917
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+27 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
ታህሳስ 18/2018 ዓ.ም
የከተሞች ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማፋጠን በትኩረት መስራት እንደሚገባ የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ወ/ሮ ትብለጥ ኢስጢፍኖን ገለጹ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የማኔጅመነት ቡድን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ባለፉት ስድስት ወራት በከተሞች የተከናወኑ የልማት ስራዎች የመስክ ምልከታ እና ድጋፍ ባደረጉበት ወቅት ነው።
በመስክ ምልከታው በወረዳው ርዕሠ ከተማ መሃል አምባ የኮብልስቶን ንጣፍ መንገድና የዲች ግንባታዎች፣ ከኢሎ ማዞሪያ መሃል አምባ እየተገነባ የሚገኘው የኮንክሪት አስፓልት፣ የትምርህት ጽ/ቤት G±2 ህንጻ ግንባታ፣መሃል አምባ ዙሪያ ማስፍፊያ የመብራት ዝርጋታና ትራስፎርመር ተከለ፣በሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ የተገነቡ የንጽህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታና ታንከር ግንባታ፣የመሃል አምባ ከተማ ቄራ ግንባታ፣ኢንጌ መዋለ ህጽናት እና አዳራሽ ግንባታ እንዲሁም መሃል አምባ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የካፍቴሪያ ግንባታ እና ሌሎችንም ልማቶች ተዘዋውረው የመስክ ምልከታ በማድረግ በተለይም የመሀል አምባ የፈርጅ 3 ጥያቄ የሚመልስ ተግባራቶች በመኖራቸው ሁሉም ርብረብ የሚጠይቅ መሆኑን ግብረ መልስ ሠጥተዋል።
የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ወ/ሮ ትብለጥ ኢስጢፍኖን የመስክ ምልከታው አለማ አስመልክተው እንዳሉት በወረዳው በዘንድሮ በጀት አመት በከተሞች የተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ለማየትና በዞን ደረጃ መተገዝ ያለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት በማድረግ እንዲፈቱ ለማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።
ከተሞችን ማልማትና ማበልጸግ እንድሁም ለነዋሪዎች የተመቹ ማድረግ የመንግስት ትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ ሁሉም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚያስፈልግ ወ/ሮ ትብለጥ እስጢፍኖስ አክለው አስታውቀዋል።
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው የከተሞች ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ለማፋጠን በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አቶ ሚፍታ አክለውም በዘንድሮ በጀት ለከተሞች መሰረተ ልማት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ በረካታ የልማት ስራዎች እየተሠሩ እንደሚገኙ ጠቅሠው በወረዳው ውስጥ ያሉ ከተሞች እድገት እንዲያፋጥኑ ኢንቨስትመንቶችን በማበረታታት በልዩ ሁኔታ እንደሚሠራ አስገንዝበዋል።
በ2018 በ2ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም በጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ተማም አደም ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት 7 ፕሮጀክቶች 35 ሚሊያን ብር በላይ በጀት ተያዞላቸው የተሰሩት የመሀል አምባ ቄራ ግንባታ ፣ወ/ዲሴና የመሀል አምባ የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ ስራ፣በከተሞች ማስፋፊ አካባቢ የመብራት ዝርጋታ እና የትራንስፎርመር ዝርጋታ ርክክብ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪ የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት ግንባታ 4 መዋለ ህፃናት መመሪያ ክፍል ግንባታ በአራት ማዘጋጃ ቤቶች እና የወ/ዲሴ ፅ/ቤት ግንባታ፣ የኢንጌ መዋለ ህፃነት ግንባታ፣እንዲሁም መንግስት የባለሃብቱን፣ የህብረተሰቡን እና ረጂ ድርጅቶችን አቅም በመጠቀም የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋኑን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ እየተሰራ ባለው ስራ አበረታች ለውጥ ማስመዝገብ መቻሉን የገለጹት አቶ ተማም አደም ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተፈፃሚ እያደረገ ያለው የንፁህ መጠጥ ውሃ ስራ 120 ብር በላይ በሆነ ወጪ 1 ባለ 100 ሜትር ኪዮብ እና 1ባለ 50 ሜትር ኪዮብ ተገጣጣሚ ታንከር ስራ፣ 10 የቦኖ ግንባታን ጨምሮ ከ10 ኪሎ ሜትር መስመር ዝርጋታ እና 3 የትራንስፎርመር ተከላና መስመር ዝርጋታ ግምታ መደረጉን አቅርበዋል።
በወረዳው የመልካም አሰተዳደር ችግር የሆኑ ቀጣይ ልዩ ትኩረት በመስጠት በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት መውቅሮች በቅንጅት መፍታት የሚያስፈልጋቸው አሰተዳደር ፅ/ቤት የቢሮ ግንባታ፣የትምህረት ፅ/ቤት የቢሮ ግንባታ ለረዥም ጊዜ የቆየ ሲሆን የኢንጌ እና ጅማ ማዘጋጃ ቤቶቾ የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማድረግ አንጻር በልዩ ትኩረት መሰራት እንዳለበት በውይይቱ ተመላክቷል።
በመስክ ምልከታና በድጋፉ ላይ የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ ኢስጢፍኖስ፣ የየዘርፉ ኃላፊዎችና የማኔጅመንት አካላት፣የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣
የወረዳው ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተማም አደም እና የማኔጅመነት አባላት ተገኝተዋል።
ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም
ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለማልማት የሚያስችሉ ተግባራት በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን
የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ቢሮ ገለፀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨
ይህ የተገለጸው ከማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል
የተወጣጣ ቡድን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለጉዲ ትሬዲንግ ቡና ልማት ኢንቨስትማነት የመስክ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው።
በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ምክ/ዋና ዳይሬክተርና የምርት ዝግጅትና ገበያ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሳምሶን ወ/ጊዮርጊስ እንደገለጹት
በግብርናው ዘርፍ ለሀገሪቱ ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ከሚገኙ ምርቶች መካከል ቡና ተጠቃሽ ነው።
ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብና ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ቡናና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ቢሮ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሳምሶን ወ/ጊሮጊስ አስታውቀዋል።
በዛሬው እለት የጎበኙት በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ለጉዲ ቡና ልማት ኢንቨስትመነት በክልላችን በስፍትና በጥራት የመጀመሪያው የቡና ልማት እንደሆነ ገልጸው ድጋፍና ክትትሉ በክልሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሳምሶን አክለው ገልጸው።
በጉራጌ ዞን ግብርና መምሪያ የቡናና ቅመማ ቅመም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ቢረዳ እንዳሉት በዞኑ ከ55 ሺህ ሄክታር በላይ በቡና የተሸፈነ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ፍቃዱ አክለውም በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የሚገኝው ለጉዲ ቡና ልማት ኢንቨስትመነት በዞናችን በ2017 በጀት አመት 17 ኩንታል ለውጭ ገብያ በማቅረብ የመጀመሪያ እንደሆነ ተናግረዋል።
የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አ/ረሂም ርዳ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ቡናን ወደ ውጭ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ አቅም የሚፈጥር ዘርፍ መሆኑን ጠቅሠው ቡና ለሀገሪቱ ልማት የሚኖረውን አበርክቶ በአግባቡ ለመጠቀም የቡና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስራዎች በወረዳ ደረጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
በተጨማሪም የወረዳችን ያለውን እምቅ የቡና የማምረት አቅም በአግባቡ በመጠቀምና በማልማት አ/አደሮችን ወደ ዘርፉ በማስገባት በወረዳ የሚገኘውን ለጉዲ ትሬዲንግ ቡና ልማት ኢንቨስትማነት እንደ ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የገብያ ትስስር እንዲፈጠርላቸው በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ አቶ አ/ረሂም ርዳ አክለው አስታውቀዋል።
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ በወረዳው ከ3 ሺህ ሄክታር በላይ የቡና ማሳ በተለያዩ ቀበሌዎች መኖራቸውን አስታውሠው ለጉዲ ቡና ትሬዲንግ ኢንቨስትመንነት በዙሪያው ለሚገኙ አርሶ
አደሮች የቡና ችግኝ በመስጠት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በተቋማቸው በልዩ ሁኔታ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
የለጉዲ ትሬዲንግ ቡና ልማት ስራስኪያጅ የሆኑት
አቶ ጸጋዬ ዘገየ የቡና ልማት በ200 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚገኝ ጠቅሠው 78 ሄክታሩ ቡና መተከሉን እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የምስራች ቡና በ17 ሄክታር 70 ኩንታል ምርት መገኙቱን የገለጹት አቶ 17 ኩንታል ለአለም ገብያ ማቅራባቸውን አስታውቀዋል።
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን አዘጋጅነት በወልቂጤ ከተማ ለሚካሄደው ዞናዊ ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና ውድድር የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ተሳታፊ ስፖርተኞች ሽኝት ተደረገ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከታህሳስ 18/2018 ዓ.ም በሚጀምረው ዞናዊ ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳን ወክለው ለሚሳተፉ ስፖርተኞች ሽኝት በዛሬው እለት ተደረገላቸው።
ለልዑክ ቡድኑ ሽኝት ያደረጉት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዳሉት እንኳን ለ2018 ዓ.ም ዞናዊ ልዩ ልዩ የስፖርት ሻምፒዮና በሰላም አደረሳችሁ በማለት ስፖርት በዋነኝነት ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባሻገር ስፖርት ለሰላም፣ ለወዳጅነት፣ ለፍቅር ከፍተኛ ሚና ያለው መሆኑን አስረድተዋል።
በውድድሩ በስፖርታዊ ጨዋነት እንዲሁም በሁሉም ዘርፍ ውጤት ለማምጣት መጫወት እንዳለበቸው የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው ከውጤት ባሻገር የስፖርት ስነ-ምግባር ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ለስፖርተኞች አሳስበዋል።
የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም በበኩላቸው ለልዑክ ቡድኑ
አጠቃላይ የወረዳውን ህዝብ ወክለው የሚወዳደሩ እንደሆነ አንስተው በስፖርታዊ ጨዋነት በመጫወት በሁሉም የስፖርት አይነት ውጤታማ እንደምትሆኑ እተማመናለሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።
አቶ ሸምሱ አክለውም ዞናዊ ልዩ ልዩ ስፖርቶች ሻምፒዮና ላይ በስድስት የስፖርት አይነቶች እንደሚሳተፉ ጠቅሠው በውድድሩ ላይ ውጤታማ ለመሆን እንዲሁም በስፖርታዊ ጨዋነት ዙሪያ ከስፖርተኞች በቅርበት እየተወያየን ችግሮችን እየፈታን እንሄዳለን ብለዋል።
ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ በይፋ ተጀመረ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የአርሶ አደሮች የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ምዝገባ ማስጀመሪያ የንቅናቄ መድረክ በቡታጅራ ከተማ ተካሂዷል
በብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ እንደገለጹት በክልሉ አርሶ አደሩ የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆን የተጀመረውን ስራ ቀጣይነት ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
የክልሉ ህዝብ የፋይዳ መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆን የተያዘውን ግብ ለማሳካት ቅንጅታዊ አሰራርን ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ሲሉም ኃላፊው ጠቁመዋል።
ፋይዳ መታወቂያ የህብረተሰቡን የልማት እና የመልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት የሚያስችል ነው ያሉት ኃላፊው በተለይ የአርሶ አደሮችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንደሚያሳድግም አብራርተዋል።
ፋይዳ መታወቂያ የአርሶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማረጋገጥ የሚያስችል ስለመሆኑም አቶ ይግለጡ ጠቁመዋል።
ፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ትክክለኛና ህጋዊ ማንነትን የሚያረጋግጥ፣ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲኖር እንዲሁም በአገልግሎት ሰጪውና በተጠቃሚው መካከል ተአሚኒነትን የሚጨምር ስለመሆኑም አስረድተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ተወካይና የቢሮው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አህመድ ሀቢብ በበኩላቸው የፋይዳ ዲጅታል መታወቂያ ስራውን ለማሳካት ዋናው ጉዳይ ተገቢ ትኩረት መስጠት እንደሆነም አመላክተዋል።
የአርሶ አደሩን መረጃ ለማሰባሰብ የግብርና ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸው ፣በስራው ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ተቀራርቦ ለመፍታት ቢሮው በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም አሳውቀዋል።
ያሉንን እድሎች በመጠቀም መሰረታዊ መረጃዎችን በማሟላት የፋይዳ መታወቂያን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባም አቶ አህመድ አስረድተዋል።
በክልሉ 10 ሺ የግብርና ባለሙያዎች መኖራቸውን የገለጹት አቶ አህመድ የአርሶ አደሩን መረጃ በተገቢው መንገድ በማጠናከር ለውጤታማነቱ መስራት ይገባል ብለዋል።
በክልሉ ግብርና ቢሮ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልሃፊዝ ሁሴን መድረኩ መግባባት የተፈጠረበትና ዕቅዱን ለማሳካት ቅንጅት የተፈጠረበት ነው ብለዋል።
በየደረጃው የሚገኙት አደረጃጀቶች ለስራው ስኬታማነት የበኩላቸውን ሚና መወጣት እንዳለባቸውም ስራ አስኪያጁ ጠቁመዋል።
መረጃው የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።
ሦስቱ የመንግሥት ትኩረት አቅጣጫዎች
መንግሥት የሀገር ግንባታ ሂደቱን ለማጽናት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ለሶስት ዋና ዋና ጉዳዮች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ዲሞክራሲን መገንባት፣ ተቋማትን ማጠናከርና ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር፡፡ እነዚህ ሦስቱ ምሰሶዎች ሀገራዊ አንድነትን፣ ሰላምና ብልጽግናን፣ እንዲሁም ዜጎች በመተማመን እና በተጠያቂነት ላይ የተመሠረተ የጋራ ራዕይ እንዲኖራቸዉ የሚያደርጉ ቁልፍ መሰረቶች ናቸው፡፡
ዲሞክራሲን የመገንባት ሂደት ለአንድ ሀገር ወሳኝ ተግባር ሲሆን፣ በዋናነት ነፃ፣ ገለልተኛ እና ብቁ ተቋማትን ማቋቋም ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ፡፡
ተቋማቱ የሚመሩባቸዉ ህጎችና የአሰራር ሥርዓቶች፣ የተቋማቱ አወቃቀርና አደረጃጀት፣ እንዲሁም ለህዝብ ያላቸዉን ተዓማኒነትን መጠበቅ አስፈላጊ በመሆኑ መንግሥት በዚህ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራበት ይገኛል፡፡
ጠንካራ የዲሞክራሲ ባህልና ሥርዓት የሚገነባው ጠንካራ የዴሞክራሲ ተቋማት ሲፈጠሩና ሲጠናከሩ መሆኑን መንግሥት በጽኑ የሚገነዘበው ጉዳይ ነዉ፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ባለፉት 7 ዓመታት በዲሞክራሲ ተቋማት ግንባታ ሂደት ውስጥ ሁለተናዊ ሪፎርም ሥራዎችን ስታከናውን ቆይታለች፡፡
እነዚህ ሪፎርሞች የሀገሪቱን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑትን የዲሞክራሲ ተቋማት ገለልተኛ እና ጠንካራ አድርጎ ለመገንባት መንግሥት ምን ያህል ቁርጠኛ እንደሆነ ያሳየባቸው ናቸው፡፡
የነዚህ ተቋማት መጠናከር በአንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም እና ልማት እንዲረጋገጥ እንደ ዋንኛ ምሰሶ የሚወሰድ ነው፡፡
በተለይም ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ በዲሞክራሲ ተቋማት ላይ የታዩ ተጨባጭ ለውጦች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን ለመጠበቅ፣ እንዲሁም የሕዝቡን ዕምነት ለማጠናከር ወሳኝ እርምጃ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡
መንግሥት በተለይ ተቋማዊ ዐቅምን በማሳደግ እና ነፃነትን በማረጋገጥ፣ የዲሞክራሲ ምህዳርን እንዲሰፋ ለማደረግ የሚጠበቅበት ግዴታ ብቻ ሳይሆን ዲሞክራሲ የሚያብብበትን አስቻይ ዐውድና ማዕቀፍ ለመፍጠር ዓለማው አድረጓል፡፡
ይሄንን ከግብ ለማድረስ በተለይ የፀጥታ፣ የፍትሕ፣ የሲቪልና የሚዲያ ተቋማት፣ እንዲሁም ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሕዝብን ማዕከል አድርገው እንዲሰሩ መንግሥት በቁርጠኝነት በመደገፉ እንደ ሀገር ገለልተኛ ተቋማት እንዲፈጠሩ በማደርረግ ተጨባጭ ዉጤቶች እንዲመዘገቡ አስችሏል፡፡
ሌላው መንግስት በትኩረት እየሰራበት ያለው ጉዳይ እንደ ሀገር ብሔራዊ መግባባትን መፍጠር ነዉ፡፡
ይህ ሂደት ዋና ዓለማ ያደረገው መላዉ ሕዝብ፣ ተቋማት፣ አመራርና ሠራተኛዉ በሀገራዊ ራዕይ ላይ በተለያዩ ድምጾች የጋራ እድገትን በመገንባት ሀገራዊ ህለውና እና ብልጽግና እንዲረጋገጥ እንዲሁም በዜጎች መካከል መተማመን እና ሀገራዊ አንድነትን እንዲፈጠር ማድርግ ነው ፡፡
ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ የብዙሃን ድምጽ የሚሰማበት የፖለቲካ ዐዉድ ለመፍጠር አያሌ የፖለቲካ ማሻሻያዎችን አድርጋለች፡፡
በዚህም እስከዛሬ በነበሩ መንግሥታት ያለተሞከረውን ጫፍ ወጥተው የሚታዩ ተቃርኖ ሀሳቦችን ለማጥበብና ለማቀራረብ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን በማቋቋም፣ ሀገራዊ የውይይት መድረክ እንዲፈጠር ተደርጓል፡፡
በዚህም ገና ከወዲሁ በርካታ ለዉጦች እየታዩ ሲሆን ውሳኔው ለምንመኛት የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን መሆን የማዕዘን ድንጋይ ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡
በአጠቃላይ መንግሥት መልአተ ሕዝቡን በማስተባበር ጠንካራና ብልጽግናዋን በልጆቿ ያረጋገጠች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እያደረገ ባለው ዘርፈ ብዙ ጥረት ዲሞክራሲን መገንባት፣ ተቋማትን ማጠናከርና ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠርን ጉዳይ በልዩ ትኩረት የሚሰራበት ዋንኛው አጀንዳው ሆኖ ይቀጠላል ፡፡
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በ2018 በጀት አመት በመንግስትና ማህበረሰቡ በማሳተፍ 46 ኪሎ ሜትር የመንገድ ስራ ለማከናወን በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ገለጸ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በወረዳው ባለፉት 5 ወራት 6.9 ኪሎ ሜትር አዲስ የጠጠር መንገድና 4.2 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና እንዲሁም 9 ስትራክቸሮች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ረጋ በ2018 በጀት አመት በመንግስትና ህብረተሠቡን በማሳተፍ እንዲሁም የአካባቢ ተወላጅ ባለሃብቶችን በማስተባበር 46 ኪሎ ሜትር መንገድ ለመገንባት ታቅዶ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ባለፉት 5 ወራት 6.9 ኪሎ ሜትር አዲስ የጠጠር መንገድና 4.2 ኪሎ ሜትር የመንገድ ጥገና መደረጉን የገለጹት አቶ አሸብር 9 ስትራክቸሮችን ጨምሮ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት የመንገድ መሠረተ ልማቶች መከናወኑን አስታውቀዋል።
ከመሃል አምባ አዳር ገብያ 4.2 ኪሎ ሜትር ጠጠር መንገድ ጥገና እና ትቦ ስራ፣ከመሃል አምባ ገዎ 3 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድና ሶስት ትቦዎች ፣ከመሃል አምባ ቀጡጥ 2.7 ኪሎ ሜትር መንገድና ሶስት ትቦዎች እንዲሁም ከጥላሞ ኤፍስቲ -ሼሆች መስጂድ 1.2 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድና 1 ትቦ
በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን አቶ አሸብር አክለው ገልጸዋል።
መንገድ ሰፊ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያው እድገት የሚረጋገጥበት እንደሆነ የተናገሩት ኃላፊው መንገድ ወላድ እናቶችን ወደ ጤና ተቋም እንዲሄዱና የግብርና ስራዎች የሚያሳልጥ እንደሆነ ያወሱት አቶ አሸብር የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በተገቢው ምላሽ ለመስጠት ህብረተሠቡና ባለሃብቶች የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ገልጸው የተገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ህዝቡ በባለቤትነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባው አስገንዝበዋል።
