fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
925
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+47 روز
+1130 روز
آرشیو پست ها
ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2018 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም በመሀል አምባ ከተማ እየገመገመ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ መድረኩም አጠቃላይ የወረዳው የሩብ አመት አፈፃፀም በሴክተር ኃላፊዎች እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን በጥንካሬ እና በጉደለት ተግባራትን ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ይሆናል። በግምገማ መድረኩም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን፣የወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች ተገኝተዋል። ዝርዝር መረጃውን አጠናቅረን የምናደርሳችሁ ይሆናል።

የተቀዳሚ ሙፍቲህ ሐጂ ዑመር እድሪስ ህልፈትን በማስመልከት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ያስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የነበሩት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በማረፋቸው ኀዘን ተሰምቶኛል። ሐጂ ዑመር በአመራር ዘመናቸው የተለያዩ ወገኖች ወደ አንድነት እንዲመጡ እና የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሕግ ዕውቅና እንዲኖረው ያደረጉትን አስተዋጽዖ ሁሌም እናስታውሰዋለን። ለቤተሰቦቻቸው እና ለመላ ኢትዮጵያ ሙስሊሞች መጽናናትን እመኛለሁ።

ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም የህብረተሰቡን የጤና ባለቤትነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን አስገነዘቡ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በወረዳው “በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እዉቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ/ም ማጠቃለያ የጤና ጉባኤ ዛሬ ተካሂዷል። የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ሰይፉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የጤና ሴክተሩ በ2017 በጀት ዓመት በርካታ ስራዎች መስራቱን ተከትሎ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልፀዋል። የጤና አገልግሎት ተደራሽነት ጥራትና ፍትሀዊነት በማረጋገጥ የእናቶችና ህፃናት ሞት መቀነስ ተችሏል ያሉት ኃላፊው በሽታን አስቀድሞ መከላከል መሰረት በማድረግ የመፀዳጃ ቤት ሽፋን ከማሳደግ በተጨማሪ 7 ቀበሌዎችን ከአይነድር ጽዱ በማድረግ ማስመረቅ መቻሉን በመጥቀስ ህብረተሰቡ በከፈለው ልክ ሳይሆን በህመሙ ልክ መታከም እንዲችል ከ75 በመቶ በላይ አባዎራዎችን የማዐጤመ አባል ማድረግ እንደተቻለም አክለዋል። የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። አክለውም መንግስት የህብረተሰቡን የጤና ባለቤትነት ለማረጋገጥ እያከናዋናቸው ባሉ ዘርፈ-ብዙ ተግባራት የተሻለ የጤና ዉጤት እየተገኘ ስለመሆኑም አብራርተዋል። በአንፃሩ በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ በሚል እየተካሄደ ያለውን ግብ ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንዲቻል በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸዉ ያሳሰቡት ዋና አስተዳዳሪዉ መንግስት ለጤናው ዘርፍ እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የፅ/ቤቱ ዋና ሀላፊ አቶ ሙባሪክ ሰይፉ “በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት የማስፈን ጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ በሁሉም ደረጃ መፍጠር” ዓላማው ያደረገ የንቅናቄ ሰነድ አቅርበዋል። በተጨማሪም የፅ/ቤቱ ልማት እቅድ ባለሙያ የሆኑት አቶ ገለቱ አያንሳ የ2017 ዓ/ም ዕቅድ አፈፃፀም አቅርበው ዉይይት ተደርጎ የቀጣይ አቅጣጫ ተመላክቷል። የአገልግሎት አሰጣጥ መጓደል፣ የአምቡላንስ አገልግሎት አሰጣጥ ችግር፣ የመድሃኒት አቅርቦት ውስንነት፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ የተሟላ አለመሆኑን ከተነሱ ሃሳብና አስተያየቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። በመድረኩ ማጠቅለያ ወቅት የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ለተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት እንዳሉ በጤናው መስክ የተያዙ ውጥኖች መሳካት እንዲችሉ ሁሉም አካላት በይቻላል መንፈስ ተቀናጅቶ በተደራጀ መልኩ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። የወረዳው ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙባሪክ ሰይፉ በበኩላቸዉ ጥራቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ ምርታማ ዜጋ ለመፍጠር የተጀመረው ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸው ከጉባዔ መድረኩ በኩል በጉድለት የተነሱ ጉዳዮች የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ እንደመሰራ አስታውቀዋል። በመጨረሻም በ2017 ዓ/ም የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ፣ የጤና ተቋማት፣ሞዴል እማወራዎች፣ ለቀደሞ የወረዳውጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ለሚድሮክ ኢንቨስትመነት ግሩፕ እና ለአሚን ጠቅላላ ሆስፒታል የተዘጋጀላቸውን የእውቅና ሽልማት ከዕለቱ እንግዶች እጅ ተቀብለዋል። ዘገባው የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ፅ/ቤት ነው።

ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ የሚኖሩ የከሲብ ወንጀላ መረዳጃ ማህበር ከ550 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የትምህርት መማሪያና ማጣቀሻ መጽሃፍቶችና የተማሪዎች ወንበር ከሲብ ማራንቶ ቀበሌ ለሚገኙ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በርክክቡ ወቅት እንዳሉት እውቅት የሁሉም ነገር ቁልፍ መሳሪያ ነው። መንግስት ጠንካራ የትምህርት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች በመንደፍ ህብረተሠቡን ተወላጅ ባለሃብቱንና ረጂ ድርጅቶችን በማሳተፍ የትምህርት ተቋማትን ከማስፍፍት በተጨማሪ የትምህርት ቁሳቁስ ለማሟላት አጽኖት ሠጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። አቶ ሚፍታ አክለውም የአንጮት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ 2ኛ ደረጃ ለማሳደግ የወረዳው መንግስት በርካታ ስራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ጠቅሠው በዘንድሮ በጀት አመት ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በመመደብ ግንባታዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በመሆኑም ተወላጆች የአዲሱ ካሪኩልም መጽሃፍት አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረጉ ሲሆን በዛሬው እለትም ከ550 ሺህ በላይ የተማሪዎች መማሪያና ማጣቀሻ መጽሃፍት እንዲሁም የተማሪዎች መቀመጫ ኮንበይን ዴስኮች ድጋፍ ያደረጉ የከሲብ ወንጀላ መረዳጃ አባላት የሰሩት ስራ ለሌሎች አርዓያነት የሚጠቀስ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው ድጋፉን በማድረግ የተሳተፉ አካላትን በወረዳው ህዝብና መንግስት ስም አመስግነዋል። የወረዳው ትምህርት ቤቶች ጽህፍት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየው ኬኔ መንግስት የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ አዲስ ፍኖተ ካርታ ቀርጾ ወደ ተግባር ገብቷል። ሃገራችን ባጋጣሟት ወቅታዊ ፈተናዎች ምክንያት መጽሃፍ በበቂ ማቅረብ እንዳልተቻለ ገልጸዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመፍታት መንግስትና ህብረተሠቡ ተቀራርበው መሰራት በመቻላቸው አሁን ላይ አበረታች የሆኑ ውጤት ማየት እየተቻለ ሲሆን ዛሬ 550 ሺህ ብር በላይ የተማሪዎች መማሪያና ማጣቀሻ መጽሃፍ እና የተማሪዎች ወንበር ድጋፍ ያደረጉ ተወላጆችን በትምህርት ሴክተሩ ስም አመስግነው መሠል እገዛዎች መጠናከር ይኖርበታል በለዋል። የከሲብ ወንጀላ ልማትና መረዳጃ አባል የሆኑት አቶ ተማም አረብ ድጋፋን አስመልክተው እንዳሉት ከሲብና ማራንቶ ቀበሌ ለሚገኙ አምስት 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማለትም ለኮንበል፣ለአዳዘር፣ አንጮት ፣እንደብዮ ቁጥር 1 እና ወልያባቦ ትምህርት ቤቶች የሚሆን 2 ሺህ የተማሪዎች መማሪያና ማጣቀሻ መጽሃፍ፣ 60 የተማሪዎች ኮንባይን ዴስክ፣ 130 ቆርቆሮ እና አንድ በርና መስኳት ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል። አቶ ተማም አክለውም በየትምህትቤቱ የሚስተዋሉ የመማሪያ መጽሃፍ፣ የመማሪያ ክፍል የጥራትና የግብዓት ችግሮችን ለመፍታት የሚያደርገውን ጥረት እንደ ተወላጅ ህብረተሠቡን ማገዝ በቀጣይም ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል። የከሲብ ወንጀላ ልማትና መረዳጃ ሰብሳቢ የሆኑት ዶክተር አቡበከር አስፋ በመድረኩ ተገኝተው ተማሪዎች በስነ ምግባር ታነጽው ውጤታማ እንዲሆኑ የህይወት ተሞክሮቸው በመቅረብ አስተማሪ ምክራቸውን ለግሰዋል። በመጨረሻም ይሄን በጎ ተግባር ላስተባበሩ አካላት የወረዳው መንግስት የእውቅና ሠርተፋኬት በማበርከት ፕሮግራሙ ተጠናቋል።

ጥቅምት 09/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ የጤና ጉባኤ "በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በመሀል አምባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉባኤው ላይ ወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እና የወረዳ አመራሮች፣የዞን ጤና መምሪያ ተወካዮች፣ የጤና ተቋማት ኃላፊዎች፣ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የቀበሌ ሊቀመንበሮች ፣ የሴቶች ተወካዮች፣የህዝብ ክንፍ አባላትና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ተጨማሪ መረጃዎች ይዘን እንመለሳለን!!!

የሳምንቱ አበይት ዜናዎች ጥቅምት 9/2018 ዓ.ም 👉🏼‎ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አንበልታ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በከፊሉ፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በክልሉ ፈጠራና ፍጥነት በመጨመር የተከናወኑ ስራዎች አፈጻጸም ውጤታማ ነው :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሸው ጣሰው (ዶ/ር ) ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ጥቅምት 07/2018 ዓ.ም 👉🏼‎በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመስኖ ቅድመ ዝግጅት አሁናዊ ሁኔታ በከፊል፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎👉🏼‎የህብረተሠቡን የንጹህ መጥ ውሃ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እየተደረገ ያለውን ርብርብ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት ገለጸ። ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ እንኳን ደስ አላችሁ ‎👉🏼‎የጉራጌ ዞን ትራንስፖርት መንገድ መምሪያ ባካሄደው 2017 ዓ.ም የተግባር አፈፃፀም ሴክቶሪያል ጉባኤ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ትራንስፖርት መንገድ ልማት ጽ/ቤት በአጠቃላይ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በገዳባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሶዶ አይብገረን ቀበሌ እየለማ የሚገኝ የጤፍ ማሳ አሁናዊ ቁመና በምስል፦ 👉🏼‎ፋኦ ለኢትዮጵያ "ዘላቂ የደን ልማት አያያዝና አጠቃቀም" በሚል ዘርፍ እውቅና ሰጠ ‎፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ‎ 👉🏼‎ከተሞችን በሚፈለገዉ ደረጃ በማልማት ለነዋሪዎች ምቹና ማራኪ ለማድረግ የሚደረገውን ርብርብ በየደረጃው የሚገኙ አካላት ማገዝ እንደሚጠበቅባቸው የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል የዲጂታል ስርዓት አስጀመረ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የትምህርት ጥራት በላቀ ደረጃ ለማረጋገጥ የተቀረፁ 5 ኢንሼቲቮች ይፋ ሆኑ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎እንኳን ደስ አለን እንኳን ደስ አላቹ!!! የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢንርጂ ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ከዞን መዋቅሮች 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆን ችሏል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ - ብዝኃ ኃይልን የማስፋፊያ መንገድ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎ሴቶችን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ተጠቃሚ ለማድረግ በተጠናቀቀው በጀት አመት አበረታች ስራዎች መስራቱ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ  ፍርድ ቤት ከነሐሴ 01 ጀምሮ በከፊል ተዘግቶ የነበረውን የፍርድ ቤት አገልግሎት ከጥቅምት 03/2018 ዓ.ም በይፋ መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገለፀ።  ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በገዳባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አንበልታ ቀበሌ እየለማ የሚገኝ የጤፍ ማሳ አሁናዊ ቁመና በምስል፦ ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ 👉🏼‎በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ወጣቶችና ስፖርት   ጽ/ቤት አዘጋጅነት በመንግስት ሰራተኞች የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል ሲካሄድ የቆየው የክረምት ወራት የእግር ኳስ ውድድር በባንኮች አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨