fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

رفتن به کانال در Telegram
925
مشترکین
+224 ساعت
+27 روز
+830 روز
آرشیو پست ها
ነሐሴ 03/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአብይ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ከዞን በተሰጠው ግብረ መልስ ላይ ውይይት ተካሄዷል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የጉራጌ ዞን የበጎ ፍቃድ ቴክኒክ ኮሚቴ አማካኝነት በተደረገው ድጋፍና ክትትል በተሰጠው ግብረ ላይ እንዲሁም የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስካሁን ተግባራት አፈፃፀም የአብይ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የበጎ ፈቃድ ስራዎች በተገኙ አበረታች ውጤቶችና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ተቀምጧል። በውይይቱ ላይ የጉረጌ ዞን ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ እና የወረዳው ደጋፊ አመራር፣የጉረጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊ እና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ሸሃቡ እንዲሁም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን እና የወረዳው የበጎ ፍቃድ አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

ነሐሴ 02/2017 ዓ.ም ለክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ስኬታማነት የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብድል ረሂም ርዳ ገለጹ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስካሁን ተግባራት አፈፃፀም እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ ግምገማ አካሂዷል። የወረዳው ወጣቶችና ስፓርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስካሁን ተግባራት አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት በወረዳ ደረጃ እስካሁን በ15 የክረምት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች ከ26 ሺህ በላይ ወጣቶች ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን ከ49 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ከመንግስትና ከህብረተሠቡ ሊወጣ የነበረውን 29 ሚሊዮን 221 ሺህ 490 ብር በላይ ማዳን መቻሉን አስታውቀዋል። 12 የአቅመ ደካማና አረጋዊያን አዳዲስ ቤቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን እንዲሁም 17 ቤቶች የማደስ ስራ መከናወኑን በሪፖርቱ ተመላክቷል። የውይይት መድረኩን የመሩት ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት አብይ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አ/ረሂም ርዳ የክረምት የበጎ ፍቃድ ስራ የመልካም አስተሳሰብ እሴቶች መገለጫ መሆኑን ገልጸው ውጤቱ የግለሰብን ብሎም የሀገርን የመልካምነት እሴት አጉልቶ የሚያሳይ መረዳዳትን፣ አብሮነትንና አንድነትን የሚያስተሳስር ተግባር መሆኑን አስገንዝበዋል። አቶ አብዳል ረሂም ርዳ አክለውም የብልጽግና ፓርቲ አንዱ መለያ እሴቱ ሠው ተኮር መሆኑን ጠቅሠው የበጎ ፍቃድ ተግባራት በረካታ አቅመ ደከማ ዜጎችን ማዕካል አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ ስኬታማነቱ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ መሆኑንም አስተውቀዋል። የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም አብይ ኮሚቴው በየ ሴክተሩ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎትን በማኔጅመንት ዋና አጀንደ አድርጎ ሊገመግም እንደሚገባ ገልጸው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባራትን ስኬታማ ለማድረግ የድጋፍና የክትትል አግባብ ሂደት በማጠናከር በየደረጃው ያለውን ማህበረሰብ በማስተባበር ተግባሩን ቅንጅተዊ አሰራር በመጠቀም በቁርጠኝነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። የውይይት መድረኩ በተሻለ ሁኔታ የተፈጸሙ ተግባራት በተገቢው ማጠናከር እንዲሁም በጉድለት በተለዩትን በቀሪ የክረምት ጊዜያት አሟጠው በመጠቀም ከችግራቸው ፈጥነው እንዲወጡ የቀጣይ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቋል።

ድል እና ኢትዮጵያ የተሣሠሩ ናቸው። ነገር ግን ከድሎች ሁሉ የሚበልጥ ድል አለ፡፡ እሱም ድልን በአነሰ ኪሣራ ማረጋገጥ እና ከዘላቂ ውጤት ጋር ማስተሣሠር ነው። ከድል ሁሉ የሚበልጠው ድል፣ ድልን ብቻ ሳይሆን ስትራቴጂያዊ ግብን ጭምር ማረጋገጥ ነው። ዘላቂ ድል ማለት ውስጣዊ ባንዳዎችን ብቻ ሳይሆን ውጫዊ ጠላቶችን ጭምር ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ መርታት ነው። ብልጽግና ብዝኃ ዐርበኝነትን ይጠይቃል። የደም ብቻ ሳይሆን የላብ መሥዋዕትነትን ይጠይቃል። ዐርበኝነት እና ዝግጁነት የሀገርን ታሪክ ይቀይራሉ። እኛ የብልፅግና ምክር ቤት አባላት ራሳችን ተግተን ሕዝብንም ለማትጋት ተነሥተናል። ራሳችን ጠርትን ሕዝቡንም ለማጥራት ወስነናል። እንደ ዐርበኛ አመራር በልካችን ለመታገል ቆርጠናል። የብልፅግና አመራር የኢኮኖሚም የግንባርም ዐርበኛ ነው። ሕዝብን ያስተባብራል። በግንባር ይፋለማል። ደጀኑንም ያጠናክራል። እኛም ይሄንን ከወትሮው በበለጠ ለመፈጸም ቃላችንን በድጋሚ እናድሳለን። ዘመናችን ብዝኃ ታታሪነትን ይጠይቃል። ዓለም ተለዋዋጭ እና ብዙ ቀውስ አለበት። ሀገራችን ዘርፈ ብዙ የሕዝብ ፍላጎቶችና ችግሮች አሉባት። እንዲሁም የተለያዩ አደናቃፊ ኃይሎች ይፈትኗታል። እንዲህ ባለ ጊዜና ሁኔታ አመራርነት ዘርፈ ብዙ ብቃቶችን እና ታታሪነቶችን እንደሚጠይቅ ተረድተናል። ታሪካዊ ጠላቶቻችን እና ውስጣዊ ባንዳዎች ኢትዮጵያን ለማዳከም ቆርጠው ተነሥተዋል። በዚህ ወቅት በአንድ በኩል የጠላትን ጥቃት መከላከል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ዘላቂ ግቦቻችንን እና ዓላማዎቻችንን መተግበር እንደሚያስፈልገን በዝርዝር ተነጋግረን ወስነናል። በየደረጃው ያለን አመራሮች በአንድ ጊዜ ብዙ ተግባራትን የምንፈጽም መሆን እንዳለብን የተግባባን ሲሆን፤ ጠላትን ስንከላከል እና ጸጥታን ስናስከብር ከልማት የምንደናቀፍ መሆን የለብንም። ብልፅግና ብዝኃነታችንን ያከበረ፤ አንድነታችንን ያስተሣሠረ ፓርቲ ነው። ከትናንት የተማረ ነገን ያሣመረ ትርክት ያነገበ ፓርቲ ነው። የጠላትን አፍራሽ ትርክት ለመመከትና የእኛን ትርክት ለማጋባት ዲጂታል ዐርበኝነትን በሚገባን ልክ እንጠቀማለን። ጠላት የሀገርን አንድነት ለማፍረስ እና ብልጽግናዋን ለማደናቀፍ በበቀል ስሜት አፍራሽ ትርክት ሰንቆ ተነሥቷል። እኛ ማንነታችን የተሣሠረበትን እና ርዕያችን የተሰነቀበት ትርክታችንን ለሕዝብ ለማጋባት ዐርበኛ ልንሆን ወስነናል። ሕዝብን እያማረሩ ያሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የሕዝብን ርካታ ለመጨመር በትኩረት እንሠራለን። የሕዝብን የቅሬታ ምንጮች በመለየት እንፈታለን። የሕዝብን ቅሬታ በመስማት፣ በዕቅድና በክትትል ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንተጋለን። ሕዝባዊና ብሔራዊ ለሆነው ዓላማችን ውስጣዊ ዕንቅፋት የሆነው ሠርጎ ገብነትን እናጠራለን፤ ብሔርተኝነትን እንገራለን፤ ሌብነትንና ሕዝበኝነትን ለማጥፋት እንታገላለን። በውጭና በሀገር ውስጥ የሚኖረው የውጭ ምንዛሬ እንቅስቃሴ በሀገር ፍቅር ስሜት እንዲንቀሳቀስ በማድረግ፣ እንዲሁም የሸቀጦችን ዝውውር ጤናማነት በማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር የሚሠሩ የውጭና የውስጥ ጠላቶችን እንታገላለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ መጪው ሰባተኛ ሀገራዊ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ሕጋዊ፣ እና የሕዝቡ ምልዐተ ተሳትፎ የሚንጸባረቅበት እንዲሆን እንደ ብልፅግና ፓርቲ አመራርና አባል ብሎም እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በንቃት እንሳተፋለን። ከላይ የገለጽናቸው ውሳኔዎቻችንና ቃል የገባናቸው ግቦች ተሳክተው የኢትዮጵያን ብልጽግና በአስተማማኝ መሠረት ላይ ለመመሥረት እንድንችል፣ መላው የብልፅግና አባላትና ኢትዮጵያውያን በኅብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲሰለፉ ጥሪ እናደርጋለን። የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ #prosperity

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት መግለጫ እኛ የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባላት ከሐምሌ 30 እስከ ነሐሴ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረግነው መደበኛ ስብሰባ በዓለማዊ፣ አህጉራዊ፣ ቀጣናዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በዝርዝር ተወያይተናል። ምክር ቤታችን አሁን ባለው የጂኦ ፖለቲካ ሁኔታ ውስጥ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ስለሚከበርበት መንገድ ተመልክቷል፡፡ በመደመር መንገድ ወደ ብልጽግና ለመድረስ እየተደረገ ስላለው ጥረትም ገምግሟል። በዓለማችን ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ለሀገራችን ዕድልና ፈተና ይዘው መምጣታቸውን የተመለከተው ምክር ቤቱ፣ ፈተናዎችን በመሻገርና ዕድሎችን በመጠቀም ይበልጥ የሀገራችንን ጥቅም ስለምናስጠብቅባቸው ስልቶች በስፋት ተነጋግሮ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። እንደሚታወቀው፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የገጠመንን ጦርነት በአሸናፊነት ተወጥተናል። በአሸናፊነት መወጣት ብቻ ሳይሆን፣ ወታደራዊ ድላችንን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ቋጭተናል። ዳሩ ግን ይፈልጉት የነበረው የተራዘመ ጦርነት በስምምነቱ የተጨናገፈባቸው ጠላቶቻችን ሌሎች ስልቶችን ወደ መሞከር ገብተዋል። ምንም እንኳን እንዳሰቡት እየሆነላቸው ባይሆንም፣ እነዚህ አካላት በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ጽንፈኞችን በመጠቀም የመንግሥትን ኃይልና የሕዝብን አንድነት ለመከፋፈል ጥረት ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። በታሪካዊ ጠላቶቻችን መሪነት እና አስተባባሪነት፣ በአንዳንድ ባንዳ ጽንፈኞች መሣሪያነት ዛሬም ጠላቶቻችን የጦርነት አምሮታቸው አልቆመም። ባለፉት ሁለት ዓመታት ጠላቶቻችን የሕዝብንና የመንግሥትን አንድነት ለመፈታተን ሁለት መንገዶችን ተጠቅመው ነበር። አንደኛው በየአካባቢው ግጭትን ማበራከት ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በዲጂታል ሚዲያ መንግሥትን ማሳጣት ነው። ነገር ግን በሁለቱም ዘመቻዎች እንዳሰቡት አትራፊ መሆን አልቻሉም። ኢትዮጵያን የማዳከም ዕድላቸው እየጠበበ ነው። ባለንበት ልንከስም እንችላለን የሚለው ሥጋታቸውም ጨምሯል። ዛሬ ያለነው ትውልድ፣ ከታሪካዊ ስብራቶቻችን እና ከዓለም ነባራዊ እውነታ ተምረናል። እንደ ድሮው በተቀደደልን ከመፍስስ ይልቅ፣ ብሔራዊ አንድነታችንንና ተቋማዊ ዐቅማችንን ለማጠናከር እየሠራን ሲሆን ይሄም ተጋላጭነታችንን በእጅጉ ቀንሶታል። ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ ብሔራዊ ራዕያችንን ማሳካት የሚችል ብሔራዊ ዐቅም መገንባታችን ይቀጥላል። ከሁሉ በላይ አዲሱ ስልታችን ሰላማዊ የፖለቲካ ዕድሎችን አሟጥጦ ይጠቀማል። ተግዳሮቶች በበረቱባቸው ባለፉት ሰባት ዓመታት፣ በሁሉም መስክ ድል አስመዝግበናል። በተለይም በሦስት ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ተጨባጭ ለውጥ አምጥተናል፡- • ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች በተግዳሮቶች ሳይበገሩ አንሠራርተዋል። ይሄም ውስጣዊ ተጋላጭነታችንን አጥብቦ፣ ባንዶችን ቦታ አሳጥቷል። • በዓባይ ላይ ተገቢውንና ሕጋዊውን ተግባር በማከናወን በቀጣናው ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመናችንን ለውጠናል። • የባሕር በር የማግኘት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ መብታችንን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርገነዋል። በዚህም በቀይ ባሕር የነበረንን ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና ለመመለስ ከአንድ ምዕራፍ በላይ ተራምደናል። ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦቻችን በተግዳሮቶች ሳይረቱና ሳይዋጡ በስኬት እየተራመዱ ናቸው፡፡ ለውስጣዊ ተጋላጭነታችን መነሻ መሆናቸው ቀርቶ፣ ወደ ብሔራዊ ዐቅምነት ተቀይረዋል። ውስጣዊ ስንጥቃቶችን በሽብልቅ እያሰፉ፣ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር አብረው ኢትዮጵያን ለመውጋት ለሚተባበሩ ባንዳዎች፣ ብሔራዊና ብሔረሰባዊ አጀንዳ አሳጥተናቸዋል። ፖለቲካችን ማንነትን ከሚያጫርተው የፖለቲካ ገበያ እንዲወጣ አድርገነዋል። በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ላይ ተመሥርቶ ብልጽግናን በሚያረጋገጥ መንገድ ቀይሰነዋል። በአንድ በኩል በጀመርናቸው ተቋማዊ ሪፎርሞች እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የሀገራችንን ውስጣዊ ዐቅም አጠናክረናል። በሌላ በኩል ደግሞ የጂኦፖለቲካውን ቅኝት በሚገባ በመገንዘብ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች አስከብረናል። ኢትዮጵያ ያለ ጥርጥር እያንሠራራች ነው። በዓይን አይቶ፣ በእጅ ነክቶ፣ በመረጃ አጣርቶ፣ በመስክ ተሠማርቶ፣ ይሄንን እውነት ማረጋገጥ ይቻላል። ከሀገራዊ እስከ ዓለማዊ መድረኮች ለዚህ ስኬት ሚልዮን ምስክሮች አሉ። ይህ ግን ለታሪካዊ ጠላቶቻችንና ለእነርሱ ተላላኪዎች የሚዋጥላቸው አይደለም። ስለዚህም ኢትዮጵያን ከመንገዷ ለማስቀረት የመጨረሻውን ሙከራ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በዚህ የመጨረሻ ሙከራቸው ስድስት ስልቶችን ለመጠቀም እንደተነሡ ምክር ቤታችን ገምግሟል። እነዚህም ለግድያ የሚፈላለጉ ኃይሎችን በጥቅም ማስተሣሠር፤ ኢትዮጵያን በሑከት ውስጥ ማቆየት፤ በመልካም አስተዳደር ችግር የተነሣ የሚፈጠሩ የሕዝብ ቅሬታዎችን ለዐመጽ መጠቀም፤ ብሶት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን ማራገብ፤ ሚዲያዎችን የሑከት መቀስቀሻ መሣሪያ ማድረግ፤ እንዲሁም በውጭ ምንዛሬ እና በሸቀጦች በኩል የኢኮኖሚ አሻጥርን መሥራት ናቸው። ይሄንን የታሪካዊ ጠላቶቻችን የመጨረሻ ሙከራ ለመጨረሻ ጊዜ ለማምከን እኛ የብልፅግና ምክር ቤት አባላት በቃልም በተግባርም ዝግጁ፣ ቆራጥና ውጤታማ መሆን እንዳለብን ተገንዝበናል። በዋናነትም በሚከተሉት ሰባት ጉዳዮች ላይ ከሚጠበቅብን በላይ ለማከናወን ቆርጠን ተነሥተናል። • ግጭትን ሊያስቀሩ የሚችሉ ሰላማዊ አማራጮችን በሁሉም አቅጣጫ ለመሞከርና በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ለሚወስኑ ታጣቂዎች አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ፤ • የሰላምን አማራጭ ባለመቀበል በሕዝብና በሀገር ንብረት ላይ ችግር ለመፍጠር በሚነሡ ኃይሎች ላይ በተጠናከረ መንገድ ሕግ ለማስከበር፤ • በየደረጃው የሚነሡ የሕዝብ የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕና የኢኮኖሚ ጥያቄዎችን በኢትዮጵያ ዐቅም ልክ በየደረጃው ለመመለስ፤ • ተገቢውንና እውነተኛውን መረጃ ለሕዝብ በየጊዜው ለመስጠትና ሐሰተኛ መረጃዎችን ለማጋለጥ፤ • በየተቋማቱ ተመድበው የዲሲፕሊን ጉድለት፣ሙስናና የአስተዳደር በደል የሚያደርሱ የሥራ መሪዎችንና አገልጋዮችን ለመታገል፤ • በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪ፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ እንደዚሁም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የጀመርናቸውን የልማት ሥራዎች የበለጠ ስኬታማ በማድረግ፤ የተጀመሩ ኢኒሼቲቮችን ለውጤት በማብቃት፤ የሕዝብን ተሳትፎ ባረጋገጠ መልኩ የከተማና የገጠር ትራንስፎርሜሽን ለማረጋገጥ፤ • በዲፕሎማሲው መስክ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች በሁሉም መንገድ ለማስከበር፤ ከመግባባት ላይ ደርሰናል። በአጠቃላይ እኛ የብልፅግና ምክር ቤት አባላት፣ የኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ከታቀደለት ጊዜ ፈጥኖ እንዲሳካ ለማድረግ “መመከት፣ መትጋትና ማጥራት” በሚል መርሕ ቀጣዩን ተግባራችንን ለማከናወን ወስነናል። የጠላቶቻችንን ፈተና እና ሤራ እንመክታለን። የኢትዮጵያ ብልጽግና በሁሉም መስክ እንዲሳካ ከወትሮው በበለጠ እንተጋለን። ለብልጽግና ጉዟችን ዕንቅፋት የሚሆኑትን አስተሳሰቦች፣ ባህሎች፣ ልማዶች፣ ሠርጎ ገቦች እና ባንዳዎች ደግሞ ተግተን እናጠራለን። እኛ የምንወደው ሀገር፣ የምንቆምለት ሀገራዊ ዓላማ እና ሕልም አለን። የምናገለግለው ሕዝብ አለን። የምንገነባው ሀገር አለን። የሚናስከብረው ብሔራዊ ጥቅም አለን። ጠላት ደግሞ እነዚህን ሁሉ ማጥፋት፣ ለማፍረስና ለማሰናከል ይፈልጋል። ማልማት፣ መገንባት እና ማጽናት፤ ከማጥፋት፣ ከማደናቀፍ፤ ከማሰናከል እና ከማፍረስ በላይ ዐቅምና ትጋት ይጠይቃል።

ዜና ሹመት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 12ኛ አመት 29ኛ መደበኛ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ኸይሩ መሀመድ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ በመሆን ተሹመዋል። ነሀሴ 2/2017 ዓ.ም(ወልቂጤ) የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ የተለያዩ ሹመቶችን የሰጡ ሲሆን:- የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 12ኛ አመት 29ኛ መደበኛ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ኸይሩ መሀመድ የጉራጌ ዞን ዋና አፈ-ጉባኤ በመሆን ተሹመዋል። እንዲሁም ክብርት ወይዘሮ ከድጃ ተማም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ በመሆን በመሾም ቃለ መሀላ ፈጽመዋል።

ነሐሴ 01/2017 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት 4ኛ ዙር 12ኛ አመት 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ከምክር ቤቱ አባላት ከተሰጡ አስተያየቶች ጥቂቶቹ:- 👉 የአርሶ አደሮች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከላት ማጠናከር ይገባል። 👉 የጉራጌ ብሄር ባህልና ቋንቋ ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች አበረታች ቢሆኑም በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ተግቶ መስራት ይገባል። 👉 የጉራጌ ማህበረሰብ አንድነት ለማጠናከር እና ባህላዊ እሴቶቹ ተጠብቀው እንዲቆዩ በበጀት አመቱ አርአያነት ያላቸው ተግባራት ተከናውነዋል። 👉 የዞኑ አስተዳደር እያስገነባው ያለው 2ኛ ደረጃ አዳሪ ት/ቤት ግንባታ የሚገኝበት ደረጃ አበረታች መሆኑና ጉራጊኛ ቋንቋን ለማሳደግ የተወሰዱ እርምጃዎች ይበል የሚያሰኙ ናቸው። 👉 ዞኑ ያለውን የሰው ሀይል እውቀት፣ ጉልበትና ክህሎት በመጠቀም በሁሉም ዘርፎች ግንባር ቀደም የልማት ስራዎች እያከናወነ ቢሆንም ህብረተሰቡን የሚመጥን ልማት ለማከናወን አሁንም በትኩረት መስራት ይገባል ። 👉 በዞኑ የሚገኙ መዋቅሮች ተመጣጣኝ አፈፃፀም እንዲኖራቸው በማድረግ የቤተሰብ ብልፅግና ማረጋገጥ ይገባል። 👉 በየእርከኑ በሚሰጡ ፈተናዎች የተማሪዎች የማለፍ ምጣኔ ለማሳደግ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ግብዓት ለማሟላት የተጀመሩ ስራዎች ማጠናከር ይገባል። 👉 የጉራጌ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ባህል፣ ታሪክና ቋንቋ ለማሳደግና አንድነትን ለማጠናከር ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክት በመሆኑ በቀጣይ በላቀ ደረጃ ማከናወን ይገባል። 👉 ግንባታቸው የተጓተተው የከሬብ እና የመጌቻ መስኖ ፕሮጀክቶች ችግር በመፍታት አገልግሎት እንዲሰጡ መሰራት አለበት። 👉 በዞኑ በየመዋቅሩ የሚስተዋሉ የመንገድ ችግሮች በመፍታት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል። 👉 በዞኑ በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች በመፍታት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን መንግስት የጀመራቸው ስራዎች ይበልጥ አጠናክሮ ማሰቀጠል ይጠበቅበታል። 👉 የመብራት መቆራረጥና የሀይል አቅርቦት እጥረት በአምራቾች ኢንዱስትሪ ዘርፍ በተሰማሩ ወጣቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ ይገኛል በልዩ ትኩረት መሰራት ያስፈልጋል ። 👉 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች የሌላቸው መዋቅሮች በቀጣይ ትኩረት ቢሰጣቸው እንዲሁም 👉 ዞኑ ገቢ የመሰብሰብ አቅሙን ይበልጥ ለማሳደግ ሁሉም አማራጮች መጠቀም ይገባል። መረጃ የጉራጌ ዞን ኮምዩኒኬሽን ነው።

ሐምሌ 28/2017 ዓ.ም የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸዉ እያደገ መምጣቱም የጉራጌ ዞን ሴቶች ህጻናት ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ በጉመር ወረዳ በአረቅጥ ሸለቆ ቀበሌ የችግኝ ተከላ ፣ የቁሳቁስ ድጋፍ፣ ሴቶች በጓራቸዉ እየሰሩት ያለዉን የግብርና ስራዎች እንቅስቃሴ ምልከታም ተካሄዷል። ‎ የጉራጌ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ ነጅብያ መሀመድ እንዳሉት በዞኑ በሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ዉጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሆነ አስረድተዋል። ‎ ሴቶች በተናጠል ከማልማት በአደረጃጀት ታቅፈው ሲያለሙ ዉጤታማነታቸዉ የጎላ እንደሆነም ያስረዱት ሀላፊዋ ሴቶች በልማት ህብረት እና በግል በተሰማሩበት የተለያዩ ዘርፎች እና የቁጠባ ባህላቸዉ እያደገ መጥቷል በመቻሉ ከ200 ሚሊየን ብር በላይ እንደቆጠቡም አብራርተዋል። ‎ በኦሞ ፣በንግድ ባንክና በሌሎችም ተቋማቶች የተቆጠቡ ገንዘቦች ሴቶች እራሳቸዉ ከዘመኑ ጋር አብረዉ እንዲሄዱ ፣ ተስማሚ ቴክኖሎጂዎች እንዲጠቀሙ እንዲሁም የእርሻ ማሳዎች ጭምር በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች አጅበዉ እንዲያለሙ የቆጠቡት ገንዘብ አንቀሳቅሰዉ መጠቀም እንዳለባቸዉ አስረድተዋል። ‎ በጉመር ወረዳ በአረቅጥ ሸለቆ ቀበሌ እናቶች በጓሯቸዉ እያለሙት ያለዉን የግብርና ስራ ተዛዙረዉ የተመለከቱ እንደሆነም ጠቁመዉ እናቶችም የተሻለና ዉጤታማ ስራ እየሰሩ ይገኛል ብለዋል። እናቶች በጓራቸዉ የመኖ ሳር በመትከል ፣የባቄላና የበቆሎ ማሳ እንዲሁም የተለያዩ አትክልቶች የማልማት ስራ በስፋት እየሰሩ እንደሚገኝም አስታዉቀዋል። ‎ የሴቶች ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎአቸዉ እያደገ መምጣቱም በተጨባጭ እየተረጋገጠ እንደሆነም ጠቅሰዉ ሴቶች በጋራ እንዲያድጉ የማድረግ ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡ ‎ መንግስት የወል መሬቶች አካባቢ ቅድሚያ በልማት ህብረት ለተደራጁ ሴቶች እየተሰጡ ያለበት ሁኔታ መኖሩም አብራርተዉ ሴቶችም በጋራ የሚያለሙት ማሳቸዉ እየተሻሻለ ያለበት ሁኔታ መኖሩም አስረድተዋል። ‎ ከመጋቢት 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ አንደኛዉ ዙር ሞዴል መመረቃቸውና አሁን ደግሞ ሁለተኛዉ ዙር መስከረም 30/2018 ዓ.ም ሞዴል ቀበሌ የሚያስመርቁም እንደሆነም አስረድተዋል። ‎ በዛሬ እለት ለጉመር ወረዳና ለአረቅጥ ከተማ አስተዳደር ተጋላጭ ለሆኑ እናቶችና ህጻናት የትምህርት ቁሳቁስ ፣የንጽህና መጠበቂያ ፣ የፉርኖ ዱቄትና ሌሎችም ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸዉም ጠቅሰዋል፡፡ ‎ የጉመር ወረዳ ሴቶችና ህጻናት ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ ዙልፋ ሸምበጅ እንዳሉት በወረዳዉ የሴቶች የልማት ህብረት አባላት ዉጤታማ ስራ እየሰሩ ሲሆን በዚህም የገቢ አቅማቸዉና የቁጠባ ባህላቸዉ እያደገ መሆኑም አብራርተዋል። ‎ በወረዳዉ 17 ሺህ 310 አባላት ፣1ሺህ 7 መቶ 31 የ1ለ10 እንዲሁም 577 የልማት ህብረት መኖሩንና ከነዚህ ዉስጥም የተወሰኑት የልማት ህብረቶች ሞዴል እንደሆኑም ተናግረዋል። ‎ ሴቶች በእርሻ ስራ ፣በንግድ ስራ በኢንተርፕራይ በመደራጀት ዉጤታማ ስራ እየሰሩ በግልና በልማት ህብረታቸዉ ቁጠባቸዉም እያሳደጉ ይገኛል ብለዋል። የሴቶች የልማት ህብረት በአካባቢያቸዉ የኢኮኖሚ ገቢ የሌላት እናት በመለየት እራሷን እንድትችል የመደገፍና የማብቃት ስራም እንደሚሰሩም ጠቁመዉ የዞኑ ሴቶች ህጻናት መምሪያ በወረዳዉ ለሚገኙ ተጋላጭ ለሆኑ እናቶችና ህጻናት ያደረገው የተለያዩ የቁሳቁስ ድጋፍ አመስግነዋል። መረጃው የጉራጌ ዞን ኮምዩኒኬሽን መምሪያ ነው።

ከእንጦጦ እስከ አራት ኪሎ ፕላዛ ተሠርቶ የተጠናቀቀው ኮሪደር (ኢፕድ)

ሐምሌ 27/2017 ዓ.ም 5ኛው ዙር ኬሮድ የ15 ኪሎሜትር የጎዳና ሩጫ በጉራጌ ዞን ርዕሰ መዲና በሆነችው ወልቂጤ በድምቀት እየተካሄደ ይገኛል። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨ ኬሮድ ሰላም ለማብሰር። አንድነት ለማጠናከር፣ ተተኪ አትሌቶች ለማፍራትና የህብረተሰቡ ጤና ለመጠበቅ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው። በሩጫው ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ ታዋቂ አትሌቶች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሰራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ የጉራጌ ዞን፣ የወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች የከተማው ነዋሪዎች እና ሌሎች እንግዶች ተሳትፈዋል።