth dose Vaccin) ስልጠና እና የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ከ10 ዶዝ ወደ 5 ዶዝ መቀየሩ እንዲሁም አንድ አመት አልፏቸዉ ምንም ዓይነት ክትባት ያልተከተቡ ልጆችን አፈላልጎ መከተብን accelerated mini _catch up data triangulation ላይ ትኩረት ስልጠና ዛሬ መስጠት ጀመረ።
በስልጠናው ላይም የጤና ጣቢያ ሀላፊዎች፣የጽ/ቤት ባለሙያዎች፣ የትስስር ባለሙያ፣ የመረጃ ባለሙያ፣ የክትባት ክፍል ተጠሪ፣ የእናቶችና ህፃናት አስተባባሪዎች እና ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናው ለተከታታይ ሁለት ቀናት እንደሚሰጥ ተመላክቷል።
መስከረም 25/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ እየለማ የሚገኝ ለውዝ፣በርበሬ እና ነጭ ሽንኩርት አሁናዊ ቁምና በምስል በከፊሉ፦
አዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች የቀን ውሎ አበል አከፋፈል ይፋ ሆነ
***
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲሱን የመንግሥት ሰራተኞች የቀን ውሎ አበል አከፋፈል ይፋ አድርጓል።
በተጨማሪም ኮሚሽኑ ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ለመንግሥት የፌዴራል ተቋማት የሰው ሀብት እና ብቃት ሥራ አስፈፃሚዎች በአዲሱ የመንግሥት ሰራተኞች ደሞዝ እና የአበል አከፋፈል ዙሪያ መመሪያ ተሰቷል።
በአከፋፈል የአፈፃፀም ሁኔታ ላይም ሰፊ ውይይት መካሄዱን ኮሚሽኑ አስታውቋል።
#EBC #ebcdotstream #Ethiopia
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
መስከረም 25/2018 ዓ.ም
👉🏼 ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶክተር) የክልሉ ጤና ቢሮ ያዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይ መርቀው ከፈቱ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ኦቼና አንቀዲን ቀበሌ እየለማ የሚገኝ ስንዴ ክላስተር የሰብል ቁምና በምስል በከፊሉ፦በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ኦቼና አንቀዲን ቀበሌ እየለማ የሚገኝ ስንዴ ክላስተር የሰብል ቁምና በምስል በከፊሉ፦
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ
ለመሀል አምባ ኮንስትራክሽንና እንዱስትሪያል ኮሌጅ
ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮችን ድጋፍ አደረገ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዟን አስመረቀች 🔥
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ህብረተሰቡንና በጎ ፍቃደኞችን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል ስራ እየተሠራ እንደሚገኝየገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼 የምንገኝበት ምዕራፍ በዓላማ ፅናትና በእመርታዊ እይታ መመራትን የሚጠይቅ ነዉ።
የርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) መልዕክት
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ
"የታደሰ ጂኦእስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ትጋት"በሚል መሪ ቃል ከመንግስት ሰራተኞች ውይይት መድረክ በመሃል አምባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በ2017 በጀት አመት በተለያዩ ቀበሌዎች የተገነቡ ስትራክቸሮች በከፊሉ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሕዳሴ ግድብን የተመለከቱ ጉዳዮች አካቷል - ትምህርት ሚኒስቴር
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከ47,430,337.48 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ለመንገድ መሰረተ- ልማት በመያዝ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼መደመር እና ብሪክስ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የሕዳሴ ሌላኛው የኢኮኖሚ ትሩፋት - ንጋት ሐይቅ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በደት የተፈጥሮ ፍል ውሃ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶክተር) የክልሉ ጤና ቢሮ ያዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይ መርቀው ከፈቱ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶክተር) የክልሉ ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ በጤናው ልማት የተሰሩ ስራዎችን በሚመለከት ያዘጋጀውን የፎቶ አውደ ርዕይ መርቀው ከፍተዋል።
በመርሃ-ግብሩ በኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፣ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የዞኖችና ልዩ ወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።
"በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው አመታዊ የጤና ጉባኤ ማጠቃለያ ርዕሰ መስተዳድሩና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት የምክክር መድረክ የሚያካሂድ ይሆናል።
