1 326
مشترکین
+224 ساعت
+87 روز
+9730 روز
آرشیو پست ها
በድሬዳዋ አስተዳደር ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የክህሎት ውድድር ተጠናቀቀ፤
በአገር አቀፍ ደረጃ የክህሎት በዘርፉ ሰልጣኞች ዘንድ የውድድርና የተነሳሽነት መንፈስ ለመፍጠር የዘርፉን ገጽታ ለመገንባት ማስፈጸሚያ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱ ይታወሳል፡፡
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ማዕከላት ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪ የሚያደርግ ምርጥ ቴክኖሎጂ በማቅረብና በማሽጋገር ምርታማ የሆነ ዜጋ በመፍጠር በአጠቃላይ የዘርፉን ተዋናዮች በማነቃቃት እና በገጽታ ግንባታ ረገድ የክህሎት ውድድር ማድረግ ወሳኝ በመሆኑ በአስተዳደሩ የሚገኙ ሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች፤ በክላስተር ደረጃ እንዲሁም በክልል ደረጃ አስተዳደሩን የሚወክሉ ተወዳዳሪዎች የተለዩበት ሆኖ ተጠናቋል፤
በፌደራል ደረጃ ለሚካሄደው ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር የተለዩ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከሚያገኙት ማበረታቻ በተጨማሪ የአጠቃላይ አሸናፊዎች በአህጉር እና በአለምአቀፍ ደረጃ በሚካሄዱ ውድድሮች ላይ ሀገርን ወክለው የመሳተፍ ዕድል እንደሚመቻች ተገልጿል፡፡
በውድድሩ ማጠናቀቂ የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እና የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ውድድሩን ተመልክተው ተወዳዳሪ ሰልጣኞችንም ያበረታቱ ሲሆን በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች የተሰሩ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአስተዳደር ደረጃ የ2017 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የሥራ ፈጠራ ውድድር መካሄድ ጀመረ፤
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምርና ስልጠና ኤጀንሲ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ በጋራ ባዘጋጁት የ2017 ዓ.ም የቴክኖሎጂና የሥራ ፈጠራ ውድድር በአስተዳደሩ በሚገኙት የመንግስትና የግል ኮሌጆች በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተዋናዮች (በሰልጣኝ፣ አሰልጣኝ እና አንቀሳቃሾች እንዲሁም ተቋማት) በተጨማሪም የአጠቃላይ ት/ቤት ተማሪዎችና መምህራን የሚያሳትፍ ይሆናል፤
የውድድሩ ዋና አላማም በአስተዳደሩ የሚገኙ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ችሎታ ያላቸውን ወጣቶችና የሙያ ባለቤቶች መካከል ከፍተኛ የውድድር ተነሳሽነትን መንፈስ በመፍጠር በመሰረታዊ የስራ ፈጠራ፤ ተግባራዊ ምርምር እና ቴክኖሎጂዎችን የመቅዳት፣ የማሻሻል፣ የመፍጠር፣ የማለማመድ እና የማሸጋገር ስራዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የጥራት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል አቅም እንደሚፈጥር ይታሰባል፤
በውድድሩ ማስጀመሪያ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደተናገሩት በዘርፉ ፖሊሲ በተመላከተው መሰረት የክህሎትና የቴክኖሎጂ አቅምን ሊያሳዩና ሊያሳድጉ የሚችሉ ውድድሮችን ማድረጉ በዘርፉ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን ከማነቃቃት በዘለለ ከኢንደስትሪው ጋር የሚያገናኝ ድልድይ ሲሆን አስተዳደሩም የተለየ ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
የኢፌዲሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ ባስተላለፉት መልዕክት ቴክኖሎጂ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ መሆኑን አንስተው የቴክኖሎጂ ፈጠራ ተወዳዳሪዎችን አበረታተዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራር እና ሰራተኞች 1446 ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓልን በድሬዳዋ ህፃናት ማቆያና ማገገሚያ ማእከል ከሚኖሩ ህፃናት ጋር በጋራ አክብረዋል።
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው ዓመተ-ሒጂራ የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
ታላቁ የረመዳን የፆም ወር በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ወቅት ነው፡፡ በዚህ የፆም ወቅት ሕዝበ-ሙስሊሙ ራሱን ከክፉ ነገሮች በመቆጠብና ፈጣሪውን በዱአ በመለመን ፣ እንዲሁም ያለው ከሌለው ወገኑ ጋር ተካፍሎ በመብላትና ሰደቃ በማድረግ መልካምነትን የሚያሳይበት ጊዜ ነው፡፡
በተለይም በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታይ ወንድምና እህቶች በፆሙ ወቅት በተለያዩ ሥፍራዎች በተካሄዱ የኢፍጣር ሥነ ሥርዓቶች ላይ በመሳተፍ ለሙስሊም እህት ወንድሞቹ ያለዉን አጋርነት በተግባር ያሳየ ሲሆን ፤ ህብረተሰቡም እርስ በርስ የመደጋገፍ የኖረበት ባሕሉን በተጠናከረ መልክ ያስቀጠለበት እና የተቸገሩ ወገኖችንም በማገዝ በኩል ያሳየው ተነሳሽነት የሚደነቅ ነበር።
ቢሮው በዚሁ አጋጣሚ የተለያየ ድጋፍ የሚያደርግላቸውን ኢንተርፕራይዞች ከበዓላት ጋር በተያያዘ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ መጨመር እንዳይፈጠርና በሚኖሩ የበዓል ገበያዎች የሚያቀርቧቸውን ምርትና አገልግሎቶች በጥራት በማዘጋጀት ህብረተሰቡን ተደራሽ እንዲያደርጉ በቂ ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑን ለማስታወስ እወዳለሁ።
ይህንንም ሁሉ አቀፍ አድርገን በሌሎች ስራዎቻችን መልካም ዕሴቶቻችንን ጠብቀን በጎነትን እንድናሳይ ጥሪዬን እያቀረብኩ በ2017 ዓ.ም የሚከበረው የኢድ-አልፈጥር በዓል የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የመረዳዳት በዓል እንዲሆን መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡
መልካም በዓል!
ኢድ ሙባረክ!
የድሬዳዋ አስተዳደር
ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
አቶ ሮቤል ጌታቸው

Repost from Dire Dawa Polytechnic College
የክህሎት ኢትዮጵያ 1ኛ ዙር የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅን በመወከል የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያና ከሰል ማሽን የሰሩ፡፡
ይህ ማሽን semiautomate charcoal and animal feed production machine ይባላል። ማሽኑ ፕሮሶፊስ ጁሊ ፍሎራ እየተባለ የሚጠራውና በአፋርና በሶማሌ ክልሎች የሚገኘውን አረም ለመቀነስ የተሰራ ነው። አረሙ የሚታረስ መሬትን በመሻማት የሚታወቅ እና ከፍተኛ የከርሰ ምድር ውሃን የሚመጥ በመሆኑ አረሙን ለማጥፋት በማሰብ የተሰራ ነው። በዚህም ግንዱን ወደ ከሰልነት ፍሬውን ደግሞ ከሌሎች ሰብሎች ጋር በመቀላቀል ለእንስሳት መኖነት ለመቀየር የሚያስችል ማሽን ነው። ማሽኑ ለየት የሚያደርገው ኤሌክትሪክ ካርበናይዘር የተባለው ክፍሉ ጭስ አልባ መሆኑ ነው። ማሽኑ 16 ሰዓት መስራት ይችላል።
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች የኢፍጣር መርሀ-ግብር አካሄዱ፤
መርሃ-ግብሩ በተለይም የቢሮው እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችን አብሮነት እና አንድነት በመፍጠርና በማጠናከሩ ረገድ ሚናው ላቅ ያለ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ተናግረው የዛሬውን የኢፍጣር መርሀ-ግብር ላዘጋጁ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።
በዚህ የኢፍጣር መርሃ-ግብር ላይ የቢሮው አመራሮች፣ የኮሌጆች ዲኖች እንዲሁም የአንድ ማዕከላት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል ።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ከሁሉም የአስተዳደሩ ወረዳዎች ለተወጣጡ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ገበያ እና ግብይትን በተመለከተ በንድፈ ሃሳብና በተግባር አቅማቸውን እንዲገነቡ የሚያስችል መድረክ ተዘጋጀ፤
በዚህም ሞዴል ኢንተርፕራይዞቹ የሚፈጠርላቸውን የገበያ እድሎች እንዴት እንደሚጠቀሙ በተለይም ከተቋማትና ከደንበኞቻቸው ጋር የሚኖራቸውን ግንኙነት በሚያሻሽሉበትና በሚያሳድጉበት አግባብ ላይ ግንዛቤ ተፈጥሮላቸዋል፡፡
በተያያዘ በቀጣይ ለሚዘጋጀው ባዛር ያላቸውን አገልግሎትና ምርት ለህብረተሰቡ በማቅረብ እራሳቸውን የሚያስተዋውቁበትና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት እንዲሆን ለዚህም በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከላት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ አሳስበዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአስተዳደሩ የገጠር አራቱም ወረዳዎች ስር የሚገኙና በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ድጋፎች የሚደረግላቸው ኢንተርፕራይዞችን ወደ ሞዴል ኢንተርፕራይዝነት ለማሳደግ የሚያስችል የመስክ ምልከታና ልየታ ቀጥሎ በአሰሊሶ ወረዳ ተካሄደ።
በዛሬው ዕለትም በአሰሊሶ ወረዳ የተለዩ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ምልከታ የተደረገ ሲሆን ቀሪ የአስተዳደሩ ገጠር ወረዳዎች ላይ የሚገኙ ኢንተርፕራይዞች በተመሳሳይ ምልከታ እና ልየታ የሚደረግ ሲሆን ከዚህ በፊት ይነሳ የነበረውን የተደራሽነት ጥያቄዎች ለመመለስ የቢሮው አቅጣጫ አካል መሆኑም የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሀ/ማርያም አስታውቀዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
መጋቢት 19/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ