fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
923
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+37 روز
+730 روز
آرشیو پست ها
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ህዳር 21/2018 ዓ.ም 👉🏼‌‎ በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህዳር 22 በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ለሚከፈተው ሀገር አቀፍ የንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛር የሚቀርብ ማር፣ ቂቤ እንዲሁም የግብርና ሰብሎች ማዘጋጀቱን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና'' በሚል ርዕስ ለፖሊስ አመራርና አባላት ስልጠና ተሠጠ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በመገምገም በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ ስልጠናን እስከ ታችኛው አመራራችንና አባላችን እንዲደርስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ውይይት ተደርጓል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር በገጠርና በከተማ ኢንቨስትመነት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ አቅጣጫዎች አስቀመጠ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ አመራሩ የወሰደውን ስልጠና እንደ ተጨማሪና አዳጊ እድል በመጠቀም በቁርጠኝነትና በትጋት በመስራት ህብረተሰቡን የሚመጥን ስራ ማከናወን እንደሚጠበቅበት የጉራጌ ዞን ዋና አስተደዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ገለጹ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‌‎ ወንጀልን አስቀድሞ መከላከልና መቆጣጠር  እንደሚገባ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ገለፀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨

ህዳር 20/2018 ዓ.ም በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ህዳር 22 በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ለሚከፈተው ሀገር አቀፍ የንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛር የሚቀርብ ማር፣ ቂቤ እንዲሁም የግብርና ሰብሎች ማዘጋጀቱን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በኤፌድሪ ፌደሬሽን ምክር ቤትና በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መስተዳዳር አዘጋጅነት የሚካሄደውን 20ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች በዓልን ምክንያት በማድረግ በክልሉ ጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የሚዘጋጀው የንግድ ኢግዚቪሽንና ባዛር የሚቀርብ ማር ፣ ቂቤ እንዲሁም የግብርና ሰብሎች በማዘጋጀት በዛሬው እለት ወደ ጉራጌ ዞን ተደራሽ ማድረጉን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል። የንግድ ኤግዚብሽንና ባዛሩ የወረዳውን በተለይም የግብርና ምርትና አገልግሎቶችን በስፋት ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ በተጨማሪም የገበያ ትስስር በመፍጠር በወረዳችን የሚገኙ ምርቶቻችንን የሚያስተዋውቁበት እንደሆነ ተመላክቷል።

ህዳር 20/2018 ዓ ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሰ ቁመና'' በሚል ርዕስ ለፖሊስ አመራርና አባላት ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጠው ስልጠና ተጀምሯል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ስልጠናው የፖሊስ አመራርና አባላት አለም አቀፋዊና ሀገራዊ ሁኔታን በሚገባ በመገንዘብ እና በመተንተን ኢትዮጵያን በሁለንተናዊ ጉዳዮችና የጂኦ-ስትራቴጂ ቁመናዋን ከፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑንም በመርሀግብሩ ማወቅ ተችሏል። በስልጠና መድረኩ ላይ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት አዛዥ ተወካይ ኢንስፔክተር ጀማል አስፍር የተገኙ ሲሆን የስልጠና ሰነዱን ያቀሩቡት የገ/ጉ/ወ/ወ/ፖሊስ ፅ/ቤት የማህበረሰብ አቀፍ የወንጀል መከላከል ዋና ስራ ሂደት አስተባባሪ ም/ኢንስፔክተር በመሀመድ አባተ ቀርቦ በሁለት ቡድን በመሆን ጥልቀት ያለው ውይይት እንደሚደረግ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። ዝርዝር መረጃ ተከታትለን እናደርሳለን

ህዳር 20/2018 ዓ.ም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 50ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ምክር ቤቱ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች የሚከተሉት መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል። 1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ላይ ነው፡፡ ስትራቴጂው ለዜጎች አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ የቴክኖሎጂ አቅምን ለማሳደግና መሰረተ ልማቶቹን ለማስፋፋት፣ መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን በተሻለ መንገድ ማሳካትን ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ ምክር ቤቱም በስትራቴጂው ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በምክር ቤቱ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 2. ከዚያም ምክር ቤቱ የተወያየው ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር ጋር በተፈረሙ ሁለት የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ዘላቂ እና ንፁህ የኢነርጂ ተደራሽነት ለውጥን ለማፋጠን ፕሮግራም ማስፈፀሚያ የሚውል 294,900,000 ኤስ. ዲ. አር የብድር ስምምነት ሲሆን የ6 አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ38 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ሁለተኛው የምስራቅ አፍሪካ የክህሎት ትራንስፎርሜሽን እና ቀጠናዊ ውህደት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል ተጨማሪ 20,000,000 ኤስ. ዲ. አር የብድር ስምምነት ሲሆን የ6 አመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ31 አመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቅ ነው፡፡ ሁለቱም ብድሮች ከወለድ ነጻ እና 0.75% የአገልግሎት ክፍያ የሚከፈልባቸው ናቸው፡፡ ምክር ቤቱም የብድር ስምምነቶቹ ከአገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ መሆናቸውን በማረጋገጥ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል። 3. በመቀጠል ምክር ቤቱ የተወያየው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቴአትር ለሚሰጧቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈሉ የአገልግሎት ክፍዎችን ለመወሰን በቀረቡ ሁለት ረቂቅ ደንቦች ላይ ነው፡፡ ተቋማቱ አገልግሎት ለመስጠት የሚያወጡትን ወጪ ሸፍነው ገቢያቸውን በማሳደግ ጥራት ያለው አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ በማስፈለጉ የተገልጋዩን አቅም ባገናዘበ መልኩ የአገልግሎት ክፍያ ተመን ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በረቂቅ ደንቦቹ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትመው ከወጡበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረጉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 4. ቀጥሎም ምክር ቤቱ የተወያየው በአራት የሁለትዮሽ ስምምነቶች ላይ ነው፡፡ የመጀመሪያው ከህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ መንግስት ጋር በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ለማድረግ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡ ሌሎቹ ሁለት ስምምነቶች ከህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ መንግስት እና ከብራዚል ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር ፍርደኞችን ለማስተላለፍ የተደረጉ ናቸው፡፡ ሌላው ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ መንግስት ጋር የተደረገው የአሳልፎ መስጠት ስምምነት ነው፡፡ ምክር ቤቱም ስምምነቶች ቢጸድቁ ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር ዉጤታማ የወንጀል መከላከል የሁለትዮሽ ትብብር የሕግ ማዕቀፍ ለመፍጠር የሚያስችላት መሆኑን በመገንዘብ ረቂቅ አዋጆቹ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 5. ሌላው ምክር ቤቱ የተወያየበት አጀንዳ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ ረቂቅ ደንብ ነው፡፡ የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010ን ሙሉ ለሙሉ ስራ ላይ ለማዋል የሚያስፈልጉ ስርዓቶችን በአዋጁ እና በተሻሻለው የኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1358/2017 መሰረት ግልፅ እና ተጠያቂነት በሰፈነበት መልኩ ለመተግበር እንዲያስችል ሆኖ ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል። ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ 6. በመጨረሻም ምክር ቤቱ የተወያየው የኢሚግሬሽን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 114/1997 ለማሻሻል በቀረበ ደንብ ላይ ነው፡፡ ተቋሙ በአዋጅ የተሰጠውን ተግባርና ሀላፊነት ለመወጣት እንዲያስችለው ደንቡ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ መረጃው ኤፍ ኤም ሲ ነው።

"ዲሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት!!" በሚል መሪ ቃል በክልላችን የሚከበረው 20ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል፣ በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ዛሬ የነበረው ዞናዊ ማጠቃለያ ፕሮግራም በምስል!!

ህዳር 20/2018 ዓ.ም ወቅታዊ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን በመገምገም በመደመር መንግስት እይታ የዘርፎች እምርታ ስልጠናን እስከ ታችኛው አመራራችንና አባላችን እንዲደርስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ላይ ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ውይይት ተደርጓል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልጽግና ፖርቲ ጽ/ቤት በመደመር መንግሥት እይታ የዘርፎች እምርታ በሚል መሪ ቃል በስልጠና ያገኙትን እውቀትና ልምድ  በመጠቀም ፀጋዎቻችን መለየት ህዝብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የበለጠ መትጋት እንደሚገባ አሰወቀ በመድረኩ ተመላክቷል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ስልጠናው የታለመለትን ግቦች ለማሳካትና፣ጠንካራ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ለማጎልበት የሚያስችል ከመሆኑም ባሸገር በአመራሩ ዘንድ ቁጭትና ተነሳሽነት የፈጠረ ስልጠና እንደነበር አስታውቀዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም የንቅናቄ ተቋማት አካባቢ የገቢ አሰባሰብ፣በግብርና፣የጤና እንዲሁም የትምህርትና ሌሎችም ተግባራት በልዩ ትኩረት እንዲሁም በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ ስልጠናው እንደ መደመር መንግስት በብዝሀ ዘርፍ ትስስር ወደ ስልጣኔ ሽግግር ለማምጣትና የዘርፎችን እምርታ ለማረጋገጥ በውይይትና በመስክ ጉብኝት ያገኟናቸውን እውቀትና ልምዶች በዕቅድ በማካተትና ወደ ስራ ለመቀየርና የወረዳችን ሁለንተናዊ ብልፅግና እውን ለማድረግ አቅም የፈጠረ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም ስልጠናው ጠንካራ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን መፍጠር በሚያስችል መልኩ መሰጠቱ ለቀጣይም መልካም ግብአቶች የተገኘበት እንደሆነ ኃላፊው ገልጿል። በመድረኩ የተገኙ አመራሮች ስልጠናው በየአካባቢያው ያሉ ጸጋዎችን ለይቶና አቅዶ የማይቻል የሚመስሉ ተግባራትን የመፈጸም ልምድ ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት፣በፈጠራ፣በፍጥነትና በጥራት እንዲሁም በአንድ አለማ በህብረት በትብብር እና በቅንጅት ለመስራት ቁጭትና ተነሳሽነት የፈጠራ ስልጠና እንደነበር አብራርተዋል። በመድረኩ ላይ የወረዳው ዋና አስዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴንና የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳ እንዲሁም ጠቅላላ የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

ህዳር 18/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር በገጠርና በከተማ ኢንቨስትመነት አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ የተለያዩ አቅጣጫዎች አስቀመጠ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር በውይይቱ በገጠርና በከተማ ኢንቨስትመነት ዙሪያ በግብርና ዘርፍ የቡና ልማት እንዲሁም ዘመናዊ የእንስሳት ሃብት ልማትና ወተት መቀነባበሪያ፣ ማዳያ፣በሆቴልና ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተለያዩ ኢንቨስትመነት ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይቶ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በመድረኩ እንዳሉት ወረዳችንን ለማልማትና ኢንቨስትመንቱን ለማጠናከር በተለያዩ ከተሞችና ገጠር ቀበሌዎች መሬት አጥሮ የተቀመጡ ቦታዎች እንዲለሙ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል። የኢንቨስትመንት ዘርፉን ውጤታማ ለማድረግ የሚመለከታቸው አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ባለሀብቱ ከመንግስት ጋር በቁርኝት በመስራት ወረዳውን በማሳደግ እንዲሁም የስራ ዕድል ፈጠራን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል። የተጀመሩ ስራዎች አጠናክሮ ለመቀጠል ወረዳውን ብሎም ህዝቡን የሚጠቅም አምራች ኢንዱስትሪ መፍጠር የሁላችንንም ጥረት እንደሚጠይቅ አቶ ሚፍታ ሁሴን አስገንዝበዋል። አንዳንድ የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የተሻለ ወረዳ ለመፍጠር ኢንቨስትመንት ያለው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ ባለሀብቱ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት፣ በኢንቨስትመነት ስም በተለያዩ የወረዳችን ቦታ ታጠረው የተቀመጡ ስፍራዎች በአሠራሩ መሰረት እንዲያለሙ ማልማት በማይችሉ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባ የገለጹት አስተያየት ሠጪዎቹ አዲስ ኢንቨስትመነት ወደ ወረዳ ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት በቁርጠኝነት ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ህዳር 16/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች የዘንድሮ ዓመት የቡና ምርት አሁናዊ ቁመና በምስ በከፊሉ፦