698
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
አንተ ልዩ ነህ
ብዙ ሰዎች በቀላሉ ያቆማሉ ነገሮች ሲጠናባቸው እንቅፋት ሲበዛባቸው
መሸሽን እራሳቸውን ማግለልን ይመርጣሉ ብዙ ሰዎች የሰዎችን ወቀሳ
ትችትን በመፍራት ህልማቸውን መኖር ያቆማሉ የሚወዱትን ነገር ለማግኘት ይፈራሉ ሰምተሀል ብዙ ሰዎች ነው ያልኩት አንተን አይጨምርም አንተማ ልዩነህ በማንም ወቀሳ አትበገርም ችግር ቢገጥምህም ትቀጥላለህ ፍርሀትህን ድል ትነሳለህ ማንም ባይረዳህም ትጓዛለህ ያሰብክበት ትደርሳለህ አንተን ልዩ የሚያደርግህ ይህ ነው ይህ ነው አንተን አሸናፊ የሚያደርግህ አሸናፊዎች ደግሞ ነገሮች ቢወሳሰቡም ሁኔታዎች ቢያስቸግሩም እስኪያሸንፋና ድል እስከሚነሱ ይጓዛሉ እንጂ ተስፋ ቆርጠው
ወይም ፈርተው አያፈገፍጉም እኚ ናቸዉ
ድል አድራጊዎች ማንኛውም ሰው አሸናፊ መሆን አይችልም አሸናፊ መሆን የሚችሉት ለሚሰሩት ነገር ልባዊ መነሳሳት የሚቀጣጠል የሚነድ ፍላጎት
ያላቸው ናቸዉ ።
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
የሚፈላ ውኃ ድንችን ሲያፈርሰው እንቁላልን ግን ያጠነክረዋል ።
በህይወታችሁ የሚያልፍ የትኛውም ሁኔታ ሊያፈርሳችሁም ሊያጠነክራችሁም ይችላል። ጉዳዩ ለሁኔታው የሰጣችሁት ምላሽ ይወስነዋል::
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
አንተ የትኛው ነህ? ምረጥ!
በዚህ አለም ሁለት አይነት ሰዎች አሉ፤ የመጀመሪያዎቹ ጊዜያዊ ደስታቸውን ያስቀድሙና ዘላለም ይለፋሉ፤ ሁለተኞቹ ግን ነገን አስበው ለጊዜው ይለፉና ዘላለም ያርፋሉ።
ህይወት ምርጫ ናት፤ ነገ የሚያኮራህን ውሳኔ አሁኑኑ ወስን! ተነስና እሰራዋለው ያልከውን ስራ! አደርገዋለው ያልከውን አድርግ! ወዳጄ ለዛሬ ደስታ ብለህ ነገህን አታበላሽ! ዳይ ተነስ!
https://t.me/yoni4600
አሸናፊ ነህ!
ሰው ምንድነው ቢሉ ደጋግሞ ያሰበውን ነው ይባላል፤ ስለዚህ ለማን ብለህ ነው አብዝተህ የጎደለህን ከሰው ያሳነሰህን የምታስበው?!
በቃ ተዓምር መስራት እንደምትችል ባንተ ምክንያት መጀመሪያ የራስህ ከዛ የቤተሰቦችህ ህይወት እንደሚቀየር አስብ እሱን እውነት ለማድረግ የምትችለው ጥግ ድረስ ጣር የቀረውን ለፈጣሪ ተወው!
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
ሁሌም ማስታወስ ያለብን!
▸ ያለፈው መቼም አይመስልም
▸ አስተያየቶች አንተን ሊገልፁህ አይችሉም
▸ የሁሉም ሰው መንገድ የተለያየ ነው
▸ ፍርጃዎች ስለአንተ አይደሉም
▸ አብዝቶ ማሰብ መከፋትን ያመጣል
▸ ደስታ ሁሌም በውስጥህ ነው
▸ አስተሳሰብህ ሙድህን ይወስናል
▸ ፈገግታ ከሰው ወደሰው ይተላለፋል
▸ መልካምነት ምንም ክፍያ የለውም
▸ አስፈላጊ ሲሆን መተው እና ወደ ፊት መራመድ ስህተት የለበትም
▸ በጊዜ ሂደት ነገሮች ሁሉ መልካም መሆናቸው አይቀርም።
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
"የተሰጠንን ብናዉቅ የጎደለን የለም"
ያገባዉ👉ምን አለ ላጤ በሆንኩ፤
ላጤዉ👉መች ይሆን አግብቼ የማርፈዉ፤
ሀብታሙ👉መች ይሆን አእምሮዬ እርፍ የሚለዉ፤
ደሀዉ👉መች ይሆን ሀብታም ሆኜ ኑሮዬ የተመቻቸ የሚሆነዉ፤
ሽማግሎዉ👉ምን አለ ወጣት ነቴን በተመለሰ፤
ወጣቱ👉ምን አለ ህፃን ሁኜ ሁሉን ነገር ያለ ተጠያቂ ነት ባደረኩ፤
ህፃን👉መች ይሆን ትልቅ የምሆነዉ፤
በህይወት ያለዉ👉ምን አለ ከዚ ህይወት በተገላገልኩ፤
የሞተዉ👉ምን አለ ትንሽ ጊዜ ወደ ኋላ ተመልሼ የሰራዉትን መጥፎ ነገር ባስተካክል፤
አይ የሰዉ ልጅ ! የሰዉ ልጅ ምንም አይነት ፀጋ በእጁ ቢኖር ከማመስገን ይልቅ ለማማረር ምላሱን ያረዝማል !
እባካቹህ እህት ወንድሞቼ
ለሰከንድ እንኳን፦
እግር የሌለዉ ስላለ ጫማ
የለኝም ብለን አናማር፤
ብርሀን የሌለዉ ስላለ
መነፅር የለኝም ብለን አናማር፤
ጤና የሌለዉ ስላለ ምቾት
ጎደለኝ ብለን አናማር፤
ስላልተደረገልን መዉቀስን
ትተን ስለ ተደረገልን እና መስግን !
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
#10ሩ
➢1. ፀሐይ ወዳጅን ትመስላለች
ስትመጣ ሁሉ ነገር ሲያበራ ስትሄድ ግን
ሁሉ ነገር ጭልምልም ይላል ።
➢ 2. ለመጀመሪያ ጊዜ ያየህን አካል ሺህ ጊዜ አንተን ለማየት እንዲመኝ ማድረግ የምትችለው በስነ-ምግባርህ ብቻ ነው።
➢ 3.አትጨነቅ!
በህይወትህ ውስጥ በጣም ሲያስጨንቁህ ከርመው "አያልፉም" ብለህ ስታስባቸው የነበሩ ከባባድ ነገሮች አልፈዋል። ምናልባት አሁን ረስተሃቸው ይሆናል። አሁንም ቢሆን ይህ ቀን ያልፍና ትረሳዋለህ። በቃ አስብ እንጂ አትጨነቅ!!
➢4.ጥሩ ከመፈለግ ጥሩ ሆኖ መገኘት ይቀድማል
"አንቺ ጠዋት ተንስተሽ ፊትሽን ስታጥብ ሌላኛዋ ደግሞ ጠዋት ተንስታ ኩላሊቷን የምታሳጥብ አለችና ምንም ባይኖርሽም ጤናሽን አሟልቶ ለሰጠሽ ጌታሽ ሁሌ አመስግኚው" !!
➢ 5.አባት ለአይነስውር ልጁ የተናገረው
" ልጄ ሆይ!
እዚች ምድር ላይ ባለማየት ያጣኸው ነገር ቢኖር የእናትህን ፊት ብቻ ነው! "
እናት
➢ 6. ከተብቃቃህ ትንሹ ብዙ ነው
◌ ከተስገበገብክ ብዙው ትንሽ ነው
◌ ከወደድክ ሩቁ ቅርብ ነው
◌ከጠላህ ቅርቡ ሩቅ ነው
ስላለፈው እያሰብክ የዛሬ ቀንህን አታበላሽ...ያ አንዴ አልፏል ዛሬን ተደሰተው።
➢ 7. ስላለፈው እያሰብክ የዛሬ ቀንህን አታበላሽ...ያ አንዴ አልፏል ዛሬን ተደሰተው።
➢ 8.ጭንቀት የነገን ችግር ላይፈታ የዛሬን ቀን ያበላሻል።
. ጭንቀትህን አስወግደህ ዝም ብለህ ተደሰት።
➢ 9. ኑሮህን ስታማርር ይበልጥ ህይወትህ እየመረረ ይሄዳል
የሚያስደስት ነገር ባይኖርም ፈገግ እያልክ ህይወትህን ለማጣፈጥ ሞክር።
➢10. ድመት አይጥ እንድትይዝ ተብሎ ችቦ አይበራላትም
◊ አንተም እንድትደሰት ተብሎ ልዩ ተዐምር አይፈጠርም...በቃ ደስስስ ይበልህ
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
#የተፈጠርነው_ባጋጣሚዎች_አይደለም
✍አጋጣሚዎቻችን እንኳን አጋጣሚ አይደሉም። በህይወታችን ማንኛውንም ነገር የሚሆነው በአጋጣሚወች አይደለም፡ በምርጫችን እንጂ።
ጥሩ ገጠመኞችን እንኳን እንዲገጥሙህ ጥሩ የምታስብና ጥሩ ቦታ የምትገኝ መሆን አለብህ። በርግጥ ጥሩ አስበህ መጥፎ ገጥሞህ ይሆናል እሔ የሆነው ግን እድለቢስ ስለሆንም አይደልም።
✍በየትኛውም አይነት መንገድ ብታልፊ
ምንም አይነት ፈተና ቢደረስብህ አለምን ታስፈልጋታለህ። ባይገርምህ እንደኔ አላዋቂ ብትሆንም እንኳን አለምን ህዝብን እናስፈልገዋለን......
✍ለራስህ ይሄን እውነት ንገር..
✍በናትህ በዚህ ምድር እንደ አንተ አይነት ሰው የለም....አንተ የምትፈታውን ችግር ማንም አይፈታውም። ጳጳስ ፡ፓስተር፡ ሼህ፡ ፈላስፋ፡ ዶክተር ምን አለፋህ አይችሉም። ምክንያቱም ያንተ መክሊት ነው።
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
#_የስኬት_ቁልፍ
ራዕይ
ጥረት
ፍላጎት
ትኩረት
ታማኝነት
ራስን መሆን
በራስ መተማመን
ለራስ ክብር መስጠት
ሁሌም በትጋት መስራት
ስንሳሳት ይቅርታ መጠየቅ
ለለውጥ እራስን ማዘጋጀት
ለሚገጥመን ያለመንበርከክ
ከስህተት ለመማር ራሰን ማዘጋጀት፡፡
#ፈጣሪ
አንድ የእምነት ሰው ፀጉሩን ሊስተካከል ወደ አንድ ፀጉር አስተካካይ ቤት ይሔዳል እናም በመሀል ጫወታ ይጀምራል
°
ፀጉር_አስተካካይ : 'ታውቃለህ ፈጣሪ የለም !'
°
ተስተካካይ: በመገረም 'እንዴት' ?
°
አስተካካይ: 'አይታይህም'?
°
ተስተካካይ : 'ምኑ'?
°
አስተካካይ :'እንዴ ፈጣሪ ቢኖር እኮ ይሄ ሁሉ ጦርነት ፣ረሀብ ፣ችግር ፣ስርአት አልበኝነት አይኖርም ነበር ስለዚህ ፈጣሪ አንዴ ፈጥሮን ትቶን ሔዷል ወይ ሞቷል' ።
°
ተስተካካይ : 'ታውቃለህ ፀጉር አስተካካይ የሚባል የለም'
°
አስተካካይ : (ግራ በመጋባትና እንዲሁም በመገረም) 'እንዴት'?
°
ተስተካካይ :'ፀጉር አስተካካይ ቢኖርማ ፀጉሩ የጎፈረ ፂሙ የተንዠረገገ ሰው አይኖርም ነበር' ።
°
አስተካካይ :'እነዚህ ሰዎች እኮ ወደ ፀጉር
አስተካካይ አለመምጣታቸው ነው እንጂ ቢመጡማ ኖሮ አንድም ፀጉሩ የተንዠረገገ እና የተንጨበረረ ፀጉር አታይም ነበር'
°
ተስተካካይ :'ትክክል ብለሀል በአለማችን ያለው ችግርም ይኸው ነው ሰው ከፈጣሪው ስለራቀ ነው እንጂ ፈጣሪ ስለሌለ አይደለም።
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
ለ ጠቅላላ አዉቀት 😜
#የኢኮኖሚ ፍልስፍና በቀላል ቋንቋ
#socialism ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ አንዱን ለጎረቤት ትሰጣለህ
#Communism ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ መንግስት ሁለቱንም ወስዶ ወተት ይሰጥሀል
#fascism ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ መንግስት ሁለቱንም ወስዶ ወተት ይሸጥልሀል
#Nazism ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ መንግስት ሁለቱንም ወስዶ አንተን ይገድልሀል
#Capitalism ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ አንዷን ሸጠህ ወንድ ወይፈን ትገዛለህ። ላሞችህን ታበዛለህ የኢኮኖሚ እድገት ታገኛለህ ፤ ጡረታ ትወጣለህ ፤ ትርፍ ላይ ትኖራለህ።
#modern-capitalism ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ አንዷን ሸጠህ ወንድ በሬ ትገዛለህ። ላሞችህ ይበዛሉ። ትርፍ ላይ ትሆናለህ ፤ የጎረቤቶችህን ላሞች ትገዛለህ እነሱንም በትንሽ ደሞዝ እረኛ አድርገህ ትቀጥራቸዋለህ ፤ ያልቻሉት ይሞታሉ።
#American-society ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ አንዷን ሸጠህ የቀረችዋን እንደ አራት ላሞች ምርት እንድትሰጥ ታደርጋታለህ። ከአቅሟ በላይ ስለምታመርት ትሞታለች። የሞቷን መንስኤ ለማጣራት አማካሪ ትቀጥራለህ።
#French-society ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ፤ ግን ሶስተኛ ላም ስለፈለግህ አድማ (ሰልፍ) ትሄዳለህ
#German-society ፦ ሁለት ላሞች አሉህ 100 አመት እንዲኖሩ ታደርጋቸዋለህ ፤ በወር አንዴ ብቻም ትመግባቸዋለህ።
#China-society ፦ ሁለት ላሞች አሉህ ወተት ለጓደኞችህ ትሸጣለህ ትርፋማ ትሆናለህ ከዛ የፕላስቲክ ወተት እያመረትህ ለአለም ገበያ ታቀርባለህ።
#African-society :- ሁለት ላሞች አሉህ ፤ በአንድ ወር ውስጥ ሁለቱንም አርደህ ትበላለህ። ከዛ አለማቀፉ ህብረተሰብ እና ተራድኦ ድርጅቶች ሌላ ላሞች እንደሚሰጡህ ተስፋ ታደርጋለህ!!
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
✍አጋጣሚዎቻችን እንኳን አጋጣሚ አይደሉም። በህይወታችን ማንኛውንም ነገር የሚሆነው በአጋጣሚወች አይደለም፡ በምርጫችን እንጂ።
ጥሩ ገጠመኞችን እንኳን እንዲገጥሙህ ጥሩ የምታስብና ጥሩ ቦታ የምትገኝ መሆን አለብህ። በርግጥ ጥሩ አስበህ መጥፎ ገጥሞህ ይሆናል እሔ የሆነው ግን እድለቢስ ስለሆንም አይደልም።
✍በየትኛውም አይነት መንገድ ብታልፊ
ምንም አይነት ፈተና ቢደረስብህ አለምን ታስፈልጋታለህ። ባይገርምህ እንደኔ አላዋቂ ብትሆንም እንኳን አለምን ህዝብን እናስፈልገዋለን......
✍ለራስህ ይሄን እውነት ንገር..
✍በናትህ በዚህ ምድር እንደ አንተ አይነት ሰው የለም....አንተ የምትፈታውን ችግር ማንም አይፈታውም። ጳጳስ ፡ፓስተር፡ ሼህ፡ ፈላስፋ፡ ዶክተር ምን አለፋህ አይችሉም። ምክንያቱም ያንተ መክሊት ነው።
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
one💚💛❤️
ሰው መሆን 😳
ለአንድ ጥበበኛን
"እገሌ እኮ መብረር ይችላል"አሉት፡፡
"ምኑ ይገርማል ታድያ ከእርሱ ያነሱት እነ ዝንብ እና ትንኝ ሁሉ ይበሩ የለም እንዴ!" በማለት አጣጠለባቸው፡፡
"እንትና እኮ ውሃ ላይ መሄድ ይችላል፡፡"አሉት፡፡
"ምኑ ይገርማል ታድያ ቁራጭ ጣውላም ባህር ውሃ ቢጥሉት አይሰምጥም ውሃ ላይ ይሄዳል እኮ" አላቸው፡፡
.
"እንግዲያውስ ባንቱ እይታ ገራሚው ነገር ምንድነው?" አሏቸው፡፡
ሰው መሆን ሲሉ ቀጠሉ ----
እጅግ አስደናቂው ነገር ሰዎች የቱን ያህል ቢያጠፉም አለማጥፋት ፤ የያዙት አላማና መርህ ሳይለቁና ሳይስቱ በከባድ ፈተናዎች መሃል ከሰዎች ጋር መኖር
አለመዋሸት
አለመስረቅ
አለማታለል
እምነት ለጣሉብህ መታመን ፤
የተማመኑብህን አለማሳፈር ፤
ሰዎችን በየትኛውም መልኩ ቀልባቸውን አለመስበር፡፡
እጅግ አስደናቂ ነገር ይህ ነው፡፡
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
ምንድነው የምትፈራው?
መቼስ የሁላችንም መልስ የሚሆነው ማጣትን ነው አይደል? ገንዘህብ ፤ ስራህን ፤ ፍቅረኛህን ፤ ክብርህን ፤ ሰላምን ሌላም ሌላም ብዙን ነገር ብቻ ሁሉም ውስጥ የምንፈራው እነዚህን ሁሉ ማጣትን ነው ታዲያ ማጣትን ፈርተህ ላለማጣት በመፍራት ብቻ ያለህን ሁሉ ለምን ትነጠቃለህ! መድረክን ፈርተህ ድፍረትህን ለምን ታጣለህ? የተሰጠህን እድል ገፍተህ የት ወጥተክ ትለማመዳለክ? ቤትክ ውስጥ ሰው በሌለበት ማንም ሳያይክ? ከዛስ? ዛሬ እንዳይሳቅብህ በማሰብ ብቻ የነገ ህልምህ ተቀምተክ ከመኖር ዛሬን ተሳስተክ ብትታረም ነገን ትልቅ ስንቅ ታዘጋጅለታለክ ስለዚህ ፍራና እየፈራክም አድርገው!
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
የዛሬው ጥረትህ!
ጠንካራ ሰው ለራሱ ብቻ አይኖርም፤ አንተን የሚጠብቁ ብዙ ሰዎች አሉ፤ ላንተማ አንድ እንጀራ እና አንድ ክፍል ቤት በቂህ ነበር፤ እሱን ለማሳካት ትልቅ ዋጋ መክፈል አይጠበቅብህም፤ ትልቅ ነገር የሚፈልግ ግን ትንሹን ስራ እንኳን ለነገ አያሳድርም።
ከአልጋህ ተነስ፣ ስፖርቱን ስራ፣ ሻወሩን ውሰድ፣ መፅሀፉን ግለጥ ወይ ስራውን ጀምረው! ወዳጄ የዛሬው ጥረትህ ተጠራቅሞ ነው ታላቅ የሚያደርግህ!
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
ከሮበርት ሙጋቤ ንግግሮች አንዱን እንቀንጭብ
*=====*//*======*//*========*
ደሞዝ የመጣ ቀን ዶሮ ትበላለህ ። በማግስቱ ደሞዝ ሲያንስብህ የዶሮ ውጤት (እንቁላል) ትበላለህ ።
በቀጣዩ ቀን ደሞዝህ የበለጠ ሲሳሳ ደግሞ የዶሮ ምግቦችን(በቆሎ እና ገብስ) ትመገባለህ። በተከታዩ ቀን ደሞዝህ ሲሟጠጥ ደግሞ አንተ እራስህ ዶሮ ትሆንና የምትበላውን ነገር ፍለጋ ወዲያ ወዲህ በመባዘን ጊዜህን ታሳልፋለህ ።
🥇የሰዎችን አድናቆት እንደ ትልቅ መስፈርት መውሰድ ከጀመርክ በአንተ ላይ ሙሉ ስልጣን እየሰጠሀቸው ነው። ዛሬ አድናቆታቸው በደስታ ሰማይ ሊያደርስህ ይችላል ነገ ግን ከባድ ትችትና ስድባቸው ሞራልህን መሬት ፈጥፍጦ ራስህን እንድትጠላ ሊያደርግህ ይችላል።
ስለዚህ የሰዎች አድናቆትም ሆነ ትችት የእነሱን ምልከታ እንጂ ያንተን ትክክለኛ ቦታ አያሳይም! አስተያየታቸውን ግን ራስህን ለማሻሻል ትጠቀምበታለህ እንጂ በፍፁም አምነህ አትደገፍበትም።
♨️መልካም ቀን ወገን❤
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ
ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
#አንዳንድ_ሀሳቦች
✍... አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፣ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡
☮ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡ ወዳጄ ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡ በነገሮች አትረበሽ፡
ጭንቀትህን አስጨንቀው ፡ "ካህሊል ጅብራል እንዲህ ይላል ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡ "
☮አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ታሪክህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ብቻ ነው፡
☯"መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው:" በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው
የምን ተስፋ መቁረጥ
ጋሽ ስብሀት ገ/እግዝያብሄር
Yoni motivation
ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !!
Yoni
https://t.me/yoni4600
https://t.me/yoni4600
