fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+47 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
መስከረም 23/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ኦቼና አንቀዲን ቀበሌ እየለማ የሚገኝ ስንዴ ክላስተር የሰብል ቁምና በምስል በከፊሉ፦

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቴክኒክና ሙያ ቢሮ  ለመሀል አምባ ኮንስትራክሽንና እንዱስትሪያል ኮሌጅ ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተሮችን ድጋፍ አደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የመሀል አምባ ኮንስትራክሽንና እንዱስትሪያል ኮሌጅ ዲን የሆኑት ወ/ሪት ሰላማዊት ኡርባኖስ ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንደገለፁት የኮሌጁን ተግባር በተሻለ መልኩ ለማሳለጥ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ጠቅሠው ለተደረገላቸው ድጋፍ ላቅ ያለ ምስጋናቸውን በተቋማቸው ስም ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጋዟን አስመረቀች 🔥 ***** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት መርቀዋል። በሶማሌ ክልል ካሉብ የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት በዓመት 111 ሚሊዮን ሊትር የማምረት አቅም አለው። #NaturalGas #PMAbiy

መስከረም 22/2018 ዓ.ም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ህብረተሰቡንና በጎ ፍቃደኞችን ያሳተፈ የወንጀል መከላከል ስራ እየተሠራ እንደሚገኝየገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት በወንጀል መከላከል ዙሪያ መሃል አምባ ከተማ ከተደራጁ የሠላም ኮሚቴ እና አጋዥ ኃይሎች ጋር በዛሬው እለት ውይይትና ምክክር ባደረጉበት ወቅት ነው። የውይይት መድረኩን የመሩት የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ተወካይ ኢንስፔክተር ጀማል አስፍር የሀገርንና የአከባቢውን ሠላምና ደህነነት ለመጠበቅ የሠላም ኮሚቴ አጋዥ ሃይሎች ጋር ተቀናጅተው መስራት የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ኢንስፔክተር ጀማል አክለውም የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ህብረተሰቡንና በጎ ፍቃደኞችን ባሳተፈ መልኩ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ የሚገኘው የወንጀል መከላከል ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መከላከል አስተባባሪ የሆኑት ምክትል ኢንስፔክተር መሀመድ አባተ በበኩላቸው ሠላም የሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ የሠላም አጋዥ ኃይሎችን በስልጠና በማጠናከር እንዲሁም በማደራጀት የተጠናከረ ስምሪት በመስጠት የከተማውን ሰላም ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። የተለያዩ አደረጃጀቶችን በተገቢው በማደራጀትና በማጠናከር ለፖሊስ የሚያደርጉት ድጋፍና ወንጀል የመከላከል ተግባር ውጤታማነት ማሳደግ እንደሚገባ ምክትል ኢንስፔክተር መሀመድ አባተ አክለው ገልጸዋል።። በውይይቱ የተሳተፉ የሠላም አጋዥ በበኩላቸው በመሃል አምባ ከተማ ላይ የሚያደርገውን ጥረት በማገዝ፣ እኛም የከተማችንን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ፣ የምናደርገውን ተሳትፎ በተሻለ መንገድ አጠናክረን እንቀጥላለን በማለት የፖሊስ ተቋም አገልግሎት አሠጣጥ እንዲሁም በሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ሠጥተዋል።

የርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) መልዕክት የምንገኝበት ምዕራፍ በዓላማ ፅናትና በእመርታዊ እይታ መመራትን የሚጠይቅ ነዉ። የጀመርነዉን የሠላም፣ የዴሞክራሲና የልማት ግንባታ ሂደት በማጠናከር ፣ ለላቀ ህብረተሰባዊ ተጠቃሚነት ተግተን እንሠራለን፤ የባንዳና የባዳ አደናቃፊ ዘመቻዎችን በጋራ እየመከትን፣ ለጋራ ህልማችን/ለጋራ ራዕያችን እዉን መሆን በጋራ እንተጋለን። ለኢትዮጵያ ፣ ለክልላችን፣ በአጠቃላይ ለሕዝቦቻችን ሁለንተናዊ ብልጽግና እዉን መሆን በብሩህ ተስፋዎቻችን ተበረታተን ፣ በይቻላል ወኔ ጀግነን በህብረት እንተጋለን ።

መስከረም 22/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "የታደሰ ጂኦእስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ትጋት"በሚል መሪ ቃል ከመንግስት ሰራተኞች ውይይት መድረክ በመሃል አምባ ከተማ እየተካሄደ  ይገኛል።

አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ሕዳሴ ግድብን የተመለከቱ ጉዳዮች አካቷል - ትምህርት ሚኒስቴር አዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን የተመለከቱ በርካታ ምዕራፎች አካቷል አለ የትምህርት ሚኒስቴር። በሚኒስቴሩ የማሕበራዊ ሳይንስ ሥርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያ መሪ ስራ አስፈጻሚ ኡመር ኢማም የግድቡ መመረቅ የታሪክ ትምህርትን ከፖለቲካዊ ትርክት ወደ ማህበረ ኢኮኖሚያዊ ይዘት እንዲቀየር አድርጎታል ብለዋል፡፡ አዲሱ ሥርዓተ ትምህርትም ግድቡን የተመለከቱ በርካታ ምዕራፎች እና ንዑስ ምዕራፎችን ማካተቱን አመላክተዋል፡፡ የሕዳሴ ግድቡ አጠቃላይ ሁኔታ በሥርዓተ ትምህርት ውስጥ መካተት ሉዓላዊነትን የሚያረጋግጥ እና የሀገር ፍቅር የሚያሰርጽ መሆኑን ጠቁመው÷ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነትና ትውልድን ለመገንባት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እንዳለው አንስተዋል፡፡ ስለግድቡ አጠቃላይ ሁኔታ ህጻናት እና ታዳጊዎች መማራቸው ብሔራዊ ኩራት እና ለተጨማሪ ስራ ተነሳሽነት የሚፈጥር እንዳለውም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ስሟ ሲጠራ ሰንደቅ ዓለማዋ እና ብሔራዊ መዝሙሯ አብረው እንደሚስተጋቡት ሁሉ ሕዳሴ ግድቡም ብሔራዊ አርማ እንዲሆን ለማድረግ በትምህርት ሥርዓቱ ውስጥ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡(ኤፍ ኤም ሲ)

መስከረም 19/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከ47,430,337.48 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ለመንገድ መሰረተ- ልማት በመያዝ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከ 65 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የጠጠር መንገድ ዝርጋታና የተለያዩ የስትራክቸሮች ስራዎችን በማከናወን ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን አክሎ ገልጿል።   የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ አሸብር ርጋ መንግስት የህብረተሰቡን የመንገድ ተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ በረካታ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል። ቀበሌን ከቀበሌ፣ ቀበሌን ከወረዳና ከሌሎች አጎራባች አካባቢዎች ጋር ለማስተሳሰር ሰፊ ርብርብ መደረጉን የተናገሩት ኃላፊው በበጀት ዓመቱ ብቻ በወረዳ መንግስት፣ ተወላጅ ባለሃብቶችን ጨምሮ ህብረተሰቡን በማስተበበር ከ 65 ሚሊዮን  ብር በላይ በሆነ ወጪ የገጠር መንገድ ግንባታ፣ የተለያዩ ስትራክቸሮች ስራ፣ የድልድይ ግንባታ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች በማከናወን አ/አደሩን ማስጠቀም ስለመቻሉ ገልጸዋል።   የመንገድ መሰረተ ልማት ለአንድ ሃገርና አካባቢ ሁለንተናዊ ብልጽግና የአንበሳውን ድርሻ ይጫወታል ያሉት አቶ አሸብር በ2017 በጀት ዓመት በወረዳ መንግስት በመንገድና በስትራክቸር ስራ ከፍተኛ ለውጥ የተመዘገበበት እንደነበርም አውስተዋል።   ይኽውም  የቁርባኖ ቀበሌ ማዕከል መግቢያ እስትራክቸሮችና ድልድይ፣ ከጅማ ዋና መንገድ ሀድራ ጥሮና ጨረጌ የጠጠር መንገድ እስትራክቸሮችና ድልድይ፣ከጎራ ቲቲሌ እስትራክቸሮች፣ከአቄበል አላባቦ የጠጠር ስራ ፣ከጅማ አረዳ ጠጠር ዳምፕ ማድረግ ስራ ፣ከጅማ -ፍቴ -ጠንቆሌ የአፈር እና የጠጠር ስራ፣ ከጠንቆሌ ሴባ ዋቤ የአፈር ጠረጋ፣ ፣ከቦልጫመኝ እስከ ሙሉካ ት/ት ቤት የበጋ መንገድ፣ከመ/አምባ ቀጡጥ መንገድ የጠጠር ዳምፕ ስራና እስትራክቸር ፣ከመ/አምባ-ሼሆች መንገድ የጠጠር ዳምፕ ስራና እስትራክቸር፣ከመ/አምባ-ገዎ የጠጠር ዳምፕ ስራ፣ከመ/አምባ -አዳር ገበያ የጥገና ስራ፣ የመ/አምባ መናሀሪያ የመሰረተ ልማት ግንባታ ፣የአበባን ድልድይ ግንባታ የተጠናቀቀበት እና የውልቆ ድልድይ ግንባታ የጀመረበት ፣የደመካሽ ድልድይ እና ሌሎች ያልተጠቀሱትን ጨምሮ በዚህ ልማት በጠቅላላው ከ59 ኪ.ሜ በላይ የጠጠርና የበጋ መንገድ እንዲሁም በርካታ እስትራክቸሮች ተገንብተው ለአገልግሎት የበቁ ሲሆን ለዚህም ከመንግስት ከ 40 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልጸዋል።  በጠቅላላው በወረዳ መንግስት እና በህብረተሰብ ተሳትፎ ለተሰሩ ስራዎች ከ 65 ሚሊዮን ብር ወጪ ስለመደረጉ አስታውቀዋል። በዘንድሮ 2018 በጀት አመት ለደሩ ፕሮጀክቶች 39,430,000 በጀት የተያዘ ሲሆን 8 ሚሊዮን ብር ደግሞ ለአዲስ ፕሮጀክቶች ተመላክቷል ኦቼና አንቀዲን ቀበሌ ከገርጋራ አባከና መንገድ ጥገና፣ከሲብና ማራንቶ ቀበሌ ከኮንበል አዳዘር መንገድ ለጠጠር ማምረቻ፣ከፈንጀሌ ሃደሮ መንገድ ለጠጠር ማምረቻ፣ሠፍቶ ቀርሳ ቀበሌ ከጉታራይ ከምስ ገብያ መንገድ ስትራክቸር ስራ፣ጠይባ ቀበሌ መድረሳ መግቢያ የጠጠር መንገድ፣ከእሬሶ ቦሮቦር ሠፍቶ ማዕካል ስትራክቸር ስራ፣ዘሬ ቀበሌ ከሸርት ኤለጎ የአፍር ጥርጊያ መንገድ ስራና ቱቦ ቀበራ፣ዘልዋን ሠፍቶ ቀበሌ ከሲሪ ከቢር ሃሚድ መስጅድ የጠጠር መንገድ፣ገሬኖ ቀበሌ ከንፍስአንቾ ሙልካ ትምህርት ቤት ጠጠር ማምረቻና ስትራክቸር ስራ በጀት የተያዘ መሆኑን አቶ አሸብር ረጋ ገልጸዋል። በመጨረሻም አቶ አሸብር ርጋ ባስተላለፉት መልዕክት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ስራዎች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎባቸው እንደሚደሚሰራ ጠቁመው ህብረተሰቡም የተገነቡለትን የመንገድ መሰረተ ልማት ስራ በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባው ገልጸዋል።