1 318
مشترکین
+324 ساعت
+207 روز
+15030 روز
آرشیو پست ها
ዜጎች ሥራ ፈጣሪ፣ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አመርቂ ሥራዎች ተሠርቷል፡- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
*
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት አምስት ዓመታት ባስመዘገባቸው ውጤቶች እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ውይይትና የሥራ ፈጠራን የሚያሳይ ክህሎት ኢትዮጵያ ዐውደ ርዕይ በኢዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል ተጀምሯል።
የሥራ ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል በንግግራቸው ተቋሙ ባለፉት አምስት ዓመታት አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡንና ዜጎች ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑና ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ በርካታ ሥራዎች ማከናወኑን ገልጸዋል።
ዜጎች ወቅቱ በሚጠይቀው ዲጂታል ዘርፍ ጭምር ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በዲጂታል ሙያ ዘርፎችም እንዲሳተፉ መደረጉን ጠቁመዋል።
መድረኩ በሥራ ዕድል፣ በክህሎት ልማት እንዲሁም በአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ የተመዘገቡ ዋና ዋና የልማት ስኬቶችን፣ ልምዶችንና የወደፊት አቅጣጫዎችን ለማመላከት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።
ለአራት ቀናት በሚቆየው በሥራ ፈጣሪዎች ኤግዚቪሽን የተሳተፉ ወጣቶች የሥራ ፈጠራ ክህሎታቸውን እያዳበሩና የተለያየ ሙያ ባለቤት በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ባለፉት አምስት አመታት በርካታ ወጣቶች ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩና ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ እድሎችን ማመቻቸቱም ተጠቁሟል።
በዐውደ ርዕይዩ የቀረቡ የፈጠራ ሥራዎችን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮን (ዶ/ር) ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጎብኝተውታል።
©️ EBC
ዜጎች ሥራ ፈጣሪ፣ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አመርቂ ሥራዎች ተሠርቷል፡- የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
*****

በመሃሪ አለሙ
©️ EBC
በድሬዳዋ አስተዳደር ከ1 ሺህ በላይ ወጣቶችን የሚያሳትፍ "አብረን ኮድ" የዲጂታልና የኮዲንግ ሥልጠና ኢኒሼቲቭ ተጀመረ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከቢቲኔት ቴክኖሎጂ ሶሉሽንስ ኩባንያ ጋር በመተባበር "አብረን ኮድ — Abren Code" የተሰኘ የወጣቶች የኮዲንግና ዲጂታል ክህሎት ማበልጸጊያ ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል።
ይህ ሥልጠና ከ1 ሺህ በላይ ለሆኑ የአስተዳደሩ ወጣቶችና ሴቶች የሚሰጥ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም ወጣቶች ባሉበት ቦታ ሆነው በዓለም አቀፍ የዲጂታል ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል ነው። በሥልጠናውም የዌብ ፕሮግራሚንግ፣ የአንድሮይድ መተግበሪያ ማልማት፣ የዳታ ሳይንስ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መሠረታዊያን የተሰኙ አራት ዋና ዋና የቴክኖሎጂ ዘርፎች በተግባር ይሰጣሉ።
©️ DireTvአማርኛ | ነሐሴ 24 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ
የ2019 ዕቅድ በተግባር የሚተረጎምበትን አቅጣጫ ለማስቀመጥ ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት ተወያዩ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለቢሮው ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት በማቅረብ በዕቅዱ አፈጻጸም ዙሪያ የጋራ ውይይት አካሂዷል።
በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ንግግር በማድረግ፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ የቢሮውን የሥራ አቅጣጫ በግልጽ መልኩ የሚያስቀምጥ ከመሆኑ ባሻገር በተግባር የሚመዘን ውጤት ለማምጣት የሁሉም ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በውይይቱም የቢሮው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ በዋና ዋና የሥራ አቅጣጫዎች፣ በአፈጻጸም ስልቶችና በሚጠበቁ ውጤቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።
የቢሮው ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላትም በዕቅዱ ላይ ሃሳብ፣ አስተያየትና የማሻሻያ ጥቆማዎችን አቅርበዋል።
የጋራ ውይይቱ ዕቅዱ ከተግባራዊ አቅምና ከነዋሪው ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም፣ የተጠያቂነትና የአፈጻጸም ባህል እንዲጎለብት እንዲሁም የተቀናጀ የሥራ አመራር እንዲጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል፣ በ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ከአጠቃላይ ሠራተኞች በላቀ ውጤት ላጠናቀቁ ሠራተኞች ዕውቅና ተሰጥቷል።
ዕውቅናው በላቀ አፈጻጸም የሚሰሩ ሠራተኞችን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነትን ለማጠናከርና በቢሮው ውስጥ የውጤታማነት ባህልን ለማስፋፋት ያለውን ሚና ያሳያል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ተሞክሮዎች የተገመገሙ ሲሆን፣ የ2019 ዕቅድ በተሻለ አፈጻጸም፣ በተጠናከረ ትብብርና በሚታይ ውጤት እንዲመራ የጋራ ኃላፊነት እንዲወሰድ አቅጣጫ ተቀምጧል።
“የተሻለ ዕቅድ፣ የተቀናጀ ሥራ፣ የተሻለ ውጤት!”
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. | ድሬዳዋ

በውይይቱም የቢሮው የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ በዋና ዋና የሥራ አቅጣጫዎች፣ በአፈጻጸም ስልቶችና በሚጠበቁ ውጤቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዷል። የቢሮው ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላትም በዕቅዱ ላይ ሃሳብ፣ አስተያየትና የማሻሻያ ጥቆማዎችን አቅርበዋል።
የጋራ ውይይቱ ዕቅዱ ከተግባራዊ አቅምና ከነዋሪው ፍላጎት ጋር እንዲጣጣም፣ የተጠያቂነትና የአፈጻጸም ባህል እንዲጎለብት እንዲሁም የተቀናጀ የሥራ አመራር እንዲጠናከር የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።
በሌላ በኩል፣ በ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸማቸውን ከአጠቃላይ ሠራተኞች በላቀ ውጤት ላጠናቀቁ ሠራተኞች ዕውቅና ተሰጥቷል።
ዕውቅናው በላቀ አፈጻጸም የሚሰሩ ሠራተኞችን ለማበረታታት፣ የሥራ ተነሳሽነትን ለማጠናከርና በቢሮው ውስጥ የውጤታማነት ባህልን ለማስፋፋት ያለውን ሚና ያሳያል።
በመድረኩ የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ተሞክሮዎች የተገመገሙ ሲሆን፣ የ2019 ዕቅድ በተሻለ አፈጻጸም፣ በተጠናከረ ትብብርና በሚታይ ውጤት እንዲመራ የጋራ ኃላፊነት እንዲወሰድ አቅጣጫ ተቀምጧል።
“የተሻለ ዕቅድ፣ የተቀናጀ ሥራ፣ የተሻለ ውጤት!”
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም. | ድሬዳዋ
በአገር አቀፍ ደረጃ የ50 ሺህ ወጣቶችን የሥራ ዕድል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጠው ፕሮጀክት “ብቃት”
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት 50 ሺህ ወጣቶችን በ27 ከተሞች በሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የታቀደው የ4ኛው ዙር የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክት የግንዛቤ መድረክ በድሬዳዋ ተጀመረ።
ከ27 የአገሪቱ ከተሞች የተውጣጡ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች በፕሮጀክቱ የትግበራ ዕቅድና በManagement Information System (MIS) አጠቃቀም ላይ ለሦስት ቀናት በተዘጋጀው የስልጠና መድረክ ላይ ተሳታፊ ይሆናሉ።
በመክፈቻው ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮጀክቱ ወጣቶች በተማሩት ሙያ ተግባራዊ ልምድ እንዲያገኙ፣ ከሥራ ዓለም ጋር ቀድመው እንዲተዋወቁና ወደ ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲሸጋገሩ የሚያግዝ ወሳኝ የወጣቶች ልማት መርሃ ግብር መሆኑን ገልጸዋል።
ብቃትን ወደ ልምድ፣ ልምድን ወደ ሥራ!
ድሬዳዋ
ነሐሴ 21 ቀን 2018 ዓ.ም.
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የደብረ ታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡
#EIPC ነሃሴ 21 .2018 ዓ.ም ድሬዳዋ
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በዘርፉ ባሳየው ከፍተኛ የስራ አፈፃፀምና መነቃቃትን ጨምሮ አጠቃላይ በኮሌጁ ባስመዘገባቸው ተጨባጭ ውጤቶች ጋር ተያይዞ በርካታ ኮሌጆች ተቋማችንን መዳረሻቸው እያደረጉ የሚገኙ ሲሆን በዚህም የደብረ ታቦር ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች ጭምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ተገኝተው የስራ ልምድ ልውውጥ ማካሄድ ችለዋል::
ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ጨምሮ ጠቅላላ የተቋም አፈፃፀም በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲንኖች እና EASE ፕሮጀክት አስተባባሪ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል::
ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው ገለፃና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻነት በነበረው ማጠቃለያ ውይይትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው በሚገኘው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ ያሳየው የላቀ አፈፃፀም በሌሎች አቻ ኮሌጆችም ጭምር ሞዴል ተደርጎ እንዲታይ ያስቻለው መሆኑንም ገልፀዋል::
በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን ማድረግ ችለዋል::
ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡-
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr
በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001
በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1
በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+4
በእቅዶቹ መሰረት ኮሌጁ በሃገር አቀፍ ደረጃ ውጤት እንዲያመጣ ሁሉም አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት አመት እቅድ የፊርማ ስነ- ሰርዓት አከናወነ፡፡
የምስራቅ አፍሪካ የቴክኒክና ሙያ የልህቀት ማእከል የሆነው የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ከም/ዲኖች፣ከስራ ክፍሎች ዳይሬክተሮች እንዲሁም ከትምህርት ክፍል ተጠሪዎች እና ኬዝ ቲም አስተባባሪዎች ጋር የፊርማ ሰነ-ስርዓት አከናውኗል።
በፊርማ ስነስርአቱ ላይ በመገኘት ለእቅድ ፈጻሚ ክፍሎች መልእክት ያስተላለፉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ እንዳሉት በ2019 በጀት አመት የያዝናቸው እቅዶች ኮሌጃችን በከተማ ብቻ ሳይሆን በሃገር አቀፍ ደረጃ የተሸለ ውጤት እንዲያመጣ ለእቅዱ ተፈጻሚነት ሁሉም አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ያሉ ሲሆን አያይዘውም ለማህበረሰቡ የምንሰጠው አገልግሎት ዘመናዊና ተደራሽ እንዲሆን የኮሌጁ የስራ ክፍሎችና ሰራተኞች በግልጽነትና በታማኝነት እና በትጋት ልንሰራ ይገባናል ብለዋል፡፡
በዛሬው እለት በተከናወነው የፊርማ ስነስርአትና የእቅድ ርክክብ ስርአት ላይ የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ከውጤት ተኮር ት/ት ስልጠና ም/ዲን ከሆኑት አቶ ቢቂላ ታደሰ እና ከኢ/ኤ/ቴ/ሽ ም/ዲን ከሆኑት ወ/ሮ ትግስት በዙ ጋር የፊርማ ሰነ-ስርዓት እና የስራ ርክክብ ያደረጉ ሲሆን ሁለቱ ም/ዲኖች ደግሞ በስራቸው ከሚገኙ የትምህርት ክፍል ተጠሪዎችና ኬዝ ቲም አስተባባሪዎች ጋር ተፈራርመዋል።
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ነሀሴ 21/2018
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው የክህሎት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል በተለያዩ ሙያዎች በልምድ ያካበቱ ዜጎችን በመመዘን የሙያ ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት እየሰጠ መሆኑን የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሚን አብዱላሂ ገልጸዋል።
እንደ ኃላፊው ገለጻ የክህሎት ምዘናው በልምድ የተገኘ ክህሎትን በማረጋገጥ ዜጎች በሥራ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሥራ ዕድላቸውን እንዲያሰፉ እያስቻለ ይገኛል።
©️ DireTv
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
#ዜና| አድራ ኢትዮጵያ ለ250 የድሬዳዋ ወጣቶች የሥራ ዕድልና የክህሎት ሥልጠና የሚያመቻች አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ
የአድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን እና ከኢትዮ-ጣልያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር የሥራ ማስጀመሪያ ውይይት አካሂዷል።
አድራ ኢትዮጵያ እና አድራ ጀርመን ከድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር የቀረጹት ይህ ፕሮጀክት፤ በከተማዋ ለሚገኙ ሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራንና ራሳቸውን እንዲችሉ የሚያስችሉ ተግባራትን ለማከናወን ያለመ ነው።
ከአድራ ኢትዮጵያ ጋር የተጀመረው አጋርነት ባለፉት ዓመታት ላቅ ያለ ውጤት ማስመዝገቡን ያስታወሱት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ዋና ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፤ ለአሁኑ ወጣቶች የተሻለ ዕድል ለመፍጠር ፕሮጀክቱ ለሦስት ዓመት ተኩል ቆይታ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ይህ ፕሮጀክት በቆይታው ወጣቶችን በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርግና ተጨባጭ ውጤት የሚመዘገብበት እንደሚሆንም ኃላፊው እምነታቸውን ገልጸዋል።
አቶ ሮቤል አክለውም አድራ ፕሮጀክት በተለይም የወጣቶችን አቅምና ችሎታ በማሳደግ፣ በሥራና ማኅበራዊ ልማት እንዲሁም በአረንጓዴ ክህሎት ልማት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ተቋም መሆኑን አስታውቀዋል።
በዚህ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ወጣቶችን በማሰልጠን በአገር አቀፍ ደረጃ አንድ ሺህ፣ በድሬዳዋ ደግሞ 250 ወጣቶችን ወደ ሥራ ዓለም ለማስገባት መታቀዱን የአድራ ኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዶክተር ዘሪሁን አዋኖ ገልጸዋል። ፕሮጀክቱ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲችሉና ማኅበረሰባቸውን እንዲጠቅሙ የሚያስችል የክህሎት በረከት የሚያስገኝ መሆኑንም አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የልማትና ማኅበራዊ አገልግሎት ኮሚሽን ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ አባያ በበኩላቸው፤ ሥልጠናው ወጣቶችን በአረንጓዴና ዲጂታል ክህሎት በማቅናት ከሥራ ፈላጊነት ወደ ሥራ ፈጣሪነት እንዲሸጋገሩና ራሳቸውን እንዲደግፉ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል።
#DireTvአማርኛ | ነሐሴ 20 ፥ 2018 ዓ.ም | ድሬዳዋ