fa
Feedback
Southwest Region electric utility

Southwest Region electric utility

رفتن به کانال در Telegram

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
343
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز

در حال بارگیری داده...

ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
ژانویه '25
ژانویه '25
+343
در 0 کانال‌ها
پست‌های کانال
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተቋም ደረጃ ይከበራል “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 7ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተቋሙ ሁሉም ሪጅኖችና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተከብ
የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተቋም ደረጃ ይከበራል “ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ አንድነታችን” በሚል መሪ ቃል የሚከበረው 7ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተቋሙ ሁሉም ሪጅኖችና የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ተከብሮ ይውላል፡፡ የሰንደቅ ዓላማ ቀን የጥቅምት ወር በገባ የመጀመሪያ ሰኞ ቀን የሚከበር መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

2
+9
بدون متن...
0
3
+8
بدون متن...
0
4
የደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በክልሉ ለሚገኙ በአቅም ምክንያት ትምህርታቸውን መከታተል ለማይችሉ ተማሪዎች የትምህርት መማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ። አገልግሎት ሰጪ ተቋሙ በክልሉ በተመረጡ እና ዕድሚያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ነገር ግን በአቅም ዉስንነት የት/ት ቁሳቁስ መግዛት ላልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ከ660 በላይ ለሚሆኑ የመግዛት አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች በየክፍል ደረጃው ብርሃን ለሁሉም የሚልና የተቋሙ አርማ ያለበትን ደብተር ድጋፍ አደረገ። በድጋፍ ስነስርአቱ የደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳሬክተር አቶ ብርሃኑ ገብሬ ፣ የቤንች ሸኮ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ፣ የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ስንታየሁ ጋይድ፣ የካፋ ዞን ት/ት ቢሮ ና የቦንጋ ከተማ አስተዳደር ት/ት ፅ/ቤት ሃላፊዎች ተገኝተዋል። የደቡብ ምዕራብ ክልል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳሬክተር አቶ ብርሃኑ ገብሬ እንደገለጹት ተቋሙ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ስርጭትን ለህብረተሰቡ ከማድረስ በተጨማሪ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ስራዎችን እየሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። ከዚህም አኳያ በበአላት ጊዜ ለአረጋውያን መዓድ ማጋራት፣ በማረሚያ ተቋማት ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረግና እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ለማስገባት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ዳሪክተሩ አክለው ገልጸዋል። በ2017 የትምህርት መርሃ ግብር ከ660 በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መማር እንዲችሉ ከ205 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጪ ከ3887 በላይ ደብተር በክልሉ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ መደረጉም ተጠቅሷል። በእለቱም በክልሉ ስር ለሚገኙ የመማሪያ ቁሳቁስ መግዛት ለማይችሉ ተማሪዎች ትምህርት ቤት በመሄድ ከ660 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በየትምህርት ደረጃቸው ድጋፍ መደረጉ የተገለጸ ሲሆን በቀጣይ በተመሳሳይ ድጋፍ የሚደረግ መሆኑ ተነግሯል። ተቋሙ ብርሃን ለሁሉም በሚል መርህ ደብተሩን ሲያሳትም ከኤሌክትሪክ ብርሃን በተጨማሪ የእውቀት ብርሃንም ለዜጎች ተደራሽ እንዲሆን አልሞ የሚሰራ መሆኑም ተጠቅሷ። በርካታ ተማሪዎች ደብተር መግዛት ባለመቻል በአሮጌ ደብተር የሚማሩና ከትምህርት ገበታም ውጪ እንዳይሆኑ ሌለቀችም ተቋማት ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቀርቧል። # ወቅታዊና ቴኩስ መረጃዎችን ለማግኘት. የማህበራዊ ትስስር ገፃችን አባል ይሁኑ ፌስ ቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=61553800812715 ቴሌግራም t.me/EEUSWR ድረ-ገፅ https://WWW.eeu.et
0
5
ውድ#የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን በመስከረም ወር የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት ማስላት እንዳለብዎ ያውቃሉ? ካለወቁ በምሳሌ እናስረዳዎ!! አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4
ውድ#የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን በመስከረም ወር የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ እንዴት ማስላት እንዳለብዎ ያውቃሉ? ካለወቁ በምሳሌ እናስረዳዎ!! አንድ ደንበኛ በመኖሪያ ቤቱ 4 ባለ 60 ዋት አምፖሎች በቀን ለ6 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢያበራ፣ 3000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ በቀን ለ2 ሰዓት በወር ለ10 ቀናት ቢጠቀም እና 1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ በቀን ለ5 ሰዓት በወር ለ30 ቀናት ቢጠቀም ፤ በዚህም መሰረት፡- 1ኛ. 4 አምፑል X 60 ዋት x 6 ሰዓት x 30 ቀናት = 43,200 ዋት.ሰ፣ 2ኛ.3000 ዋት ኤሌክትሪክ የኃይል የሚጠቀም የእንጀራ ምጣድ x 2 ሰዓት x 10 ቀናት=60,000 ዋት.ሰ፣ 3ኛ.1000 ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠቀም ምድጃ x 5 ሰዓት x ለ30 ቀናት = 150,000 ዋት.ሰ፣ ሶስቱም ሲጠቃለሉ 43,200 ዋት.ሰ + 60,000 ዋት.ሰ + 150,000 ዋት.ሰ = 253,200 ዋት.ሰ ይሆናል፡፡ ይህም ወደ ኪሎ ዋት ሰዓት ሲቀየር 1 ኪሎ ዋት ሰዓት = 1000 ዋት ሰዓት በመሆኑ፤ 253,200 ዋት ሰዓት = 253.2 ኪሎ ዋት ሰዓት ይሆናል፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ከላይ በምሳሌው የጠቀስነው ደንበኛ በወር 253.2 ኪ.ዋ.ሰ የኤሌክትሪክ ኃይል ቢጠቀም በተቀመጠው እርከን መሰረት በ2.46 ብር ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት 253.2 ኪ.ዋ.ሰ x 2.46 ብር= 622.872 ብር ይመጣል፡፡ የአገልግሎት ክፍያ ብር 42.95 እና የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ 10 ብር ሲደመርበት በአጠቃላይ የደንበኛው ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ 675 ብር ከ 80 ሳንቲም ይሆናል ማለት ነው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
0
6
ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ይፈፅሙ! ከዚህ በተጨማሪም
ውድ #የድህረ_ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኛችን የተጠቀሙበትን ወርሃዊ የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ከዚህ በፊት በሚከፍሉበት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ተቋሙ በዘረጋቸው ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ይፈፅሙ! ከዚህ በተጨማሪም ወርሃዊ የቆጣሪ ንባብ እየተወሰደ መሆኑን ያረጋግጡ! የቆጣሪ ንባብ ካልተወሰደ ለተጨማሪ ውዝፍ እዳ የሚዳርግ በመሆኑ ወቅቱን የጠበቀ ንባብ መወሰዱን ያረጋግጡ፤አለመነበቡን እርግጠኛ ከሆኑ በአቅራቢዎ ለሚገኙ የደንበኞች አገልግሎት መስጫ ማዕከል በመሄድ ያሳውቁ፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
0
7
ውድ ደንበኞቻችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ስትፈፅሙ ማወቅ የሚገባችሁ ሁኔታዎች፡- 👉 ማንኛውም ደንበኛ የቅድመ ኤሌክትሪክ ኢነርጂ ፍጆታ ሂሳቡን ሲከፍል በራሱ ኮንትራት አካውንት ቁጥር መሆኑ
ውድ ደንበኞቻችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ ስትፈፅሙ ማወቅ የሚገባችሁ ሁኔታዎች፡- 👉 ማንኛውም ደንበኛ የቅድመ ኤሌክትሪክ ኢነርጂ ፍጆታ ሂሳቡን ሲከፍል በራሱ ኮንትራት አካውንት ቁጥር መሆኑን ማረጋገጥ አለበት፤ 👉 ደንበኛው የፈፀመው የቅድመ ክፍያ ሂሳብ የሚውለው ለተጠቀመበት የኤሌለክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ብቻ እንደሆነ ማወቅ ይኖርበታል፤ 👉 የትኛውም ደንበኛ ከተቀመጠው ቅድመ ክፍያ በላይ ቀሪ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ የሚፈለግበት ከሆነ በተለመደው የክፍያ ቢል የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቀሪ ሂሳቡን መክፈል አለበት፤ 👉 ደንበኞች የኤሌክትሪክ ኢነርጂ ፍጆታ ሂሳብ ትክክለኛነት ላይ ቅሬታ ካላቸውና ቅሬታው ተጣርቶ ትክክለኛ ሆኖ ከተገኘ፤ የተሳሳተው ቢል ታርሞ እንዲከፍል በማድረግ ለቆጣሪ ማስመርመሪያ የከፈለው ገንዘብ ለፍጆታ ሂሳብ ክፍያ እንዲዞር ይደረግለታል፡፡ 👉 የትኛውም ደንበኛ የተቀመጠለትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ቢል ሂሳብ በመክፈያ የጊዜ ሰሌዳ ሳይከፍል ከተገኘ፤ የኃይል አቅርቦቱን ማቋረጥ እደተጠበቀ ሆኖ ዘግይቶ ለፈፀመው ክፍያ ቅጣት እንደሚከፍል ማወቅ ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪም የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ግሩፕ ቢሊንግ እንዲመቻችት የሚፈልግ የትኛውም ደንበኛ በስሙ በአንድ ወይም በሌላ አካባቢ በተለያየ ወይም በተመሳሳይ የታሪፍ መደብ ውል ላደረጋው ቆጣሪዎች በአንድ የክፍያ ደረሰኝ መክፈል ከፈለገ፤ ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመሄድ መጠየቅ ይችላል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
0
8
የደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው ደንበኞቹ እና ሠራተኞቹ እንኳን ለ2017 ዓ/ም አዲስ ዓመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ ሲል ታላቅ ደስታ ይሠማዋል ። በዓሉ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የመ
የደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለመላው ደንበኞቹ እና ሠራተኞቹ እንኳን ለ2017 ዓ/ም አዲስ ዓመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ ሲል ታላቅ ደስታ ይሠማዋል ። በዓሉ የጤና ፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብና የአብሮነት እንዲሁም ለላቀ ልማት የምንተጋበት እንዲሆንልን መልካም ምኞታቸውን የገለፁት የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ገብሬ ናቸው እንደ ስራ አስፈፃሚው ገለፃ በዓሉን ስናከብር በኤሌክትሪክ ከሚከሰት አደጋ ራሳችንም ሆነ ንብረቶቻችንን እንጠብቅ ፣ ደረጃቸውን በጠበቁ የኤሌክትሪክ ማብሰያ ዕቃዎችን በጥንቃቄ በመጠቀም የሚከሰተውን አደጋ መከላከል እንደሚቻል አስገንዝበዋል ። ይሁን እንጂ ድንገት ለሚፈጠር የሀይል መቆራረጥ ወይንም ለሚከሰት የኤሌክትሪክ አደጋ በክልላችን በሁሉም አገልግሎት ማዕከላት የአስቸኳይ ጥገና ግብረሃይል የተቋቋመ ስለሆነ በአካል በመቅረብ ወይንም ስልክ በመደወል አፋጣኝ አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻል ገልፀዌል ። በድጋሚ መልካም አዲስ ዓመት የደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት # ወቅታዊና ቴኩስ መረጃዎችን ለማግኘት. የማህበራዊ ትስስር ገፃችን አባል ይሁኑ ፌስ ቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=61553800812715 ቴሌግራም t.me/EEUSWR ድረ-ገፅ https://WWW.eeu.et
0
9
بدون متن...
0
10
ሰባት መቶ ሀምሳ ሺህ ቤተሰቦችን በሶላር ሆም ሲስተም ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ፕሮግራም አካል (ADELE) በአለም ባንክ በሚደገፍ የ50.5 ሚሊየን ዶላር በጀት በቀጣይ አምስት ዓመታት ከዋናው ኤሌክትሪክ መስመር ርቀው የሚገኙ 750 ሺ አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የኢነርጂ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ ገለጹ፡፡ ፕሮግራሙ በአምስት ዓመታት ውስጥ ገጠራማ የሆኑና ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ከ2.5 እስከ 50 ኪ.ሜ ርቀው የሚገኙ አባውራዎችን የሶላር ሆም ሲስተም ተጠቃሚ ለማድረግ ታላሚ ተደርጎ የሚተገበር ነው ብለዋል፡፡ እንደ ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ገለጻ በቀጣይ ሁለት ዓመታት በፕሮግራሙ በሀገሪቱ 400 ወረዳዎች 350 ሺ አባውራዎችን የሶላር ሆም ሲስተም ተጠቃሚ ለማድረግ 10 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተበጅቶ ወደ ተግባር ተገብቷል ብለዋል፡፡ ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሱልጣን ወሊ የመጀመሪያ ዙር የፕሮግራሙ አካል የሆነውን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ከ45 ሺህ በላይ አባውራዎችን በሰባት ክልሎች የሶላር ሆም ሲስተም ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችለውንና 150 ሚሊየን ብር ወጭ የሚደረግበትን የውል ስምምነት ከዘጠኝ የሶላር ቴክኖሎጂ አቅራቢና አከፋፋይ አገር በቀል ድርጅቶች ጋር ተፈራርመዋል፡፡ በሶላር ሆም ሲስተም ቢያንስ ለአንድ ቤተሰብ አባላት ከአምስት (5) አስከ አስራ ሁለት (12) ዋት ፒክ ሀይል በማመንጨት ለመብራት፣ ለቻርጅ፣ ለሬዲዮና ለሌሎች መሰል አገልሎቶች ጥቅም ይሰጣል ብለዋል፡፡ በፊርማ ስነስርዓቱ የተገኙት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ድርጅቶቹ በገቡት የውል ስምምነት መሰረት ጥራት ያለው ስራ በመስራት ሀላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው በማሳሰብ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚደርግላቸው አሳውቀዋል፡፡ በመጨረሻም ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ውል የወሰዱ አገር በቀል ድርጅቶች ችግሩን በይበልጥ ተረድተው መንግስት ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በሀይሉ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት አሻራቸውን ሲያኖሩ ወገኖቻቸውን እየጠቀሙ መሆኑን በመረዳት ለቀጣዩ ስራቸው ውጤታማነት ስንቅ የሚሆናቸውን መልካም ስራ በመስራት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ሲሉ ክቡር ሚኒስትሩ አቅጣጫና ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡
0
11
የተቋማችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሽፈራው ተሊላ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችና ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው አዲሱ የኤሌ+3
የተቋማችን ዋና ስራ አስፈጻሚ ኢንጅነር ሽፈራው ተሊላ የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችና ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ በሚደረገው አዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማስተካከያ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በተመለከተ ምን ምን ሃሳቦች አንስተዋል፡- 👉በበጀት ዓመቱ 426 ሺህ 290 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ተደርገዋል፣ 👉100 የኤሌከክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ፤116 የገጠር ከተሞችና መንደሮችን ተጠቃሚ ተደርገዋል፣ 👉ከኢነርጂ ሽያጭ፣ ከአዲስ ሃይል ማስቀጠያ እና ከማያገለግሉ ንብረቶች ማስወገድ ለመሰብሰብ ከታቀደው 44.85 ቢሊየን ብር ውስጥ 42.47 ቢሊየን ብር በመሰብሰብ የእቅዱን 95 በመቶ አሳክቷል፡፡ 👉ሆኖም ተቋሙ ከተለያዩ የገቢ አማራጮች የተጠቀሰው ገቢ ቢገኝም፤ ለኢነርጂ ኃይል ግዢ፣ ለመደበኛና ለካፒታል በጀት በአጠቃላይ ከ53.9 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጓል፣ 👉የመልካም አስተዳደርን ከማስፈንና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አንጻር በ88 አመራርና ሰራተኞች ላይ ከጹሑፍ ማስጠንቂያ እስከ ስንብት የሚደርስ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል፣ 👉ማህበራዊና ሃላፊነቱን ለመወጣትና ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ጎን ለመቆም የተለያዩ የአይነትና የገንዘብ ድጋፎችን የተደረገ ሲሆን፤ በገንዘብ ደረጃ ሲገለፅ ከ57 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
0
12
ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን /ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንድትሳተፉ ስለመጋበዝ/ ተቋማችን በ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀም፣ በ2017 በጀት ዓመት ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ዙሪያ እንዲሁም በአዲሱ የኤሌክትሪክ
ለሁሉም መገናኛ ብዙሃን /ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንድትሳተፉ ስለመጋበዝ/ ተቋማችን በ2016 በጀት ዓመት አፈፃፀም፣ በ2017 በጀት ዓመት ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ዙሪያ እንዲሁም በአዲሱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ላይ ነገ ረቡዕ ነሃሴ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡ ጋዜጣዊ መግለጫው ሜክሲኮ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንግድ ሥራ ት/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ንብ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 17ኛ ፎቅ ላይ ስለሚሰጥ፤ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን በቦታው ተገኝታችሁ በጋዜጣዊ መግለጫው እንድትሳተፉና መረጃውንም ተደራሽ እንድታደርጉልን በአክብሮት እንጋብዛለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
0
13
ተቋርጦ የነበረው የሃይል አቅርቦት ተጠግኖ አገልግሎት ጀመረ። *** በደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ ቤንች ሸኮ ፣ ዲማ ፣ምዕራብ ኦሞ ዞን እና በከፊል ካፋ ዞን ከአራት ቀን በፊት ሰብስቴሽን ባጋጠመው ብልሽት ስርጭት ተቋርጦ እንደነበረ ይታወቃል ። በመሆኑም የኤሌክትሪክ ሃይል /EEP / ሠራተኞች ባደረጉት ጥረት ከሸካ ዞን እና ሜጢ ከተማ በስተቀር አገልግሎቱን ዛሬ ከሰአት ቡኋላ መስጠት ጀምሯል ቀሪዎችም እስከ ነገ 25/12/2016 ዓም ድረስ እልባት እንሚያገኝ እየገለፅን በትዕግስት ለተጠባበቃችሁ ደንበኞቻችን እና ይህን እልህ አስጨራሽ ጥገና ስራ ላሳካችሁ የEEP ሠራተኞች ከልብ እናመሠግናለን ። # ወቅታዊና ቴኩስ መረጃዎችን ለማግኘት. የማህበራዊ ትስስር ገፃችን አባል ይሁኑ ፌስ ቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=61553800812715 ቴሌግራም t.me/EEUSWR ድረ-ገፅ https://WWW.eeu.et
0
14
+6
بدون متن...
0
15
በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ትግበራ ከሰራተኞች ጋር ውይይት ማካሄድ ጀመረ። *** የደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2017 በጀት አመት ዕቅድ ትግበራ ውይይት ከፈፃሚ የክልሉ ሰራተኞች ማካሄድ ጀመረ ። ውይይቱም ባሳላፈው በጀት ዓመት ዕቅድ ክንውን የነበሩ ክፍቶቶችን በመሙላት የተሻለ ልምዶችን በማዳበር የተሻለ አፈፃፀም እንድናመጣ ያግዘናል ተብሏል በተጨማሪም ተቋሙ ከበፊቱ በተለየ መልኩ ገና ከመጀመሪያው በዕቅድ ዙሪያ ሰራተኛው ተገንዝቦ ምን እንዲሰራ ማወቅ አለበት በማለት መወያየታችን ለአፈፃፀማችን ወሳኝ ግብአት ነው በማለት ተሣታፊ ሰራተኞች ገልፀዋል ውይይቱም ቀጣይ ስለሆነ በማጠቃለያ ውይይት ዝርዝር ማብራርያ ይዘን እንቀርባለን። # ወቅታዊና ቴኩስ መረጃዎችን ለማግኘት. የማህበራዊ ትስስር ገፃችን አባል ይሁኑ ፌስ ቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=61553800812715 ቴሌግራም t.me/EEUSWR ድረ-ገፅ https://WWW.eeu.et
0
16
በብልሽት ምክንያት አገልግሎቶ መቋረጡን ስለማሳወቅ፦ **** በክልላችን ማለትም በቤንች ሸኮ ፣ በከፊል ማሻ ዞን፣ ዲማና ሌሎች አካባቢዎች በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በኩል ሰብስቴሽን ማከፋፈያ ጣቢያ ባጋጠመው ብልሽት አጠልግሎት ስርጭት ተቋርጧል ። ስለሆነም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሰራተኞች ችግሩን ለመቅረፍ በቦታው ተገኝተው እየሰሩ ስለሆነ ክቡሯን ደንበኞቻችን ለተፈጠረው ብልሽት ይቅርታ እየጠየቅን ስራው ተጠናቆ አገልግሎት እስከሚጀምር ድረስ አማራጭ ኃይል በመጠቀም በትዕግስት እንድትጠባበቁ በአክብሮት እናሳውቃለን ። # ወቅታዊና ቴኩስ መረጃዎችን ለማግኘት. የማህበራዊ ትስስር ገፃችን አባል ይሁኑ ፌስ ቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=61553800812715 ቴሌግራም t.me/EEUSWR ድረ-ገፅ https://WWW.eeu.et
0
17
بدون متن...
0
18
" እየተከልን እናበራለን !" በሚል የክልሉ መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ ተከናወነ በደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት 600 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር የዘንድሮዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግ+9
" እየተከልን እናበራለን !" በሚል የክልሉ መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ ተከናወነ በደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት 600 ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀንበር የዘንድሮዉ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በክልላችን በተለያዩ አካባቢዎች ተከናዉኖ አረፈደ ፡፡ የክልሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሃኑ ገብሬ እንደገለፁት የዘንድሮ ዘመቻ ለየት የሚያደርገዉ ችግኝ መትከል የአየር ብክለት ከመቀነሱም በላይ ሲያድጉ ለምግብነት እና ለተለያዩ ጥቅም ላይ ሊዉል የሚችል ችግኝ ዝርያ መተከሉ የተለዬ ያደርገዋል ስለሆነም ዘንድሮ ለክልላችን ከካፋ ዞን አስተዳደር በተፈቀደልን የችግኝ መትከያ ቦታ 550 የቸግራቪሊያ ችግኝ የተተከለ ሲሆን በተጨማሪም በክልሉ ስር ባሉ የተቋሙ አገልግሎት ማዕከል ይዞታዎች ሙዝ፣ ማንጎ ፣ አቮካዶ ፣ የወይራ ዛፍ እና የደረጃ ዛፍ 248 ችግኞች በድምሩ 798 ችግኞች የተተከሉ ሲሆኑ በዘመቻዉ ነብቃት ለተሳተፉት የክልሉ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞችን እንዲሁም የመትከያ ቦታ ላዘጋጀልን የካፋ ዞን አስተዳደርን ልባዊ ምስጋናቸዉን በማቅረብ መርሃ ግብሩን አጠናቀዋል ፡፡ # ወቅታዊና ቴኩስ መረጃዎችን ለማግኘት. የማህበራዊ ትስስር ገፃችን አባል ይሁኑ ፌስ ቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=61553800812715 ቴሌግራም t.me/EEUSWR ድረ-ገፅ https://WWW.eeu.et
0
19
ለክቡራን ደንበኞቻቸን በሙሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመላው ኢትዮጵያ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እያከናወነ በመሆኑ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የኃይል ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት ዛሬና ነገ+1
ለክቡራን ደንበኞቻቸን በሙሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በመላው ኢትዮጵያ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እያከናወነ በመሆኑ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የኃይል ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት ዛሬና ነገ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም እንደሚችል አሳውቋል። ተቋሙ የማሻሻያ ሥራው አጠናቅቆ መደበኛ የኃይል አቅርቦት እስሰሚመለስ ድረስ፤ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉና ሌሎች ጊዜያዊ የኃይል አማራጮች እንድትጠቀሙ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
0
20
አዲስ የኤሌክትሪክ ቆጣሪ በዚህ ዋጋ በቀላሉ በአጭር ቀን የቆጣሪ ባለቤት እንደሚሆኑ ያውቃሉ ? ******* እንግዲያውስ ከዚህ በታች በተገለፀው ከቤትዎ እስከ ፖሉ ድረስ በሚያስፈልገው የኬቢል ርቀት መጠን አሁን በተቀመጠው ወቅታዊ ዋጋ ስሌት መሠረት በሁሉም አገልግሎት ማዕከሎቻችን በመቅረብ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ ። የደቡብ ምዕራብ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት
0