fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید 👈

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
924
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+57 روز
+1030 روز
آرشیو پست ها
ፕሬስ ሪሊዝ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት የእውቅናና የሽልማት ፕሮግራም ሊያካሂድ ነው። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ፅ/ቤት አጠቃላይ የ2017 በጀት አመት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገም እንዲሁም በመመዘን የእውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም ነገ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ሊያዘጋጅ መሆኑን የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ፍሪስ ከማል ተናግረዋል። አቶ ፍሪስ እንደተናገሩት የዕውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓቱ ተቋማትና ባለሙያዎች የበለጠ ተግተው እንዲሰሩና ሕዝቡን በታማኝነት እንዲያገለግሉ አቅምና ተነሳሽነትን የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት።

ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም የ2018 ዓመተ ምህረት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማ በምስል፦ FMC

ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ቅርንጫፍ ፅ/ቤት በ2018 የመጀመሪያ ሩብ አመት ከ50 ሚሊዮን 717 ሺህ ብር በላይ ገቢ በመሰብሰብ የእቅዱን 76 በመቶ ማሳካት መቻሉን አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በ2018 በጀት አመት 265 ሚሊዮን 049 ሺህ 886 ብር ታክስ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑንም አክሎ ገልጿል። የወረዳው ገ/ባ/ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ረመዳን ከድር አፈጻጸሙን አስመልክተው እንደገለጹት በ2018 ዓ.ም አንደኛ ሩብ አመት 66 ሚሊዮን 261 ሺህ 721.50 ብር ገቢ ለመሰብሰብ በማቀድ ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሠው ከመደበኛ ገቢ 58 ሚሊዮን 492 ሺህ 606 ብር ገቢ ለመሰብሰብ በማቀድ 46 ሚሊዮን 981 ሺህ 510.70 ብር ታክስ መሰብሰብ ተችሏል ያሉት ኃላፊው ይህም የእቅዱን 80.32 በመቶ ማከናወን እንደተቻለ አብራርተዋል። ከማዘጋጃ ቤት ገቢ 7 ሚሊዮን 769 ሺህ 115.50 ብር ገቢ በሩብ አመቱ ለመሰብሰብ የተያዘውን እቅድ መሰረት በማድረግ 3 ሚሊዮን 735 ሺህ 621 ብር ገቢ መሰብሰቡንና የእቅዱን 48.1 ተግባራዊ ስለመደረጉ ገልጸው ሁሉም ማዘጋጃ ቤቶች ገቢም አሟጦ ከመሰብሠብ አንጻር ያለው ውስነት አፈጻጸሙን ዝቅ አድርጎታል ብለዋል። በመጀመረያው 3 ወራት 66 ሚሊዮን 261 ሺህ 721 ብር ታክስ ለመሰብሰብ ታቅዶ 50 ሚሊዮን 717 ሺህ 132.32 ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 76.54 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ አቶ ረመዳን ከድር አስታውቀዋል። የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈጻጸም ከአመቱ እቅድ ጋር ሲነጻጸር የመደበኛ ገቢ 20% ማዘጋጃ ቤት ገቢ 12 % መሆኑን አቶ ረመዳን አክለው ገልጸዋል። በመጨረሻም አቶ ረመዳን ከድር ባስተላለፉት መልእክት ገቢ ለአንድ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ልማት መረጋገጥ አይነተኛ ሚና የሚጫወት እንደመሆኑ ህብረተሰቡ የሚሾልኩ ገቢዎችን ሲመለከት ለተቋሙ ጥቆማዎችን በመስጠት ሃላፍትናውን ሊወጣ እንደሚገባ እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ገቢ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊሠሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ሲል የዘገበው የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ነው።

ጥቅምት 12/2018 ዓ.ም የተሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመፈጸም እና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የአመራሩን አቅም ማሳደግ ይገባል :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር ) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል"ብቁ አመራር ለላቀ ውጤት" በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ ክልላዊ የአመራር የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በተለያየ ወቅት የሚሰጡ ስልጠናዎች የአመራሩን አቅም እውቀት፣አስተሳሰብ ለማሻሻል ፣የተለያዩ ችግሮችን ለመሻገር፣አዳዲስ አስተሳሰቦችን መሰረት አድርጎ ለመስራት አቅም ይሆናሉ ብለዋል። የተሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመፈጸም ያስችላል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሻለ እገዛ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል። የአቅም ግንባታ ስልጠናው አመራሩ በቂ ህልም እና ራዕይ እንዲሰንቅ ያስችላል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። በሌላ በኩል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የአመራሩን ጊዜ እና ግንዛቤ በማቀራረብ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል። ከመንደር አጀንዳዎች በመውጣት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር የህዝብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ የሚያስችል ስልጠና መሆኑንም አብራርተዋል። የነጠላ ትርክቶችን በማረም የጋራ ትርክቶችን መፍጠር ተገቢ ስለመሆኑ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ የሚያስተውል፣በምክንያታዊነት የሚያምን እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ማስፈን የሚያስችል አመራር በመፍጠር ረገድ ስልጠናው የላቀ ጠቀሜታ እንዳለው ጠቁመዋል። አመራሩ የስልጠናውን አላማ በመረዳት በክልሉ የተጀመሩ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በውጤታማነት ለመተግበር በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበትም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ብላቱ በበኩላቸው ለሁለንተናዊ ብልጽግና የሚተጉ ሀገራዊና ክልላዊ የልማት ግቦቻችንን በስኬት የሚፈጽሙ አመራሮችን ለመፍጠር የጥናትና ምርምር እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው ብለዋል። በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ስራቸውን በብቃትና በውጤታማነት ማከናወን የሚያስችላቸው ስልጠና ስለመሆኑም ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በመጎራጉር ቀበሌ በገጠር ስራ እድል ፈጠራ በተደራጁ ወጣቶች ከ20 ሄ/ር በላይ በኩታ ገጠም የሚለማ ስንዴ እና ገብስ አሁናዊ ቁመና በምስል በከፊሉ፦

ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም የመሀል አምባ ከተማ የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የወረዳው መንግስት ከከተማው ማዘጋጃ ቤትና ከከተማው ነዋሪ በቅንጅት እንደሚሰራ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን አስታወቁ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በመሀል አምባ ከተማ በመልካም አስተዳደር እና በልማት ጉዳዮች ከከተማው ህዝብ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄዷል። የመሀል አምባ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ መሀመድ አወል ለመድረኩ የተዘጋጀውን የልማትና የመልካም አስተዳደር አፈጻጸምና የቀጣይ እቅዶች አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። በመድረኩ የተገኙ ነዋሪዎች በስጡት አስተያየት የመሀል አምባ የከተማ አሰተዳደር ወይም የፍርጅ ሶስት ጥያቄ ትኩረት እንዲሰጠው ፤የመሀል አምባ ከተማ ገፅታ ለመቀየር እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ፣ የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የነበሩ ለመፍታት የተደረገው እንቅስቃሴ ለአብነት የመራብት ፤የውሀ ፤የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ከፈታና እና ድልድይ ግንባታ እንዲሁም የረዥም ጊዜ የህዝቡ ጥያቄ የነበረው የኮንክሪት አስፓልት መንገድ ፕሮጀክት በፍጥነት እየተገነባ መሆኑ በጥንካሬ የጠቀሱ ሲሆን በአንጻሩ የመሀል አምባ ከተማ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ስፍራ በዘላቂነት ያለመቅረፍ ፣ማስፋፊያ ሰፈር የመብራት እና የውሀ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን አለመቻላቸው ፣በከተማው ውስጥ ተሰርተው ያልተጠናቀቁ ቤቶች የሌባ መሸሸጊያ መሆናቸው በከተማው የተሻሻለ የህዝብ የጋራ መፀዳጃ ቤቶች አለመኖራቸው ፣ የመሀል አምባ የከተማ መስተዳድር ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ በትኩረት መሰራት እንድለበት በጉድለት ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። የውይይት መድረኩን የመሩት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እንደተናገሩት ባለፈው በጀት አመት በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥያቄ ለመመለስ ጥረት መደረጉን አንስተው አዲስ መንገድ ከፈታና ጠጠር ማንጠፍና የተለያዩ ድልድይ ስትራከቸሮች፣ የመብራት ዝርጋታ፣ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ካሳ በመክፈል ለማህበራት አገልግሎት የሚውል መሬት መዘጋጀቱ እንዲሁም የመሀል አምባ ማዘጋጃ ቢሮ ግንባታ፣ የመሀል አምባ ጌጠኛ ንጠፍ መንገድ መስረቱን ገልጸዋል። በ2018 በጀት አመትም ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ የመሠረተ ልማትና ተያያዥ ስራዎች ለመስራት መታቀዱን ተናግረዋል። በመጨረሻም አቶ ሚፍታ እንዳሉት የመሀል አምባ ከተማ ከፈርጅ 4 ወደ ፈርጅ 3 ማሳደግ በዘንድሮ በጀት አመት ትኩረት ተስጥቶት እንደሚሰራ ጠቅሠው የከተማውን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ የወረዳው መንግስት ከከተማው ማዘጋጃ ቤትና ከከተማው ነዋሪ በቅንጅት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል።

‌‎ጥቅምት 11/2018 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመሀል አምባ ማዘጋጃ ቤት የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያው ሩብ አመት በመልካም አስተዳደር እና በልማት ጉዳዮች ከከተማው ህዝብ ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የመሀል አምባ ማዘጋጃ ቤት ስራስኪያጅ የሆኑት አቶ መሀመድ አወል የ2018 የመጀመሪያው ሩብ አመት የመልካም አስተዳደርና የልማት ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ መቻሉን ገልጸዋል። ‌‎በህዝብ ውይይት መድረኩ ላይ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ፣የወረዳው ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አ/ረሂም ርዳን ጨምሮ ሌሎችም የከተማው አመራሮች፣የሀይማኖት አባቶችና የከተማው ነዋሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ። ዝርዝር መረጃውን አጠናቅረን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የየደረጃው አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊ ሁኔታዎች ላይ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየደረጃው ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ክልላዊ የፖለቲካና የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ በሰባቱም ክላስተሮች፣ ዞኖችና የልዩ ወረዳዎች ውይይት እያደረጉ ነው። ‎ ‎ፈጣንና አስደማሚ ዕድገት በክልሉ መመዝገቡ በመድረኮቹ የተነሳ ሲሆን፣ለዚህም በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ህዝብ ሚና ከፍተኛ እንደነበርም ውይይት ተደርጎበታል። ‎በአጠረ ጊዜ ክልሉን የብልጽግና ተምሳሌትና የምርጥ ተሞክሮ መቀመሪያ ለማድረግ የሚያስችሉ ጠንካራ ስራዎች በየደረጃው እየተከናወኑ እንደሚገኙ አመራሮቹ በውይይታቸው አረጋግጠዋል። ‎ ‎የክልሉ አመራር ውጤት እያስመዘገበ እንዳለና ህዝቡም በአመራሩ ላይ ዕምነት እያሳደረ ስለመምጣቱም በመድረኮቹ ተነስቷል። ‎ ‎የተጀመሩ አጓጊና ተስፋ ሰጪ ስራዎችን በማጠናከር የክልሉን ህዝቦች ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ አመራሩ የተግባር እና የአመለካከት አንድነት መፍጠር እንደሚገባውም ተብራርቷል። ‎ ‎በክልሉ በርካታ ድሎች እየተመዘገቡ ቢሆንም አንዳንድ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መሰረት በማድረግ በውስን አካባቢዎች የግል ፍላጎታቸውን በህዝብ ስም ለማሟላት ነጠላ ትርክት የሚነዙ ውዢንብር ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉም በመድረኮቹ ተነስቷል። ‎ ‎የክልሉ መንግስት ያደሩ የህዝቦች ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት ያደረገውን ጠንካራ ጥረት የገመገሙት አመራሮቹ ፣የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ በየአካባቢው የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እንደሚሰሩም አሳውቀዋል። ‎ ‎በመድረኮቹ ጠንካራ የፖለቲካ ስራ መስራት፣በቂ ተግባቦት መፍጠር፣የህግ የበላይነት ማረጋገጥ፣የውስጠ ፓርቲ ዴሞክራሲን ማጠናከር፣የሰላ ትግል ማድረግ፣ፍጥነትና ፈጠራ የታከለበት ስራ መስራት፣ገዢ ትርክትን በመገንባት የህዝቦች አንድነትን ማጎልበት በድምሩም የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የጋራ መግባባት ተደርሷል። የወልቂጤ ክላስተር የክልል አመራሮች፤ የጉራጌ ዞን እና የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በጋራ በክልሉ ወቅታዊ የፓለቲካና የፀጥታ ሁኔታ በዛሬው እለት ተወያይተዋል።