fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
924
مشترکین
-224 ساعت
+37 روز
+630 روز
آرشیو پست ها
የአፋልጉኝ ማስታወቂያ ተፈላጊ ታዳጊ ሁስንያ አርጋ ግራኝ ትባላለች ዕድሜ 8 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ነዋሪ ስትሆን በቀን 18/12/2017 ዓ.ም ከምትኖርበት ከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ወደ አ/አ የሄደች ሲሆን የመኖሪያ አድራሻዋ አዲስ አበባ አብነት አካባቢ በቀን 24/12/2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5 ሰዓት ከቤት እንደወጣች አልተመለሰችም ተፈላጊዋ ከቤት ስትወጣ ሰማያዊ ቀሚስ የለበሰች ሲሆን ተፈላጊዋ ያገኘ ወይም ያለችበት ለጠቆመን ወሮታውን ከፋይ ነኝ ይላል ፈላጊ ወላጅ አርጋ ግራኝ!!! 0921009272 ወይም 0913161412

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ነሐሴ 25/2017 ዓ.ም 👉🏼‎ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ " ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! "በሚል መሪ ቃል ያለፉት ዓመታት ጉዞዎች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚወያይ የአመራር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ በማዕ/ኢ/ክ/የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት መሥራች ጠቅላላ ጉባዔ እና የዞኑን የስራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ አካሄደ ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ "ኢቶብያነ ተምሳየ ጌ" ቢላን ቡር ቃል የቴለፉ አይዶቸ ተሬሻትወ የዉፍትሉፍት ቀስድ ደር የጥሬመተ የሮሻት ደውር ባውጄነይ አያም ተጄመረ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ " ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! "በሚል መሪ ቃል ያለፉት ዓመታት ጉዞዎች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚወያይ የአመራር መድረክ መካሄድ ጀመረ። 👉🏼‎የጉራጌ ዞን አስተባባሪ አካላት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመገኘት አጠቃለይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ገመገሙ ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የተፈጠሩ ዕድሎችንና ተግዳሮቶችን ለይቶና ተረድቶ የሃሳብ የበላይነት በማስረጽ ረገድ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የላቀ ድርሻ አለው- አቶ ዘሪሁን እሸቱ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ክቡር የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ለአመራሮች ካስተላለፏቸው ቁልፍ መልዕክቶች። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ "በሚል መሪ ቃል በዘንድሮ አመት እየተከንወኑ የሚገኙ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች በምስል በከፊሉ፦ 👉🏼‎በመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጊቢ ውስጥ በወረዳው መንግስት በጀት ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘው ካፍቴሪያ በምስል በከፊሉ፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የክልሉ መንግስት የህዝቡን የማደግና የመልማት ፍላጎትና ጥያቄዎች የበጀት አቅምን ባገናዘበ መልኩ  ደረጃ በደረጃ ለመመለስ በልዩ ትኩረት ይሰራል!! ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎👉🏼‎ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ከደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ገቢ መሰብሰቡን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎ 👉🏼‎የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ፤ የደም ጠብታ የላብ ጠብታ የዕንባ ጠብታ የውኃ ጠብታ ድምር ውጤት መሆኑን፣ ይህ ግድብ ህያው ምልክት ሆኖ ለትውልድ ሲመሰክር ይኖራል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ኢትዮጵያ ደግሳለች ! የምድራችን ረዥሙ ወንዝ ዓባይ በኢትዮጵያውያን  ያበረ ክንድ  ለጋስነቱ ለእናቱ ሆኗል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ ምስረታን ጨምሮ የስራ አስፈፃሚ እና የስራ አመራር ምርጫ መድረክ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ቤደር ቀበሌ በክረምት በጎ ፍቃድ የአቀመ ደከማ ቤት ግንባታ በከፊሉ፦

ናሴ 24 2 ክም 17 ኢ/ዘ "ኢቶብያነ ተምሳየ ጌ" በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ "ኢቶብያነ ተምሳየ ጌ" ቢላን መሳኪ ቃል የቴለፉ አይዶቸ ተሬሻትወ የዉፍትሉፍት ቀስድቸ ደር ወባጀ ያትሬሻን የመሳኪቸ ደውር ዪትረሻንን። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የሮሻቲ ወ የወባጃይ ደውር ባውጄነይ አያም በሼሽት ደረቦ ዪትረሻን ቲሆን በጌስሚ አያም ዪኤጥላን ዮናን።

ነሐሴ 24/2017 ዓ.ም ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ " ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር! "በሚል መሪ ቃል ያለፉት ዓመታት ጉዞዎች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የሚወያይ የአመራር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የስልጠናና የውይይት መድረኩ በዛሬው እለትም በ3 ቡድኖች በመሆን እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በነገው እለትም የሚቀጥል ይሆናል።

ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም በማዕ/ኢ/ክ/የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት መሥራች ጠቅላላ ጉባዔ እና የዞኑን የስራ አስፈፃሚ አባላት ምርጫ አካሄደ ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በ2017 ምርጫ በአምስቱም ዘርፍ ከኡለማዎች፣ከሙህራን፣ከወጣቶች፣ከሴቶችና ከስራ ማህበረሰብ ክፍሎች ህዝበ ሙስሊሙን ሊወክሉ የሚችሉ አባላትን ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና አካታች በሆነ መንገድ በመምረጥ መስራች ጉባዔ በመመሥረት ለቀጣይ አምስት አመት ዞኑን የሚመሩ ስራ አስፈፃሚዎ ችን መርጧል ። በዚህ መሰረት የጉራጌ ዞን እስልምና ጉዳዮች ምክርቤት 1/ ሸይኽ አባስ ያሲን ሰብሳቢ 2/ ኡስታዝ ጀሚል ሁሴን ምክትል ሰብሳቢ 3/ኡስታዝ ሷሊህ ጀማል ፀሃፊ 4/ኡስታዝ አብድልፈታ ሼህ ተማም አባል 5/ኡስታዝ ጅላሉ ያሲን አባል 6/ኡስታዝ ሀሰን ሸሪፍ አባል 7/ሀጅ ነስሩ ያሲን አባል 8/ሚፋታህ ያሲን አባል 9/ሀምዲያ ሳዲቅ አባል ሆነው ሲመረጡ ቀጥሎ ላለው መጅሊስ መዋቅር ጉራጌ ዞንን የሚወክሉ ተወካዮች 1ኛ ሸይኽ ሰአድ ጅላሉ የፌደራል ተወካይ 2ኛ ሸይኽ አብድልበር ዘይኑ የክልል ተወካይ 3ኛ ሸይኽ ባቂል በደዊ የክልል ተወካይ 4ኛ ሸይኽ በህጃ አብድልጀሊል የክልል ተወካይ 5ኛ አቶ ደጉ አብራር የክልል ኦዲትና ኢ/ተወካይ በመሆን ተመርጠው በጉባዔው ፊት ቃለ መኃላ ፈፅመዋል ። በዚህ የጠቅላላ ጉባዔ ምስረታ ላይ የፌደራል ምርጫ አስፈፃሚ ኡስታዝ ሪያድ እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፉዓድ ሙሀመድ እና ሌሎችም የክልሉና የዞኑ መጅሊስ የ2017ምርጫ አስፈፃሚ ቦርድ አባላት ተገኝቷል። #ምርጫችን በመስጅዳችን !! #ምርጫችን ለፅኑ ተቋም !! መረጃው የጉራጌ ዞን ኮሚኒኬሽም መምሪያ ነው።

ናሴ 23/17 ኢ/ዘማን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ "ኢቶብያነ ተምሳየ ጌ" ቢላን ቡር ቃል የቴለፉ አይዶቸ ተሬሻትወ የዉፍትሉፍት ቀስድ ደር የጥሬመተ የሮሻት ደውር ባውጄነይ አያም ተጄመረ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በሮሻት ደውሪ ደር የጉራጌ ዞን ፍይናንስ መሳኪ ወቢ የሀሠኒ አብዶ፣ የወረዳይ ቡር አቲንዳዳሪ የሁሴኒ ሚፍተ ፣የወረዳይ ብልጽግና ባርቲ ክትበት ጋር ወቢ የርዳይ አ/ረሂምነ ደበላኒ የወረዳይ አስተባባሪቸ መሳኪቸ እነምኮንገ የኧበሌ ሊኧመምበርቸወ ብል አስናጂቸ ተረኸቧን። በደውሪ የጉራጌ ዞን ፍይናንስ መሳኪ ወቢ የሀሠኒ አብዶ ሮሻቲ በጥሬመተ ክስክስ ሁስብ ባቦት ሮሻቲ አጄመሯን። የወረዳይ ብልጽግና ባርቲ ክትበት ጋር ወቢ የርዳይ አ/ረሂም ለሮሻቲ የዝጋጁ ሰነድቸ አአረቧን። ክስክሲ ዬንዜነ ይትክነበልናን!!

ናሴ 23 2 ክም 17 ኢ/ዘ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ "ኢቶብያነ ተምሳየ ጌት" ቢላን መሳኪ ቃል የቴለፉ አይዶቸ ተሬሻትወ የዉፍትሉፍት በስድ ደር የጥሬመተ የሮሻት ደውር ባውጄነይ አያም ተጄመረ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በሮሻት ደውሪ ደር የጉራጌ ዞን ፍይናንስ መሳኪ ወቢ የሀሠኒ አብዶ፣ የወረዳይ ቡር አቲንዳዳሪ የሁሴኒ ሚፍተ ፣የወረዳይ ብልጽግና ባርቲ ክትበት ጋር ወቢ የርዳይ አ/ረሂምነ  ደበላኒ የወረዳይ አስተባባሪ አካላትና መሳኪቸ አነምኮንገ የኧበሌ ሊኧመምበርቸወና ብል አስናጂቸ ታደሟን። በደውሪ የጉራጌ ዞን ፍይናንስ መሳኪ ወቢ የሀሠኒ አብዶ ሮሻቲ በጥሬመተ ክስክስ ሁስብ ባቦት ሮሻቲ አጄመሯን። የወረዳይ ብልጽግና ባርቲ ክትበት ጋር ወቢ የርዳይ አ/ረሂም ለሮሻቲ የዝጋጁ ሰነድቸ አአረቧን።

ነሐሴ 22/2017 ዓ.ም የጉራጌ ዞን አስተባባሪ አካላት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመገኘት አጠቃለይ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ከወረዳው ጠቅላላ አመራር ጋር ገመገሙ ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በግምገማ መድረኩ ላይ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የጉራጌ የዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አለማየው ገ/መስቀል እና የጉረጌ ዞን አስተባባሪ አካላት እንዲሁም የወረዳው ጠቅላላ አመራሮች ተሳትፈዋል። ወረዳው ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስትና በፓርቲ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውንና የበለጠ ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው መሆኑን የተጠቀሰ ሲሆን በሂደቱ የተስተዋሉ ችግሮችም መኖራቸውንና እነዚህን ችግሮች አመራሩ መፍታት እንደሚገባውም በማሳሰብ ተጨማሪ የወረዳው አስተባባሪ አደረጃጀት ላይ ማስተካከያ ተደርጓል። በዚሁ መሰረት፦ 1፡ የወረዳው ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ጠይብ አስፍር 2፡የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፕላንና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ዘይነብ ወራቄ በመሆን በአስተባባሪ ደረጃ ተደራጅተዋል። በመድረኩ የአመራሩ የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነት በመፍጠር የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በውጤታማነት መፍታት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።