fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
925
مشترکین
+224 ساعت
+27 روز
+830 روز
آرشیو پست ها
ክቡር የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ለአመራሮች ካስተላለፏቸው ቁልፍ መልዕክቶች ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል!! #Guragezone #Leadership

በመሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጊቢ ውስጥ በወረዳው መንግስት በጀት ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘው ካፍቴሪያ በምስል በከፊሉ፦

ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እስከ ነሐሴ 20/2017 ድረስ ከ34 ሺህ በላይ ወጣቶችን በማስተፍ 61 ሺህ የህብረተሠብ ክፍሎች ማስጠቀም መቻሉን እንዲሁም ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ መንግስትና ህብረተሰቡ ሊወጣ ይችል የነበረውን ገንዘብ ማዳን መቻሉን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት ፅህፈት ቤት አክሎ አስታውቋል። የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም የእስካሁን አፈጻጸሙን አስመልክተው እንደገለጹት ወጣቶች በልማትና በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ በመሳተፍ ተጠቃሚ ከሚሆኑባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው የወጣቶች የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ ተጠቃሽ ነው ሲሉ ገልፀዋል። የዘንድሮውን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ39 ሺህ 1 መቶ 13 በላይ ወጣቶች በተመረጡ 15 የስምሪት መስኮች ላይ ተሰማርተው መጠነ - ሰፊ እንቅስቃሴ በማድረግ በረካታ ስራዎች መሠራታቸውን አስታውቀዋል። እስካሁን ያለውን አፈጻጸም አስመልክተው እንዳሉት ከጤና አንፃር በቁጥር 121 ዩኒት ደም ልገሳ ለመሰብሰብ ታቅዶ 26 ዩኒት ደም ለእናቶች መሰብሰብ መቻሉ፣ 1228 የህብረተሠብ ክፍሎች ነጻ ምርመራና የምክር አገልግሎት እና ለ3 አቅመ ደካሞች ነጻ የህክምና አገልግሎት መሰጠቱን ገልጸው በክረመቱ ከ4.1 ሚሊዮን በላይ ዘርፍ ብዙ ጥቅም ያላቸው ችግኞች በወጣቶች መተከላቸውን ፣ 150 ቶን ቆሻሻ በከተሞች መወገዱን አንስተዋል። ከማህበረሰብ ድጋፍና ክብካቤ አኳያ 24 ቤቶችን ጠግኖ በማደስ አቅመ-ደካማ አረጋውያንን ከብርድና ከዝናብ መታደግ ስለመቻሉ ጠቅሰው 21 አዲስ ቤቶች በመንግስትና በህብረተሠብ ተሳትፎ እየተገናቡ ሲሆን 7 ቤቶች መጠናቀቃቸውም ጠቅሠው ከዚህ ውስጥ 1 ቤት የዘማች ቤተሠብ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ሸምሱ አክለውም 1018 ለሚሆኑ አቅመ ደካሞችና ማዕድ የማጋራት ስራ ተሠርቷል እንዲሁም 12 ደርዘን ደብተር 2 ፓኬት እስክሪብቶ ለተማሪዎች ተደራሽ መደረጉና 52 ተማሪዎች የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት እየወሠዱ ሲሆን 48 ተማሪዎችና የመንግስት ሠራተኞች መሠረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና መውሠዳቸውን ገልጸዋል። 30 አዲስ አንስተኛ መሸጋገሪያ የእንጨት ድልድዮች የተገነቡ ሲሆን 1.25 ኪሎ ሜትር የመንገድ ዳር ቦይ ከፈታ ስራዎች በበጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተሰርተዋል በተጨማሪም በትምህርት ፣ በምግብ ዋስትናና የግብርና ልማት እንዲሁም የመንገድ ደህንነትና ትራፊክ አገልግሎት፣ ስራ አጥ ወጣቶች ልየታን ጨምሮ በስፖርት መስኮች አበረታች እንቅስቃሴ እየተደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰው በአንፃሩ የሃብት አሰባሰብ፣ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ጉድለቶች በቀጣይ ወስዶ መቅረፍ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ሸምሱ የበጎ ፈቃድ የዘወትር ተግባርና ልምድ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባና የመደጋገፍና መረዳዳት ባህላችንን አጠናክረን ማስቀጠል ይኖርብናል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። አቶ ሸምሱ በመጨረሻም እንደገለጹት እስካሁን ዘንድሮ የክረምት ወራት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት 34 ሺህ 093 ወጣቶች በበጎ ፈቃድ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ላይ ሲሆኑ 61 ሺህ 872 የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ 35 ሚሊዮን 598 ሺህ 810 ብር መንግስትና ህብረተሰቡ ሊወጣ ይችል የነበረውን ገንዘብ ማዳን ተችሏል ሲል የዘገበው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መንግስት ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

የክልሉ መንግስት የህዝቡን የማደግና የመልማት ፍላጎትና ጥያቄዎች የበጀት አቅምን ባገናዘበ መልኩ ደረጃ በደረጃ ለመመለስ በልዩ ትኩረት ይሰራል!!

ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም ‎ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ከደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች ‎ገቢ መሰብሰቡን በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት አስታወቀ። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት ከመደበኛ 223,970,424 ከማዘጋጃ ቤቶች 31,070,462 በድምሩ 2 መቶ 65 ሚሊዮን 040,886 ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል። ‎ ‎በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በተያዘው በጀት ዓመት የደረጃ ሐ ግብር ከፋዮችን ግብር ለማስከፈል ከሐምሌ 1 እስከ ሐምሌ 30/2017 ዓ/ም በያዘው እቅድ የ2018 በጀት ዓመት የደረጃ ሐ ግብር ከፋይ 1162 ነጋዴዎች 3 ሚሊዮን 046 ሺህ 040 ብር በግብርና በታክስ በመሰብሰብ የእቅዱን 100% ማሳካት መቻሉን የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ጀሊል ቱሉ ገልጸዋል፡፡ ‎ ‎አቶ አ/ጀሊል ቱሉ አክለውም ለዚህ ስኬታማ ውጤት ማስመዝገብ የግብር ከፋይ ነጋዴዎች ተነሳሽነትና የባለድርሻ አካላት ቅንጅት የተሻለ መሆኑ እንዲሁም የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በትጋት መስራታቸው ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ ‎የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት የወረዳውን አመራርና የቀበሌ አመራሮችና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ሰፊ ሰራ የተሰራ ሲሆን የግብር መክፈያ ማዕከላትን በከተሞች በመቋቋም ግብር ከፋዩ ነጋዴ ተጨማሪ ወጪ ሳያወጡ በአቅራቢው ግብር እንዲከፍል አገልግሎት የወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ሲሰጥ መቆየቱን ገልጸዋል። ‎ ‎በአጠቃላይ በዚህ በጀት ዓመት የደረጃ ‹‹ሐ›› ግብር ከፋዮች ከተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ አስቀድመው ‎ከሐምሌ 01 እስከ ሐምሌ 05/2017 ዓ.ም ‎ለመሰብሰብ በተደረገው ንቅናቄ ውጤታማ እንደሆነ ጠቅሠው በዚህ ተግባር ላይ የተሳተፉ አካላት ማለትም የወረዳው አስተባባሪና የወረዳው አመራር ፣የዞን ድጋፍ፣የፀጥታው መዋቅር የቀበሌ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ርብርብ በማደረጋቸው በገቢ ጽ/ቤት ስም ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበው በዘንድሮ በጀት አመት የገቢ አሰባሰብ ተግባር ላይ የገቢ ጉዳይ የሁሉም አካል በመሆኑ ድጋፍና እገዛችሁ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል። ‎

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት የኢትዮጵያ ማንሠራራት ጅማሮ፤ የደም ጠብታ የላብ ጠብታ የዕንባ ጠብታ የውኃ ጠብታ ድምር ውጤት መሆኑን፣ ይህ ግድብ ህያው ምልክት ሆኖ ለትውልድ ሲመሰክር ይኖራል።

ኢትዮጵያ ደግሳለች ! የምድራችን ረዥሙ ወንዝ ዓባይ በኢትዮጵያውያን ያበረ ክንድ ለጋስነቱ ለእናቱ ሆኗል። እናም ኢትዮጵያ ደስታ ላይ ናት ።ኢትዮጵያ የቁጭት እና ትካዜ ገጿን በመጨረሻው ሳቅ ተክታለች ። የግጭት እና ጦርነት ፣ የረሃብና የተስፋ ቢስነት ሽንቁሯን ለማስፋት ለሚደክሙ ድግሱ መርዶ ቢሆናቸው እንጂ ድንኳን ሰባሪ ይሉት አይነት ወዳጅ መስሎ ለመታየትም ብርታቱ የላቸውም ። ''ብነካው ተነኩ አንቀጠቀጣቸው'' ያለችው የድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ትንቢት በድግሱ ዋዜማም አለቀቃቸውም ። ሆኖም ለወዳጅም ለጠላትም ኢትዮጵያ ደግሳለች ። ይህ ድግስ የሰላም እና የልማት ነው ። ለጥቁር ህዝቦች የነጻነት ፀሀይን ፈንጥቃ ፤ ቀኝ ገዥዎችን ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ያስባለችው ኢትዮጵያ ፣ ዛሬም ግዙፉን በራስ የመቆም የሚዳስሰው የመቻል ቅርስን ሀቁን እና እውነቱን እንዲውጥ የሚያስችለውን ህዳሴ ግድብን ልትመርቅ ነው ። አሸናፊነትን ፣ ጀምሮ መጨረስን ፣ በትውልድ ቅብብል የሀገር የዘመናት ህልምን ማሳካትን ፣ ሀገር በጸና የጋራ ሀብቷ በጥረት እና ትግል መጽናቱን ለድግሷ ታዳሚዎች አቅርባለች ። እናም እጅ ለእጅ ተያይዘው ምድር እስክታረግድ የስኬትን ከፍታ የዘመናት ተረት ተረትን በመቀየር የሚጋሩት ነው ። በጉባ በረሃ ከ14 አመት በፊት መጀመሩ ሲበሰር የደስታ ሲቃ ያለቀሱ ዛሬ የሀሴት ዳንኪራን የሚረግጡበት ከፍታቸው ነው ። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ''ቀደምት ኢትዮጵያውያን ወደ ነበሩበት የአለም የስልጣኔ ጠርዝ ለመድረስ የህዳሴ መንገድ ጀምረዋል'' ያሉትን በአታካች ድርድር የድርሻቸውን የተወጡትን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን የኋልዮች ላስታወሰ የቁርጠኝነት ሀውልት ሆኖ ፤ ''ተስፋ ሳይሆን ሪቫን እንቆርጣለን ''ባሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ፍጻሜው ሲበሰር ባለ ድልም ፣ ባለ እድልም የሆነው ትውልድ በኢትዮጵያ ድግስ መፈንጠዙ የሚጠበቅ ነው ። የታላቁ የህዳሴ ግድብ የመጠናቀቅ ብስራትን የኔ ግድብ ነው ። IT’S my dam ! የጋራ አቋማችንን ሲያዩ ያልነቁ ፣ ዛሬም 'ድር ቢያብር አንበሳ ያስር' ብሂላችን ትርጉሙ በገቢር ጉባ ላይ ቢገለጥ ለተምታታባቸው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ፕሮጀክት ድል ፣ የቅዥት ምናብ ውስጥ እያመላለሳቸው ይመስላል ። የምናብ አድማሳቸው ወሰን የፈረንጆቹ 1929 እና 1959 የሚል የቀኝ ግዛት ውል ላይ ቢጸናም የኢትዮጵያን የተጨበጠ ህልም ግን በወል ሀብታቸው ፤ የወል ታሪክ እያስከተባቸው ይገኛል። ሰሞነኛው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን ጨምሮ ያካለለው የዲፕሎማቶቻቸው ሩጫ በባከነ ሰአትም ቢሆን በቀኝ ግዛት ውሎች ትዝታን አድምጡልን ካልሆነ በቀር ፤ አባይ ሰም እና ወርቅ ለሆነባቸው ኢትዮጵያውያን 'እንዘጭ እንቦጭ 'እስከመቼ እንዲሉ ቢያደርጋቸው እንጂ ከድግሱ ደፋ ቀና ሸብረክ አያደርጋቸውም ። በርግጥ የደስታውን ጣሪያ በፕሮፓጋንዳ ጥላ ውስጥ ሸፍኖ አንዳች ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ መላላጥ እና መጋጋጥ መሆኑን እርቃኑን የሚታይ ክሹፍ ዲፕሎማሲ ነው ። እናማ ይህ ድግስ የወንዝ ተገድቦ ሀይል ማመንጨት ብቻም አይደለም ።ይህን ደስታ ከመዳፋችን ፈልቅቆ ለማውጣት ለሚጥሩ የሚነግራቸውም ጠንካራ መልእክት አለው ። የአድዋ ድላችንን - ለመደሰት 7 አመት ቅድመ - አያቶቻችን ጠብቀዋል ። እዚህ ጋር 'የትርክት እዳና በረከት ' በተሰኘውን የሙአዝ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መጽሃፍን እንግለጥ - ''መጀመሪያው የአድዋ ድል በአል የተከበረው ጦርነቱ በተካሄደ በሰባተኛው አመት በ1895 ዓ.ም ነው ። በአሉም ሲከበር የትእቢትና የጥጋብ እንዳይሆን ጥንቃቄ ተደርጓል ። እግዚአብሄርን ለማመስገን መሆኑም ተገልጧል ።በዚህ ክብረ በአል ላይ ያልተሳፈ የኢትዮጵያ የህዝብ አይነት አልነበረም ። '' ስለዚህም ድላችንን በደስታ እንዳንዋሃድበት ፣ ግጭት እና ጦርነት ያከሰመ መልካችንን እንዳናፈካ የአሸናፊነት ወኔያችን ከጅግጅጋ ሞያሌ ፣ ከጋምቤላ መቀሌ ከጎንደር እስከ ባሌ በአንድ ድምጽ እንዳይስተጋባ አለም ቢቀያየርም ቅሉ በታሪካዊ ጠላትነት የቆሙ እዛው በተውናቸው የቀኝ ግዛት መንደር ናቸው ። ሆኖም ኢትዮጵያዊያን የህዳሴ ግድብ ለልጆቻቸው የአሸናፊነት ልእልና የሚያወርሱበት ጥሪታቸው ነውና ስኬታቸውን ይደሰቱበታል ፤ ይፈነጥዙበታል ፤ ይደልቁበታል ፤ ይንቀባረሩበታልም ። የቅርብ አመታት የጋራ ደስታችን በአትሌቶቻችን ወርቆች ፣ ከ31 አመት በኋላ በአሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ፣ እንዳሻን አፍሪካ ዋንጫ የሄድንበት የታሪክ እጥፋቶች በጋራ ስቀናል ። ደግሞ ወርሃ ሰኔ በ16ተኛው ቀን 2010 ዓ.ም የፖለቲካ ለውጥ እንዲሁ የኢትዮጲያን ድግስ በጋራ ተቀምጠን ፈገግ ማለታችንን አንረሳም ። እናማ አሁንም እንደ አደይ አበባ ቀለማት የኢትዮጲያ የተስፋ ፍንጣቂዎች ስፍራቸውን ይዘዋል ። ምክንያቱም ለዳግማዊ አድዋ ኢትዮጵያ ደግሳለች ። አልጀዚራ ከ14 አመት በፊት Struggle over the nile የተሰኘ ተከታታይ ሶስት ዘጋቢ ፊልም የአባይ ጂኦ ፖለቲካ ታሪካዊ እሰጣ ገባዎችን ወደ ኋላም ወደፊትም ሊዳስስ ሞክሮ ነበር ። ይህም የጋራ ክሮቻችንን ማጽኛ የመሰረተ ድንጋይ ከተቀመጠ ሁለት ወራቶች በኋላ እንደማለት ነው ። በጊዜው ለናይል ኢኒሼቲቭ ድርድሮች ለጋራ ራእይ ፣ የጋራ ወንዛችንን እንጠቀም ላሉት አስር የወንዙ የበይ ተመልካች ሀገራት ይሰጣቸው የነበረው ምላሽ ፊት ከመንሳት አለመተናነሱን ያስመለክተናል ። በወቅቱ የኬኒያ የውሃ ዘርፍ የስራ ሀላፊ ጆን ኒዮሮ አባይን በጋራ በስምምነት ከመጠቀም ውጭ ምንም አማራጭ እንደሌለ ተናግሯል ። ኢትዮጵያ እንደጀመረችው ግድብ ሁሉ ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትም አይደግሙትም ማለት አይቻልም ብለው ነበር ። ፍትሃዊነት ያኔም በመዝገበ ቃላቷ ላይ የሌለ የምትመስለው ሀገር ዛሬም እዛው ነች ።የናይል ኢኒሼቲቭ ግን ወደ ኮሚሽን አድጓል ። ጥርስ ወደ ማውጣትም እየተንደረደረ ይገኛል ። ወንዙን በታንኳ ለመሸራሸር በምስል ለማህደራቸው ማስጌጫ ያደረጉት በርካታ የተፋሰሱ አባል ሀገራት ግን የራእይ መጋራት ከጉባ የህዳሴ ግድብ ምረቃት ድግስ ጠንካራ መልእክት እንደሚሰድላቸው አይጠረጠርም ። ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ''የማይደርቅ የማይነጥፍ ፣ ለዘመን የጸና ።'' እንዳለችው ሁሉ ባለግርማ ሞገሱ አባይ ፣ ኢትዮጲያን ግርማ አልብሶ ለህዳሴውም ተደግሷል ። ጠሪ አክባሪ ነው እንግዶቿም ይጠበቃሉ ። ኤፍ ኤም ሲ

ነሐሴ 18/2017 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ ምስረታን ጨምሮ የስራ አስፈፃሚ እና የስራ አመራር ምርጫ መድረክ ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የጠቅላላ ጉባዔ ምስረታን ጨምሮ የስራ አስፈፃሚ እና የስራ አመራር ምርጫ መድረክ ተካሄደ!! ምርጫው ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ አካታችና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ እንዲካሄድ በሁሉም መስኪዶች ውይይት መደረጉንና 3 አስመራጭና 3 ቅሬታ ሰሚ የማዋቀር ስራ መሰራቱን ተመላክቷል። ምርጫው በ5 ዘርፎች ማለትም ከኡለማ፣ ከሙህራን፣ከወጣቶች ፣ከሴቶችና ከማህበረሰብ ህዝበ ሙስሊሙን የሚወክሉ አባላት ምርጫ ተካሄዷል። በመድረኩ 9 ስራ አስፈፃሚ ጨምሮ 99 አባላት ያሉት የወረዳ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የስራ አስፈፃሚ እና የአባላት ምርጫ ተካሄዷል። በመጨረሻም የወረዳው ሸሬዓ  ፍርድ ቤት ሰብሳቢ ሼህ ግራኝ ለተመረጡ አካላት ቃላ መሃላ እንዲያደርጉ በማድረግ እና የዱአ ፕሮግራም በማካሄድ ተጠናቋል።