cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

✍وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا📖 ✍ጌታዬ ሆይ እውቀት ጨምርልኝ በል📖እውቀት የሚቀሰምበት ጉርፕነው::ወደ ቻናላችን እንኳንበሰላም መጡጣ

ሙሀደራ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
189
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

➲ትዕግስት 〰〰〰〰 ↪️ክፍል አንድ↩️ ➖➖➖➖➖➖ ➥ #ትዕግስት ከእስልምና ሐይማኖት ደረጃዎች ትልቁና ከፍ ያለ ቦታየሚሰጠው ነው፡፡ ➥ትዕግስትን ፣ አላህ ሱበሀኑሁ ወተአላ በቁርኣን ውስጥ በርካታ ቦታዎች ላይ አውስቶታል፡፡ ኢማም አህመድ ራሂመሁሏህ ተአላህ ትዕግስትን አስመልክቶ የሚከተለውን ተናግረዋል፡- "ذكر الله الصبر في القرآن الكريم في أكثر من تسعين موضعا" ➥“አላህ ሱበሀነሁ ወተአላ ትዕግስትን ፣ በተከበረው ቁርኣን ፣ ከዘጠና በላይ በሚሆኑ ቦታዎች ላይ አውስቶታል፡፡” መዳሪጅ አስ ሳሊኪን፡ 1/130 ➥ይህ የኢማም አህመድ ንግግር ትዕግስት ፣ ከፍ ያለ ቦታ የሚሰጠው መሆኑን ፤ ባሮች የታዘዙትን ለመስራት ፣ የተከለከሉትን ለመተው ፤ አላህ በወሰነባቸው መከራ እንዳይቆጩና እንዳያማርሩ በጣም የሚያስፈልጋቸው መሆኑን በግልጽ የሚጠቁም ነው፡፡ ➥ትዕግስት ፣ ለባሮች በጣም አስፈላጊ ፣ በማንኛውም ሁኔታቸው የማይነጠል ጓደኛቸው ሊሆን ይገባል፡፡ ያለትዕግስት የታዘዙትን መስራት አይችሉ ያለትዕግስት ወንጀልን መራቅ አይችሉም ፤ያለትዕግስት አላህ የወሰነባቸውን ውሳኔ ሳይበሳጩ ወደው መቀበል አይችሉም፡፡ በማንኛውም ሁኔታ በትዕግስት መሸለምን ለሙስሊም ምን በጣም አስፈላጊ አደረገው! ➥በቁርኣን ውስጥ ስለትዕግስት ፣ በተለያየ መልኩ በርካታ ቦታዎች ላይ አላህ ሱበሀነሁ ወተአላ አውስቷል፡፡ ➥ ትዕግስትን የሚያዙ ፣ እርሱን መቃረን ክልክል መሆኑን የሚገልጹ ፣ የትዕግስትን ባለቤቶች የሚያወድሱና የሚያሞካሹ ፣ ለትዕግስተኞች ያዘጋጀውን የተነባበረ ምንዳና ያማረ ፍጻሜ የሚያወሱ ለታጋሾች ወሰን የሌለው ብስራትን የሚያወሱ አንቀጾች መጠዋል፡፡ ➥ትዕግስተኞችን አላህ እንደሚወዳቸው ፤ በእርዳታው ፣ በጥበቃውና በእገዛው ከትዕግስተኞች ጋር እንደሆነ ግልጽ አድርጓል፡፡ ይህ ሁሉ ፣ ትዕግስት ደረጃው ላቅ ያለ ፣ ቦታው ከፍ ያለ እንደሆነና እርሱ በጣም አስፈላጊያችን መሆኑን ይጠቁማል፡፡ ➥ትዕግስት በርካታ ጎኖች እና ገጽታዎች ያሉት በመሆኑ ስለርሱ ብናወራ ሰፊ ከመሆኑ የተነሳ ቦታ አይበቃንም፡፡ ታዲያ ንግግራችን በተወሰነ ክፍል ብቻ እንዲገደብ ሆኗል፡፡ እርሱም “ሰዎች በሚያደርሷቸው ስቃዮችና መከራዎች ላይ መታገስ” የሚል ነው፡፡ ➥የሰዎች ተፈጥሯዊ ባህሪ እና ስነምግባር የተለያየ በመሆኑ በዚህ ዓለም ሲኖር ከእንግልትና ከመከራ ሰላም ሊሆን አይችልም፡፡ ታዲያ ሙስሊም በሚገጥሙት መከራዎች እና ፈተናዎች ላይ በትዕግስት ሊዋብና ሊሸለም ይገባዋል፡፡ ኢንሻአላህ ይቀጥላል ክፍል ሁለት ➢ኢንሻአላህ ትዕግስት የምትለዋን ኪታብ በተከታታይ በፅሁፍ የምናቀርብላችሁ ይሆናል አላህ ሁላችንንም በምናነበውና በምናውቀው ነገር ተጠቃሚዎች ያድርግልን!! ሺር አድርጉት⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️ https://t.me/joinchat/AAAAAFfWT8MnOTBo42gK-w
نمایش همه...
ተጋበዙልኝ ጣፋጭ ቲላዋ💦✍️
نمایش همه...
وان_ربك_لهو_العزيز_الرحيم_❤️‍_محمد_هشامM4A_128K.m4a9.86 KB
ውሀ ምድርን ህያው እንደሚያደርጋት ሁሉ ቁርአንም ቀልብን ህያው ያደርጋታል። ኢብኑል ቀይም ከቁርአን ጋር እንኑር...! = t.me/https_Asselefya1
نمایش همه...
AUD-20180306-WA0000.mp32.94 MB
ፊትናው በዛ ሀያእ ጠፍቶ ወጣ ስንል በመንደሩ ሴትም ወንድም በመኖሩ እሷም በወንዱ ስታፈጥ ወንዱም አይቷት ሲያገጥ ከንፈሯ መስሎ ወጥ በወጥ ይዟት ሲዞር ጎጥ ለጎጥ እጁን ትከሻዋ ላይ ማኖሩ ሲያቅፋት አለማፈሩ ሳትሆን ለሱ ባለቤቱ ወይ አይደለች ውድ እህቱ አልወለዳት ልጁ አይደለች ያልተፈቀደችለት አጅ ነብይ ነች እሷም ስቴድ አለማፈሯ ፊቷን አስመስላው አቧሯ ቀሚሷን ማሳጠሯ ብጣሽ ሻርፕ አርጋ ለፀጉሯ ብቅ ስትል በመንደሩ የሽቶዋ ሽታ በሰፈሩ ወንዶትን ሁሉ መጥራቱ ወደ ሀራም መጎተቱ ሀያእ አጥታ ልጅቱ ፈሳድ ሞላው ከቤቱ ጉዱ ተወርቶ አለማለቁ የሴት ከወንድ ድብልቁ በየቦታው መማቀቁ በየ ሚዲያው መሳሳቁ ሀያእ ቢጠፋ ከመንደር ወንጀል ቢበዛ በሀገር የፀሀዪ እንዲ ማቃጠል የብርዱ እንዲህ መቆምጠል በሌላ አይደለም አታማር ቻለው ምንም ቢመር ያንተው የኔም ወንጀል ሲበዛ ይከረፋል ለመስማትም ይቀፋል ሲያዩትም ያስከፋል ከኛአልፎ ለንፁሀኑም ይተርፋል ተውባ አድራጊ ጠፍቶ ፈሳድ ባለሙ ተስፋፍቶ ዛሬ ብትጮህ በደረቁ ህዝብ እንዲህ ማለቁ እሬሳ አይቶ መሳቀቁ ጉድኮ ነው መብዛቱ የወንጀላችን ማስጠላቱ ዳኢ ተብዬ ያ ወንዱ ዘፈን ሙዚቃ በመፍቀዱ ኢስላማዊ ፊልም ማለቱ ቢድአውን ማስፋፋቱ በዲኑ ላይ መጫወቱ ተውሂድ ሱናን በመርሳቱ አቤት ምድር ማስጠላቱ በዚህ ፈሳድ መሞላቱ ሲያንሰን ነው ፀሀይ ብርዱ ጠፍቷል ሁሉ መዋደዱ በዑለሞቻችን ማሾፍ በዝቶ ቢደአን ስንወድ ሱናን ጠልቶ እርስበርስ እዝነት ጠፍቶ ወሬያችን እንቶ ፈንቶ አይናፋርነት ተጠልቶ ፊትናው በዛ ሀያእ ጠፍቶ አይናፋርነት ተጠልቶ ስቃይ በዛ እዝነት ጠፍቶ። ,
نمایش همه...
👍 3
🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 በአጥፊዎች መመሳሰል ውጉዝ ነው ~ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ [مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ] "በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው።" 📚[ሶሒሕ አቢ ዳውድ፡ 3401] ⛔️ሙስሊም የሆነ ሰው ራሱን የማንም ቆሻሻ ባህል ማራገፊያ አያደርግም። ሰው እንዴት የፍቅረኛሞች ቀን (Valentine Day) የሚሉት የዝሙት ማስፋፊያ ልማድ ያስተዋውቃል? ዝሙትኮ በኢስላም ህይወት የሚያስነጥቅ ከባድ ወንጀል ነው። ከቻላችሁ በስርአት አግቡ። ካልሆነ አላህ እስከሚያገራላችሁ ድረስ በተቅዋና በሶብር ጠብቁ። በብልግና ውስጥ የሚፈለግ ደስታ ርክስትና ውርደትን ነው የሚያመጣው። ⛔️ሌላው የሚገርመው ነገር በትምህርት ተቋማት ውስጥ ''የእብድ ቀን (Crazy Day)" ብለው የሚያከብሩ መኖራቸው ነው። ትምህርት ቤቶች ይህንን ነው ለሃገርና ለትውልድ የምታወርሱት? ይሄ አደራን መብላት አይደለም? ወላጆች ሆይ! ይህንና መሰል የተጨመላለቁ ባህሎችን ለልጆች የሚያወርሱ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ልጆቻችሁን አታስተምሩ። ⛔️ከነጮች ከተወረሱ ነውረኛ ባህሎች ውስጥ ሌላው April the Fool የተሰኘው የጅላጅሎች ልማድ ነው። ያልተከሰቱ ሃሰተኛ ነገሮችን በመንገር ሰዎችን በማስደንገጥ ይዝናናሉ። ሰዎች ላይ ከሚፈጠረው ከባድ ድንጋጤ ይልቅ የራሳቸውን ቅፅበታዊ ደስታ ያስቀድማሉ። ውሸት በኢስላም ሐራም ነው። ለቀልድ እያሉ ማቅረቡ እውነታውን አይቀይረውም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- [وَيْلٌ لِلَّذِي يُحَدِّثُ بِالْحَدِيثِ لِيُضْحِكَ بِهِ الْقَوْمَ فَيَكْذِبُ وَيْلٌ لَهُ وَيْلٌ لَهُ ] "ሰዎችን ለማሳቅ ብሎ እየዋሸ ወሬን የሚያወራ ሰው ወዮለት! ወዮለት! ወዮለት!" 📚[አቡ ዳውድ፣ ነሳኢይ፣ ቲርሚዚይ እና አሕመድ የዘገቡት ሲሆን ሸይኹል አልባኒይ “ሐሰን” ብለውታል፡፡] ውሸቱ ሰዎችን ማስደንገጥ ሲኖርበት ደግሞ ይበልጥ የከፋ ወንጀል ይሆናል። የሌሎችን ብልሹ ባህል በማስፋፋት መልክ ሲቀርብ ደግሞ የበለጠ ፀያፍ ይሆናል። በጠቅላላው የቀረቡት ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ራሳችንን የሌሎች አጉል ባህል ማራገፊያ ልናደርግ አይገባም። ልጆቻችንንም ከእንዲህ አይነቶቹ ጎጂ ባህሎች ለመጠበቅ ልናነቃ ይገባል። IbnuMunewor https://telegram.me/ibnukedir
نمایش همه...
ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር(አቡ ዓማር)

የአላህ  መልዕክተኛ (ﷺ)  እንዲህ  ብለዋል፦ (ከሰዎች መካከል የመልካም በር ከፋች የሆኑና የመጥፎ በር ዘጊዎች የሆኑ አሉ ፤ እንዲሁም ከሰዎች መካከል የሸር  በር ከፋች የሆኑና የመልካም በር ዘጊ የሆኑ አሉ። አላህ የመልካም በር መክፈቻ ቁልፍ በእጁ ላደረገለት ‘ጡባ’ አለለት ፤  አላህ  የመጥፎ  በር መክፈቻ  ቁልፍ  በእጁ  ላደረገለት  ‘ወይል’ አለለት።) [ኢብኑ ማጃህ (237) ዘግበውታል። 

  🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 የፈጅር ሰላት ሱና በሦስት ነገሮች ይለያል…… 💎አንደኛው፦      ከሁሉም ሱንናዎች በላጭ ነው። ነብዩﷺ «ركعتا الفجر خير من الدنيا وما فيها» «የፈጅር ሁለት ረካዓዎች ከዱንያና በውስጧ ካለው ነገር ሁሉ በላጭ ናቸው።» ብለዋል። 💎ሁለተኛው፦      ጉዞም ላይ ይሁን ሀገር ላይ ተኩኖ ይሰገዳሉ። በተቃራኒው የሌላ ሰላት ሱናዎች ጉዞ ላይ ተኩኖ አይሰገዱም። 💎ሦስተኛው፦        የተለየ የተገደበ የሆነ ሱራ ይቀራባቸዋል። እሱም በመጀመሪያው ረከዓ 📖 "قل يا أيها الكافرون" እና: በሁለተኛው ረከዓ 📖"قل هو الله أحد" ነው።    /ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን አላህ ይዘንላቸው/ (شرح بلوغ المرام / ج4 / ص151). 🔻 ለፈጅር የምትሞላው አላርም ላይ 4 ደቂቃ ብቻ አሻሽለህ ብትሞላ «ከዱንያ እና ከያዘችው ነገር በአጠቃላይ የሚበልጥ» ኸይር ማግኘት ትችላለህ። Copy https://telegram.me/ibnukedir
نمایش همه...
ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር(አቡ ዓማር)

የአላህ  መልዕክተኛ (ﷺ)  እንዲህ  ብለዋል፦ (ከሰዎች መካከል የመልካም በር ከፋች የሆኑና የመጥፎ በር ዘጊዎች የሆኑ አሉ ፤ እንዲሁም ከሰዎች መካከል የሸር  በር ከፋች የሆኑና የመልካም በር ዘጊ የሆኑ አሉ። አላህ የመልካም በር መክፈቻ ቁልፍ በእጁ ላደረገለት ‘ጡባ’ አለለት ፤  አላህ  የመጥፎ  በር መክፈቻ  ቁልፍ  በእጁ  ላደረገለት  ‘ወይል’ አለለት።) [ኢብኑ ማጃህ (237) ዘግበውታል። 

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.