fa
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
917
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+27 روز
+930 روز
آرشیو پست ها
ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም የጉራጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት መምሪያ የ2018 በጀት አመት የ5 ወራት አፈጻጸም አስመልክቶ የማኔጅመንት ቡድን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ድጋፍና ክትትል አደረገ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የዞን የማኔጅመነት ቡድኑ በጽ/ቤት እንዲሁም በመስክ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በተሰሩ የስራ እድል ፈጠራዎች በመንቀሳቀስ ተመልክተዋል። የድጋፍና ክትትሉ ዋና ዓላማ ያለፉት አምስት ወራት አፈጻጸም ያሉበትን ደረጃ ለማየት እንደሆነ ተገልጿል። በድጋፍ ወቅት በጥንካሬና በጉድለት የተለዩ እንዲሁም በቀጣይ በልዩ ትኩረት መሰራት የሚገባቸው ጉዳዮች ግብረ መልስ በመስጠት እና የጋራ መግባባት ተፈጥሮል።

የሕዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት፡- 👉🏾ፋይዳን፣ 👉🏾ዲጂታል ከፍያን፣ 👉🏾ዳታ ልውውጥን የሚያዋህድ ነው በዚህም፡- 👉🏾የአንድን ሰው ማንነት በቀላሉ ለማረጋገጥ፣ 👉🏾ደኅንነቱ የተጠበቀ ክፍያ ለመፈፀም፣ 👉🏾ደኅንነቱ የተጠበቀ የዳታ ልውውጥ ለማድረግ ያስችላል

ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ የመስኖ ስራዎች እንቅስቃሴ በምስል በከፊሉ፦

ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ማዕከል እና ታዳጊ ከተሞች ላይ "የጉባ ብስራቶች፣ የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውይይት ተካሄደ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በወረዳው በሚገኙ በተለያዩ አራት ማዘጋጃ ቤቶች "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ተካሂደዋል። መድረኮቹ በመሃል አምባ፣ኢንጌ፣ጅማ እና ኮንበል ማዘጋጃ ቤቶች ተካሂዷል። ለውይይቱ መነሻ የሚሆን ሰነድ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። የውይይት ዋና አላማው ህዝቡ ራሱ የተሳተፈባቸው የመደመር መንግስት ትሩፋት የሆኑ ዋና ዋና ስኬቶችና ቀጣይ ብስራቶች ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር እነዚህን ድሎችና ብስራቶችን ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ከማድረግ እንጻር ህዝቡ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ማዘጋጀት እንደሆነ ተመላክቷል። በተጨማሪም በተለያዩ ግዚያት በህዝብ የተነሱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ መንግስት የሄደበትን ርቀትና የደረሰበትን ደረጃ ህዝቡ እንዲረዳ የሚያደረግ መድረክ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ብልጽግና ፓርቲ እና የመደመር መንግስት የልማቱ ባለቤት የሆነውን ህዝብ በማሳተፍ እና በማዳመጥ የሚያደርጉት ህዝባዊ ውይይት በቀጣይነት የመንግስትን የማስፈፀም አቅም እና የህዝቡን የነቃ ተሳትፎ እያጎለበተ ለመሄድ የሚያስችል ነው። በመድረኩ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት የተሠጠ ሲሆን መንግስት የህዝብ ጥያቄዎች ተቀብሎ በሂደት ለመመለስ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ተጠቁሞ በስኬት የተጀመሩ ስራዎች ከዳር በማድረስ ኢትዮጵያን ለማበልፀግ በሚደረገው በልማት ጉዞ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል የበኩሉን መወጣት እንዳለበት በመግባባት መድረኮቹ ተጠናቀዋል። በመድረኮቹ ላይ የዞንና የወረዳ መካከለኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም "የጉባ ብስራቶች የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመሃል አምባ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመድረኩ "የጉባ ብስራቶች ፣የመደመር መንግስት ትሩፋቶች" በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ፅሁፍ እና በየከተሞች የተሰሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷበታል። በመድረኩ የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሠን፣የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንዲሁም የወረዳ አመራሮችና የመሃል አምባ ከተማ ነዋሪዎች

ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም አዲሱ የ“ዜሮ ግቦች” ንቅናቄ ለኢትዮጵያ ብልጽግና ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተዋወቀው እና ሀገራችን ልትደርስበት የሚገባት አምስት ዋና ዋና የ“ዜሮ” ግቦች ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ ነው። እነዚህ አምስት ወሳኝ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፡- 1. ዜሮ ተረጂነት (Zero Dependency) የትውልዱ ትልቁ እዳ የሆነውን ድህነት እና የእርዳታ ጠባቂነትን ታሪክ መቀየር በምግብ ራስን በመቻል ማንም ሰው ለምግብ እጁን የማይዘረጋበትን ሀገር መገንባት ዋናው ግብ ነው። 2. ዜሮ መሬት ጦም ማሳደር (Zero Uncultivated Land) መሬት የሀብት ምንጭ ነው። አንዲትም ስንዝር መሬት ሳትታረስ እና ምርት ሳትሰጥ ጦሟን እንድታድር አይፈቀድም። በጋ እና ክረምት በመስራት ምርታማነትን ማሳደግ ግዴታ ነው። 3. ዜሮ ተፈናቃይነት (Zero Displacement) ዜጎች በገዛ ሀገራቸው ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያ እንዲኖሩ አይገባም። የተፈናቀሉትን መመለስ እና ዳግም መፈናቀል እንዳይኖር ዘላቂ ሰላምን ማስፈን። 4. ዜሮ ኮንትሮባንድ (Zero Contraband) የሀገርን ኢኮኖሚ የሚቦረቡረውን እና ህጋዊ የንግድ ስርዓትን የሚያዛባውን የኮንትሮባንድ ንግድ ሙሉ በሙሉ ማድረቅ። 5. ዜሮ ሸፍታ እና ሌባ (Zero Crime/Banditry) ሰላም ለሁሉም መሰረት ነው። በጫካ የታጠቁ ሀይሎችን (ሸፍታ) እና በከተማ የሚንቀሳቀሱ ሌቦችን በማጽዳት የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ሰላማዊ ሀገር መፍጠር። እነዚህን "የዜሮ ግቦች" ለማሳካት የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ተሳትፎ ያስፈልጋል!!

ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም የስርዓተ ጾታን ጉዳይ በልማት ሂደት ውስጥ ማካተት የሴቶችን አቅም ማሳደግና የውሳኔ ሰጭነት ብቃት ማሳደግ እንደሚገባ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽ/ቤት ገለጸ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ይህ የተገለጸው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ፅ/ቤት በስረዓተ ፆታ መካተት እና የልማት ለውጥ መመሪያ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና በሰጠበት ወቅት ነው። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ መህዲ በመድረኩ ላይ ፆታዊ ጥቃት እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች በሴቶችና ህፃናት ውስብስብ ችግሮች እንደሚያስከትሉ ጠቅሠው የስርዓተ ጾታን ጉዳይ በልማት ሂደት ውስጥ ማካተት የሴቶችን አቅም ማሳደግ፣ የውሳኔ ሰጭነት ብቃት ማሳደግና አሰራርን ማሻሻል ያስፈልጋል ያሉት ወ/ሮ ፈትያ መህዲ ሌሎች በሁሉም ዘርፎች አካታችና እኩል ተጠቃሚነት ላይ አሳታፊ ለማድረግ ያለመ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል። የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት የጽ/ቤቱ የሴቶችና ህጻናት ማካተትና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ስራ ሂደት አስተባባሪ በአቶ መርሻ አስቻለው አማካኝነት ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይትና ምክክር ተካሄዷል። ሴቶችና ህፃናት ተቋም የሴቶችን መብት ማስጠበቅ እንደሚገባው፣በሴቶች ላይ የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶች ሁሉም በጋራ መከላከል እንደሚገባ፣ ወንጀል የፈፀሙ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ ማድረግ፣በየተቋማቱ የህፃናት ማቆያ መዘጋጀት እንዳለበት እንዲሁም ሴቶችን በጎልማሳ ትምህርት ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል ያሉት የስልጠና ተሳታፊዎቹ የተሠጠው ግንባዜ ጥሩ ነው ሁሉም የሚመለከተው ባለሙያ ወደ ራሱ ተቋም ወስዶ መስራት ያስፈልጋል፣ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ የተሳካ እንዲሆን ቅንጅታዊ አሠራሮች ማጠናከር እንደሚገባ ከመድረኩ ተመላክቷል። የወረዳው ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፈቲያ መህዲ ከመድረኩ ለተነሱ ሀሳብ አስተያየት ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰው ጥቃት በየደረጃው የሚገኙ አካላት የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው ገልጸው ለሴቶች መብት ጥሰት የተጋለጡ ሴቶችን ተገቢውን ፍትህ እንዲያገኙ እንዲሁም አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። በመጨረሻም ወ/ሮ ፈትያ ባስተላለፉት መልዕክት ከፆታዊ ጥቃት የፀዳ እና ለሴቶች ሚመች አከባቢ ለመፍጠር ሁሉም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። በስልጠና መድረኩ የተቋማት የስርዓተ ፆታ ተጠሪዎች እና ልማት እቅድ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።