925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ90 ቀን እቅድ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ተገመገመ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የወጡ መመሪያዎችን ለመተግበር ሁሉም አካል መተባባር እንደሚገባው የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራ ምክርቤት የ2017 በጀት አመት ማጠቃለያና የ2018 እቅድ የምክክር መድረክ "ክህሎት መር ስራ እድል ፈጠራ ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል በወልቂጤ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በአንድ ቀን 700 ሚሊየን ዛፎችን ለመትከል ያቀድነው ዕቅድ ከታሰበው በላይ ተሳክቷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመትከል ማንሰራራት"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼"በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ- ግብር በሠፍቶ ቀርሳ ቀበሌ ዙጋርት ንኡስ ተፍሰስ ላይ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2017 በጀት አመት የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራ እና አገልግሎት ለእስረኞች እና ለመሀበረሰቡ መድረጉን አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼አረንጓዴ አሻራ "በመትከል ማንሰራራት" በ7ኛ ዓመት 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር
ሐሙስ - ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን በጋራ ይተክላሉ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ኮንስትራክክሽን እና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ከወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር በመሠረታዊ የኮምፕዩተር መሠረታዊ ዕውቀት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘንድሮ ዓመት በሚከናወነው "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ- ግብር ከ2 መቶ 73 ሺህ በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞች እንደሚተከል የወረዳው ግብርና ጽ/ ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉረጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ተቋማት የ2017 በጀት አመት የ12 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት ግምገማ መድረክ ተካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ከዳር ማድረስ እንደሚገባ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼አሚን አጠቃላይ ሆስፒታል በጉራጌ ዞን ገዳበኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለእናቶችና ህፃናት ክፍል የሚውሉ ግምታቸው 620,000(ስድስት መቶ ሀያ ሺህ) ብር የሚደርስ የህክምና ቁሳቁሶችንና መገልገያዎችን ድጋፍ አደረገ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም የወረዳውን የክረምት በጎ ፈቃድ አስመልክቶ መልእክት አሰላልፈዋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 73 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል ማለፋቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
👉🏼በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጥላሞ ቀበሌ ኩታገጠም የመኸር ድንች ማሳ በምስል፦
ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ90 ቀን እቅድ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ተገመገመ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ90 ቀን የእስካሁን እቅድ አፈጻጸም የስራ ሪፖርት ቀርቦ የወረዳው አጠቃላይ አመራር ባለበት ተገምግሟል።
በግምገማው ወቅታዊ ተግባራትን በተለይም የወጣቶች ስራ እድል ልየታና ስምሪት ፣ ብድር ስርጭት ፣ አመላለስና ቁጠባ፣ የክርምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች ፣ የሁሉም ዘርፍ የግብርና ስራዎች ፣ የፋይዳ መታወቅያ ምዝገባ ፣ የECODRS አፈፃፀም እንዲሁም ሌሎችም የፓርቲና የመንግስት ስራዎች አፈፃፀም ላይ ትኩረት በማድረግ በዝርዝር ተገምግሟል።
የጉራጌ ዞን የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊና የወረዳው ደጋፊ አመራር አቶ ሙረድ ያሲን ባለፉት ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም የታዩትን ጉድለቶችን በመለየት በቀጣዮቹ ወራት ዕቅድ ለማከናውን ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል ።
በቀሩት ወራት ውስጥ የተሻለውን አፈጻጸም ለማስመዝገብና የ90 ቀን ዕቅድ ከግብ እንዲደርስ የወረዳው አመራር ከቀበሌ አመራር ጋር በጋራ በመቀናጀት ከመቸውም ግዜ በበለጠ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ሙራድ አክለው ገልጸዋል።
በመጨረሻም አቶ ሙራድ የህብረተሰቡን ዘላቂ ጥቅምና የወረዳውን ብልፅግና ሊያረጋግጥ በሚችል መልኩ ወቅታዊ ስራዎችን በመስራት ግንባር ቀደም ሚናውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች ከወረዳው ተጨባጭ ሁኔታ አንዳንድ አስተያየቶች ተነስተዋል።
በመንግስትና በፓርቲ የ90 ቀናት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ በተነሱ ነጥቦች ላይ ከመድረክ አቅጣጫዎች በመስቀመጥና በመገምገም ተጨማሪ ስምሪት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
በግምገማ መድረኩ የጉራጌ ዞን የስራ እድል ፈጠራ እና ኢንተርፕራይዝ ልማት መምሪያ ኃላፊና የወረዳው ደጋፊ አመራር አቶ ሙረድ ያሲን፣የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ እና ሌሎች አስተባባሪ አካላት እንዲሁም ጠቅላላ የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል ።
ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም
በትራንስፖርት ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የወጡ መመሪያዎችን ለመተግበር ሁሉም አካል መተባባር እንደሚገባው የጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው ተቋሙ ከወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በትራፊክ ደህንነት ዙሪያ ለአሽከርካሪዎች የተሀድሶ ስልጠና በመሀል አምባ እና ኢንጌ ከተሞች በሠጠበት ወቅት ነው።
መድረኩን ያስጀመሩት የወረዳው የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ሊሊ ሙደሲር እንደገለፁት የስልጠናው ዋና ዓላማ በሰውና በንብረት ላይ የሚደርስ ጉዳት መቀነስ እንደሆነ አንስተው የትራንስፖርት ዘርፉ በአዲሱ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ መሠረት ለህዝብ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
አሽከርካሪዎች በስነ-ምግባር ታንፀው የትራንስፖርት ህግና ደንብ በሚገባ ተረድተው በማሽከርከር የንፁሃንን ህይወት እና ንብረት ማዳን እንዳለባቸው ጠቅሠው በዚህ ስልጠና ሰርተፊኬት ያልያዘ ማንኛውም አሽከርካሪ ማሽከርከር እንደማይችልና ሁሉም አሽከርካሪዎች ስልጠናው በአግባቡ በመሰልጠን የትራፊክ ህጎችና ደንቦች ጠንቅቆ በማወቅ ከትራፊክ አደጋ እራሱንና ማህበረሰቡን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
ለስልጠና የተዘጋጀውን ሠነድ የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የመንገድ ደህነንት ባለሙያ የሆኑት አቶ ጌጤ ገሰሰ እና ዋና ሳጅን ታደለ ብርሃኑ አማካኝነት የቀረበ ሲሆን በሁለቱም ከተማ የሚገኙ የመኪና፣ ባጃጅና የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ሐምሌ 25/2017 ዓ.ም
የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራ ምክርቤት የ2017 በጀት አመት ማጠቃለያና የ2018 እቅድ የምክክር መድረክ "ክህሎት መር ስራ እድል ፈጠራ ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል በወልቂጤ ከተማ ማካሄድ ጀመረ።
የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን የወጣቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ገልፀዋል።
የወጣቶች የሥራ አጥነት ችግር ማቃለልና የህብረተሰቡ የኑሮ ውድነት ጫና መቀነስ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በየደረጃዉ ያለዉን የሥራ አጥነት ችግር ለመቀነስ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደተግባር መገባቱን አቶ ሙራድ አስገንዝበዋል።
ይህንን ተከትሎ ምክርቤቱ በ2017 በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በመገምገም በቀጣይ በጀት አመት የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል።
በመድረኩ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል፣ የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እና ሌሎች የዞን፣ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የኦሞ ባንክ፣ የልማት ባንክ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ፣ የደቡብ ካፒታል የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
ሐምሌ 24/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመትከል ማንሰራራት"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተካሄዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በመትከል ማንሰራራት"በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በሠፍቶ ቀርሳ ቀበሌ ዙጋራት ንኡስ ተፍሰስ ላይ በዛሬው እለት ተካሄዷል።
በዚህ ወቅት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለፁት የብልፅግና መንግስት ኢኒሼቲቭ የአረንጓዴ ልማት "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ እንደ ሃገር 700 ሚሊዮን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሚሠጡ ችግኞች ለመትከል ግብ ተጥሎ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሠው ዛሬ ችግኝ ብቻ ሳይሆን በህብረተሰቡ ዘንድ ፍቅር፣ አንድነትና መዋደድ መትከል ስለመቻሉ አብራርተዋል።
የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ ባለፉት ዓመታት በወረዳ ደረጃ በተሠሩ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን የተጎዱ ስፍራዎች ማገገማቸውንና ወደ ምርታማነት መቀየራቸውን በመግለፅ ዛሬ በሠፋቶ ቀርሳ እና ዋቦን ቀበሌዎች ላይ የአንድ ጀንበር መርሃ ግብር በርካታ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው ህብረተሰቡ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን የተከሉትን መንከባከብና የፅድቀት መጠኑን ማሳደግ ይኖርበታል ብለዋል።
የጉራጌ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተር ፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙራድ ያሲን ባስተላለፉት መልዕክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ( ዶ/ር ) ኢኒሼቲቭ እየተከናወነ ያለው የአረንጓዴ አሻራ ስራ በሃገሪቱ የአየር ንብረት ኢኮኖሚ መስክ ውጤታማ ስራ ተከናውኗል ብለዋል።
በአንድ ጀምበር ተከላ መርሃ-ግብር በሃገር ዓቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን ችግኞች በተሳካ መልኩ መተከላቸውን አውስተው ለተከላው መሳካት የበኩላቸውን ሁሉ ለተወጡ አካላት ያመሰገኑ ሲሆን በዚህ ስራ ህዝቡ አንድነትንና ፍቅርን የተከለበት ነው ያሉት አቶ ሙራድ ህዝቡ የተተከለውን ችግኝ በዘላቂነት መንከባከብ እንደሚገባው አሳስበዋል።
የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ደንና አካባቢ ጥበቃ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ አ/ሃፊዝ በዕለቱ በሠፋቶና ዋቦን ቀበሌዎች በተደረገ እወጃ ከ27 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን 99 ሄ/ር መሬት ላይ በርካታ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ስለመተከላቸው አስታውቀው የተተከሉ ችግኞች ከንክኪ በፀዳ መልኩ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።
