قناة أبي عبدالرحيم (አብዱራህማን ሹመት)
رفتن به کانال در Telegram
👇 https://t.me/abuabdirehim https://t.me/abuabdirehim ያለቁ የኪታብ ደርሶችን ማስቀመጫ ቻናል https://t.me/durus_abu_abdirehim2 ይቀላቀሉ ⟰⟰⟰⟰⟰⟰⟰⇧⇧⇧⇧
نمایش بیشتر2 204
مشترکین
-224 ساعت
-127 روز
-7330 روز
آرشیو پست ها
Repost from كتب و تفريغات / د. عبدالعزيز الريس
النكت_العوالي_على_رسالة_المولد_للشوكاني_ط2_د_عبدالعزيز_بن_ريس_الريس.pdf1.71 MB
سئل سفيان الثوري عن الكلام، فقال: "دع الباطل، أين أنت عن الحق؟! اتبع السنة، ودع البدعة".
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጥያቄ፦
አንዲት ሴት ለእናቷ ገንዘብ ሰጥታ በገንዘቡ ሐጅ እንድታደርግ መስፈርት አስቀመጠችባት፤ እናት ግን በገንዘቡ ወንድ ልጅዋን መዳር ፈለገች። ይህን ማድረግ ይፈቀድላታልን?
📝 መልስ፦
لا يجوز لها ذلك، لأن البنت ما طابت نفسها أن تعطيها المال إلا بهذا الشرط، للحج، فعليها أن تطلب من ابنتها أن تأذن لها، ثم أيضاً إذا كانت المرأة ما حجت فيجب عليها أن تحج بهذا المال وأن تقدم الحج على تزويج ولدها، وسييسر الله لولدها الزواج، الحج تعلق في ذمتها لأنها صارت مستطيعة إذا وجدت المحرم، وبالله التوفيق.
ይህን ማድረግ አይፈቀድላትም። ምክንያቱም ልጅዋ ይህን ገንዘብ ለእናቷ ለመስጠት የፈቀደችው በዚህ መስፈርት (ለሐጅ ብቻ እንዲሆን) ነው። ስለዚህ እናት የልጇን ፈቃድ መጠየቅ ይኖርባታል።
ደግሞም እናት እስካሁን ሐጅ ያላደረገች ከሆነ፣ ይህን ገንዘብ ለሐጅ ማዋል እና ሐጅ ማድረግ እና ልጅዋን ከማጋባት ማስቀደም ግዴታ ይሆንባታል። አላህ ለልጅዋ ጋብቻውን ያገራለታል። እናትየው (አብሯት የሚሄድ) መሕረም ካገኘች አቅም እንዳላት ስለሚቆጠር ሐጅ የማድረግ ግዴታ በእሷ ላይ ወድቆባታል።
ወቢልላሂ ተውፊቅ።
ፊትዋው የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም ነው።
ምንጭ፦ https://t.me/ibnhezam/22672
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የሰኞ ፆም እና መውሊድ
~
የመውሊድ አክባሪዎች ለዚህ ቢድዐ ከሚያጧቅሷቸው “ማስረጃዎች” ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ሰኞን ከሚፆሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የተወለዱበት ቀን መሆኑን መግለፃቸው ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ “እንዲያውም መውሊድ መከበር የተጀመረው በራሳቸው በነቢዩ ﷺ ነው” ይላሉ። ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃ ሊሆናቸው አይችልም። ምክንያቱም፦
1. ፆምና ጭፈራን ምን አገናኘው?!
እናንተ'ኮ በጭፈራ እንጂ በፆም አይደለም የምታከብሩት። ተግባራችሁ ባልተመሳሰለበት በምን ስሌት ነው የሰኞን ፆም ለጭፈራ ማስረጃ የምታደርጉት? የልደት ቀናቸውን በጭፈራና በድግስ ማሳለፍ ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲይም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ማስረጃ ጥቀሱ!
ደግሞም ነብዩ ﷺ ሰኞን የሚፆሙበትን ምክንያት ሲናገሩ “ስራዎች ሰኞና ሐሙስ ቀን (ወደ አላህ) ይቀርባሉ። እናም ፆመኞ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” ነው ያሉት። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2959] የናንተ ተግባር ግን “ጨፋሪ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” የሚል ነው የሚሰጠው።
2. እናንተ'ኮ ሰኞ ቀን አይደለም የምታከብሩት!
ረቢዑል አወል 12 ሁሌ ሰኞ ጋር አይገጥምም። ኧረ እንዲያውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ሆነ ብለው በያመቱ እሁድ ቀን ብቻ የሚያከብሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ ህዳር ወር ላይ፣ ሌሎች ጥቅምት ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ረጀብ ወር ላይ የሚያከብሩ አሉ። እንኳን ቀኑና ወሩም አይገናኝም። አመት ጠብቆ የልደት ቀናቸውን ማክበር ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪይም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲይም ፈፅሞ አልተገኘም።
ስለዚህ እየተፈፀመ ያለው ነገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ባህል ማስቀጠል ብቻ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሱና የተጨነቃችሁ ይመስል ከናንተ ፀያፍ ተግባር ጋር የማይዛመደውን የነብዩን ﷺ ሳምንታዊ የሰኞ ፆም ማጣቀስ ማምታታት አይደለም ወይ?
3. ሰኞን ብትጠብቁም ከጥፋትነት አይወጣም!
ሌላው ቀርቶ በየሳምንቱ እየጠበቃችሁ ሰኞን ብታከብሩ እንኳ የናንተ ተግባር በሺርክ የታጨቀ፣ በቢድዐ የተወረረ እና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ነው። አሁንማ ጭራሽ የብልግና መፈፀሚያም ሆኗል። ደግሞስ ነብዩ ﷺ ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራ አላከበሩ? ጭፈራ በምን ስሌት ነው ዒባዳ የሚሆነው? በዚህ ላይ ሺርክ ሲጨመርበት ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል።
4. ከሰኞ ፆም ጋር በቂያስም አይገናኝም!
የሰኞን ፆምና የመውሊድን ጭፈራ በቂያስ ማገናኘትም ጭራሽ የሚያዋጣ አይደለም። የሐሙስን የሱና ፆም በጭፈራና በውዝዋዜ ማሳለፍ ይቻላልን? በደስታ እንድናሳልፍ የታዘዝናቸውን ሁለቱን አመታዊ ዒዶቻችንን በፆም ማሳለፍ ይቻላል? በፍፁም! የምስጋና ሱጁድን በሩኩዕ መቀየር ይቻላል? ዒባዳኮ በታዘዘው መሰረት እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ አይፈፀምም። እውነት ከመውሊድ የሚፈልጉት አላማ ለአላህ ምስጋና መግለፅ ከሆነ ሊከተሉ የሚገባው ነብዩ ﷺ የተከተሉትን እርምጃ ብቻ ነበር። “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነውና።” [ሙስሊም፡ 2042] እሳቸው ደግሞ የተወለዱበት ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራና በውዝዋዜ ምስጋናቸውን አልገለፁም። እየተፈፀመ ያለው እሳቸው ከሰሩት በተቃራኒ ነው። ታዲያ ለምን ነብዩን ﷺ የበቃቸው አይበቃንም?! ለምንስ ከሳቸው ፊት እንሽቀዳደማለን? አላህ እንዲህ ብሏል፦
{يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ}
{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ። አላህንም ፍሩ። አላህ ሰሚ አዋቂ ነው።} [አልሑጁራት፡ 1]
ነብዩስ ﷺ “በኔ ላይ መልካም ምሳሌ አይኖርህምን? በአላህ ይሁንብኝ! እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ከማናችሁም በበለጠ ድንበሮቹን ጠባቂ ነኝ” ብለዋል። [አስ-ሶሒሐህ፡ 1782]
5. ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ ፆም እንጂ ስለ ረቢዑል አወል 12 አልተናገሩም!
ነብዩ ﷺ ሰኞ ቀን እንደተወለዱ በግልፅ የተናገሩ ሲሆን ረቢዑል አወል 12 መወለዳቸውን በተመለከተ ግን አስተማማኝና ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ጠንካራ ማስረጃ አለመምጣቱ በራሱ ቀኑ ያን ያክል አንገብጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው። መውሊድ ዛሬ የሚሰጠውን ያክል ክብደት ቢኖረው ኖሮ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ መወለዳቸውን እንደነገሩን ሁሉ ከአመቱ ወራት ውስጥ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ በግልፅ በነገሩንና እንድናከብረውም ባስተማሩን ነበር።
6. የሰኞ ፆም እንጂ የረቢዑል አወል 12 መውሊድ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም
በሱና ድርሳናት ላይ የሰኞ ፆም ትኩረት ተችሮት የተወሳ ሲሆን ረቢዑል አወል 12ን የሚመለከት ግን አንድም መረጃ የለም። ምክንያቱም ሊቀርብ የሚችል መረጃ የለምና። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አራቱ ሱነኖች፣ የፊቅህ ኪታቦችን፣ … ብንፈትሽ ረቢዑል አወል 12ን በደስታ፣ በጭፈራ፣ በተለየ ዒባዳ፣ በሶደቃ እንድናሳልፍ የሚጠቁም አንድም መረጃ አይገኝም። ይህም የሰኞ ፆም ለመውሊድ መረጃ እንደማይሆን ጠቋሚ ነው። ቢሆን ኖሮ ከመውሊድ አጋፋሪዎች በፊት እነ ቡኻሪ ይረዱት ነበርና።
7. ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ዒድ አይደለም!
በኢስላም ዒድ እንዳማይፆም የታወቀ ነው። ሰኞ ቀን መፆም ግን የተወደደ ነው። ከመሆኑም ጋር ይህ መፆሙ የሚወደደው ሰኞ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ከገጠመ መፆም አይፈቀድም። ይህም የተወለዱበት ቀን ዒድ እንዳልሆነ በተጨባጭ የሚያሳይ ነው። ነብዩም ﷺ ሰኞን መፆም የሚወደድ እንደሆነ አስተማሩ እንጂ “ቀኑ ዒድ ነው” አላሉም። እለቱ ዒድ ቢሆን ኖሮ በፆም አያሳልፉትም ነበር። የመውሊድ አክባሪዎች ግን ቀኑን ዒድ አድርገውታል። በሚደንቅ ሁኔታ “ቀኑ ዒድ ስለሆነ መፆም አይቻልም” እስከማለት የደረሱ አሉ። "መዋሂቡል ጀሊል ሸርሕ ሙኽተሶሪል ኸሊል" የተሰኘውን ከታብ ገፅ 2/406 ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሙሐመድ ብኑ አሕመድ በኒስ፣ ኢብኑ ዐባድና ሌሎችም እንዲሁ እለቱን ዒድ ነው ይላሉ። የሚያሳፍር! ታዲያ እንደዚያ የሚሉ ከሆነ ለምን ነብዩ ﷺ በፆም ያሳለፉትን ሰኞን ለዚህ ድርጊታቸው መረጃ ያደርጋሉ? ዒድ ይፆማል እንዴ?
ቀንደኛ የመውሊድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑል ዐለዊይ ግን መውሊድን መሀይም እንጂ በዒድ አይገልፀውም ይላል። መውሊድ ዒድ (በዓል) ነው የምትሉ የዋሀን ሆይ! መሃይማን ባትሆኑ ኖሮ መውሊድን ‘ዒድ ብላችሁ አትገልፁትም ነበር’ እየተባላችሁ ነው! በርግጥ እሱ በዚህ በኩል የሚነሳውን ትችት ለመሸሽ ያክል ነው ይህን የሚለው። እንጂ ዞር ብሎ “ቀኑ ከዒድም በላይ ነው” ይላል። [አልኢዕላም፡ 8] የቢድዐ ፍቅር ሰዎቹን የት እንደሚያደርሳቸው ተመልከቱ። ለዚህ ሙግቱ ከከንቱ ትንተና ባለፈ ከቁርኣንም ከሐዲሥም ከሰለፎች ንግግርም አንድም ሊያቀርበው የሚችለው ነገር የለም።
ሲጠቃለል የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም እና አመታዊ የሱፍያ ጭፈራ በየትም አቅጣጭ አይገናኝም። አራምባና ቆቦ ነው።
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2014)
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
🔴 *نصيحة لكل مسلم ومسلمة :*
*كن سلفياً على الجادة ، متمسكاً بأصول أهل السنة وعاملاً بها غير ملتفت للمخالفين ، مترفعاً عن كثير من الأمور في الساحة ، ومجانباً للمراء والجدل ، وتاركاً ما لا يعنيك ، ومعتزلاً ما يؤذيك ، ومحباً الخير لكل مؤمن ومؤمنة ، وبانياً ما تستطيع من خير الدنيا والآخرة في بلدك*
Repost from አቡ አዩብ ሙሃመድ ሰይድ ሙሃመድ
ለበጋ ምዝገባ ላይ ነን !
የምንሰጣቸው ትምህርቶች
📌ከቃዒዳ —ሒፍዝ
📌ሙራጀዓ ማስተካከል
📌የአቂዳ ኪታቦች
📌የፊቅህ ኪታቦች
📌የአደብ ኪታቦች
📌የተጅዊድ ኪታቦች
📌የሲራ ኪታብ
📌የአዝካር ኪታብ
📌አረበኛ ቋንቋ
🔷የትምህርት አሰጣጣችን
📍ለወንዶች
—መርከዝ ላይ በአዳሪ
—ከትምህርት ጋር መርከዝ ላይ በአዳሪ
—በተመላላሽ
—እድሜ ከ 9—19
📍ለሴቶች
—በተመላላሽ
—እድሜ መነሻ 9 መድረሻ ያለ ገደብ
ቀደመው ይመዝገቡ ያለን ቦታ ውስን ነው!!
📲0925887118
📲0910497171
📲0935564734
የመርከዙ ቻናል እና ጉሩፕ
https://telegram.me/abutoiba
https://t.me/Merkez_Abi_Ayub
tiktok.com/@attewhid6
tiktok.com/@ebrahim_haydera
وصية لقمان لابنه منهج متكامل
وصية من أجمع الوصايا القرآنية في باب تربية الأبناء؛ فقد جمعت بين تصحيح الاعتقاد، وإقامة العبادة، ومراقبة الله، والأخلاق، والآداب
بل تعتبر منهج متكامل في بناء الإنسان الصالح: عقيدة صحيحة، وعبادة، ومراقبة لله، ودعوة إلى الخير، وصبر، وتواضع، وحسن أدب الاجتماعية
قال تعالى:
﴿وَإِذْ قَالَ لُقْمَانُ لِابْنِهِ وَهُوَ يَعِظُهُ يَا بُنَيَّ لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ وَوَصَّيْنَا الْإِنسَانَ بِوَالِدَيْهِ…﴾ [لقمان: 13-14]
إلى أن قال:
﴿يَا بُنَيَّ إِنَّهَا إِن تَكُ مِثْقَالَ حَبَّةٍ مِّنْ خَرْدَلٍ فَتَكُن فِي صَخْرَةٍ أَوْ فِي السَّمَاوَاتِ أَوْ فِي الْأَرْضِ يَأْتِ بِهَا اللَّهُ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَطِيفٌ خَبِيرٌ يَا بُنَيَّ أَقِمِ الصَّلَاةَ وَأْمُرْ بِالْمَعْرُوفِ وَانْهَ عَنِ الْمُنكَرِ وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ ۖ إِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ وَاقْصِدْ فِي مَشْيِكَ وَاغْضُضْ مِن صَوْتِكَ ۚ إِنَّ أَنكَرَ الْأَصْوَاتِ لَصَوْتُ الْحَمِيرِ﴾ [لقمان: 16-19].
فتدرّجت الوصية:
١-التوحيد أولًا: ﴿لَا تُشْرِكْ بِاللَّهِ﴾؛ فصلاح العقيدة أساس كل صلاح.
التحذير من الشرك: ﴿إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ﴾.
٢-بر الوالدين: بعد النهي عن الشرك مباشرةً، مما يدل على عظيم حقهما.
مراقبة الله: ﴿إِن تَكُ مِثْقَالَ حَبَّةٍ… يَأْتِ بِهَا اللَّهُ﴾؛ تربية للابن على استحضار علم الله وإحاطته.
٣-إقامة الصلاة: لأنها أعظم صلة بين العبد وربه بعد التوحيد.
٤-الدعوة إلى الخير: ﴿وَأْمُرْ بِالْمَعْرُوفِ وَانْهَ عَنِ الْمُنكَرِ﴾.
٥-الصبر: ﴿وَاصْبِرْ عَلَىٰ مَا أَصَابَكَ﴾؛ لأن طريق الاستقامة والدعوة لا يخلو من المشقة.
٦-التواضع وترك الكبر: ﴿وَلَا تُصَعِّرْ خَدَّكَ لِلنَّاسِ﴾.
٧-ترك الخيلاء والفخر: ﴿وَلَا تَمْشِ فِي الْأَرْضِ مَرَحًا﴾.
٨-الاعتدال وحسن الأدب: ﴿وَاقْصِدْ فِي مَشْيِكَ وَاغْضُضْ مِن صَوْتِكَ﴾.
فالتربية القرآنيةليست محصورة في السلوك الظاهر، وإنما تبدأ من التوحيد، واصلاح الباطن ثم تنتقل إلى العبادة ومراقبة الله، ثم إلى إصلاح النفس، ثم إلى حسن التعامل مع الخلق.
ومن لطيف التربية في الآيات أن لقمان كان يقول لابنه: ﴿يَا بُنَيَّ﴾؛ ففيها رفق وشفقة وتقريب للولد، ثم يعظه بأصول عظيمة جامعة.
فوصية لقمان ليست مجرد نصائح أخلاقية متفرقة، بل هي منهج متكامل في بناء الإنسان الصالح: عقيدة صحيحة، وعبادة، ومراقبة لله، ودعوة إلى الخير، وصبر، وتواضع، وحسن أدب
أ.د عبد السلام السحيمي
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
በመጨረሻም ሙስጠፋ -አላህ ይምራውና- አሁን ሀገር አቋርጦ ተጉዞ እየተማርኩባቸው ነው የሚላቸው ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒይ ስለ ሸይኽ ረቢዕ ምን እንዳሉ አውስቸ ፅሁፌን አጠናቃለሁ።
▫️ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒይ:-
↩️ فقد سئل فضيلة الشيخ عبدالعزيز الراجحي –حفظه الله-: ما نصّه: بعض الناس يتهم من تمسك بالمنهج السلفي بأنّه جامي، ويحذر من الشيخ ربيع والشيخ النجمي والشيخ زيد بن محمد هادي المدخلي وغيرهم من أهل العلم؟
"ከፊል ሰዎች የሰለፊያን መንሃጅ አጥብቆ የያዘን አካል ጃሚይ ነው ይላሉ። ከሸይኽ ረቢዕ፣ ከሸይኽ አሕመድ አንነጅሚይ፣ ከሸይኽ ዘይድ አልመድኸሊይና ከሌሎችም የዒልም ባለቤቶች ያስጠነቅቃሉ። ተብለው ተጠየቁ።
فأجاب بقوله: ((الألقاب لا تغيّر، النبز بالألقاب لا يصلح، المهم ثقل الشخص، المشايخ نعرف أن معتقدهم سليم، ومن أهل السنة والجماعة، الشيخ ربيع والشيخ أحمد والشيخ زيد لا غبار عليهم)).
ሸይኹም -ሓፊዘሁላህ- እንዲህ ሲሉ መለሱ:- "ስያሜ ለውጥ አያመጣም። በቅፅል ስም መሰየምም አይገባም። ዋናው የሰወየው ማንነት ነው። የተወሰቱ መሻኢኾች ዓቂዳቸው እንከን የሌለበት መሆኑን እናውቃለን። ከአህሉሱናዎችም ናቸው። ሸይኽ ረቢዕ ሸይኽ አሕመድ ሸይኽ ዘይድ ምንም አይነት አቧራ (እንከን) የለባቸውም።"
↩️ وسئل –أيضاً-: ما رأيكم في كتب وأشرطة الشيخ ربيع بن هادي المدخلي –حفظه الله، هل تنصحون بقراءة كتبه واستماع أشرطته؟
በሌላም ጊዜ "ስለ ሸይኽ ረቢዕ ኪታቦች እና ካሴቶች ምን ይላሉ? ኪታቦችን በማንበብና ካሴቶችን በማዳመጥ ይመክሩናልን?" ተብለው ተጠየቁ።
فقال: ((نعم، لا بأس بها، كتبه وأشرطته ما رأينا فيها ما ينتقد، ما انتقدت فيها شيئاً، أشرطته جيّدة، وكتبه جيدة ومفيدة)) [من شريط لدى تسجيلات منهاج السنّة بالرياض].
እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ "አዎ! ችግር የለባቸውም። ኪታቦቹም ካሴቶቹም ውስጥ የሚተቹ ነገሮችን አላየንም። ካሴቶቹ ምርጥ ናቸው። ኪታቦቹም ምርጥና ጠቃሚዎች ናቸው።"
የሸይኹ ንግግር ይህን ይመስላል። የሌሎችም የሱንና ዑለማኦች በተመሳሳይ "ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊይ የሱንና ዓሊም ናቸው።" ይሉናል። መነሻና መድረሻ የሌላቸው የኸዋሪጅ ስራ አስፈፃሚ እና የተክፊር አቀንቃኝ የሆኑት እነ ሙስጠፋ ደግሞ "የሱንና ሰው አይደሉም። ሙርጂእ ናቸው።" ይላሉ። ማንን መስማትና መቀበል እንዳለብህ እራስህ ታቃለህ።
ይህን ስል ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ እኛ ሸይኽ ረቢዕም ይሁኑ ማንም ዓሊም አያጠፋም አይሳሳትም ማለታችን አይደለም። ነገር ግን የሱንና ዓሊም የሱንና ዓሊም ነው። ስህተቱ እንደ ስህተት እውቀታዊ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል እንጅ ማንም የመንደር ጎረምሳ እገሌ ሙርጅእ ነው እያለ ሊላገግ አንፈቅድለትም። እናም ማንሳት የፈለኩት ሸይኽ ረቢዕን ከሱንና ውጭ ናቸው የሚለው የነ ሙስጠፋ አቋም የሓዳዲያና የተክፊሮች ቅዠት እንጅ ሁሉም የሰለፊያ ዑለማኦች ሸይኽ ረቢዕ የሱንና ሰው መሆናቸውን ያረጋገጡት እወነታ መሆኑን ነው።
የነ ሙስጠፋ ቁማር ግን እንዲህ ነው ከገባህና ከሰማሃኝ። የሆነን አቋም ሲዪዙ በሆኑ ዓሊሞች ለመጠለል ይሞክራሉ የፈለጉትን ይሰቅላሉ የፈለጉትን ያወርዳሉ። ትላንት የሕየል ሓጁሪን በጭፍን ተከትለው ሃገር ሲያምሱ እያለ ሲሉ የነበረው ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ የሕያን ጠብ እርግፍ አድርገው ትተው ላመጡት የተክፊር ጉዞ በመዲና ዑለማኦች እራሳቸውን ይወሽቃሉ። የመዲና ዑለማኦች ያሉበትና የነእርሱ ጉዞ ግን ሰማይና ምድር ነው። እስኪ መልሱልን ሸይኽ ረቢዕን ኢብኑ ባዝ ናቸው ሙርጂእ ያሉት? ወይስ ሸይኽ ፈውዛን? ወይስ ራጂሒይ እስኪ ንገሩን። አላህ ሁላችንንም ለሚወደው መንገድ ይምራን።
رحم الله الشيخ المجاهد ربيع السنة وأسكنه فسيح جناته،
ሐምሌ 6/2017
በድጋሜ የተለጠፈ
የቴሌግራም ቻናል
=
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
▫️. ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊሕ ኢብኑ ዑሠይሚን -ረሒመሁላህ-
↩️ قد سئل الشيخ العلامة محمد بن صالح بن عثيمين –رحمه الله- عن الشيخ ربيع كما في (شريط الأسئلة السويدية) فقال :” أما بالنسبة للشيخ ربيع فأنا لا أعلم عنه إلا خيراً والرجل صاحب سنة وصاحب حديث”.
ኢብኑ ዑሰይሚን ስለ ሸይኽ ረቢዕ ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መለሱ:- "ሸይኽ ረቢዕን በተመለከተ ከእርሳቸው ኸይርን እንጅ አላቅም። ሰውየው የሱንና እና የሓዲሦ ባለቤት ናቸው።"
↩️ وجاء في الشريط الأول الذي هو بعنوان (كشف اللثام عن مخالفات أحمد سلام ) -عبر الهاتف من هولندا-:
سؤال: ما هي نصيحتكم لمن يمنع أشرطة الشيخ ربيع بن هادي بدعوى أنها تثير الفتنة وفيها مدح لولاة الأمور في المملكة وأن مدحه ـ أي مدح الشيخ ربيع للحكام ـ نفاق؟
الجواب : "رأيُنا أن هذا غلطٌ وخطأٌ عظيم، والشيخ ربيع من علماء السنة، ومن أهل الخير، وعقيدته سليمة، ومنهجه قويم. لكن لما كان يتكلم على بعض الرموز عند بعض الناس من المتأخرين وصموه بهذه العيوب."
በሌላም ቦታ የሸይኽ ረቢዕን ካሴቶች ከማዳመጥ ስለሚከለክሉ ሰዎች ተጠይቀው እንዲህ ይላሉ:- "ይህ ታላቅ ስህተት ነው። ሸይኽ ረቢዕ ከሱና ዑለማኦች ውስጥ ናቸው። ከኸይር ባለቤቶችም። ዓቂዳቸውም እንከን የለሽ መንሃጃቸውም የተስተካከለ ነው። ..."
↩️ وسئل ما نصّه: يقال أن منهج الشيخ ربيع يخالف منهج أهل السنة والجماعة؟
فأجاب بقوله: "ما أعلم أنه مخالف، والشيخ ربيع أثنى عليه أهل العلم المعاصرين، أنا ما أعرف عنه إلا خيراً" [شريط ثناء أئمة الدعوة على الشيخ ربيع].
"የሸይኽ ረቢዕ መንሃጅ የአህለሱንና ወልጀማዓዎችን ይቃረናል ይባላል?" ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም "እኔ መቃረናቸውን አላቅም። ሸይኽ ረቢዕ ማለት የዘመናችን ዑለማኦች አወድሰዋቸዋል። እኔ ከርሳቸው ኸይርን እንጅ አላቅም።"
▫️.ሸይኽ ፈውዛን -ሐፊዘሁላሁ ተዓላ-
↩️ قد أثني عليه الشيخ العلامة صالح بن فوزان الفوزان –حفظه الله- في تقديمه لكتاب “منهج الأنبياء في الدعوة إلى الله فيه الحكمة والعقل” و في تقديمه لكتاب “جماعة واحدة لا جماعات” في الرد على عبدالرحمن عبدالخالق،
ሸይኽ ፈውዛን ለሸይኽ ረቢዕ ብዙ መፅሃፎች መግቢያ ሲፅፉ በርካታ ውዳሴዎችን ተችረዋቸዋል። አንዴ ደግሞ ተጠይቀው በዚህ መልኩ መልስ ሰጥተዋል።
↩️ وسئل فضيلته في شريط ” الأسئلة السويدية ” (5 ربيع الآخر 1417 هـ) فقال بعد ما ذكر الشيخ ربيعاً مع مجموعة من أهل العلم: "كذلك من العلماء البارزين الذين لهم قدم في الدعوة، فضيلة الشيخ عبدالمحسن العباد، فضيلة الشيخ ربيع هادي ...،"
▫️. ሸይኽ ሙቅቢል አል'ዋዲዒይ -ረሒመሁላህ-:
↩️ فقد سئل فضيلة الشيخ العلامة مقبل بن هادي الوادعي –رحمه الله-: في شريط ” الأسئلة الحضرمية”: ما رأيك فيمن يقول عن الشيخ ربيع أنه متهّور؟
فأجاب –رحمه الله- : "الشيخ ربيع له خبرة بمعرفة الواقع لأنه عاش مع الإخوان المفلسين زمناً طويلاً -والحمد لله- هو أحسن من يعالجون الأمور وينكر على المبتدعة ابتداعهم فأسال الله أن يحفظه.
ሸይኽ ሙቅቢልም በዚህ መልኩ አወድሰዋቸዋል። የሸይኽ ረቢዕን ኪታቦችና ካሴቶች እንድንጠቀምባቸውም በዚህ መልኩ ይመክራሉ።
↩️ وقال الشيخ –رحمه الله- في جواب له على سؤال: "وأنا أنصح الأخوة بالاستفادة من كتب أخينا الشيخ ربيع بن هادي –حفظه الله تعالى- فهو إن شاء الله [بصير] بالحزبيين، ويخرج الحزبية بالمناقيش .... ،"
↩️ وقال في كتاب “تحفة القريب والمجيب” السؤال (75): "وأنصح بقراءة كتاب أخينا في الله ربيع بن هادي “جماعة واحدة لا جماعات وصراط واحد لا عشرات” فهو كاف واف".
በሌላም ቦታ ሰዎች ከታላላቅ ዑለማኦች ጋር ግንኙት እንዲኖራቸውና ከቻሉም ወደእነርሱ በአካል እንዲጓዙ ሲመክሩ ሸይኽ ረቢዕን ለምሳሌ ያወሳሉ።
↩️ وقال في السؤال (123): "الذي ننصح به، أن يراسلوا أهل العلم، وان استطاعوا أن يرحلوا إليهم فعلوا، مثل الشيخ الألباني، والشيخ ابن باز، والشيخ عبدالمحسن العباد، والشيخ ربيع بن هادي، والشيخ ابن عثيمين، فإن استطاعوا أن يرحلوا إليهم فعلوا، وإن لم يستطيعوا أن يرحلوا إليهم فبواسطة الهاتف والمراسلات".
በሌላም ጊዜ ወደ እነርሱ ሊመለሱባቸው ስለሚገቡ ዑለማኦች ተጠይቀው ሲመልሱ "ሸይኽ ረቢዕ የጥመት አንጃዎችን በማወቅ ረገድ ከአላህ ተዓምራቶች አንዱ ነው" ሲሉ ያወዱሷቸዋል።
↩️ وفي السؤال (135) لما سئل عن العلماء الذين يرجع إليهم قال: "والشيخ ربيع بن هادي المدخلي، فهو آية من آيات الله في معرفة الحزبيين، لكن لا كآيات إيران الدجالين"
↩️ وفي السؤال (140) سئل: مَن مِن علماء السعودية تنصحون بالأخذ عنهم وحبذا لو ذكرت لنا بعض الأسماء؟
فقال: "أمّا الذين أنصح بالأخذ عنهم والذين أعرفهم فهم الشيخ: عبدالعزيز بن باز حفظه الله، والشيخ محمد بن صالح بن عثيمين حفظه الله، والشيخ ربيع بن هادي حفظه الله،..."
ሸይኽ ረቢዕ ታላቅ የሱንና ዓሊም ለመሆናቸው የተወሱት ታላላቅ አኢማዎች ውዳሴ ከበቂም በላይ ነው። እነዚህን ለምሳሌ አወሳሁ እንጅ ከነዚህም ውጭ እነ ሸይኸ አሕመድ አንነጅሚይ፣ ሸይኽ ዘይድ ኢብኑ ሙሐመድ አል'መድኸሊይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲላህ አስሰቢል፣ ሸይኽ ሷሊሕ አስሱሓይሚይ፣ ሸይኽ ዑበይድ አልጃቢሪይ፣ ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒ እና ሌሎችም በዓለም የሚገኙ ታላላቅ ዑለማኦች በጣም በተዋቡ ገለፃዎች ሸይኽ ረቢዕን አወድሰዋቸውል።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
~ ሙስጠፋ ዓብደላህ እና ዑለማኦች
የሙስጠፋ ዓብደላህ ማንነት ዛሬም ያልገባቹህ ካላቹህ እዚህ ጋ ሸይኽ ረቢዕ ላይ ሐያእ በጎደለው አንደበቱ እንዴት እንደሚላገግ ተመልከቱ። የእርሱን የተክፊር አካሄድ አጥብቀው ስለኮነኑና የሓዳዲያዎችን ፀያፍ ገፅታ በሚገባ ስላብራሩ ብቻ አስፀያፊ በሆነው የኢርጃእ ቢድዓ ይወርፋቸዋል። ሙርጂኣዎች አህለሱናዎች አለመሆናቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ሙስጠፋ እከተላቸዋለሁ እያለ የሚሞግታቸው የመዲና ዑለማኦችም ይሁኑ በዓለም ያሉ የሱና ዑለማኦች ግን ሸይኽ ረቢዕ -ረሒመሁሏህ- ታላቅ የሱንና ዓሊም፣ የሰለፊያ ረዳት እና የቢድዓ ሰዎችን አንገት ያስደፉ ታላቅ ሙጃሂድ መሆናቸውን ባንድ ድምፅ ይመሰክራሉ። ሸይኽ ረቢዕን ያወደሱ ዑለማኦች እጅግ በጣም በርካታ ናቸው። ከእነርሱ ውስጥ የተወሰኑትን እናውሳ።
◾️ ለምሳሌ :-
▫️. ሸይኽ ኢብኑ ባዝ -ረሒመሁሏህ-:
↩️ قال الإمام العلامة سماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز -رحمه الله تعالى- "الشيخ ربيع من خيرة أهل السنّة والجماعة، ومعروف أنّه من أهل السنّة، ومعروف كتاباته ومقالاته" [شريط بعنوان ثناء العلماء على الشيخ ربيع-تسجيلات منهاج السنة].
"ሸይኽ ረቢዕ ከምርጥ አህለሱንና ወልጀማዓዎች ናቸው። ከአህለሱንና መሆናቸው የታወቀ ነው። እንደዚሁም ኪታቦቹና ንግግሮቹም ታዋቂ ናቸው።"
↩️ وقد سئل ـ رحمه الله تعالى ـ عن الشيخ ربيع بن هادي والشيخ محمد أمان فقال: "بخصوص صاحبي الفضيلة الشيخ محمد أمان الجامي والشيخ ربيع بن هادي المدخلي، كلاهما من أهل السنة، ومعروفان لدي بالعلم والفضل والعقيدة الصالحة،" [شريط الأسئلة السويدية].
ስለ ሸይኽ ሙሐመድ አማን እና ስለ ሸይኽ ረቢዕ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ:- "ሁለቱም የተከበሩ የሱንና ሰዎች ናቸው። ሁለቱም እኔ ዘንድ በዒልም፣ የተከበሩ በመሆናቸውና በትክክለኛ ዓቂዳቸው የታወቁ ናቸው።"
↩️ وقال-رحمه الله-: "وإخواننا المشايخ المعروفون في المدينة ليس عندنا فيهم شك، هم أهل العقيدة الطيبة ومن أهل السنة والجماعة مثل الشيخ محمد أمان بن علي، ومثل الشيخ ربيع بن هادي ... ،" [شريط توضيح البيان].
"መዲና ውስጥ ያሉ የታወቁ መሻኢኾችና ወንድሞቻችን እነርሱን በተመለከተ እኛ ዘንድ ምንም አይነት ጥርጥር የለም። እነርሱ የምርጥ ዓቂዳ ባለቤቶች ናቸው። ከሱንና ሰዎችም ናቸው። ምሳሌ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ፣ ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ፣..."
↩️ وقال الشيخ العلامة ربيع بن هادي المدخلي في كتابه “إزهاق أباطيل عبداللطيف باشميل” (ص:104): "لقد زرت سماحة الشيخ ابن باز –حفظه الله- فنصحني بالرد على كل مخالف للحق والسنة. ونِعْمَة النصيحة، فما أعظمها، وأوجبها على من يستطيع القيام بها."
ሸይኽ ረቢዕ እንዲህ ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝን አንዴ ዘየርኳቸውና በማንኛውም ሐቅን የተፃረረ አካል ላይ መልስ እንድሰጥ መከሩኝ። ያማረች ምክር!! ምን የገዘፈች አደረጋት!! በእርሷ ለሚቆምባት አካል ምን የወጀበች አደረጋት!"
↩️ قال الشيخ خالد بن ضحوي الظفيري: "وقد سمعت بأذني الشيخ ابن باز –رحمه الله- يقول مخاطباً الشيخ ربيعاً: "يا شيخ ربيع رد على كل من يخطئ، لو أخطأ ابن باز رد عليه، لو أخطأ ابن إبراهيم رد عليه…" وأثنى عليه ثناءً عاطراً، والله على ما أقول شهيد. [الثناء البديع من العلماء على الشيخ ربيع]
ሸይኽ ኻሊድ እንዲህ ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን እንዲህ ብለው ሲያናግሩ በጆሮየ ሰምቻለሁ:- "ሸይኽ ረቢዕ ሆይ! በማንኛውም የተሳሳተ አካል ላይ ረድ አድርግ (መልስ ስጥ)። ኢብኑ ባዝም ቢሳሳት መልስበት። ኢብኑ ኢብራሂምም ከተሳሳቱ መልስባቸው።"
↩️ ويقول الشيخ خالد أيضا : "بل قد أذن له سماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز بالتدريس في مسجده وذلك قبل وفاته بأشهر، مما يدل على أنه توفي وهو عنه راض." [المصدر السابق]
እንዲህም ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ከመሞታቸው ከወራት በፊት ሸይኽ ረቢዕ በመስጅዳቸው እንዲያስተምሩ ፈቅደውላቸዋል። ይህም ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን እንደወደዷቸው መሞታቸውን ነው የሚያመላክተን።"
¤ ከዚህም ውጭ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን ያወደሱባቸው ንግግሮች በጣም በርካታ ናቸው። የሸይኽ ኢብኑ ባዝን ንግግር ደጋግሜ ያወሳሁት እነ ሙስጠፋ እንከተላቸውዋለን እያሉ በሚሞግቱት ቀጣፊዎች መሆናቸውን ለማሳየት ያክል ነው።
▫️. ሸይኹል አልባኒይ -ረሒመሁላህ-:-
↩️ قال الشيخ العلامة المحدث محمد ناصر الدين الألباني –رحمه الله- في شريط (الموازنات بدعة العصر للألباني) بعد كلامٍ له في هذه البدعة العصرية: "وباختصار أقول: إن حامل راية الجرح والتعديل اليوم في العصر الحاضر وبحق هو أخونا الدكتور ربيع، والذين يردون عليه لا يردون عليه بعلم أبداً، والعلم معه،"
"ባጭሩ በዘመናች የጀርሕ እና ተዕዲል ባንዴራ ተሸካሚ በእርግጥም ወንድማችን ዶ/ር ረቢዕ ናቸው። በእርሱ ላይ መልስ የሚሰጡ ሰዎች መቸም በእውቀት ላይ አይመልሱም። እውቀት ከእርሱ ጋር ነው።"
↩️ ويقول أيضا عن الشيخ ربيع والشيخ مقبل رحمهم الله تعالى: "... فهؤلاء الذين ينتقدون الشيخين ـ كما ذكرنا ـإما جاهل فيُعلّم، وإما صاحب هوى فيُستعاذ بالله من شره، ونطلب من الله -عز وجل- إما أن يهديه وإما أن يقصم ظهره." شريط ( لقاء أبي الحسن المأربي مع الألباني )
ሸይኹ በሌላ ጊዜ ስለ ሸይኽ ሙቅቢል እና ስለ ሸይኽ ረቢዕ እንዲህ ሲሊ ተናግረዋል:- "ሁለቱን ሸይኾች የሚተች አካል ወይ መሃይም ነው ሊማር ይገባዋል። ወይ ስሜቱን ተከታይ ነው።...."
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
የተክፊሪዩ ሙስጠፋ ዓብደላህ ጋጠወጥነት እዚህ ደርሷል።
t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3666
t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3667
t.me/Abu_lmran_Alaseriy/3668
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from قناة ابن محمد الولوي (abu abdirehman)
في مثل هذا اليوم ٢١ صفر سنة ١٤٤٢هـ ، توفي فضيلة الشيخ العلامة المتفنن في العلوم #محمد_بن_علي_بن_آدم_الإتيوبي الولّوي -رحمه الله-؛ صاحب المؤلفات النافعة، والشروحات الماتعة، ونزيل مكة المكرمة، والمدرس في المسجد الحرام، وفي دار الحديث الخيرية»
غاب جسده وبقيت آثاره،
شروحاته ومؤلفاته شاهدة على عُمرٍ أفناه في خدمة الوحيين.
فجزاه الله عن الإسلام والمسلمين خير الجزاء وحمه الله رحمة واسعة وتقبله في الصالحين.
مما أفدته من أهل العلم :
غيّر عتبة بابك!
قال إبراهيمُ عليه السلام: «إذا جاء زوجك فأقرئي عليه السلام، وقولي له: يغيّر عتبة بابه.» فلما أخبرته، قال إسماعيل: «ذاك أبي، وأمرني أن أفارقك.» فطلّقها.
وفي هذه الكناية فراسة عظيمة، لأن عتبة الباب هي أول ما يُدخل عليه للبيت، والمرأة إذا كانت غير صالحة، فهي تُدخل المفاسد والمشاكل والمخاسر، فلا تطيع أمراً، ولا تحفظ نفساً، أما إذا كانت صالحة صابرة حافظة لزوجها، صالحة في كلامها وحالها، فهي تُدخل على البيت أنواع البركات والرحمات، وينشأ تحت يديها الأولاد الصالحون المصلحون، وفي صبر هاجر لما تركها إبراهيم ولما أراد أن يذبح ولدها لآية دالة على طيب الأم فلذا اختيرت بأن تكون جدة لسيد المرسلين الحبيب محمد صلى الله عليه وسلم، وإن طيبوبة الأصول تنتقل إلى الفروع، وقد تزهو الفروع على أصولها.
منقول
قال سفيان الثوري رحمه الله :
"ثَلاثَةٌ مِنَ الصَّبْرِ: لا تُحَدِّثْ بِمَعْصِيَتِكَ،
ولا بِوَجَعِكَ، ولا تُزَكِّ نَفْسَكَ"
📚حلية الأولياء (٦/٣٨٩)
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"የ19 ዓመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ወደ ህክምና ማዕከል በሄደችበት ማደንዘዣ በመውጋት አስገድዶ መድፈር የፈፀመው ዶ/ር በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ" የሚል ዜና አየሁኝ።
"በሃኪም እንዴት ይሄ ይፈጸማል?" ማለት ሞኝነት ነው። በሃኪም ቀርቶ በሃይማኖት አስተማሪም ይፈጸማል። መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው። ማንኛዋም ሴት ከባዳ ወንድ ጋር ተገልላ ልትገኝ አይገባትም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
لا يخلوَنَّ رجلٌ بامرأةٍ فإنَّ الشيطانَ ثالثُهما
"አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋር ብቻውን አይነጠል፤ ምክንያቱም ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነውና።" [ቲርሚዚይ፡ 2165]
"ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነው" የሚለው አጉል መልካም እምነት እንዳያዘናጋን ጥብቅ ማሳሰቢያ ነው። ስለዚህ ያልታሰበ ከባድ ጥፋት የመድረስ እድሉ ከፍተኛ ነው ማለት ነው።
ህክምናን በተመለከተ ሴቶች አማራጭ ካለ በሴቶች ታከሙ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ ከቤተሰብ ጋር እንጂ ብቻችሁን ወንድ ሃኪም ዘንድ አትግቡ። ወይም ሴቶች ነርሶች ካጠገባችሁ እንዲሆኑ አናግሩ። እዚህ ላይ "ውጭ ቆዩ" የሚሉ ሃኪሞች ይኖራሉ። (መግቢያየ ላይ የጠቀስኩትም ክስተት በዚህ መልኩ የተፈፀመ ነው።) እንዲህ አይነት ሃኪም ሲገጥመን ቢቻል ማስረዳት፣ ካልሆነ መጋፈጥ ይገባል። ፈቃደኛ የማይሆኑ ሃኪሞችና ሃኪም ቤቶች ዘንድ አትሂዱ። ቆራጥ ከሆንን ለራሳቸው ሲሉ ያስተካክላሉ።
ለሃኪሞች ማሳሰቢያ፦
ከባዳ ሴት ጋር ተገልሎ መቆየት እንደማይቻል አትዘንጉ። ስለዚህ ስታክሙ ቤተሰብ በቅርብ እንዲኖር አድርጉ። ወይም ረዳቶች ባቅራቢያችሁ ይኑሩ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠማችሁ የምትሰሩበትን ክፍል በሩን ክፍት አድርጉት።
በነገራችን ላይ እንኳን ባዳ የሆነ አካል በቤተሰብ መሀል ራሱ መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል። ለዚያም ነው ኢስላም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥብቅ መመሪያ ያስቀመጠው። ነብያችን ﷺ ልጆችን አስር አመት ሲሆናቸው መኝታቸውን ለያዩዋቸው ብለዋል። ለአስር ዓመት ልጆች! ስለዚህ ቤተሰብ አላህ ባገራለት ልክ መኝታቸውን ሊለያያቸው ይገባል። ሁሉም አንድ ክፍል ውስጥ የሚተኙ ከሆነ ሴቶችን አንድ ጥግ፣ ወንዶችን ደግሞ ሌላ ጥግ ማድረግ ይገባል። በቂ ክፍሎች ካሉ ሴቶችን የብቻ አንድ ክፍል፣ ወንዶችን የብቻ ሌላ ክፍል ማድረግ ይገባል። ከተቻለ ወንዶችን ከወንዶች፣ ሴቶችንም ከሴቶች ፍራሻቸው ቢለያይ ጥሩ ነው።
አጉል መልካም ግምት ሊያዘናጋን አይገባም። "የዘመድ ልጅ ነው"፣ "ቤተሰብ ነው"፣ "ሸይኽ/ ኡስታዝ ነው"፣ "የጎረቤት ልጅ ነው"፣ "እንግዳ ነው"፣ "ስርአት ያለው ጨዋ ልጅ ነው"፣ "ትልቅ ሰው ነው"፣ የመሳሰሉ የዋህ ድምዳሜዎች ከባድ ዋጋ ያስከፍላሉ። እንኳን ሴቶችን ከወንድ፣ ወንዶችን ከወንድም መኝታቸውን መለየት ይገባል። ሌላው ቀርቶ አባት ወይም ወንድም ቢሆኑ እንኳ ጥሩ ያልሆነ አዝማሚያ የሚያሳዩ ከሆነ የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
