fa
Feedback
The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus - EECMY

رفتن به کانال در Telegram

The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus (EECMY) is a national Lutheran church with more than 10 million members.

نمایش بیشتر
3 520
مشترکین
+324 ساعت
+147 روز
+4030 روز
آرشیو پست ها
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ አዲስ አበባ ሲኖዶስ 2ኛ መደበኛ ጉባዬውን ህዳር 15/ 2015 ዓ.ም በእንጦጦ ማህበረ ምዕመናን አካሂዷል። * * * * ጉባዬውም የቤተክርስቲያኒቱ አመራሮች፣ የተቀባይ ማህበረ ምዕመናን እና የሲኖዶሱ አጋር ተቋማት ባቀረቡት ሰላምታ የጀመረ ሲሆን የሲኖዶሱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ኪሮስ ቀጥለው መራሄ ንግግር አድርገዋል። ባደረጉትም ሰፊ ንግግር ሲኖዶሱ ከተመሰረተበት ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ዘጠኝ አመታት በመዲናዋ ውስጥ ስላከናወናቸው የወንጌል፣ የልማት እና የማህበራዊ አገልግሎቶች ያብራሩ ሲሆን ጨምረው ሲኖዶሱ እና በስሩ ያሉ ማህበራነ ምዕመናን ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች በዝርዝር አስቀምጠዋል። አያያይዘውም ከተማዋ አህጉር ዓቀፍና ዓለም ዓቀፍ የዲፕሎማቲክ ግንኙነቶች እና ትላልቅ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗ የተነሳ በተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ቋንቋዎች ሊኖር ስለሚገባው ልዩ ወንጌል የማዳረስ አቀራረብ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል። መራኔ ንግግሩንም ተከትሎ ጉባዬው በሲኖዶሱ የከተማዋን የስነ ሕዝብ አወቃቀር ባማከለ መልኩ ወንጌልን የማዳረስ ስራዎችን መስራት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክሯል። በማጠቃለያውም ጉባዬው ላለፉት ሁለት የአገልግሎት ዘመናት ሲኖዶሱን ሲመሩ የነበሩ አመራሮችን በታላቅ ምስጋና በማሰናበት ለቀጣይ አራት ዓመታት ሲኖዶሱን የሚመሩ መሪዎችን መርጧል። በዚህም መሰረት ፦ ፩ - ቄስ ዶ/ር ፅጌ በረዳ -ፕሬዚዳንት ፪- ቄስ ዶ/ር ዘላለም ቸርነት - ምክትል ፕሬዚዳንት እና ፫- አቶ ምንተስኖት ተከተል - አቃቤ ንዋይ በመሆን ሲኖዶሱን የሚመሩ ይሆናል። የቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ አዳዲስ የተመረጡ የሲኖዶስ መሪዎችን ቃለ-መሀላ አስገብተዋል። ፕሬዝዳንቱም አክለው በቤተክርስቲያኒቱ ታሪክ ለሁለተኛ ጊዜ ቤተክርስቲያን ሴት የሲኖዶስ መሪ ያገኘችበት ታሪካዊ ቀን መሆኑን ጠቅሰዋል። ቤተክርስቲያን ለተመረጡት አዳዲስ መሪዎች የአገልግሎት ስኬት ትፀልያለች።

የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት 12ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ * * * * የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ 12ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በአቡጃ: ናይጄሪያ ከህዳር 19-23, 2023 እ.ኤ.አ ተካሂዷል:: ከጠቅላላ ጉባኤው በፊት የሴቶች እና የወጣቶች ቅድመ ጉባኤ ከህዳር 17-18, 2023 እ.ኤ.አ ተካሂዷል:: በጠቅላላ ጉባኤው ላይ የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት አባል ቤተክርስቲያናት መልዕክተኞች፣ አጋር ድርጅቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እመንግዶች ተገኝተዋል:: የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል ፕሬዚደንት እና ጠቅላይ ጸሐፊም በጉባኤ ተሳትፈው መልዕክት አስተላልፈዋል:: በጉባኤው የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች የቀረቡ ሲሆን: የውይይት እና ልምድ ልውውጥ ጊዜም ተደርጓል:: በጉባኤው የ2024-2028 ያለው ስልታዊ እቅድ እና አዲሱ የመተዳደሪያ ደንብም የጸደቀ ሲሆን: አዳዲስ መሪዎች እና የአመራር ኮሚቴዎችም ተመርጠው ለአገልግሎትም ተመድበዋል:: የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ ኢየሱስ በመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ በ5 መልዕክተኞች ተሳትፋለች:: በአጠቃላያ 12ኛው የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጠቅላላ ጉባኤ የድርጅቱን 60ኛ የምስረታ በዓልን ጎን ለጎን እያከበረ: 'የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል' በሚል ርዕስ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ ተካሄዶ በሰላም ተጠናቋል:: መሪ ጥቅስ:- "...የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና..." 2ቆሮንቶስ 5:14 ህዳር 2016/2023 አቡጃ: ናይጄሪያ 🇳🇬 === YAA'IIN WALIIGALAA WALDOOTA KIRISTAANAA GUUTUMMAA AFRIKAA 12FFAA GAGGEEFFAME * * * * Yaa'iin Waliigalaa Waldoota Kiristaanaa Guutummaa Afrikaa 12ffaan Abuujaa, Naayijeeriyaatti Sadaasaa 18-23, 2023ALA gaggeeffameera. Yaa'ii Waliigalaa duratti yaa'iin duraa kan dubartoota fi kan dargaggootaa Sadaasaa 17-18, 2023ALA gaggeeffameera. Yaa'ii Waliigalaa kanarratti bakka bu'ootni waldoota Kiristaanaa miseensota ta'an, keessummootni garagaraa hojii kana tumsanii fi kkf argamaniiru. Kaawunsilii Waldoota Kiristaanaa Addunyaa irraas Pirezidaantiinii fi Barreessaan Olaanaan argamaniiru, ergaas dabarsaniiru. Yaa'ii kanarratti barreeffamootni qu'annaa mata duree garagaraa irratti kan dhiyaatan yoo ta'u, marii fi yeroon muuxannoo waliif jirjiiruus gaggeeffameera. Yaa'icha irratti karoorri waggaa shanii dhaabbatichaa (AACC) bara 2024-2028 fi Dambiin Ittiin Bulmaataa haaraan kan ragga'e yoo ta'u, gaggeessitoota haaraa fi koree hojii gaggeessituu filamaniifis yeroon ramaddii hojii godhameera. W/K/W/W/Makaana Yesuus Itoophiyaa bakka bu'uudhaan gaggeessitootnii fi tajaajiltootni (delegates) shan hirmaatanii jiru. Walumaagalatti, Yaa'iin Waliigalaa Waldoota Kiristaanaa Guutummaa Afrikaa 12ffaan Abuujaa, Naayijeeriyaatti kabaja Ayyaana waggaa 60ffaa dhaabbatichaa kabajaa bifa milkaa'aa ta'een xumurameera. Luqqisii Duree Yaa'ichaa: "...jaalalli Kiristoos nu dirqamsiisa..." 2Qorontoos 5:14 Sadaasa 2016/2023 Abuujaa, Naayijeeriyaa🇳🇬 ===== The 12th General Assembly of All African Churches * * * * The 12th General Assembly of the All African Churches Conference was held in Abuja, Nigeria from November 19-23, 2023. Before the General Assembly, a pre-assembly of women and youth was held on November 17-18, 2023. At the General Assembly, the delegates of the member churches of AACC, partner organizations and other invited guests were present. The President and Secretary General of the World Council of Churches also participated in the conference and delivered a message. Various theological articles were presented at the conference and there was time for discussion and experience exchange. The strategic plan for 2024-2028 and the new bylaws of AACC were also approved by the General Assembly, and AACC New leaders & governing committees were also elected and installed for service. The EECMY participated in the General Assembly of All African Conference of Churches with 5 delegates. In general, the 12th General Assembly of All African Churches was successfully held in Abuja, the capital of West African country, Nigeria, while celebrating the organization's 60th anniversary. Leading Bible Verse:- "...the love of Christ compels us..." 2Corinthians 5:14 November 2016/2023 Abuja: Nigeria 🇳🇬

ከፕሮሚሲዮ የመጡ ልዑካን የኢትዮጲያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስን ዋና ጽሕፈት ቤት ጎበኙ * * * * ልዑካኑም በዋና ጽሕፈት ቤት በነበራቸው ቆይታ በቤተክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ቄስ ዶ/ር ዮናስ ይገዙ እና ጠቅላይ ጸሐፊው ቄስ ተሾመ አመኑ አቀባበል የተደረገላቸው ሲሆን የቤተክርስቲያኒቱን ታሪክ እና የወንጌል አገልግሎ በሚመለከት አጠር ያለ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። በቀድሞ ስያሜው የዴኒሽ ኢቫንጄሊካል ሚስዮን ፤ በአሁን ስያሜው ፕሮሚስዮ ተብሎ በመጠራት ላይ የሚገኘው የሚስዮን ተቋም ላለፉት 75 ዓመታት በኢትዮጲያ የተለያዩ አከባቢዎች የወንጌል እና መሃበራዊ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል። የተቋሙ አመራሮች እና የቦርድ አባላት ያካተተው ልዑክ ወደ ኢትዮጲያ የመጣበት ዓብይ ጉዳይ 75ኛ ዓመት የሚስዮን ተቋሙን በዓል አስመክቶ ሆኖ ልዑካኑም በቀሪ ቆይታቸው በተለያዩ ስፍራዎች በመዘዋወር የአገልግሎት መስኮችን የሚጎበኙ ይሆናል።

Delegates of Promissio visited The Ethiopian Evangelical Church Mekane Yesus Head Office                                *  *  *  * During their time at the head office, the delegates were welcomed by the president of the church, Rev. Dr. Yonas Yigezu and the general secretary, Rev. Teshome Amenu. They were also briefed about the history of the church and mission works. The mission organization that used to be called Denmark Evangelical Mission, and now Promissio has been working in Ethiopia on mission and social services for the past 75 years. Delegates’ comprising the organization leaders and board members' primary reason for visits to Ethiopia is the 75th anniversary of promissio. On the rest of their stay, the team will be visiting different service fields of the organization. _ _ _ ለአማራጭ የመረጃ ምንጭ ፌስቡክ ቻናላችንን ይከታተሉ 👉 https://www.facebook.com/profile.php?id=100072514116480&mibextid=ZbWKwL

የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ- የወጣቶች ቅድመ ጉባኤ                     * * * * የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ 12ኛው ጠቅላላ ጉባኤ የወጣቶች ቅድመ ጉባኤ በአቡጃ: ናይጄሪያ ተካሂዷል:: በዚህ የወጣቶች ቅድመ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዋል: የውይይት እና ልምድ ልውውጥ ጊዜም ተደርጓል:: የኢ/ወ/ቤ/ክ/መካነ  ኢየሱስን በመወከል በወጣቶች ጉባኤ የተሳተፈው የቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወንድማገኝ ኡዴሣ 'የወጣቶች ድርሻ በሰላም እና ሀገር ግንባታ' በሚል ርዕስ በወጣቶች ጉባኤ ላይ ጽሁፍ አቅርበዋል:: 12ኛው የመላ አፍሪካ አብያተ ክርስቲያናት ጠቅላላ ጉባኤ የድርጅቱን 60ኛ የምስረታ ጉባኤ እያከበረ: 'የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል' በሚል ርዕስ በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ናይጄሪያ ዋና ከተማ አቡጃ እየተካሄደ ይገኛል:: መሪ ጥቅስ:- "...የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና..." 2ቆሮንቶስ 5:14 ህዳር 2016/2023 አቡጃ: ናይጄሪያ 🇳🇬 === YAA'II WALIIGALAA WALDOOTA KIRISTAANAA GUUTUMMAA AFRIKAA, YAA'II DARGAGGOOTAA                          * * * * Yaa'iin Dargaggoota Afrikaa, Waldoota Kiristaanaa Miseensa Waldaa Tokkummaa Yaa'ii Waliigalaa Afrikaa ta'an, yaa'ii Waliigalaa 12ffaa dhaabbatichaa (All Africa Conference of Churches) Magaalaa Abuujaa, Naayijeeriyaatti gaggeeffame. Sagantaa kanarratti mata duree garagaraa irratti barreeffamni dhiyaateera, irrattis mari'atamee hojiitti hiikuudhaaf ejjannoon fudhatameera. Waldaa Warra Wangeelaa Makaana Yesuus Itoophiyaa bakka bu'uudhaan kan hirmaataan Daayireektarri Qajeelcha Tajaajila Ijoollee fi Dargaggoo waldattii Wondimmaagany Uddeessaa, mata duree 'Gahee Dargaggootaa Nagaa Buusuu fi Biyya Ijaaruu Keessatti Qaban' jedhuun barreeffama dhiyeessaniiru. Yaa'ii dargaggootaa kana booda Sagantaan Waliigalaa Yaa'ii Waliigalaa Waldoota Kiristaanaa Afrikaa 12ffaa itti fufee jira, yaa'ichi hundeeffama dhaabbatichaa (AACC) waggaa 60ffaas kabajaa gaggeeffamaa jira. Luqqisii Duree:- "...jaalalli Kiristoos nu dirqamsiisa..." 2Qor. 5:14 Sadaasa 2016/2023 Abuujaa, Naayijeeriyaa 🇳🇬 === The Youth Pre-Assembly of the 12th General Assembly of All Africa Conference of Churches                        * * * * The 12th General Assembly of the All-African Churches Youth Conference was held in Abuja, Nigeria. Different presentations were presented at this youth Pre-Assembly. The Director of the EECMY Children and Youth Ministry Department, Wondmagegn Udessa, who participated in the youth Pre-Assembly, presented an article on the topic "The Role of Youth in Peace and Nation Building". The 12th General Assembly of All African Conference of Churches is celebrating the organization's 60th founding and meeting under the theme 'Christ's Love Compels Us...' and is being held in Abuja, the capital of West African country, Nigeria 🇳🇬. Theme: '...the love of Christ compels us...' 2Cor. 2023 Nov. 2023 Abuja, Nigeria 🇳🇬 #AACC #YouthPreAssembly #AllAfricaConferenceofChurches EECMY Youth Ministry

በተለያዩ ደረጃዎች በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሴት መሪዎች የምክክር ጊዜ አካሄዱ * * * * በውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሴቶን ተሳትፎ ማሳደግ ይቻል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስ
+5
በተለያዩ ደረጃዎች በቤተክርስቲያኒቷ ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙ ሴት መሪዎች የምክክር ጊዜ አካሄዱ * * * * በውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሴቶን ተሳትፎ ማሳደግ ይቻል ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ አስፈላጊነት ዙሪያ ተሰብሳቢዎቹ የመከሩ ሲሆን ለቤተክርስቲያኒቱም እቅድ ተግባዊነት ሴት መሪዎች ትስስርራቸውን በማጠናከር ሌሎች ሴት መሪዎችን የማብቃት ስራ መስነራት እንደሚገባቸው ተወያይተዋል። - - - - - Women leaders who are serving in the church at different levels held a consultation * * * * In the discussion, participants advised on the importance of all stakeholder contribution in order to increase women participation in decision making. The leaders also discussed that for the implementation of the church's plan, women leaders should network and work together to empower other women leaders.

የምሥራች ድምፅ የመገናኛ ዘደዎች አገልግሎት የየዕለቱ ጥቅሶች ከ1/3/2016-30/3/2016 ዘመነ ዮሐንስ ወንገላዊ 👉 Telegram:- https://t.me/YDRadio 👉 Our You tube :- https://www.youtube.com/@Yemisrachdimtsradio/videos

KAN JI'A 3FFAA 1/3/2016- 30/3/2016! KITAABA QULQULLUU YEROO HUNDA DUBBISUU AADAA HAA GODHANNU! Namni kalandeera kana faana bu'ee dubbise waggaa 4 giddutti wangeela guutuu dubbisee fixu ni danda'a. Kaayyoon Keenya Dhaloota hundaa bira Wangeela Ga'uudha Eebbiffamaa. Akkuma beekamu kalanderii Makana yesuus Hard Copy isaa argachaa turtaniittu; Amma immoo karaa Facebook, Telegram fi Youtube keenyaa argachuu ni dandeessu. https://t.me/ydcs_raadiyoosagaleemisiraachoo https://www.youtube.com/@Yemisrachdimtsradio/featured

የልጆች እና ወጣቶች አገልጋዮች ስልጠና በአማሮ እና አካባቢው ሲኖዶስ ===Children & Youth Ministers Training @EECMY Amaro & Surrounding Synod === የልጆች እና ወጣቶች አገልጋዮች ስልጠና ከአማሮ እና አካባቢው ሲኖዶስ ሰበኮች እና ማ/ምዕመናናት ለተወጣጡ የልጆች እና ወጣቶች አገልጋዮች ተሰጥቷል:: ልጆች እና ወጣቶችን በቤተክርስቲያኒቱ ሁለንተናዊ አገልግሎት መሰረት ቀርጾ ማሳደግ የጋራ ሃላፊነት ስለሆነ በቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምርያ ተቀርጾ እየተሰራበት ያለውን ሁለንተናዊ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት ፓኬጅን ሁሉም በጋራ እንዲሰለጥኑ ተደርጓል። ስልጠናውን የሰጡት በቤተክርስቲያኒቱ የልጆች እና ወጣቶች አገልግሎት መምሪያ የወጣቶች አገልግሎት ክፍል አስተባባሪ አቶ ጋዲሳ ረጋሳ ናቸው:: ''ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።'' ሮሜ 11:36