917
مشترکین
+124 ساعت
+17 روز
+730 روز
آرشیو پست ها
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፌደራልና
የክልል ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች በየደረጃው ከመረጣቸው ህዝብ ጋር በዛሬው እለት ውይይት በማድረግ ለወረዳው ጠቅላላ አመራር ግብረ-መልስ ሰጥተዋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የፌደራልና የክልል ምክር ቤት የህዝብ ተወካዮች በመሀል አምባ ከተማ ከመረጣቸው ህዝብ ጋር በተለያዩ ጉድዮች ዙሪያ በዛሬው እለት ውይይት አካሂደዋል ።
የፌደራልና የክልል ምክር ቤት ህዝብ ተወካዮች ከመራጩ ህዝብ ጋር በዓመት ሁለት ውይይት ያደርጋሉ።
በውይይቱም በሰላም፣ በፕሮጀክቶች አፈፃጸም፣የኑሩ ውድነት፣ በመሠረተ ልማት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ዙሪያ ላይ በሠፊው ውይይት ተደርጎበታል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች ሃሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ባለፉት ዓመታት የብልጽግና መንግስት ህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ ህዝቡን ተጠቃሚ የደረጉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ማከናወኑን ጠቅሠው በዚህም በአካባቢያቸው የለውጡ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል።
አክለውም የኑሮ ውድነቱን ከማረጋጋት ረገድ የሰንበት ገብያ፣ በቀበሌው የሚስተዋለውን የመንገድ ተደራሽነት ችግር፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ ከመሃል አምባ- ወልቂጤ አስፓልት መንገድ እንዲሁም የመብራት ዝርጋታ፣ የፍትህ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ፣የመሀል አምባ ከተማ የመስተዳደር ጥያቄ፣የትራንስፖርት ዘርፍ አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥና የመድሃኒት አቅርቦት ጉዳይ
በየደረጃው ምላሽ እንዲሰጡባቸው ሲሉ የጠየቁት ተሳታፊዎቹ በቀጣይ ጊዜያትም ከመንግስት ጎን በመሰለፍ ብልጽግናችንን ከዳር ለማድረስ እንሰራለን በማለት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
የወረዳው አስፈጻሚ አካላት ከህዝብ እንደራሴዎች የተሠጡትን ግብረ መልሶች በተገቢው በመውሠድ የእቅድ አካል አድርገው እንደሚሠሩ በመድረኩ ተመላክቷል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የፌድራል የህዝብ ተወካዮች ምክር አባል የተከበሩ ወ/ሮ ሳድያ ተማም እና የክልል ምክር ቤት የህዝብ ተወካይ የሆኑት የተከበሩ አቶ ኸይሩ መሀመድ እና ወይዘሮ ነጅቢያ ማህሙድ ከህዝቡ የሰበሰቡትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለወረዳው ጠቅላላ አመራር ግብረ መልስ በመስጠት በየደረጃው በውይይት ወቅት ለተነሱ የመሰረተ-ልማት ጥያቄዎች በፌደራል፣ በክልል፣ በዞንና በየደረጃው በሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች መልስ እንዲያገኙ ጥያቄቸውን በተገቢው እንደሚያደርሱ ክትትል እንደሚያደርጉ በመግለጽ ከውይይቱ የተገኙ ግብዓቶችን በመውሰድ የቀጣይ እቅድ አካል ተደርጎ እንደሚሰራ የፌደራልና የክልል ምክር ቤት አባላቶች ገልጸዋል።
በውይይት መድረኩ የተቋማት ከወረዳው የመንግስት ሰራተኞች የተወጣጡ ባለሙያዎች፣የመሀል አምባ ከተማ የወጣቶችና የሴቶች ተወካይ እንዲሁም የሃይማኖት አባቶችና ሽማግሌዎች ተሳትፈዋል።
የካቲት 24/2018 ዓ/ም
በቤት ውስጥ የሚወልዱ እናቶችን ቁጥር በመቀነስና የወሊድ አገልግሎትን ለማሻሻል በጤና መድን እና በንፅህና አጠባበቅ ላይ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለፀው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት በሀይጅንና ሳኒቴሽን የአከባቢ ጤና አጠባበቅ
ዙሪያ የንቅናቄ መድረክ በዛሬው በካሄደበት ወቅት ነው።
የዕለቱ የመወያያ ሰነድ ሀይጅን እና ሳኒቴሽን ስራ ሂደት ባለ ሙያ በአቶ ከድር ኸይሩ እና የእናቶችና ህፃናት ስራ ሂደት ባለ ሙያ በአቶ ሚፍታ መቻል ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓበታል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ዋና አስተዳደር አቶ ሚፍታ ሁሴን በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት
እንደተናገሩት "ጽዱ አከባቢ ጽዱ ኢትዮጵያ" እንደ ሀገር ከተቀመጡ ኢኒሼቲቮች አንዱ መሆኑን ጠቁመው ይሄንንም ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።
ከአይነ ምድር የጸዳ መንደር በማረጋገጥ በሽታን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል ስራ በመሆኑ የወረዳው ማህበረሰብ የተጀመረው የተሻሻሉ መጸዳጃ ቤቶች ተጠቃሚነት ለማስቀጠል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።
መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ከሚንቀሳቀስባቸው ተግባራት የጤናው ዘርፍ አንዱ መሆኑን የገለጹት አቶ ሚፍታ ሀገራችን በሽታን አስቀድሞ የመከላከል ፖሊሲ ቀርጾ ወደ ተግባር በመግባት መላው የህዝብ በማነቃነቅ የአካባቢና የግል ንጽህና የጋራና የግል መፀዳጃ ቤት በመገንባት ፣ንጹህ መንደር በመፍጠር አንደሚገባ ተናግረዋል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ በበኩላቸው ንፁህ አከባቢ መፍጠር አንዱ የፓርቲያችን ተልእኮ መነሻ በማድረግ ከአይነ ምድር ንፁህ መንደር አከባቢዎችን እየተመረቁ መሆኑን ገልፀው የመንገድ ዳር፤የመንግስት ፣የሀይማኖት ተቋማትና የግል መፀዳጃ ቤቶች ደረጃቸው የጠበቁ መሆን እንደሚገባ ጠቅሰው በየደረጃው ያሉ የቀበሌ ባለድርሻ አካለት ግምባር ቀደም በመሆን ማጤማን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል ።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ጤና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም አብራር ከመንግሥት ኢኒሼቲቭ ከሆነው አንዱ ንፅህና አከባቢ መፍጠር መሆኑ ገልፀው ከዚህ በፊት ከአይነ ምድር ነፃ ብለን ያስመረቅናቸው መንደሮች ተመልሰው ወደ ቀድሞ ቦታቸው እየተመለሱ ስለሆነ የተሰጣቸው እውቅና ማስቀጠል እንደሚገባቸው አስታውሰው የመንገድ ዳር መፀዳጃ ቤት እየተተወ የመጣ ተግባር በመሆኑ ተግሩን እንደ አዲስ ማነሳሳት ያስፈልገዋል ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም የእናቶች ማረፊያ ቤቶች ያላዘጋጁ ጤና ጣቢያዎች ለማሰራት ዝግጁ መሆን እንደሚያስፈልግ እና እንደ ተቋም የግብዓት እገዛ እንደሚያድርጉ ገልፀው ከማጤማ ሀብት አሰባሰብ በአለን አጭር ጊዜ ተቀናጅቶ በመስራት ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ አካላት እንደገለፁት የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥና የመድሃኒት አቅርቦት ማሻሻል እንደሚገባ፣የመጤማ መረጃ አያያዝ ውስንነት ፣ለነፍሰ ጡር እናቶች የባለሙያዎች ክትትል ጉድለት መኖሩን የገለጹት ተሳታፊዎቹ በቀሪ ቀናት መጤማን ለማሳካት በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።
በመድረኩ የወረዳው አመራሮች ፣ የጤና ባለሙያዎች ፣ የቀበሌ አመራሮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የካቲት 24/2018 ዓ/ም
ባለፉት ዓመታት ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራትን ማከናወኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ገለጹ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር" !!!
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለ7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ ማኒፌስቶና የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር ተካሄደ።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለጹት ባለፉት ዓመታት ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ በርካታ ተግባራትን አከናውነዋል ብለዋል።
በባለፉት የለውጥ ዓመታት ከፓርቲያችን ፕሮግራሞችና ማኒፌስቶዎች የታቀዱ በኢኮኖሚው፣ በማህበራዊ፣ በፖለቲካው እና በውጭ ግንኙነት ዘርፎች በርካታ የሚቆጠሩ ስኬቶች ማስመዝገብ መቻሉ አብራርተዋል።
በወረዳችን ባለፉት የለውጥ አመታት በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ማለትም የመንገድ መሰረተ ልማት፣በጤና ፣በትምህርት ፣በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በሌሎችም ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ተጨባጭ የሆኑ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል
በ2018 ዓ/ም የሚካሄደው 7ኛ ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ በማከናወን መጪው ጊዜ ከብልጽግና ጋር ብሩህ ይሆን ዘንድ በተደመረና በተሰናሰለ መልኩ ስራዎች መስራት እንደሚገባ አቶ ሚፍታ መልዕክታቸው አስተላልፈዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ የብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር ፈታኝ ወቅትን በጽናት በመወጣት አገራዊ አንድነትን ለማምጣት እየተጋ ያለ ፓርቲ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።
የብልጽግና ፓርቲ የሚመራው የመደመር መንግስት ለሀገራችን ዲሞክራሲያዊ ዕድገት መሰረቱ ሀገር በቀል ዲሞክራሲ አሳቤዎችን ማሳደግና በመግባባት ላይ የተመሰረተ አዲስ የፓለቲካ ባህል ለመገንባት ጽኑ እምነት አለው እና ለዚዚሁ እምነቱ ቀን ከለሌት የሚተጋ ፓርቲ ነው ያሉት ሃላፊው:
የብልጽግና ፓርቲ ከሀሳብ ወደ ተግባር የተሸጋገረ ፓርቲ መሆኑንም ገልጸዋል።
በተደራጀ አቅም የአንድነት ተምሳሌት የሆነውን የስንዴ ነዶን በመምረጥ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ መላው አመራራችንና አባላችን ሚናውን ሊወጣ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል ።
ብልጽግና ፓርቲ እንደ ሀገር በርካታ ተጨባጭ ለውጦችን ያስመዘገበ እና የትናንት ስብራቶችን ማከም ብቻ ሳይሆን የነገንም መዳረሻ በመተለም በዓለም የተመሰከረለት ብልጽግና ለማምጣት አቅዶ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
የመደመር ተምሳሌት የሆነውን የብልጽግና ፓርቲ የምርጫ ምልክት የ"ስንዴ ነዶ" በመምረጥ የተጀመረውን ልማት እንዲያስቀጥሉ ለህዝቡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የካቲት 22/2018 ዓ/ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከሼሽት ማዴ- አመቶ መንገድ የዳገት ቆረጣ እና የአፈር ስራዎች ያለበት ደረጃ የመስክ ምልከታ በዛሬው እለት ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እየተገነባ ያለው ከሼሽት ማዴ- አመቶ ቀሪ የስትራክቸር እና የ8 ኪሎ ሜትር የጠጠር ንጣፍ ስራዎች የወረዳው መንግስትና የአካባቢ ተዋላጅ ባለሃብቶች በጋራ እየተገነባ የሚገኝ መንገድ ነው።
በመስክ ምልከታው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴንና የአካባቢ ተወላጅ ባለሃብቶች የተገኙ ሲሆን የተሰሩ ሰራዎች በማየት በቀሪ የጠጠር እንዲሁም ሌሎች ስራዎች ላይ በመነጋገር የጋራ አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል።
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
የካቲት 16/2018 ዓ.ም
🎤 የሕዝብ ቁጥሩ ዕድገት ከኢኮኖሚው ዕድገት ጋር
ተጣጥሞ እንዲሄድ እና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስነ ህዝብ ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፕላን ልማት ፅህፈት ቤት
ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሀል አምባ ከተማ ልዩ ስሙ ጨፌ ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ ከ7 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው ትራንስፎርመር ምትክ አዲስ ባለ 100kw ትራንስፎርመር የመግጠም ስራ በስኬት ተከናውኗል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የባህል ቱሪዝም ጽ/ቤት ለባለድርሻ አካላት የ2018 የ2ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ገመገመ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ት/ቤቶች ፅህፈት ለመምህራን የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት 30 ለሚሆኑ አቅመ ደካማ ወገኖች የረመዳን ጾም አስመልክቶ ድጋፍ አደረገ፡፡
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!!
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን "ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ"አማካኝነት
የተገነባው የመሃል አምባ ከተማ ጥልቅ የንጹህ መጠጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በማስመልከት ለመላው የወረዳችን ህዝቦች በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሳይንስ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽህፈት ቤት የ2ኛ ሩብ ዓመት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ መድረክ ማካሄዱን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የሊዝ ጫረታ ማስታወቂያ
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሀል አምባ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ በተሠጠው ተግባርና ሀላፊነት ለንግድና ለመኖሪያ የሚውሉ ቦታዎች በሊዝ ጨረታ አወዳድሮ ለማስተላለፍ ዝግጁቱ አጠናቆ ተወዳዳሪዎችን ማወዳደር ይፈልጋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 የመንግስት የተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ በማስተካከል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የካቲት 21/2018 ዓ/ም
የሕዝብ ቁጥሩ ዕድገት ከኢኮኖሚው ዕድገት ጋር
ተጣጥሞ እንዲሄድ እና የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስነ ህዝብ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለፀው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፕላን ልማት ፅህፈት ቤት ከባለድርሻ አካላት በተገኙበት የግዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ባካሄደበት ወቅት ነው።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የፕላን ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘይነብ ወራቄ እንደገለፁት በማህበረሰቡ ውስጥ የሚካሄዱ ማህበራዊ ጉዳዮችን፣ ባህል፣ ትምህርት፣ ጤና፣የወጣቶች በክህሎትና ስነ-ምግባር በማነጽ የልማት እድል አድርጎ መጠቀም እንደሚገባ ገልፀዋል።
የዕለቱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በፅ/ቤቱ የስነ ህዝብ ስራ ሂደት ባለሙያ በአቶ መሀመድ ከድር ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል።
ከውይይቱ ከተነሱ ሀሳቦች መካከል በትምህርት ቤቶች
በተለያዩ ጉዳዮች ግንዛቤ እየተፈጠረላቸው መሆኑ ፤ሪፖርት ተደራሽ ከማድረግ አንፃር ውስንነት መኖሩን ፤ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች በስነ ህዝብ ክበብ አማካኝነት የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት እየተሰራ መሆኑ እና በትምህርት ቤቶች የስነ ህዝብ ክበብ አባላት መለየታቸው ያሚሉት ይገኙበታል
የፅ/ቤቱ የስነ ህዝብ ስራ ሂደት ባለሙያ አቶ መሀመድ ከደር የስነ ህዝብ ዋና አላማው ብቁ ዜጋ መፍጠር መሆኑ ገልፀው በትምህርት ቤቶች በክበቡ እየተሰሩ ያሉ ሰራዎች መኖራቸውና የክበቡ ተጠሪዎች ባላቸው ጊዜ በስነ ህዝብ ላይ መስራት እንዳለባቸው አስታውሰው መምህራን በስልጠናው የቀሰሙትን እውቀት መነሻ በማድረግ በትምህርት ቤታቸው የስነ ህዝብ ክበብ ከዕቅድ ጀምሮ የተስሩ ስራዎች በፋይል ከማደራጀት ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እስከ መላክ ያለውን ስራ በትኩረት ሊስራበት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ።
ለተነሱ ሀሳብ አስተያየት ምላሽ እና ማብራሪያ የሰጡት
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የፕላን ልማት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘይነብ ወራቄ በበኩላቸው የክበቡ ተጠሪዎች ከትምህርታቸው ጎን ለጎን ለክበቡ ሁሉም ተጠሪ በወጥነት እና ተመሳሳይ ስራ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበው ሪፖርቶችን ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ እና አባል ተማሪዎች በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ መፍጠር እንዳለባቸው ጠቅሰው ክበቡ በሁሉም ዘርፍ ተያያዥነት ያለው በመሆኑ ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንደለበት እና በየወሩ አባሎቻቸው ማወያየት እንደሚገባቸው አሳስበዋል ።
በመጨረሻም የህዝብ ቁጥሩ እድገት ከኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተጣጥሞ መሄድ ካልቻለ በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በጤናና በግብርና እንዲሁም በሌሎች መስኮች የሚያሳድረው ጫና ከፍተኛ በመሆኑ የስነ ህዝብና ልማት ችግሮችን ቀርፎ የወረዳውን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን ወስዶ መረባረብ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በመድረኩ የትምህርት ቤቶች የስነ ህዝብ ክበብ ተጠሪ መምህራን እና ባለ ድርሻ አካላት ተሳታፊ ሲሆኑ በክበባቸው የተሰራ ስራ ሪፖርት በማድረግ የተሻለ ተሳትፎ ላደረጉት መምህራን የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።
የካቲት 21/2018 ዓ/ም
ጉራጌ ዞን በክልላዊ የስፖርት ውድድሮች 177 ሜዳለያዎችን በመሰብሰብ በጠቅላላ ውድድር አንደኛ ደረጃ ሆኖ ማጠናቀቁ የዞኑ ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ረሻድ በተገኙ ውጤቶችና ዞኑ የእግር ኳስ ሻፒዮን በመሆኑ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፏል።
በጉራጌ ዞን አስተናጋጅነት በወልቂጤ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 3ኛው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና፣ የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ፍፁም ሠላማዊ በሆነ እና በደማቅ ሁኔታ በጉራጌ ሁለንተናዊ አሸናፊነት ፍፃሜውን በማግኘቱ በህዝቡ ከፍተኛ ደስታ ፈጥሯል።
በዚህ ውድድር የጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የትኛውም ሀገራዊ ስፖርታዊም ሆነ ሌሎች ኩነቶን ተቀብሎ ማስተናገድ የሚችል እንግዳ ተቀባይ፣ ሰላም ወዳድ ማህበረሰብ ያለበት መሆኑን በተግባር ማሳየት ተችሏል።
በውድድሮቹ ተሳትፎ በማሳደግ የጉራጌን ህዝብ የሚመጥን ድሎች በማስመዝገብ የዘመናት የህዝቡ መሻት ተሳክቶና ጥያቄ ተፈትቶ በሁሉም የስፖርት ዘርፍ የጉራጌን አሸናፊነት የተረጋገጠበት ነው ብለዋል አቶ ሙራድ።
ለአብነትም የጉራጌ ዞን የእግር ኳስ ቡድን ከ13 አመታት በኃላ ዘንድሮ ሻፒዮን መሆኑ እጅግ ለየት ያለ ደስታ የሚፈጠር ነው።
አቶ ሙራድ አክለውም በጠቅላላ ውድድሮች በብቃት በመሳተፍ ውድድሩን በከፍተኛ ውጤት ለማጠናቀቅ ታቅዶ በቂ ቅድመ ዝግጅትና ስልጠና በመሰጠቱ ውጤት ማምጣት ተችሏል ነው ያሉት።
በ2017 ዓ.ም ክልላዊ ልዩልዩ ስፖርቶችና የባህል ስፖርት ውድድር በ14 ውድድሮች ብቻ ተሳትፎ በማድረግ 61 ሜዳሊያዎችን አምጥቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
ዘንድሮ ግን በ17 ዘመናዊ ፣በ10 ባህላዊ በድምሩ በ27 ስፖርቶች በመሳተፍ 77 የወርቅ፣62 ብር እና 38 ነሀስ በድምሩ የ 177 ሜዳሊያዎች ጉራጌ ዞን አሸናፊና ተሸላሚ ሆኗል።
የ26 ዋንጫዎች አሸናፊ በመሆን በጠቅላላ ውድድሩን ጉራጌ ዞን አንደኛ ደረጃ ሆኖ በማጠናቀቅ የጉራጌ ማህበረሰብ የሚገልጽና የሚመጥን ውጤት መጥቷል።
በጠቅላላው በውድድሩ በተመዘገቡ ውጤቶች በተለይም ታሪካዊው የእግር ኳስ ዋንጫ አሸናፊ መሆናችን የዞኑ መንግስትና እና ህዝብ ባደረገው ድጋፍና ቁርጠኝነት የመጣ ውጤት ስለመሆኑ አቶ ሙራድ አስገንዝቧል።
የውጤቱ መምጣት ስፖርቱ ህዝባዊ መሰረት እንዲኖረው እና የስፖርት ልማት ዘርፉ እንዲነቃቃ የጎላ ሚና አለው ሲሉ ተናግረዋ።
በእለቱም ለጉራጌ ዞን እግር ኳስ ቡድን በዞኑ አስተዳደር የተበረከተለት ሽልማት በቀጣይ የአሸናፊነት ወኔ እንዲፈጠር የሚያደርግ፣ጠንካራ መሰረት የሚጥል መሆኑን አመላክተዋል።
ውድድሩ በውጤታማነት እንዲጠናቀቅ ላደረጉ የጉራጌ ዞን እና የወልቂጤ ከተማ የውድድር አስተናጋጅ ኮሚቴ አባላት፣ የጸጥታ አካላት፣ስፖርተኞች ፣በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች፣ ደጋፊዎች፣ለዞኑና ለወልቂጤ ከተማ ማህበረሰብ፣ የሚዲያ አካላት ሌሎች የበኩላቸው ጥረት ላደረጉ ለባለድርሻ አካላት ሁሉም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በጠቅላላው በ3ኛው የማ/ኢትዮጵያ ክልል የልዩ ልዩ ስፖርት ሻምፒዮና እና የባህል ስፖርት ፌስቲቫል አስተናጋጁ ጉራጌ ዞን የተመዘገበው ሁለንተናዊ ውጤት ለመላው የጉራጌ ህዝብ እንኳን ደስ አለን ፣እንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አቶ ሙራድ አስተላልፏል።
የካቲት 20/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሀል አምባ ከተማ ልዩ ስሙ ጨፌ ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ ከ7 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው ትራንስፎርመር ምትክ አዲስ ባለ 100kw ትራንስፎርመር የመግጠም ስራ በስኬት ተከናውኗል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሀል አምባ ከተማ ልዩ ስሙ ጨፌ ተብሎ የሚጠራዉ አካባቢ ከ7 ወራት በላይ ተቋርጦ የነበረው ትራንስፎርመር በህብረተሰቡ ዘንድ ትልቅ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ሆኖ መቆየቱ ይታወቃ ይህንን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በተደረገው ጥረት ዛሬ የካቲት 20/ 2018 ዓ/ም ተቀጥሎ በነበረው ምትክ አዲስ 100kw ትራንስፎርመር የመግጠም ስራ በስኬት ተከናውኗል።
እንኳን ደስ አለን ደስ አላቹ!!!
