fa
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
917
مشترکین
+124 ساعت
+17 روز
+730 روز
آرشیو پست ها
የካቲት 30/2018 ዓ/ም ባለፉት ዓመታት በተሰራው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የ2018 ዓ/ም የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ስራ መዝጊያ ፕሮግራም በወረዳው በከሲብ ማራንቶና ቀበሌ በአዳዘርና አዚት ንዑስ ተፋሰስ ተካሂዷል። በተከታይ ለ25 ቀናት ሲከናወን የነበረው ኡአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ 10 ሺህ 3 መቶ 71 ሄታር መልማቱን ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል። በወረዳው በተሰራው የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የተራቆቱ መሬቶች በማገገም ተጨማሪ መሬት በመፍጠር ለስራ እድል ፈጠራ ምቹ እድል እየፈጠረ መሆኑ ተመላክቷል። በሁሉም ቀበሌ የተሰራው የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በቀጣይ በፊዚካል ስራ በማጀብ ማፅደቅ የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ቅንጅት መኖር እንዳለበት ተገልጿል። የወረዳው የግብርና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ፣ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ም/ኃላፊና የተፈጥሮ ሀብት ዘርፍ ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ሰማንና የወረዳው ስራ እድል ፈጠራ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ እንዲሁም የቀበሌ አመራርሮችና አረሶ አደሮች የ2018 የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ የመዝጊያ መርሃ ግብር ላይ ተሳትፈዋል። ባለፉት 25 ተከታታይ ቀናት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አደረጃጀቶችና ባለሙያዎች የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

የካቲት 30/2018 ዓ.ም የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞችን ደህንነት በመጠበቅ ፍትሀዊ የሆነ የዜጎች ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት የ2018 ዓ.ም የ2ኛ ሩብ አመት የህዝብ ክንፍና የዜጎች ቻርተር ከባለ ድርሻ አካላት የውይይት መድረክ አካሄደ። የዕለቱ የመወያያ ሰነድ ሪፖርት በፅ/ቤቱ የልማት ዕቅድ ባለ ሙያ በአቶ መሀመድ ሙደሲር ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል። በሁሉም ቀበሌዎች ለአካል ጉዳተኛና አረጋውያን ተደራሽ መሆን እንደሚገባ፣ከባለ ድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ፣ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በተገቢው መለየት መቻል እንዳለበት ፣ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ላይ በልዩነት ታቅዶ መሰራት እንደሚያስፈልግ ፣በተለያዩ ድርጅቶች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ደህንነታቸው ከመጠበቅና ከውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ለሚወጡ ሰራተኞች መረጃ በተገቢው ማደራጃ እንደሚያስፈልግ ዕድሜያቸው ለስራ ያልደረሱ ህፃናት ክትትል ማድረግ ፣የሰራተኞች ክፍያ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈል የገለጽት አስተያየት ሰጪዎቹ የአካል ጉዳተኞች ችግር ለመቅረፍ እየተሰራ ያለው ስራ መበረታታት እንዳለበት አስታውቀወል። ለተነሱ ሀሳብ አስተያየት ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ መሀመድሰኢድ ደንበል እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙና ተሳትፎቸው እንዲጎለብቱ እና በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በድህነት ተጋላጭና መገለል ውስጥ ለሚገኙት የተለያዩ ድጋፍ እንዲያገኙ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ። ተወካዩ አክለውም የሥራ ስምሪት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣  የሰራተኞች ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የስራ አካባቢዎች እንዲሻሻል፣ የዜጎችን ማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት የአካል ጉዳተኞች እኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ ጽ/ቤቱ አቅዶ እየሰራባቸው ካሉ ጉዳዮች ዋነኞቹ መሆናቸው  ጠቁመው የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማሳደግ ተሳትፏቸው እንዲያድግና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ሁሉም ኃላፊነቱን በተገቢው እንዲወጣ ጥሪ አስተላልፈዋል።

የካቲት 30/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከጅማ አረዳ  11 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ እየተገነባ መሆኑን የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ከጅማ አረዳ ድረስ 11 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ከ10.4 ሚሊየን ብር ወጪ በወረዳው መንግስት አማካኝነት እየተገነባ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አክሎ አስታውቋል። የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ደንበል ከድር ግንባታውን አስመልክተው እንደገለጹት መንገድ ለአንድ ሀገርና አካባቢ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ብልጽግና የሚኖረው ፍይዳ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ የመንገድ ተደራሽነት በማሳደግ የምንፈልገውን ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገት ለማረጋገጥ የመንግስት፣ የህብረተሠቡና የባለሃብቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲሁም የመንግስትና ቅንጅታዊ አሠራር ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በዘንድሮው በጀት አመት በተቋማቸው በአዲስ ካፒታል ፕሮጀክት ከተያዙ ተግባራት አንዱ ከጅማ አረዳ 11 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ 10.4 ሚሊየን ብር በላይ በሆነወጪ መገንባቱን አስታውቀዋል። አቶ ደንበል አክለውም የጠጠር መንገዱ አምስት የገጠር ቀበሌዎችን ማለትም ጅማ ወለኔ፣ቀቻ፣ አመቶ፣ዋቦን እና አረዳ ቀበሌዎችን የሚያገናኝ እንደሆነ ጠቅሰው በአንጸሩ ህብረተሠቡ የተገነባለትን መንገድ በባለቤትነት መጠብቅና መንከባከብ እንዳለበት አስገንዝበዋል። ኢንጅነር እንደሻው ዳርፈታ የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ባለሙያ መንገዱንን ክትትል ሲያደረጉ አግኝተን በሰጡን አስተያየት የመንገድ መሰረተ ልማቶች የማህበረሰቡን እንግልትና ወጪ ከመቀነስ ባለፈ ኢኮኖሚያዊና የማህበራዊ እንቅስቃሴ መነቃቃት ትልቅ አበርክቶ እንዳለው አብራርተዋል። አርሶ አደሩ ያመረተውን ወደ ገበያ እንዲያወጣ ፣ የሸመተውን ጨምሮ ግብርና ግብዓት ወደ ቀበሌ እንዲያስገባና ማህበራዊ ጉዳዮቹን በአማራጭ ትራንስፖርት እንዲከውን የመንገድ መኖር ህይወቱን እንደሚያቀልለት ተናግረዋል። ኢንጅነር እንደሻው ዳርፈታ አክለውም ከጅማ አረዳ ድረስ 11 ኪሎ ሜትር ደረጃውን የጠበቀ የጠጠር መንገድ ከ10.4 ሚሊየን ብር ወጪ በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን ገልጸዋል። አቶ አ/ረሂም አብደላ እና አቶ ኸይሩ ከድር በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የጅማ ወለኔ ቀበሌ ነዋሪዎች ሲሆኑ በአካባቢው በነበረው የመንገድ ተደራሽነት ችግር ምክንያት አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት በወቅቱ ለገበያ በማቅረብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ እንዳይረጋገጥ አሉታዊ ጫና ከማሳደሩም በተጨማሪ ሴቶች በወሊድ ምክንያት ለከፋ ችግርና እንግልት ሲዳረጉ እንደነበር አስታውሰው አሁን ላይ ምስጋና ለመንግስት ይገባውና ሁሉም ስቃይ አልፎ በነበር ብቻ ሲወሳ ይኖራል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎቹ ጠቅሰው ለመንገድ ደህንነቱ አስፈላጊውን ጥበቃና እንክብካቤ የሚያደርጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የካቲት 27/2018 ዓ/ም አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለሚገኙ ህጻናትና አካል ጉዳተኞች ከ350 ሺህ ብር የሚያወጣ ስፔሻል ዊልቸር፣የአዋቂ ክራንች እና አርተፊሻል ጫማ ድጋፍ አደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገ/ጉ/ወ/ወ/ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ከጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት አማካኝነት 3 የህፃናት ዊልቸር 4 የአዋቂ ክራንች 2 አርተፊሻል ጫማ ድጋፍ ተደረገ። የወረዳው ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ሃይደር ዝይን እንዳሉት አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት 3 የህፃናት ዊልቸር 4 የአዋቂ ክራንች 2 አርተፊሻል ጫማ ከ350 ሺህ ብር በላይ የሚወጣ ድጋፍ መድረጉን ገልጸዋል። ለማይችሉናየጀርባ ችግር ላለባቸው፣ ራሳቸውን መቆጣጠር  የአእምሮ ውስንነት ላለባቸው ህጻናት  የሚሆን ዊልቸርና የተለያዩ የእግር ጉዳት ለሰለባቸው የአዋቂ ክራንች 2 አርተፊሻል ጫማ ድጋፍ መደረጉን አስታወቀዋል። አቶ ሃይደር አክለውም ዊልቸርና ክራንች ለማግኘት አካል ጉዳተኛ ህፃናት እና ቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን አዲስ አበባ ድረስ በመጓዝ መገኘቱን ጠቅሰው ዊልቸሩ ህጻናቶቹ ራሳቸውን ችለው እንዲቀመጡ፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲያሳልፉ እንዲሁም ልጆች በሚጫወቱበት አካባቢ ሄደው እንዲዝናኑና እንዲሳተፉ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በመጨረሻም አቶ ሃይደር ድጋፉን ላደረገው ለአጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት እና ለወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ላደረገው የትራንስፖርት ድጋፍ በራሳቸውና በተቋማቸው ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅረበው ይህን መሰል ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የካቲት 26/2018 ዓ/ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የሚገኘው ለጉዲ ቡና ልማት ኢንቨስትመንት የተዘጋጀ የታጠበ የቡና ምርት ለኤክስፖርት ገበያ በዛሬው እለት ተሸኘ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በለጉዲ ቡና ልማት ኢንቨስትመንት የተዘጋጀ 22 ኩንታል የታጠበ የቡና  ምርት ለኤክስፖርት ገበያ አቀረበ። መረጃው የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ነው።

የካቲት 26/2018 ዓ/ም ህብረተሰቡ ፌስታል ከመጠቀም ተቆጥቦ የአካባቢ ጥበቃን ከግምት ውስጥ ያስገቡ የወረቀት ከረጢቶችን እና ተደጋጋሚ ጥቅም የሚሰጡ የጨርቅ ዘንቢሎችን እንዲጠቀም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አከባቢ ጥበቃና ደን ልማት ጽ/ቤት አስታወቋል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በኢትዮጵያ የፕላስቲክ ከረጢቶችን መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ  ቁጥር 1383/2017 ዓ/ም ጥር 23/2018 ጀምሮ ስራ ላይ መዋሉን ጽ/ቤቱ አክሎ አስታውቋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አካባቢ ጥበቃና ደን  ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ አብድልሀፊዝ ጉዳዮን አስመልክቶ እንደገለጹት አዋጅ ቁጥር 1383/2017 ድንጋጌዎች ከጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን ገልጸው በግብርናው ዘርፍ እና በአካባቢ ንፅህና ላይ ፌስታል እያደረሰ ያለው ጉዳት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። ህብረተሰቡ ከፌስታል አጠቃቀም ተቆጥቦ የአካባቢ ጥበቃን ከግምት ውስጥ ያስገቡ የወረቀት ከረጢቶችን እና ተደጋጋሚ ጥቅም የሚሰጡ የጨርቅ ዘንቢሎችን እንዲጠቀም አስታውቀዋል። በወረዳ ደረጃ አዋጁን አስመልክቶ የግንዛቤ ስራዎች በተለያዩ መንገዶች እየተሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው የወረቀት ከረጢቶችና የጨርቅ ዘንቢሎችን ተኪ ምርቶችን ኢንተርፕራይዝ በማደራጀት ለነዋሪዎች ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የጽ/ቤቱ ኃላፊ ገልጸዋል። የወረቀት ከረጢቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ ከምድር ጋር ተዋህደው ማዳበሪያ መሆን የሚችሉ በመሆናቸው ፣ ለግብርናው ዘርፍም ሆነ ለአካባቢ ጥበቃ ስራ ትልቅ እገዛ እንደሚያደርግ አብራርተዋል። የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም የሚከለክለው አዋጅ ከአንድ ጊዜ በላይ ጥቅም ላይ የሚውል ፕላስቲክ ምርት ተጠቅሞ የተገኘውን አካል ከ2,000 እስከ 5,000 ብር እንደሚያስቀጣ የጠቅሱት አቶ አብዲ ለንግድ ማለትም ለህዝብ በሽያጭ ለማቅረብ ይዞ የተገኘ ከ50 ሺ ብር እስከ ከ200 ሺ ብር በማይበልጥ ገንዘብ መቀጮ እና አምስት ዓመት ጽኑ እስራት ድረስ የሚያስቀጣ እንደሆነ ለአዋጁ ተግባራዊነት ላይ በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም አቶ አብዲ ባስተላለፉት መልእክት ህበረተሰቡ በእጁ የተከለከሉ የፕላስቲክ ምርቶችን ባለመጠቀም የአከባቢውን ንፅህና መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በመጪው ቅዳሜ ይጀመራል ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በዲጂታልና በመደበኛ መንገድ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም ይጀመራል።  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ፤ መራጮች በቦርዱ አዲስ መተግበሪያ አልያም በአካል በሚደረጉ የዲጂታል ምዝገባዎች ተጠቅመው እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ዜጎች "ምርጫዬ" የተሰኘውን የሞባይል መተግበሪያ በመጠቀም ባሉበት ቦታ ሆነው መመዝገብ የሚችሉ መሆኑን የጠቆሙት ሰብሳቢዋ፣ ይህንን ማድረግ ለማይችሉ ደግሞ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት መመዝገብ እንደሚቻል ገልፀዋል። በአጠቃላይ ካሉት 45 ሺህ ምርጫ ጣቢያዎች መካከል በ17 ሺህ ጣቢያዎች ላይ የዲጂታል ምዝገባ ሥርዓቱ ተግባራዊ እንደሚሆን ሰብሳቢዋ አብራርተዋል። የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭትና የሰው ኃይል ሥልጠናዎች መጀመራቸውን የገለጹት ወይዘሮ ሜላትወርቅ፤ ጠቅላላ ምርጫው ነፃ፣ ገለልተኛና ፍትሐዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሁሉም አካላት እኩል ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።