fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
923
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+37 روز
+730 روز
آرشیو پست ها
ህዳር 25/2018 ዓ.ም ጥራት ያለውና ቀልጣፍ የጤና አገልግሎትን በብቃት ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ በመፍጠር ረገድ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ገለጹ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የአበዘት ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ/ም የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈፃፀም የቦርድ አባላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት ተገምግሟል። የቦርድ አባላት በአበዘት ጤና ጣቢያ በመዞዞር በአገልግሎት አሰጣጡ ዙሪያ፣ለእናቶች ማረፊያ የሚሆን በመኸር የለማ የገብስ ሠብል ምርት አሰባሰብ እንዲሁም በኢትዮጵያ መድሀኒት ድርጅት ድጋፍ የተደረጉ የህክምና መገልገያ ቁሳቁሶችን የመስክ ምልከታ አድርገዋል። የአበዘት ጤና ጣቢያ ኃላፊ ወ/ሮ ላምሮት ያሪሞ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በቀረበው ሪፖርት መነሻ በማድረግ የቦርድ አባላት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። የቦርድ ውይይቱን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የጤና ጣቢያው የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሚፍታ ሁሴን በዚህ ወቅት የህብረተሰቡን ጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተከናወኑ ያሉ የጤና ስራዎችን በቅንጅት መሠረት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም ከአገልግሎት ጥራት ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ችግሮችን በልዩ ትኩረት መቅረፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ የባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችና የስነ ምግባር ችግሮች፣ብልሹ አሠራሮች ማስተካከል እንደሚገባ ጠቅሠው በ1ኛ ሩብ ዓመቱ ክፍተቶችን ማረም እንደሚያስገልግ የቦርድ አባላት በአስተያየታቸው አስታውቀዋል።

ህዳር 23/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው እለት መገምገሙን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የዜጎች ቻርተር እና የህዝብ ክንፍ አባላት በተገኙበት ውይይት በዛሬው እለት አካሄደ። በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በጽ/ቤቱ የልማት እቅድ ባለሙያ አቶ አንዋር መሃመድ አማካይነት ቀርቡ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተው ውይይት ተደርጓበታል። ውይይቱ ተሳታፊዎች የቀረበውን ሪፖርት መነሻ በማድረግ እንደተናገሩት ሰፊ የሆነ ተደራሽ የገጠር መንገድ እየተሠራ መሆኑ የሚበረታታ እንደሆነ፣ ፣የትራንስፖርት ክፍያ በተገቢው ቁጥጥር ከማድረግ አንጻር፣የተሽከርካሪ ፍጥነት በተለይ ባለ ሁለት እግር፣ ከተቋማት ጋር ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራሮች ሊኖሩ ይገባል የሚሉት ተሳታፊዎች ከነሷቸው ሃሳብና አስተያየቶች ይገኙበታል። የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ረጋ ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሠጡበት ወቅት እንዳሉት ከመድረኩ የተገኙ ግብዓቶች ተቋሙ ወስዶ እንደሚሠራ ገልጸዋል። አክለውም ህብረተሰቡ የተዘረጉ የመሠረተ ልማት አውታሮችን በባለቤትነት ወስዶ መጠበቅና መንከባከብ እንደሚጠበቅበት ጠቁመው የህብረተሠቡን የመንገድ ልማት ተደራሽነት ችግር ሙሉ በሙሉ ለመፍታት የተጀመረዉን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ሊያግዙ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በመጨረሻም የትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የሚተስዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በዘንድሮ አመት በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ ገልጸው ህብረተሠቡ ለተቋሙ መረጃ በመስጠት እንዲሁም የተገነቡ መነገዶችን በባለቤትነት እንዲጠብቅ አሳስበዋል። በመድረኩ ላይ የተቋማት የልማት እቅድ ባለሙያዎች ፣ የህዝብ ክንፍና የዜጎች ቻርተር አባላት፣ እና ሌሎች በላድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ህዳር 24/2018 ዓ.ም ፍትሃዊና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም ማህበረሠብ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ "እንደ አቅሜ አዋጣለሁ፣ እንደ ህመሜ እታከማለሁ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የ2017 አፈጻጸምና የ2018 የንቅናቄ መድረክ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ተካሂዷል። የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ እንዳሉት ማጤመ የህዝቡን የጤና ዋስትና ለማረጋገጥ እጅግ ወሳኝ መሆኑን በመግለፅ፣ ፍትሀዊና ቀልጣፋ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ሁሉም ማህበረሰብ የማጤመ ተጠቃሚ እንዲሆን በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባ አሳስበዋል። በዘንድሮ አመት ከማጤመ ጋር ተያይዞ የሚተገበሩ ኢኒሼቲቮች መኖራቸው የገለጹት አቶ ላጫ፣ ህብረተሰቡ በአቅሙ ደረጃ በዝቅተኛ፣በመካከለኛና በከፍተኛ ደረጃ እየከፈለ እንዲሄድ በማድረግ የማጤመ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። ማጤመን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር አስተሳስሮ በመስራት የማጤመ ተጠቃሚ አባላቶች የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ መሆን ይጠበቅባቸዋልም ነው ያሉት። ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ አባላት በማፍራት፣ ያልተመለሱ ገንዘቦች እንዲመለሱ በማድረግ፣ ዞናል ቋት በመክፈት፣አምና የነበሩ ጉድለቶች በማረምና ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ጤናው የተጠበቀ አምራች ዜጋ መፍጠር ይገባል ብለዋል። የወባ በሽታ ለመቀነስና የማርበርግ በሽታ ለመቆጣጠር የጤና ኤክስቴንሽን ተግባራት በአግባቡ መፈፀም እንደሚገባም አቶ ላጫ ተናግረዋል። የጉራጌ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀል እንደገለጹት ስራዎችን ህብረተሰቡ ተጠቃሚ በሚያደርጉ መልኩ በጥራትና በፍጥነት በመስራት አዳጊና ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ይበልጥ መትጋት እንደሚገባ መክረዋል። በጤና ተቋማት ስነ-ምግባር በተላበሰ መልኩ ማህብረሰባችን ማገልገል ይጠበቃል ያሉት አቶ አለማየሁ የማጤመ ተጠቃሚ የህብረተሰብ ክፍሎች መረጃ ተጣርቶ እንዲያዝና የድሀ ድሀ የሆኑ አካላት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስገንዝበዋል። ጤና ተቋሟት በማጤመ ምክንያት የበጀት እጥረት እንዳይገጥማቸው ማህበረሰቡ በአቅራቢያውና በዞኑ ያሉ ሆስፒታሎችን በአግባቡ መጠቀም አለበት ብለዋል። የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በበኩላቸው በዞኑ የማጤመ አፈጻጸምና የጤና አገልግሎት አሰጣጥ በየ ጊዜው እየተሻሻለ መጥቷል። ይሁን እንጂ ለህብረተሰቡ የሚፈለገው የጤና አገልግሎት ለመስጠት በቁርጠኝነት፣በቅንጅትና በኃላፊነት መስራት ያስፈልጋል። በጉራጌ ዞን ከ1ሚሊየን 127 ሺ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች የማጤመ ተጠቃሚ መሆናቸው አስታውቀው በዘንድሮ አመትም ከ3መቶ 31 ሚሊየን 3መቶ 84 ሺ 500 ብር እንደሚሰበሰብ ተናግረዋል። አቶ አየለ አክለውም የጤና ባለሙያዎችና ቤተሰቦቻቸው የማጤመ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርአት በዘንድሮ ዓመት እንደሚጀመር ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት የሆሳእና ክላስተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት አብ ዋምሾ እንደተናገሩት ጽ/ቤቱ በስሩ ያሉ መዋቅሮች በማጤመ ዘርፍ የሚሰሩ ተግባራት በመቆጣጠር ህብረተሰቡ የማጤመ ተጠቃሚ እንዲሆን ይሰራል። ከፌደራል የሚወርዱ የድጎማ በጀቶች ሳይቆራሩጡ በጊዜያቸው እንዲወርዱ በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ የጠቆሙት አቶ ምህረት አብ ማህበረሰቡ ደግሞ በአካባቢው ባሉ ጤና ተቋሟት ቢገለገል ለስራው ይበልጥ አጋዥ እንደሚሆን አስገንዝበዋል። በውይይቱ የተገኙ አካላት እንዳሉት የማህበረሰቡን ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዋነኛ አማራጭ የጤና መድህን አባል ማድረግ ነው ብለዋል። የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ለማሳለጥ ጤና ተቋማት ልዩ ልዩ ግብአት ሊሟላላቸው እንደሚገባ ተናግረው ከክልልና ከፌደራል የሚወርዱ የበጀት ፈንዶች በአግባቡ እንዲወርዱ አንስተዋል። ማህበረሰቡ የማጤመ ተጠቃሚ በመደረጉ ጤናውን በአግባቡ እንዲጠብቅ አስችሎታል ያሉት ሀሳብ ሰጪዎቹ ይሁን እንጂ ለጤና ተቋማት የሚከፈለው ገንዘብ በወቅቱና በሚፈለገው አክል መክፈል፣የኦዲት ተደራሽነት ማስፋትና የግንዛቤ ስራዎች ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል። በመጨረሻም በ2017 በማጤመ ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ላመጡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ህዳር 23/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኢንጌ ጤና ጣቢያ ስራ አመራር ቦርድ አባላት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ወቅጣጫዎች ዙሪያ በዛሬው አለት ውይይት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የኢንጌ ጤና ጣቢያ ስራ አመራር ቦርድ አባላት የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የጤና ጣቢያውን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ባሉ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። የኢንጌ ጤና ጣቢያ ኃላፊ አቶ ደበበ ንጉሴ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ አመት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በቀረበው ሪፖርት መነሻ በማድረግ የቦርድ አባላት ሰፊ ውይይት አካሂደዋል። በመድረኩ የቦርድ አባላት እንዳሉት የተገልጋይ ህብረተሰብን ፍላጎትን መሠረት ያደረገ የመድኃኒት አቅርቦት ፣የባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችና የስነ ምግባር ችግሮች እና በሌሎች ጉዳዮች ሰፊ ውይይት ተደርጎ በጥንካሬ የተለዩ ጉዳዮችን አጠናክሮ በማስቀጠል በጉድለት የተለዩትን በቀጣይ የእቅድ አካል አድርጎ ማስተካከል እንደሚገባ እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል። የቦርድ ውይይቱን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪና የጤና ጣቢያ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሚፍታ ሁሴን በማጠቃለያ ወቅት እንዳሉት የጤና ጣቢያው አገለግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ከተገልጋይ ህብረተሰብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማረም ለህብረተሰቡ ተገቢ አገለግሎት መሠጠት እንደሚገባ ገልጸዋል። ጤና ጣቢያው ላይ ያሉ ጠንካራ ስራዎችን በተሻለ መልኩ ማስቀጠልና የአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን በማጠናከር ጤናው የተጠበቀና አምራች ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚገባ አቶ ሚፍታ አሳስበዋል።

ህዳር 23/2018 ዓ.ም እያንዳንዱ ወረዳ አንድ የገጠር ኮሪደር መስራት ይጠበቅበታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "በመደመር መንግሥት የዕይታ የዘርፎች እመርታ" በሚል ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሰጡት ስልጠና፤ በቀጣይ የሚከናወኑ 'የአንድ ግቦች' ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸው፤ እያንዳንዱ ወረዳ ሞዴል የሆኑ የገጠር ኮሪደሮች መስራት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል፡፡ የወረዳ አመራሮች ሁሉንም ማስተባበር ከቻሉ እቅዱን ማሳካት እንደሚቻል ተናግረዋል፡፡ የሚመረተው ምርት እንዳይባክን በእያንዳንዱ ወረዳ አንድ የምርት ማከማቻ እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል፡፡ እያንዳንዱ ዞን አንድ የቱሪስት መዳረሻ መስራት እንዳለበት የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህም መዳረሻ የግድ በትልቁ መሆን እንደሌለበት አንስተው፤ ሁሉም ባለው እና በቀላሉ መስራት አንደሚችል ተናግረዋል፡፡ በየአካባቢያቸው ሰዎች የሚያርፉበት እና የሚዝናኑበት ስፍራዎች እንደሚያስፈልጋቸውም ጠቁመዋል፡፡ በዞናቸው ብዙ ወጪ ሳያወጡ እንደ ሀምበሪቾ ያሉ የሚታዩ ስፍራዎች መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ ለአርብቶ አደሩ አንድ የእንስሳት የጤና ማዕከል በዞን ደረጃ አስፈላጊ ስለመሆኑም በሰጡት ማብራሪያ ገልጸዋል፡፡ አንድ የመሶብ አገልግሎት እና አንድ የሽያጭ ማዕከል በከተማ መገንባት እንደሚገባም አክለዋል፡፡ በክልል ደረጃ አንድ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት እና አንድ የግብርና ማቀነባበሪ መገንባት እንደሚያስፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡ #Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #AbiyAhmedAli #corridorproject

ህደር 05/2018 ዓ.ም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሃል አምባ ጤና ጣቢያ የ2018 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት ተግባር አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ የቦርድ አባላት በተገኙበት ገመገመ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የውይይት ሰነዱን የጤና ጣቢያ ስራአስኪያጅ አቶ ጳውሎስ ጫኔ የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪና የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደተናገሩት ማህበረሰቡን በጤናው ዘርፍ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የጤና ተቋማትን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በተቋሙ ላይ ያሉ የሰው ሀይሎችን በአግባቡ በመጠቀምና ጤናጣቢያውን ሊያሻግሩ የሚችሉ መንገዶችን ፈጥሮ መሄድና የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። በበሽታ ቅድመ-መከላከል፣ በአክሞ ማዳንና በተላላፊ በሽታዎች ህክምና እና በመሠረታዊ አገለግሎት አሰጣጥ ዙሪያ እንዲሁም ግንዛቤ ከማስጨበጥ አንጻር ጤና ጣቢያው ለህብረተሰቡ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት አለበት ያሉት አስተዳዳሪው ለውጤታማነቱ መንግስት አስፈላጊው የሆነውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊ የቦርድ አባላት በተቋሙ የውስጥ ገቢን በማሳደግ ተቋሙን ማጠናከር አገልግሎቶችን ማስፋት ያስፈልጋል ያሉት አባላቶቹ የባለሙያዎች የአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለቶችና የስነ ምግባር ችግሮች መቅረፍ እንድሚገባ አስገንዝበዋል። በመጨረሻም የጤና ጣቢያውን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ ባሉ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች ላይ ጥልቅ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠው መግባባት ተፈጥሮ መድረኩ ተጠናቋል።

ህዳር 22/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በኦቼና አንቀዲን ቀበሌ በመኸር የለማ የስንዴ ማሳ አሁናዊ ቁምና በምስል፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በዘንድሮ የመኸር ልማት 4 ሺህ 26 ሄክታር ስንዴ መልማቱን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።

ህዳር 21/2018 ዓ.ም የፖሊስ ሰራዊት አባላት ሀገርን እና ህዝብን በተሻለ ቁመና ማገልገል እንደሚገባ ተገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው"የጂኦ-ስትራቲጂያዊ ኩሱምና ወደ የታደሰ ቁመና" በሚል ርዕስ በጉራጌ ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አመራርና አባላት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በተጠናቀቀበት ወቅት ነው። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደገለጹት ለፖሊስ አባላት አለም አቀፉን የጂኦ ፖለቲካ ሁኔታ በመገንዘብ ተገቢውን ቁመና ለመያዝና የፖሊስ ሠራዊቱን አረዳድ የተሻለ ለማድረግ የሚያስችል ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል። የፖሊስ አባላት የአገልጋይነት ስሜት በመላበስ ህዝቡ የሚያማርሩና በመንግስት ላይ እምነት የሚያሳጡ ጉዳዮችን በማረም በተሻለ ቁመና ማገልገል እንደሚያስፈልግ አቶ ሚፍታ አሳስበዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም አከባቢያዊ ሁኔታዎችን በጥልቀት በመረዳት፣ ሠላምን ከማስፈን በተጨማሪ፣ የመንግስትን ወቅታዊ የትኩረት አቅጣጫ በመረዳት፣ሃገራዊ የለውጥ ሂደት ለማስቀጠል እና ለማፅናት የፖሊስ ሚና የላቀ መሆኑን ለማስገንዘብ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስታውቀዋል። የወረዳው ስላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙስማ በድሩ በበኩላቸው ጠንካራ እና በህዝቡ የሚታመን የፀጥታ ተቋም ለዘላቂ ሰላም ግንባታ አቅም እንደሆነ ጠቅሠው በየደረጃው ያሉ የፖሊስ አባልና አመራር የሀገሪቱን ስትራቴጂካዊ ጥቅሞች ለማስከበር መዘጋጀት እንዳለበት ገልጸዋል። በወረዳችን ብሎም እንደ ሀገር የተመዘገቡ አገራዊ ጥቅሞችን በማስከበርና በጋራ በመቆም የጋራ ሀገራዊ ጥቅማችንን በማጎልበት የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ ማፋጠን እንደሚያስፈልግ አቶ ሙሰማ በድሩ አክለው ገልጸዋል። በስልጠና ማጠቃለያ ወቅት አንዳንድ የፖሊስ አባላት እንዳሉት የሀገርን ክብር በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸው የተስተካከለ ፖሊሳዊ ቁመና በመያዝ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማሳጣት የሚሰሩ ሀይሎችን ለመመከት እንዲሁም የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም እንዳታጣ የሚከፈለውን ሁሉ ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች እና መከላከያ ዘዴዎች፡- 📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምንድን ነው? o የማርበርግ ቫይረስ በሽታ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት የደም መፍሰስና ትኩሳት ህመም ነው። o በሰዎችም ሆነ በሌሎች እንስሳት ላይ ይከሰታል። 📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ምልክቶች ምንድን ናቸው? 👉 ከአፍ፣ ከአፍንጫ ወይም ከቆዳ ሥር ደም መፍሰስ፤ 👉 ከፍተኛ ትኩሳት፣ ብርድ ብርድ ማለት እና ራስ ምታት፤ 👉 የጡንቻ እና ጀርባ ህመም፤ 👉 ማቅለሽለሽ፣ የሆድ ህመም እና ተቅማጥ፤ 👉 ደረት፣ ጀርባ እና ሆድ ላይ በጣም ጎልቶ የሚታይ ሽፍታ፤ 👉 ለቫይረሱ ከተጋለጡ ከሁለት እስከ ዘጠኝ ቀናት ውስጥ የበሽታው ምልክቶች ይታያሉ። 📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው? • በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ደም፣ ሽንት፣ እንባ እና ሌሎች ፈሳሾች ጋር የሚፈጠር ቀጥተኛ ግንኙነት፤ • በታመመ ወይም ሕይወቱ ያለፈ ሰው የሰውነት ፈሳሽ የተበከሉ ቁሶች፣ እንደ ልብስ፣ አልጋ ልብስ፣ መርፌና ሌሎች መገልገያዎች ጋር በሚኖር ንክኪ፤ • በበሽታው ከተያዙ የሌሊት ወፎች ወደ ሰዎች ይተላለፋል። 📌 የማርበርግ ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች ምንድን ናቸው? 👉 ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች ሲኖሩ ወደ ሕክምና ተቋም መሄድ፤ 👉 ከታመመ ሰው ጋር ንክኪና ትኩሳት ካለ በአፋጣኝ ወደ ሕክምና ተቋማት መሄድ፤ 👉ሞት በሚከሰትበት ወቅት አስከሬኑን በባለሙያ ማዘጋጀትና መቅበር፤ አላስፈላጊ ቀብር ሥነ-ሥርዓቶችን ማስቀረት እና ንክኪ ያላቸውን ቁሶች ማስወገድ። 👉 ከታመመ ሰው ደምና ፈሳሽ ንክኪ ራስን መጠበቅ፤ 👉ለታመመ ሰው እንክብካቤ በምናደርግበት ጊዜ የመከላከያ ዘዴዎችን ማለትም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እና የእንጅ ጓንት መጠቀም። 👉 እጅን በሳኒታይዘር ወይም በሳሙናና በውኃ በአግባቡ መታጠብ።