fa
Feedback
ECAEchannel

ECAEchannel

رفتن به کانال در Telegram
483
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+37 روز
+1130 روز
آرشیو پست ها
በሀገር ውስጥ ንግድ ላይ የሚያተኩር የፓናል ውይይት በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ============== አዲስ አበባ ነሐሴ 20 ቀን 2016 ዓ.ም(ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው “የኢትዮጵያን ይግዙ” የንግድ ሳምንት አካል የሆነውና ትኩረቱን በሀገር ውስጥ ንግድ ላይ የሚያደርግ የፓናል ውይይት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በፓናል ውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር የንግድ መግቢያ በር ከሆነው የንግድ ፍቃድ አሰጣጥ እስከ ቁጥጥር ሂደቱ ድረስ ሰፊ ውይይት በባለሙያወችና ባለድርሻ አካላት እንደሚካሄድ ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የንግድ ስርዓትና ላይሰንሲንግን ለማዘመን በተደረገው ስራ 89 በመቶ የሀገራችን ነጋዴዎች በኦንላይን አገልግሎት ባሉበት ሆነው ንግድ ፍቃዳቸውን ማውጣትና መደስ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ ሸማቹ ህብረተሰብ በዋጋ ንረትና በአቅርቦት እጥረት እንዳይቸገር1066የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች መቋቋመቸውን የተናገሩት ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ካለን የህዝብ ቅጥር አኳያ በቂ ባለመሆናቸው ማሳግ ላይ እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡ በተዘረጋው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ስርዓት መንግስት የነበረበትን 179 ቢሊዮን ብር እዳ ወደ 70 ቢሊዮን ብር ማውረድ መቻሉና ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ገልፀዋል፡፡

photo content

photo content
+9

“የኢትዮጵያን ይግዙ” ልዩ የንግድ ሳምንት ኢግዚቪሽንና ባዛር ተከፈተ፡፡ ነሃሴ 20 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) ======================= የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር "የኢትዮጵያን ይግዙ" በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው አገር አቀፍ የንግድ ሳምንት ኤግዚቢሽን በሚኒስቴሩ ቅጥር ግቢ ውስጥ በይፋ ተከፍቷል፡፡ ኤግዚቢሽኑ ለሚቀጥሉት 5 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ገዥና ሻጭን ማገናኘት፣ በዘርፉ ያለውን አቅም ማሳየት እንዲሁም ንግድን በተመለከተ ግንዛቤ የሚያሳድጉ ወርክሾፖች የሚደረጉበት መሆኑም ተመላክቷል፡፡ ኢግዚቪሽንና ባዛሩን መርቀው የከፈቱት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አደም ፋራህ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገር ናቸው፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያስገነባውን የወጪ ንግድ ምርቶች ማሳያ ማዕከልም በእለቱ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተመርቋል፡፡ በዚህ ልዩ የንግድ ሳምንት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የምርቶችና አገልግሎቶችን ጥራት ለማረጋገጥ በዓለም አቀፍ የአሰራር ስርዓቶች መሰረት እየሰጣቸው የሚገኙ የፍተሻ ላቦራቶር፣የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎቶችን በተመለከተ ለኤግዚቢሽኑ ጎብኚዎች ገለፃ በማድረግ የድርጅቱን አገልግሎቶች ለህብረተሰቡ የማስተዋወቅ ሥራ እየተሰራ ነው፡፡

የኢትዮጵያን ይግዙ” ልዩ የንግድ ሳምንት በነገው ዕለት በይፋ ይከፈታል፡፡ ነሃሴ 18 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) ================ “የኢትዮጵያን ይግዙ“ ልዩ የንግድ ሳምንት በ
+1
የኢትዮጵያን ይግዙ” ልዩ የንግድ ሳምንት በነገው ዕለት በይፋ ይከፈታል፡፡ ነሃሴ 18 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) ================ “የኢትዮጵያን ይግዙ“ ልዩ የንግድ ሳምንት በልዩ ልዩ መርሃግብሮች ታጅቦ ነገ እሁድ ነሀሴ 19 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ይከፈታል፡፡ በዕለቱ በመንግስትና በግል ሴክተር ተሳትፎ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገነባው የውጪ ምርቶች ማሳያ ቋሚ የኢግዚቪሽን ማእከል የመንግስት ኃላፊዎች፣ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ምሁራን ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ በተጨማሪም የቢሮ ህንፃ ምርቃት፣ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ የሚቀርቡበት ኤግዚቢሽንና ባዛር በድምቀት ይከፈታል፡፡ በንግድ ሳምንቱ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ የፓናል ውይይቶች፣ እውቅና እና ሽልማት እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚካሄዱ ይሆናል፡፡ በዚህ ልዩ የንግድ ሳምንት የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት በምርቶችና አገልግሎቶች እንዲሁም የአሰራር ስርዓቶች ከተቀመጠላቸው ሃገራዊና ዓለም አቀፋዊ የጥራት መስፈርቶች ወይም ደረጃዎች አሟልተው ወደ ገበያ እየቀረቡ ስለ መሆናቸው የሚያረጋግጥበት የፍተሻ ላቦራቶሪ፣ የኢንስፔክሽንና የሰርቲፊኬሽን አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ለመሳተፍ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ #የኢትዮጵያን ይግዙ!

የኢተምድ የሥራ አመራርና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡ ነሃሴ 17 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) ======================== “የምትተክል
+9
የኢተምድ የሥራ አመራርና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አከናወኑ፡፡ ነሃሴ 17 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) ======================== “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀንበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር በተለያዩ የሀገሪቷ አካባቢዎች እየተከናወነ ይገኛል። የዚህ ዘመን ተሻጋሪ አሻራን የመትከል መርሃ ግብር አካል በመሆን የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) የሥራ አመራር አባላት እና ሠራተኞች ከንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን በዛሬው እለት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ፓርክ ውስጥ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር “የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኝ በሚተከልበት የዚህ ታሪካዊ ቀን አካል በመሆናችን እድለኞች ነን በማለት በችግኝ ተከላው ለተሳተፉ አመራሮችና ሠራተኞችም ምስጋና አቅርበው ተሳትፎው ለመላው የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ተሳትፎ የተተከሉ ችግኞችንም በመንከባከብ እንዲደገም አሳስበዋል፡፡

‘የኢትዮጵያን ይግዙ’ የንግድ ሳምንት ሀገራችን ያላትን እምቅ አቅም ለማስተዋወቅ ያግዛል፡ =========================== አዲስ አበባ ነሐሴ14ቀን2016ዓ.ም (ንቀትሚ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በሚቀጥለው ሳምንት ‘የኢትዮጵያን ይግዙ’ በሚል መሪ ቃል የንግድ ሳምንት ኤግዚቪሽንና ባዛር ሊያካሂድ መሆኑን ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ የንግድ ዝውውርና የግብይት ሰንሰለቱ አጭር ግልፅና ቀልጣፋ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንዲሆን ማስቻል ብሎም ሀገራችን ያመረተቻቸውን ምርቶች ለዓለም ገበያ በማቅረብ የውጪ ምንዛሬ ግኝትን ማሳደግ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ሰፋፊ ስራዎችን በውጤታማነት ያጠናቀቀ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ነው ያሉት ሚኒስትሩ የሚሰሩ ስራዎችን ትውልድ እንዲያውቃቸው ለማድረግ የተሟላ ግልፀኝነት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ከዚህ ዓመት ጀምሮ በቋሚነት የንግድ ሳምንት እንደሚካሄድ ገልፀዋል፡፡ ሀገራችን የምርትና ምርታማነት ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትሩ በግብርና ምርቶች የራሷን አሻራ ለዓለም ያኖረች መሆኗን ጠቁመዋል፡፡ መንግስት በተከተለው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም እሳቤ ምርትና ምርታማነትን በሀገር ደረጃ ለማሳደግ በተደረገው ስራ ስንዴ ኤክስፖርት ማድረግ እንደተቻለ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) አብራርተዋል፡፡በሚቀጥሉት ዓመታትም ሌሎች ምርቶች ለዓለም ገበያ የሚቀርቡበትና ሰፊ ምርትና ምርታማነት ያለባት ሀገር በመሆኗ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተዘጋጀው የንግድ ሳምንት ‘የኢትዮጵያን ይግዙ’ የሚል ሁለት አንድምታዎች ያሉት መሪ ቃል መጠቀማቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያን ይግዙ ስንል ከዓለም የምናስገባቸውን ገቢ ምርቶች በሀገር ውስጥ መተካት ብሎም የውጪው ዓለም ጭምር ሀገር በቀል የሆነና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ኢትዮጵያ አምርታ ለዓለም ገበያ እያቀረበች መሆኑ ለማስተዋወቅና ያለንን አንፃራዊ ተወዳዳሪነት በመጠቀም የኢትዮጵያን እንዲገዙ ለማበረታታት እንደሆነ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ በሚዘጋጀው የንግድ ሳምንት የተለያዩ የፓናል ውይይቶች፣የወጪ ንግድ ምርቶች ማሳያ ማዕከል ምርቃ፣የተለያዩ እውቅናዎችና ሽልማቶች ከመካሄዳቸውም ባሻገር የተለያዩ መሰረታዊ ምርቶች የሚቀርቡበት በመሆኑ ማንኛውም ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ምርት የሚያገኝበት የሚገዛበት የንግድ ሳምንት እንደሚሆን እንደሆነ ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር )ተናግረዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን:- Email: fdremotri@gmail.com fdremotri@motri.gov.et facebook:-https://www.facebook.com Ethiopian-Ministry-of-Trade-and-Regional-Integration For trade license : www.etrade.gov.et website: www.motri.gov.et telegram channel :https://t.me/motri_gov_et https://t.me/etrade_gov_et https://www.youtube.com/Ethiopian Ministry of Trade& Regional Integration

ነሃሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) =================== Soft Skills, Beyond the Concept of Intelligence በሚል ርእስ የለስላሳ ክህሎት ምንነት
ነሃሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) =================== Soft Skills, Beyond the Concept of Intelligence በሚል ርእስ የለስላሳ ክህሎት ምንነትን፣አስፈላጊነቱን፣ ግለሰባዊ ክህሎቶች፣ ኢንተር- ፐርሰናል ስኪልስ እና ሌሎች ተዛማጅ ሀሳቦችን የተመለከተው እለታዊ የጥራት ቶክሾው ተካሂዷል፡፡

በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር::
በአንድ ጀምበር 600 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ዓሻራችንን እናኑር::

ነሃሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) =================== የቡድን ሥራ (Teamwork) በሚል ርእስ የቡድንንና የቡድን ሥራን ምንነት፣ የቡድን ሥራን ዓላማዎች፣ የውጤታማ
ነሃሴ 09 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) =================== የቡድን ሥራ (Teamwork) በሚል ርእስ የቡድንንና የቡድን ሥራን ምንነት፣ የቡድን ሥራን ዓላማዎች፣ የውጤታማ ቡድኖች ባህሪያት፣ የቡድን ምስረታ ደረጃዎች እና ለስኬታማ የቡድን ሥራ ጠቃሚ ምክሮችን የተመለከተው እለታዊ የጥራት ቶክሾው ተካሂዷል፡፡

photo content
+9

ኢተምድ ለአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡ ነሃሴ 09 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ (ኢተምድ) ==================== የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የISO 9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ሥርአት ሰርተፊኬት ሰጠ፡፡ በሰርተፊኬት አስጣጥ ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የውጤት ተኮር ስልጠናና ተቋማት አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር አበራ ብሩ እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ብቁ እና ተወዳዳሪ የሰው ሀይል ማፍራት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን በማስታወስ ለዚህም ኮሌጁ የጥራት ሥራ አመራር ስርአት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ባለቤት መሆኑ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ይጨምራል ብለዋል። የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ መዓዛ አበራ ሰርተፍኬቱን ባስረከቡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በምዘና ስርአት ለማለፍ የአመራር ቁርጠኝነት እና የስራ ትጋት የሚጠይቅ ተግባር መሆኑን በመግለፅ ለዚህም ኮሌጁ ያገኘው ሰርተፍኬት የአሰራር ስርአትን በማዘመን የደንበኞች እርካታን ለማሳደግ እንደሚረዳ ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ተግባረ-ዕድ ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ግሩም ግርማ በበኩላቸው ኮሌጁ የደንበኞችን እርካታ መነሻ በማድረግ የ9001:2015 የጥራት ሥራ አመራር ስርዓትን ለመተግበር ከታህሳስ 2015 ጀምሮ ወደ ተግባር በመግባት በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ የኮሌጁን ሰልጣኞች ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ብሎም ለከተማ አስተዳደሩ እሴት የሚጨምር እውቅና ማግኘቱን ገልፀዋል። ከሰርተፊኬት አስጣጥ ስነ-ስርአቱ በኃላ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ተካሂዷል፡፡

ምንጫቸው ያልታወቁ እና ከጥራት ጀረጃ በታች የሆኑ LED አምፖል፣ የኤሌክትሪክ ማከፋፈያና ዋየር ምርት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከገበያ ታገዱ። ============================= ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን እና የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን በጋራ በLED አምፑል፣በኤሌክትሪክ ማከፋፈያ እና በዋየርምርቶች ላይ በገበያ ላይ በተደረገ የገበያ ምርቶች ጥራትቁጥጥር መስረት ከገበያ ላይ በተወሰደው ወካይ ናሙና ላይበደረገው የሶስተኛ ወገን በላበራቶሪ ፍተሻ ውጤት (CES 272:2022 ፣ CES 273:2021) ፣CES 108,116፡2016፣CES 270-2024 እንዲሁም CES 111:2013 በቅደም ተከተል የደነገጋቸውንየጥራት መስፈርት ያላሟሉ እና በተደረገው የምርት ዱካ የማጣራት ሥራ መሰረት የአምራቹ ስምና አድራሻ የሌላቸው(የአስመጭውም ሆነ የአምራች ) ድርጅቱ ያልታወቁ ምርቶችመሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ስለሆነም በአዋጅ ቁጥር 813/2006፣ (CES 272:2022 እና CES 273:2021) ፣CES108,116፡2016፤CES 270-2024 እና CES 111:2013 የደነገጋቸውን የጥራት መስፈርት ያላሟሉ በመሆኑ በአንቀጽ23(1 እና 2) መሰረት ሽማቹ ህብረተሰቡ እነዚህን ምርቶችእንዳይጠቀም እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የክልል እናከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ መዋቅሮች ለሽማቹ ህብርተሰቡግንዛቤ እንዲፈጥሩ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እያሳሰበ እነዚህን ምርቶች ሲሽጥየተገኘ ነጋዴም ሆነ ግለሰብ በአዋጅ ቁጥር 813/2016 አንቀጽ 22 (10,11,13) መስረት ከሚመለከተው የፍትህ አካላት ጋር በመሆንአስፈላጊው አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃዎች እንዲወስድበጥብቅ እናሳስባለን፡፡ የምርት ጥራትን በጋራ እናስጠብቅ፡፡ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴ ለተጨማሪ መረጃ፡ Email: fdremotri@gmail.com fdremotri@motri.gov.et facebook:-https://www.facebook.com Ethiopian-Ministry-of-Trade-and-Regional-Integration For trade license : www.etrade.gov.et website: www.motri.gov.et telegram channel :https://t.me/motri_gov_et https://t.me/etrade_gov_et https://www.youtube.com/@ethiopian_ministry_of_trade