fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

رفتن به کانال در Telegram
1 317
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+287 روز
+14730 روز
آرشیو پست ها
የተርንኪ ፕሮጀክትን ወደ ሙሉ የምርት አቅም የሚሸጋገርበት ሂደት በመስክ ተጎበኘ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ካሊድ መሐመድ በመጀመሪያው የሥራ ቀናቸው በድሬዳዋ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የምርት ማዕከል የሚገኘውን የተርንኪ ፕሮጀክትን አሁናዊ ሁኔታ በአካል በመገኘት ጎብኝተዋል። በጉብኝቱም በማዕከሉ የሚገኙ የተለያዩ ማሽኖችንና በአሁኑ ወቅት እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ሂደቶችን ተመልክተዋል። ጉብኝቱ ከዓመታት በፊት የተቋቋመውን የተርንኪ ፕሮጀክት ወደ ምርትና ሥልጠና ማዕከልነት ለማሳደግ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ለመረዳትና ያለውን አቅም በተግባር ለመጠቀም የሚያስፈልጉ ቀጣይ እርምጃዎችን ለመለየት ያለመ ነው። አቶ ካሊድ መሐመድ ከጉብኝቱ በኋላ ማዕከሉ በቅርቡ ወደ ሙሉ የምርት ሥራ በመግባት የተቋሙን የምርትና የሥልጠና አቅም እንዲያሳድግ እንደሚሠሩ ገልጸዋል። በዚህም “እያመረትን እናሰለጥናለን፤ እያሰለጠንን እናመርታለን” የሚለውን መርህ በተግባር በማዋል፣ ሥልጠናን ከተግባራዊ ምርት ጋር በማስተሳሰር የተቋሙን አቅም ለማጠናከር ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል። የምርት ማዕከሉን ወደ ሙሉ የሥራ አቅም ማሸጋገር የቴክኒክና ሙያ ሥልጠናን ከተግባራዊ ልምድ ጋር ለማጣመር፣ የማሽኖችን አጠቃቀም ለማሻሻልና የኮሌጁን ተቋማዊ አቅም ለማሳደግ ወሳኝ እድል ይፈጥራልም ብለዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም

የቀድሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ አዲስ ለተመደቡት የቢሮው ም/ኃላፊ እና የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ካሊድ መሐመድ የሥራ ርክክብ አደረጉ። ‎ በሥራ ርክክብ ወቅትም ወ/ሮ ፈጡም የተቋሙን የስራ ሁኔታ፣ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና በቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮችን በተመለከተ ለአዲሱ የቢሮው ም/ኃላፊ እና የኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ካሊድ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በስተመጨረሻም ወ/ሮ ፈጡም  ለአዲሱ የሥራ ኃላፊ አቶ ካሊድ እና ለኤጀንሲው ሰራተኞች መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም

#ዜና_ሹመት!! አቶ ካሊድ መሐመድ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መላ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ
#ዜና_ሹመት!! አቶ ካሊድ መሐመድ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል። መላ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞችም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎ ይመኛሉ!!! መልካም የስራ ዘመን!!!!

#ዜና_ሹመት!! የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የከንቲባው የ
#ዜና_ሹመት!! የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የነበሩት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የከንቲባው የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል። መላ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ አመራሮች እና ሠራተኞችም መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንልዎ ይመኛሉ!!! መልካም የስራ ዘመን!!!!

የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች በሙያው የሚተማመን ብቁ ዜጋ ማፍለቂያ እየሆኑ እንደሚገኝ ተገለፀ በድሬደዋ አስተዳደር የሚገኙ ሁለቱ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች (የድሬዳዋ እና የኢትዮጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች) በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ከአንድ ሺህ ሁለት መቶ በላይ ተማሪዎች አስመርቀዋል። የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ -ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን በአንድ ሀገር በዜጎች ልማት እንዲሟሉ ከሚጠበቁት አንዱና ዋንኛው በየደረጃው ያለ ትምህርት መሰረተ ልማትና አገልግሎት መሆኑን ገልፀዋል። የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች በርካታ ዜጎቸን በተለይም ወጣቱን አምራች ሀይል እንዲሆኑ የሚያስችል እውቀትና ክህሎት እያስጨበጡ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በስነ-ስረአቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ ተመራቂዎች ከእውቀት ወደ ተግባር፣ ከክህሎት ወደ ምርታማነት፣ ከግል ስኬት ወደ ማህበራዊ አስተዋጽኦ የተሸጋገሩበት አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉ ገልፀዋል። አስተዳደራችን በንግድ፣ በትራንስፖርት፣ በሎጅስቲክስ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ያለውን አቅም ለመጠቀም ብቁ ባለሙያዎች እንደሚያስፈልጓት ይህንን ገበያው የሚፈልገውን ባለሙያ በማፍራት እረገድ ደግሞ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆች ትልቅ አስተዋጽኦ እየተወጡ እንደሚገኝ ዶ/ር ፍቃዱ ጠቁመዋል። ተመራቂዎች ብቃት እና በዉጤት ተወዳዳሪነት፣ ስራ ፈላጊ ብቻ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ መሆን፣ ሙያቸውን በታማኝነትና በሃላፊነት መተግበር በቀጣይ ጊዜያቸው ሊከተሉት የሚገባ መርህ እንዲሆን ቢሮ ኃላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል። በሌላ በኩል የቢሮው ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጆቹ  በሙያው የሚተማመንና ለሀገር የሚቆረቆር ዜጋ እንዲያፈሩ በሚያስችል አቅጣጫ መሰረት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል። ©️ DGC ጥቅምት 7/2019 ዓ.ም

#አሁን #Happening_Now የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የ2018 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ምረቃ ስነ-ስርዓት
#አሁን #Happening_Now የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የ2018 ዓ.ም የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ከድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ህጋዊ የስልጠና ፍቃድ ወስደው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚሰጡ የመንግስትና የግል ኮሌጆች የሚያሰለጥኑበት የሙያ አይነት፣ ደረጃና
+2
ከድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ህጋዊ የስልጠና ፍቃድ ወስደው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የሚሰጡ የመንግስትና የግል ኮሌጆች የሚያሰለጥኑበት የሙያ አይነት፣ ደረጃና የፍቃድ ጊዜ ዝርዝር፡፡

የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትና አፈጻጸም ለማጠናከር፦ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የወረዳ ሥራ ማዕከላትን በመስክ ጎበኙ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ የወረዳ ሥራ ማዕከላትን በአካል በመጎብኘት የሥራ አካባቢያቸውን፣ የአገልግሎት አሰጣጣቸውንና የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ተመልክተዋል። ጉብኝቱ የሥራ ማዕከላቱን ነባራዊ ሁኔታ በቀጥታ ለመረዳት፣ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመለየትና የሥራ ዕድል ፈላጊዎች ተደራሽና ተቀናጅቶ የሚሰጥ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን ለመለየት ያለመ ነው። የሥራ ማዕከላት የሥራ ዕድል ፈላጊዎችንና የሥራ ፈጣሪዎችን ከሚመለከታቸው የአገልግሎት መዋቅሮች ጋር በማገናኘት የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታት ወሳኝ ሚና አላቸው። በመሆኑም የማዕከላቱን የሥራ ሁኔታ በቅርበት መከታተልና የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመለየት ተገቢውን የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ አገልግሎቶችን ለማጠናከር ያለውን ፋይዳ ያመለክታል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም

የሥራ ማዕከላትን ተደራሽነትና አፈጻጸም ለማጠናከር፦ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ የወረዳ ሥራ ማዕከላትን በመስክ ጎበኙ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ፍቃዱ በየነ በቢሮው የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ሥር የሚገኙ የወረዳ ሥራ ማዕከላትን በአካል በመጎብኘት የሥራ አካባቢያቸውን፣ የአገልግሎት አሰጣጣቸውንና የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች ተመልክተዋል። ጉብኝቱ የሥራ ማዕከላቱን ነባራዊ ሁኔታ በቀጥታ ለመረዳት፣ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመለየትና የሥራ ዕድል ፈላጊዎች ተደራሽና ተቀናጅቶ የሚሰጥ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን ለመለየት ያለመ ነው። የሥራ ማዕከላት የሥራ ዕድል ፈላጊዎችንና የሥራ ፈጣሪዎችን ከሚመለከታቸው የአገልግሎት መዋቅሮች ጋር በማገናኘት የሥራ ዕድል ፈጠራን ለማበረታታት ወሳኝ ሚና አላቸው። በመሆኑም የማዕከላቱን የሥራ ሁኔታ በቅርበት መከታተልና የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመለየት ተገቢውን የመፍትሔ አቅጣጫ ማስቀመጥ የሥራ ዕድል ፈጠራ አገልግሎቶችን ለማጠናከር ያለውን ፋይዳ ያመለክታል። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም

የሁለቱ መንግሥት ኮሌጆች አጠናቃቂ ሰልጣኝ ተማሪዎች የምርቃት ፕሮግራም በነገው ዕለት እንደሚካሄድ ተገለጸ በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሥር በሚገኙት የድሬዳዋ እና የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የሰለጠኑ ተማሪዎች ነገ ለሚካሄደው የምርቃት ሥነ-ሥርዓት የተደረጉ የዝግጅት ሥራዎች ተገምግመዋል። ግምገማው በቢሮው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ሥር የሚገኘውን የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የሚመሩት አቶ ጀማል አደን በመሩት ሂደት የተከናወነ ሲሆን፣ ለምርቃት ፕሮግራሙ ስኬታማ አፈጻጸም የተደረጉ ዝግጅቶች፣ የተግባራት አፈጻጸምና የቀሩ ሥራዎች ላይ ውይይት ተደርጓል። ግምገማው የምርቃት ሥነ-ሥርዓቱ በተቀናጀ፣ በሥርዓት በተመራና የሰልጣኞችን የስኬት ውጤት በሚመጥን መልኩ እንዲካሄድ የዝግጅት ሂደቱን ለማጠናከር ያለመ ነው። ተመራቂ ሰልጣኝ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ! የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ – የሕዝብ ግንኙነት ድሬዳዋ | ጥቅምት 6/2019 ዓ.ም