1 325
مشترکین
+224 ساعت
+67 روز
+11030 روز
آرشیو پست ها
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
#ዜና | የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አድራ ፕሮጀክት የ 5000 ዋት ሶላር ፒቪ ኢኒስታሌሽን እና ኮሚሽኒንግ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ ።
#Dire tv አማርኛ ሚያዚያ 28/2017
በድሬዳዋ አስተዳደር በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና በአድራ ኢትዮጵያ በቅንጅት እየተሰራ ያለ የኤሌትሪክ ሀይል የሚሰራ በአይነቱ ለየት ያለ ሶፍት ዌር የተገጠመለትን የኮሌጁን የኤሌክትሪክ ዲፖርትመንት ሙሉ ለሙሉ በሶላር ሀይል ኢንዲጠቀሙ የሚያደርግ ፕሮጀክት ከጀርመን ሀገር በመጡ የሶላር ዘዴዎች የተሰራ 5000 ዋት ሶላር ፒቪ ዝርጋታ በትብብር በመስራት በይፋ የርክክብና የምረቃ መርሀ ግብር ተካሂዷል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራና ክሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸዉ በጸሀይ ሀይል የሚሰራ የሀይል ምንጭን መጠቀም ውስጥ የታዳሽ ሀይልን የመጠቀም አዲስ ልምድና አዲስ አቅምን የፈጠረ መሆኑን ገልጸው በተጨባጭ ያለዉን አስተዳደሩ የሚፈልገዉን ቴክኖሎጂ የሞላ የስራ እድልን መፍጠር ላይ ከዚህ በላይ መስራት ይገባናል ብለዋል ።ድርጅቱ ላደረገው ድጋፍም በቢሯቸውና በአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።
የአድራ ኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳሬክተር ዶ/ር ዘሪሁን አዋኖ በበኩላቸው ወጣቶች በታዳሽ ሀይል በሶላር ሀይል መሳቢያ ተከላ ሥራ ሰልጥነዉ ህዝባቸዉና ሀገራቸዉን እንዲያገለግሉ ብሎም የራሳቸውን ህይወት እንዲለዉጡ አላማ ይዞ እየሰራ ያለ ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዉ ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት በማድረግ ወጣቱ ከስራ ፈጠራ ወደ ሀብት ፈጠራ እንዲገባ የሚያነሳሳ ፕሮጀክት ነዉ ሲሉ ተናግረዋል ።
የኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁ እንደ አስተዳደር ከያዝነዉ ድሬዳዋን የዘመነች ከተማ የማድረግ ግንባታ ላይ ትልቅ ሚና የሚጫወት ፕሮጀክት ነዉ ብለዋል ።
አድራ ኢትዮጵያ ፕሮጀክቱ ሲጀመር ለ120 ሰልጣኞች የስራ እድል ለመፍጠር የታሰበ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ከ46 በላይ ሰልጣኞችን አሰልጥኖ በማስመረቅ ለሁለተኛ ዙር ምዕራፍ እንዲሁ አሰልጥኖ ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ይገኛል ።
አድራ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ላለፉት አርባ ሁለት አመታት የተለያዩ የልማት ስራዎችን በተለይ የነብስ አድንና ዜጎችን ህይወት መለወጥ ላይ ትኩረት አድርጎ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ሲሰራ የቆየ አሁንም እየሰራ ያለ ድርጅት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ከኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በአጫጭር ስልጠናዎችና በሶላር ፒቪ ሲስተም መስመር ዝርጋታና ጥገና ተማሪዎችንንና መምህራንን የማሰልጠንና የማብቃት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ከመድረኩ ተገልጿል።
ሰላም ይኄይስ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የውይይት መድረክ አካሄዱ።
"የመሃሉ ዘመን!" በሚል መሪ ቃል የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ የተወያዩ ሲሆን ውይይቱም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት ተከታታይ 7 አመታት ለውጡን ለማፅናት በተደረጉ ጥረቶች፣ የተገኙ ውጤቶች፣ ያጋጠሙ ውስጣዊ፣ ቀጠናዊና አለም አቀፋዊ ተግዳሮቶችና የተወሰዱ እርምጃዎች እንዲሁም አሁናዊ ሀገራዊ ሁኔታና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ ሆኗል።
በውይይቱም የአስተዳደሩ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንደተናገሩት የቢሮው ሰራተኞችና አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጠራ ግንዛቤ መያዛቸው እንደሀገር ሊገጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችን በሚገባ ለመቀልበስ እንዲሁም የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የኢትዮጵያን ብልጽግና እውን በማድረግ ሂደት የማይዝልና የማይታክት አቅም የሚፈጥር ይሆናል ብለዋል።
በመድረኩ "የመሃሉ ዘመን!" በሚል መሪ ቃል ለውይይት መነሻነት የሚሆን ሰነድ በቢሮው የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ቀርቦ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎበታል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 28/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
4ኛው ሀገር ዓቀፍ ክህሎት ቴክኖሎጂ እና ጥናትና ምርምር ውድድር ዛሬ በዲጂታል ተወዳዳሪነት ቀን የተለያዩ የክህሎት እና የቴክኖሎጂ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው።
የድሬዳዋ አስተዳደርም በአሰልጣኝ በሰልጣኝ እና በኢንተርፕራይዞች ተወክሎ ኢትዮጵያን አሸናፊ ለማድረግ በመወዳደር ላይ ይገኛሉ።
ከሚካሄዱ ውድድሮች ጎን ለጎን የቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽኖች እና ባዛር በኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ግቢ እየተካሄደ ይገኛል።
"ብሩህ አዕምሮዎች በክህሎት የበቁ ዜጎች"
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 28/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
ዛሬ በተጀመረው 4ኛው ሀገር ዓቀፍ የክህሎት ውድድር ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች የቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እና በቢሮው የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል ዳይሬክተር አቶ አሚን አብዱላሂ ውድድሩ በሚካሄድ በት ስፍራ በመገኘት ተወዳዳሪዎችን አበረታተዋል።
በዚህ ውድድር በአስር የክህሎት ተወዳዳሪ ሰልጣኝ ተማሪዎች፤ በሁለት አሰልጣኝ መምህራን የተዘጋጀ አንድ የተግባራዊ ጥናትና ምርምር፤ በአንድ አሰልጣኝ መምህር እና በአንድ ኢንተርፕራይዝ የተዘጋጁ ቴክኖሎጂዎች የድሬዳዋ አስተዳደርን ወክለው የሚወዳደሩ ይሆናል።
ቢሮው ለተወዳዳሪዎች መልካም እድል ይመኛል!
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 27/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ
Repost from Abiy Ahmed Ali 🇪🇹
እንኳን ለ84ኛው የዐርበኞች (የድል) በዓል አደረሳችሁ።
ቀደምት እናትና አባቶቻችን ነጻነትን በደም አስከብረው ሀገር አውርሰውናል። በዚህም እንኮራለን። እነዚህ ቀደምት ዐርበኞች በከፈሉት ዋጋ ዛሬ ቀና ብለን በነጻነት ዐደባባይ እንድንራመድ አድርገውናል። በድህነታችንና በኋላ ቀርነታችን ምክንያት ግን ነጻነታችን ሙሉ ሊሆን አልቻለም።
ነጻነታችን የተሟላ እንዲሆን ዛሬ ኢትዮጵያ የሁለተኛውን ዘመን ዐርበኞች ትፈልጋለች። የሁለተኛው ዘመን ዐርበኞች ኢትዮጵያን ወደ ሁለንተናዊ ብልጽግና በማድረስ ነጻነቷን ሙሉ የሚያደርጉ ናቸው። በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማኅበራዊ እና በዲፕሎማሲያዊ መስኮች በሚኖረው ሰላማዊ ጦርነት፣ ድህነትንና ኋላ ቀርነትን ታግለው የሚያሸንፉ ዐርበኞች ናቸው።
የዚህ ዘመን ዐርበኝነት ትጥቁ ዕውቀት፣ ክህሎት እና ዲሲፕሊን ነው። ወኔው የሀገር ፍቅር፣ ቆራጥነት እና ንጽሕና ነው። ግቡ የኢትዮጵያ ብልጽግና ነው።
ኢትዮጵያን ታላቅ ለማድረግ ሁለቱም ዓይነት ዐርበኞች ያስፈልጋሉ። ይህ ዘመን ደግሞ ይበልጥ ሁለተኛውን አርበኝነት ይሻል። ይሄ ቀን የመጀመሪያውን ዐርበኝነት መዘከሪያ፤ ለሁለተኛው ዐርበኝነት ደግሞ መሰረት ማፅኛ እንደሚሆን ተስፋዬ የላቀ ነው።
መልካም በዓል ይሁን!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም
የገጠር ስራ እድል ፈጠራ ዘርፉን ለማጠናከር በአስተዳደሩ ገጠር ቀበሌዎች ተደራጅተው የቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻል ፕሮጀክት(LLRP) ድጋፍ ሊደረግላቸው የተለዩ ስራ ፈጣሪ በሴቶችና በወጣቶች የተደራጁ ኢንተርፕራይዞችን ሁኔታ የሚመለከት የመስክ ጉብኝት ተካሄደ፡፡
ይህ የመስክ ጉብኝት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ከዚህ ቀደም በአጠቃላይ የሥራና ክህሎት ስራዎች ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ተቀናጅቶ እና ተናብቦ የገጠሩን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች በሚሰሩበት አግባብ ላይ ከገጠር ወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ የተደረገ ሆኗል።
በተለይም በገጠር ሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ትኩረት በመስጠት የገጠር ስራ ዕድልን ስርዓትን ከዚህ በፊት የነበሩ ክፍተቶችን ማረምና መለወጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ይታወሳል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 25/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢንዱስትሪዎችን ፍላጎት መነሻ አድርገው የሚሰጡ የሙያ ስልጠናዎች የሚስተዋለውን የሰለጠነ የሰው ሀይል እጥረት መቅረፍ እንደሚያስችሉ ተገለፀ::
ሚያዚያ 25/2017 ዓ.ም
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በEASE ፕሮጀክት አማካኝነት በኢንዱስትሪው የሙያ ፍላጎትን አስመልክቶ በተዘጋጀው የዳሰሳ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ::
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ባስተላለፉት መልዕክት "በቀጣይ እንደ ተቋም በሚኖረን ትግበራና ፕሮጀክቱም ትኩረት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ውስጥ አንደኛው የኢንዱስትሪውን ፍላጎት ምንነትን ተገንዝቦ ስልጠናዎችን በዛ አግባብ መስጠት በመሆኑ ይህን የፍላጎት ደሰሳ እዲዘጋጅ እድርገናል" ያሉ ሲሆን አክለውም በቀጣይ እንደ ተቋም በምናዘጋጀው የ10 አመት እስራቴጂክ እቅድ ላይ መሰል ጥናቶች እንደ ግብዓት የምናካትት ይሆናልም ብለዋል::
በኢንዱስትሪዎች ላይ የፍላጎት ዳሰሳ ከተደረገባቸው ነጥቦች አንፃር የተገኙ ውጤቶች፣ የተለዩ ክፍተቶችን በአጭር ጊዜና በረጅም ጊዜ ለመሙላት በሚያችል መልኩ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናቱ መዘጋጀቱን የገለፁት የኮሌጁ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ዲን አቶ ተሾመ ሸዋዬ ሲሆኑ አክለውም ይህን ጥናት እንደ መነሻ መሆኑን እና በቀጣይም የትኩረት ማዕከል በሆኑት ዘርፎች ላይ በልዩነትና በጥልቀት መሰል ጥናቶችን በማካሄድ ከኢንዱስትሪዎች ጋር ውጤታማ ስራዎችን ለማከናወን በእቅድ መያዙን ገልፀው በዚህ የፍላጎት ዳሰሳ ላይ ለተሳተፉ በሙሉ በኮሌጁ ስም ላቅ ያለ ምስጋናም አቅርበዋል::
በእለቱ የተዘጋጀው የኢንዱስትሪዎች የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ሰነድ በአሰልጣኝ መ/ር አቤል ዘገየ እና እሰልጣኝ መ/ር ነዋይ ይልማ አማካኝነት በመድረኩ ተሳታፊ ለነበሩ ባለድርሻ አካላት የቀረበ ሲሆን በቀረበው ሰነድም በኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚገኙ ባለሙያዎች ካላቸው የትምህርት ዝግጅት አንስቶ ከሚሰሩት ስራ አኳያ ያላቸው ተዛማችነት በዝርዝር የዳሰሰ ሲሆን በርካታ መሰል የተለዩ ክፍተቶችም በቀረበው ሰነድ ላይ ተመላክተዋል::
በመድረኩ በቀረበው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናትን መነሻ በምድረግም ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ገንቢ የሆነ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ለሰነዱ ተጨማሪ ግብአቶችም የተገኙበት መድረክ ነበር::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሚገኙ ሰራተኞች እና አመራሮችን በማሳተፍ ትግበራው በንቅናቄ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።
በዚህም ከሚያዚያ 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ የቢሮው አመራሮች እና ሰራተኞች ምዝገባ በማድረግ የዲጂታል ኢትዮጵያ ቤተሰብነታቸውን ማረጋገጥ ችለዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዚያ 24/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በአገር አቀፍ ደረጃ በተመረጡ አስፈፃሚ ተቋማት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በታሰበው የፕሮግራም በጀት አዘገጃጀትና አተገባበር ዙሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ለሚገኙ የቡድን መሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የስልጠና መድረኩ በቢሮው የዕቅድ በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ተዘጋጅቶ የቀረበ ሲሆን በዚህም በቀጣይ የጀት አጠቃቀም ውጤታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል አቅም የሚፈጥሩ ሰፊ ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሚያዝያ 24/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
