1 328
مشترکین
+224 ساعت
+87 روز
+9530 روز
آرشیو پست ها
በአስተዳደሩ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው ስድስት ወራት የስራ አጥነት ምጣኔን ከ18 ከመቶ በታች ለማድረስ የተያዘውን ዕቅድ ማሳካት መቻሉን ተገለጸ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር የ2017 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የማዘጋጃቤታዊ አገልግሎት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት በስራ እድል ፈጠራ በከተማ እና በገጠር ለ10,588 ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድሎች ለመፍጠር ታቅዶ ለ9,995 ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን የእቅዱን 94% ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።
በአስተዳደሩ የዋጋ ግሽበትን በመቆጣጠር እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ በ2016 የነበረውን የ28 በመቶ የዋጋ ንረት እና የ27 በመቶ የምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦች የዋጋ ግሸበት ለመቀነስ በስድስት ወሩ 17.3 በመቶ በማዉረድ በበጀት ዓመቱ ለታቀደዉ ከ10 በመቶ በታች ለማድረግ የተያዘውን እቅድ ማሳካት መቻሉ ተመላክቷል።
የአስተዳደሩን ገቢ በተመለከተ በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት 3.3 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ማለትም 2.8 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ የተቻለ ሲሆን የእቅዱ 85% ማሳካት ተችሏል።
የካፒታል ፕሮጀክት አፈጻጸምን በተመለከተ በበጀት አመቱ 123 አዲስ እና 35 ነባር በጥቅሉ 158 ፕሮጀክቶች በካፒታል በጀት ተደግፈው እንዲሰሩ የታቀዱ ሲሆን የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ሲታይ 14 ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁ፤ 4 ፕሮጀክቶች በመጠናቀቅ ሂደት ላይ ያሉ 60 ፕሮጀክቶች በጥሩ አፈጻጸም የተጠናቀቁ መሆናቸው በሪፖርቱ ተገልጿል።
በግብርና ዘርፍ የግብርና ምርትና ምርታማነትን የማሳደግና የአምራቹን ህብረተሰብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም ለኢኮኖሚ ዘርፍ አጋዥ ሚና ለመጫወት በአነስተኛ አርሶ አደሮች እርሻ በሚከናወኑ የሰብል፤ የእንስሳት እርባታና የከተማ ግብርናን ልማት እንቅስቃሴ እየተከናወኑ ተግባራት በተሻለ አፈጻጸም የነበራቸው መሆኑ በሪፖርቱ ተመላክቷል።
©️DGC ጥር 28/2017

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት (SNV) ጋር በመተባበር በወጣት፣ ሴቶች እና አካል ጉዳተኞች ለሚመሩ በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር ለሚገኙ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች በበግና ፍየል ማድለብ ለተሰማሩ በአጠቃላይ አስር ማህበራት ለእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ 100,000 ብር የሚገመት ስራ ማስጀመሪያ ድጋፍ ተደረገ፤
የድጋፍ ርክክብ ስነ ስርዓቱ የቢሮው ተወካይ እና የልማት ድርጅቱ ተወካይ እንዲሁም የእንስሳት ጤና እና ሀብት ልማት ተወካይ በተገኙበት የተደረገ ሲሆን የተደራጁት ወጣቶች፣ ሴቶችና አካል ጉዳተኛ ዜጎች የሥራ እድል ለራሳቸውና ለሌሎች እንደሚፈጥሩ እንዲሁም ለሌሎች ምሳሌ በመሆን በበግና ፍየል ማድለብ ላይ በአነስተኛ አቅምና እውቀት አሁን በመጀመር በቀጣይ አስፍተውና አጠናክረው እንዲቀጥሉ ከባለሙያዎች ጋር ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ይህም ድጋፍ ከዚህ በፊት ሲደረግ የነበረው ተከታታይ ድጋፍ አካል ነው፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 27/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+4
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በጫኝና አውራጅ ስራ ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች ለተከታታይ 5 ቀናት ሲሰጥ የነበረው በህይወት ክህሎት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
ወጣቶችን በህይወት ክህሎት የበቁና በስራ ቦታቸው ለሚገጥማቸው ጉዳዮች ሁሉ ፈጠራ የተሞላበት እና ተገቢውን ተግባራት እንዴት ማከናወን እንደሚችሉ ትኩረቱን ያደረገው ይህ ስልጠና ወጣቶቹን ለስራ ዝግጁ እንዲሆኑና ፈጠራ የታከለበት ስራዎችን መስራት እንዲችሉ የሚያደርግ ስልጠና እንደሆነ በስልጠናው ወቅት ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተጨማሪም ሰልጣኞቹ ከሚሰሩት ስራ ጎን ለጎን ትምህርትና ስልጠናዎችን በኮሌጁ በኩል ማግኘት እንደሚችሉ ለሰልጣኞቹ ገለጻ ተደርጓል፡፡
በኮሌጁ የተሰጠው ይህ ስልጠና በድሬዳዋ ስራ ክህሎት ቢሮ እና በኮሌጁ የተዘጋጀ ሲሆን በቀጣይም እንዲህ አይነት ስልጠናዎች በከተማና በገጠር ክላስተሮች በሰፊው የሚሰጥ ይሆናል፡፡
የኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ጥር 27/2017 ዓ.ም ድሬዳዋ
የቢሮው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከኢንደስትሪው ጋር ያለውን ግንኙነት ለአሰልጣኝ መምህራን አቅም መገንባት እና ለአጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለጸ፤
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የአሰልጣኝ ልማት ቡድን የAUTOMOTIVE ዘርፍ አሰልጣኝ መምህራን በMOENCO ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ለሁለት ወራት የሚቆይ የኢንዱስትሪ ላይ ተግባራዊ ስልጠና ያለበት ሂደት ላይ ምልከታ አደረገ፡፡
በምልከታው የካምፓኒው ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎችም ለአሰልጣኞች ያላቸውን ክህሎት እያካፈሉ መሆኑንና ይህ ግንኙነትም ከፍ ብሎ ለዘርፉ አጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ እድል ምችችት በር የከፈተ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፤
የካምፓኒው አመራሮች የዘርፉን ስትራቴጂ በመረዳት አሰልጣኞቹን ተቀብለው እያደረጉ ላሉት የቴክኖሎጂ እና እውቀት ሽግግር በዘርፉ ያለን የስልጠና ጥራት እና የኢንዱስትሪውን አጋርነት እያረጋገጠ ያለ ቅንጅታዊ አሰራር መፈጠሩ ተመላክቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 27/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የቢሮው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ከኢንደስትሪው ጋር ያለውን ግንኙነት ለአሰልጣኝ መምህራን አቅም መገንባት እና ለአጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሚገኝ ተገለጸ፤
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት የአሰልጣኝ ልማት ቡድን የAUTOMOTIVE ዘርፍ አሰልጣኝ መምህራን በMOENCO ድሬደዋ ቅርንጫፍ ለሁለት ወራት የሚቆይ የኢንዱስትሪ ላይ ተግባራዊ ስልጠና ያለበት ሂደት ላይ ምልከታ አደረገ፡፡
በምልከታው የካምፓኒው ኃላፊዎች እና አስተባባሪዎችም ለአሰልጣኞች ያላቸውን ክህሎት እያካፈሉ መሆኑንና ይህ ግንኙነትም ከፍ ብሎ ለዘርፉ አጠናቃቂ ሰልጣኞች የስራ እድል ምችችት በር የከፈተ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል፤
የካምፓኒው አመራሮች የዘርፉን ስትራቴጂ በመረዳት አሰልጣኞቹን ተቀብለው እያደረጉ ላሉት የቴክኖሎጂ እና እውቀት ሽግግር በዘርፉ ያለን የስልጠና ጥራት እና የኢንዱስትሪውን አጋርነት እያረጋገጠ ያለ ቅንጅታዊ አሰራር መፈጠሩ ተመላክቷል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 27/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ EASE ፕሮጀክት የሩብ አመት አፈፃፀምና የቀጣይ ስድስት ወር እቅድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ::
በዛሬው እለት በተካሄደው መድረክ የEASE ፕሮጀክት ወደ ትግበራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ እስከ እሁን የነበረውን የአፈፃፅም ትግበራ እንዲሁም በፕሮጀክቱ የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድን መነሻ በማድረግ ከፕሮጀክቱ ኢንዱስትሪ እድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላት ጋር የውይይት መድረክ በሀረር ተካሂዷል::
መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ በንግግራቸው እንደገልፁት ምንም እንኳን የEASE ፕሮጀክትን ወደ ትግበራ ከገባ አጭር ጊዜ ቢሆንም እስካሁን በደረስንበት አፈፃፀም መሰረት ወቅቱን ጠብቆ ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ ይህን መድረክ ተዘጋጅቷል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም በመድረኩ በሚቀርበው የEASE ፕሮጀክት የቀጣይ ስድስት ወር እቅድ ላይ ከኢንዱስትሪው አኳያ ማካተት ሚገባንና የተዘነጉ ጉዳዮች ካሉ ከመድረኩ በሚገኘው ግብዓት መሰረት እቅዱን ለማሻሻል ተቋማችን ዝግጁ እንደሆነም ገልፀዋል::
የኮሌጁ ዲን አክለውም ይህ ፕሮጀክት ሲነደፍ እንደ ሀገር ማስመዝገብ የተፈለገው ውጤት እንዳለ ጠቅሰው በዚህም መሰረት Result Framework በሚኒስቴር መ/ቤቱ ፀድቆ ሲመጣ በፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት የኛ መመዘኛ እሱ ይሆናልም ብለዋል::
በፕሮጀክቱ የእስካሁን አፈፃፀም ሪፖርት በEASE ፕሮጀክት የሞኒተሪንግና ኢቫሉዌሽን አስተባባሪ ወ/ሮ ህይወት እሸቱ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በቀረበው አፈፃፀምም የኢንዱስትሪ አድቫይዘሪንግ ቦርድ ከማቋቋም ጀምሮ የፕሮጀክቱ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በልምድ ልውውጥና ስልጠናዎች የማብቃት እንዲሁም 65 ለሚሆኑ የተቋሙ አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች የአቅም ግንባታ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ መቻሉም ተገልፇል::
በተጨማሪም በቀረበው ሪፖርት በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሚዲያ ባለሙያዎች እና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አመራሮችና ተማሪዎች ስለ ዘርፉ ያለውን የተዛባ አመለካከት መቀየር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መካሄዱም በሪፖርቱ ከቀረቡት ነጥቦች ይገኙበታል::
በመቀጠልም የEASE ፕሮጀክት የቀጣይ ስድስት ወራት እቅድ በፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ለተሳታፊዎች የቀረበ ሲሆን በዚህም በቀጣይ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ለመፈፀም በእቅዱ ላይ የተመላከት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ በተቋሙ የሪኢኖቬሽን ስራዎች ፣ የአሰልጥኞች ስልጠና፣ የኢንተርፕሩነርሺፕ ስልጠናዎች እንዲሁ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መያዙ ከብዙ ጥቂቱ መሆኑን በቀረበው እቅድ ተመላክቷል::
የመድረኩ ተሳታፊዎች በቀረበው የፕሮጀክቱ አፈፃፀምና የቀጣይ እቅድን መነሻ በማድረግ ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት የሚረዱ ገንቢ እስተያየቶችና ምክረ ሃሳቦችን በስፋት አንስተው ውይይት የተካሄበት ሲሆን ኮሌጁን ጨምሮ የኢንዱስትሪ እድቫይዘሪንግ ቦርድ አባላትም ለቀጣይ የየድርሻቸውን አሳይመንቶችን በመውሰድ መድረኩ ፍፃሜውን አጊኝቷል::
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮሚኒኬሽን
ጥር 24/2017 ዓ.ም
ሀረር
በአስተደዳደሩ ኢንዱስትሪ ፓርክ በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች በስራ ቦታ ኤች አይ ቪ ኤድስን መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተዘጋጀ።
በመድረኩ በመልዕክት ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ሃይል ከተለያዩ ቦታዎች በስራ የሚገናኙበት እንደመሆኑ መጠን ለኤች አይ ቪ ኤድስ ተጋላጭነቱን ለመቆጣጠር ቢሮዉ ተከታታይነት ያላቸውን ስልጠናዎች እያዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪ የሙያ ጤንነትና ደህንነት ባለሙያዎችን በማሰልጠን በኢንዱስትሪዎች ውስጥ እንዲቀጠሩ መደረጉ በቢሮው በኩል ትልቅ ስራ እንደተሰራ አስታውሰው ጤንነቱና ደህንነቱ የተጠበቀና የተረጋገጠ አምራች ሃይል የሆነውን ወጣት ቢሮው ባለሙያ በማዘጋጀት የሚሰሩበት ኢንዱስትሪ ድረስ በመሄድ ግንዛቤ እንዲፈጠር መደረግ መቻሉንም ኃላፊዋ አክለው ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 24/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ኢ-መደበኛ አንቀሳቃሾችን ወደ መደበኛ ኢንተርፕራይዝ እንዲሸጋገሩ ከአበዳሪ ተቋማት ጋር በመተባበር በቀጣይም ብድር የሚያገኙበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ይህን የስልጠና መድረክ ለኢ-መደበኛ አንቀሳቃሾች ሲያዘጋጅ የሥራን ጠቀሜታ በመረዳትና ለሥራ ያላቸውን ተነሳሽነት በመጨመር የራሳቸውንና የቤተሰቦቻቸውን ህይወት እንዲለውጡ አስፈላጊና ጠቃሚ የሆኑ መሠረታዊ የንግድ ክህሎቶች እንዲጨብጡ ታሳቢ ያደረገ ነው፤
የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ መቅደስ ከፈለኝ እንደገለጹት አንቀሳቃሾቹ ይህን ስልጠና ከወሰዱ በኋላ በሥራ ፈጠራና ሥራ ፈጣሪነት ላይ ግንዛቤያቸውን የሚጨምር ሲሆን በንግዱ ሙያ ውስጥ ውጤታማ ሊያደርጉ የሚያስችላቸውን ባህሪ በመላበስና ብቃቶችን እንዲያዳብሩ የሚያግዛቸው እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ
በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ አጫጫር የሙያ ስልጠና ለመስጠት የተደራጀው የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል እና መቆጣጠር እንዲሁም የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ አሰጣጥ ስልጠና በአዲሱ የሙያ ደረጃ መሰረት አጫጭር የቴክኒክና ሙያ ስልጠና እንዲሰጥ የእውቅና እድሳት ለማድረግ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ ምልከታ ተደረገ።
በአጠቃላይ ለስልጠናው አስፈላጊ የሆኑ የሰው ሃይልና የማሰልጠኛ መሣሪያዎች ስለመሟላታቸው እንዲሁም የስልጠና አሰጣጥ አቅምን በምልከታ ለማረጋገጥ በባለሞያዎች የተዋቀረ ቡድን ማሰልጠኛውን ከሚመሩ እና ከሚያስተባብሩ ባለሙያዎች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ማሰልጠኛው ለአንድ አመት የተሰጠውን የምዝገባ ፈቃድ አፈጻጸም ጥሩ መሆኑ መመልከት የተቻለ ሲሆን የቀጣይ ሶስት አመታት የስልጠና የእውቅና ፈቃድም በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ በኩል የሚያገኝ ይሆናል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥር 23/2017 ዓ.ም
ድሬዳዋ