fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
ሐምሌ 24/2017 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ኮንስትራክክሽን እና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ከወረዳው ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ፅህፈት ቤት ጋር በመተባበር በመሠረታዊ የኮምፕዩተር መሠረታዊ ዕውቀት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የመሃል አምባ ኮንስትራክሽንና ኢንደስትሪያል ኮሌጅ ዋና ዲን ወይዘሪት ሠላማዊት ኡርባኖስ ስልጠናው በሶስት መስኮች ማለትም በመሠረታዊ ኮምፕዩተር፣ ኢንተርፕረነርሺፕ እና በካይዘን  መስኮች ያተኮረ ስልጠና ስለመሆኑ ገልፀዋል። ስልጠናው መሠረታዊ የኮምፕዩተር ክህሎት ክፍተት ላለባቸው ከየሴክተር መስሪያ ቤቱ እንዲሁም ከትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ሠልጣኞች በጠቅላላው 48 ሠልጣኞች እየተሳተፉ ስለመሆኑ ገልፀዋል። በሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ መስክ የበለፀገ ዜጋ በማፍራት በፈጠራ ስራ ዘርፍም ሆነ በቴክኒክና ሙያ ስራ ብቁ ዜጋ ማፍራት የስልጠናው ዋና አላማ መሆኑን ወይዘሪሪት ሠላማዊት ኡርባኖስ ተናግረዋል። አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች በሠጡት አስተያየት የስልጠናዉ መድረክ ተጨማሪ ግንዛቤን እየፈጠረላቸው እንደሚገኝ ጠቅሰው መሰል ግንዛቤ መድረኮች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ፕሬስ ሪሊዝ በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘንድሮ ዓመት በሚከናወነው "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ- ግብር ከ2 መቶ 73 ሺህ በላይ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞች እንደሚተከል የወረዳው ግብርና ጽ/ ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው ምክትል አስተዳደሪ እና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ከድር መርጋ እንደገለፁት በወረዳው በዘንድሮው የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር "በመትከል ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሐምሌ 24 በአንድ ጀምበር በሠፍቶ ቀርሳ ቀበሌ ዙጋርት ንኡስ ተፍሰስ እና ዋቦን ቀበሌ ፏን ንዑስ ተፍሰስ ላይ ከ273 ሺህ በላይ ችግኝ ለመትከል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። በእለቱ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለቸው ፓይነስ ፓቹላ፣ ቀርከሃ፣ የፈረጅና የአበሻ ፅጅ ፣ ግራቪሊያ፣ ወይራ፣ ጃካራንዳ፣ አቮካዶ፣ ብና እና አኘል ችግኞች እንደሚከተል ሲሆን 99 ሄክተር መሬት የሚሸፍንና በተከላው ከ8 ሺህ በላይ የህብረተሠብ ክፍሎች የሚሳተፉ መሆናቸውን አቶ ከድር አክለው ገልጸዋል። በመጨረሻም አቶ ከድር መርጋ ባስተላለፉት መልዕክት ባስተላለፈው መልዕክት የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ እቅድ የተሳካ እንዲሆን ሁሉም የህብረተሠብ ክፍል በነቂስ በመወጣት የአረንጓዴ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። መርሃ-ግብሩ በነገው እለት 24/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሠዓት ጀምሮ በደማቅ ኘሮግራም ለማካሄድ ቅድመ-ዝግጅት መጠናቀቁን ተመላክቷል።

ሐምሌ 24/2017 ዓ ም በጉረጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ተቋማት የ2017 በጀት አመት የ12 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ማጠቃለያ ሪፖርት ግምገማ በዛሬው እለት እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የወረዳው የሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት የወረዳው ፕላንና ልማት ጽ/ቤት የልማት እቅድ አስተባባሪ አቶ አብድልከሪም ናስር ያቀረቡ ሲሆን ጥልቀት ያለው ውይይት እየተካሄደ ይገኛል። መድረኩ በ2017 በጀት የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል። የግምገማ መድረኩ ላይ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እና የወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል። ተጨማሪ መረጃዎችን ይዘን እንመለሳለን!!!

ሐምሌ 23/2017 ዓ.ም የመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2017 በጀት አመት የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራ እና አገልግሎት ለእስረኞች እና ለመሀበረሰቡ መድረጉን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የመሀል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የ2017 በጀት አመት የክረምት በጎ ፍቃድ ነፃ የጤና ምርመራ እና አገልግሎት ፖሊስ ጣቢያ ለሚገኙ እስረኞች እና ለመሃል አምባ ከተማ ማህበረሰብ የስኳር እና የደም ግፊት ነጻ ምርመራ በስፍራው በመገኝት አካሄዷል።

1 ቀን ቀረው አረንጓዴ አሻራ "በመትከል ማንሰራራት" በ7ኛ ዓመት 700 ሚሊዮን ችግኞች በአንድ ጀምበር ሐሙስ - ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮጵያውያን በጋራ ይተክላሉ። የክልላችን ህዝብም በዚህ ታሪካዊ ቀን አሻራዉን ለማሳረፍ ተዘጋጅቷል። #አረንጓዴዐሻራ #GreenLegacy #Ethiopia

ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ከዳር ማድረስ እንደሚገባ ተገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለፀው የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት የ2017 ዓ.ም 4ኛ ሩብ ዓመት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ መድረክ ዛሬ ባካሄደበት ወቅት ነው። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አባስ ለሙ የመክፈቻ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ፅህፈት ቤቱ ሶስት ዋና ዋና የስራ ሂደቶችን አጣምሮ በመያዝ በመንግስትና ህዝብ የተጣለበትን ሃላፍትና በመወጣት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የሆነ የኮሚኒኬሽንና ህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በመከወን የህብረተሰቡን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሚደረገዉን ርብርብ እያገዘ እንደሚገኝ ገልፀዋል። የፅህፈት ቤቱ ልማት ዕቅድ ባለሙያ ወይዘሪት በዛሽ መህዲ የ2017 ዓ.ም የ4ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይትና ምክክር ተደርጓል። ተሳታፊዎች ካነሷቸው ሃሳብና አስተያየቶች መካከል ተቋሙ ያሉትን የኤሌክትሮኒክስ፣ ህትመትና ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች በመጠቀም እያከናወነ ያለው የህዝብ ግንኙነት ስራ አበረታች ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን በቀጣይ ጊዜያት ተጠናክሮ ሊጎለብት  እንደሚገባው፣ ሴክተሩን በሰው ሃይልና በግብዓት ማስታጠቅ እንደሚያስፈልግ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ከማሳደግ አኳያ ሁሉም የድርሻውን መጫወት እንዳለበት ተሳታፊዎቹ አንስተዋል። ተሳታፊዎች ላነሱት ሃሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡት አቶ አባስ ለሙ ባስተላለፉት መልዕክት ከመድረክ የተገኙ ግብዓቶችን የዕቅድ አካል በማድረግ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደሚሰራ ጠቁመው ተቋሙ የያዛቸውን ግቦች በሚፈለገው ደረጃ ማሳካት እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ አካላት የሚጠበቅባቸውን ሃላፍትና ከመወጣት በተጨማሪ ቅንጅታዊ አሰራራቸውን አጠናክረው ሊያስቀጥሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ሐምሌ 21/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 73 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል ማለፋቸውን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት አስታውቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አለማየው ኬኔ የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ እንዳስታወቁት ዘንድሮ በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እንደ ወረዳ ወ=-683 ሴ = 768 ድ=1451 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸውን ጠቅሠው ወ=495  ሴ=564  ድ=1059 ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል ማለፋቸውን ገልፀዋል። በ2016 ዓ.ም ከነበረው ውጤት የዘንድሮ 25% መሻሻል የታየበት በመሆኑ 2017 ዓ.ም የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ዓመት ነው ብለዋል። አጠቃላይ የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ ትምህርት ቤቶች መካከል 2016 ዓ.ም 5 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ሲሆን በዘንድሮ አመት 3 ትምህርት ቤት ብቻ ምንም አይነት ተማሪ ያላሳለፈ መሆኑ በመግለፅ 19 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ማሳለፍ መቻላቸውን ገልጸዋል። ባለፉት ዓመታት በአዲሱ ትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ የፈተና አስተዳደር ስርዓት በየደረጃው በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ መደረጉ ኩረጃን ማስቀረት በመቻሉ እንዲሁም እንዲሁም በ2016 የትምህርት ውጤት ስብራት በሚል መሪ ሃሳብ በየደረጃው የተካሄዱ ውይይቶች በተያዘው አመት ካለፉት ዓመታት አንጻር በተማሪዎች ውጤት መሻሻል እንዲኖር አድርጎል ያሉት ኃላፊው በዘርፉ የተያዙ ግቦች ለማሳካት በጠንካራ ቅንጅት መስራት እንዳለበት አስገንዝበዋል ። ተማሪዎች መለያ ቁጥራቸውን https://ce.ministry.et/ ሊንክ በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ኃላፊው አስታውቀዋል።