cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Ethiopian Electric Utility

EEU Official Telegram Channel Web: www.eeu.gov.et

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
24 768
مشترکین
+1524 ساعت
+907 روز
+44230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በግንባታ ላይ ያለውን የልህቀት ማዕከል ጎበኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ኮተቤ አካባቢ አየተገነባ ያለውን የተቋሙን የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ጎብኝተዋል፡፡ የልህቀት ማዕከል ግንባታው እየተከናወነ ያለው ኮተቤ በሚገኘው የተቋሙ ግቢ ውስጥ ሲሆን አጠቃላይ ግንባታውም በ16.7 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ነው፡፡ ፕሮጀክቱ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የሚከናወን ሲሆን ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ 9 ነጥብ 3 ቢሊየን የኢትዮጵያ ብር በጀት ተመድቦለታል፡፡ በግንባታ ላይ የሚገኘው የልህቀት ማዕከል በዋናነት የኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ ሙያ ማዳበሪያ፤ ሁለገብ የሰው ኃይል ማሰልጠኛ፣ የምርምርና የልህቀት ማበልፀጊያ፣ ብሄራዊ የዲስትሪቡሽን ሲስተም ስካዳ መቆጣጠሪያ ጣቢያ፣ የዲስትሪቡዩሽን ዕቃዎች ጥራት ፍተሻ እና ላብራቶሪ ፋሲሊቲዎችን የሚያሟላ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከሉ አጠቃላይ ሲቪል ግንባታ ስራዎች ዘጠኝ የተለያዩ ስፋትና ከፍታ ያላቸው ህንፃዎች እንዲሁም በፊፋ ስታንዳርድ የሚገነባ ዘመናዊ ሁለገብ የስፖርት ማዘውተሪያ ስታዲየምን ያካተተ ነው፡፡ በመከናወን ላይ ያለው የልህቀት ማዕከል ግንባታ ከዋና ግቡ በተጨማሪ፤ደረጃውን የጠበቀ የስብሰባ አዳራሽ፣ የሰልጣኞችና እንግዶች ማረፊያ ቤቶች እና ክሊኒክን የያዘ ነው፡፡ የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል ግንባታው በቻይና ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እየተከናወነ ያለ ሲሆን፤ አጠቃላይ የግንባታ ስራውን ለማጠናቀቅ ሁለት አመታት ተቀምጦለታል፡፡ የፕሮጀክቱ አጠቃላይ የምህንድስና ጥናት፣ ዲዛይን፣ሱፐርቪዥንና ኮንትራት አስተዳደር ስራው በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን አማካኝነት የተከናወነ ሲሆን፤የፕሮጀክቱ የማማከር እና የክትትል ስራ ደግሞ መንግስታዊ ተቋም በሆነው የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን እንዲሁም በተቋሙ የግንባታ ስራዎች ቢሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
نمایش همه...
እየተከናወነ ባለው የተቀናጀ የመልሶ ጥጋና ስራ እስካሁን ከ30 በላይ የሚሆኑ የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎችን ዳግም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል በወለጋ ዞኖች በነበረው የፀጥታ ችግርና አለመረጋጋት ጉዳት የደረሰባቸውን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መለሶ ለመጠገን እየተከናወነ ባለው የተቀናጀ የመልሶ ጥጋና ስራ በርካታ የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎችን ዳግም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ ከሁለት ሳምንት በፊት የተጀመረውና በአራቱም የወለጋ ዞኖች እየተከናወነ በሚገኝ በዚህ የመልሶ ጥገና ስራ ከ81 ኪሎሜትር በላይ የሚሸፍን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና 30 የተለያዩ መጠን ያላቸው የትራንስፎርመሮችን ዳግም የመትከልና የመቀየር ስራ ተሰርቷል፡፡ እስካሁን ድረስ በተሰራው የመለሶ ጥገና ስራ ቀደም ሲል የተጠቀሱ ከተሞችና ቀበሌዎች እንዲሁም በተጨማሪ ሌሎች ከአገልግሎቱ ጋር የተገናኙ ቦታዎችን ጨምሮ ከ30 በላይ የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች ወይም መንደሮች አገልግሎቱን ዳግም ማግኘት ቸለዋል፡፡ በዚህም መሰረት በምስራቅ ወለጋ 11 ቀበሌዎችና መንደሮች፣በምዕራብ ወለጋ 9 ቦታዎች፣በሆሮ ጉዱሩ 8 ቀበሌዎችና መንደሮች እንዲሁም በቄለም ወለጋ ዞን 2 በታዎች ላይ ተቋርጦ የነበረ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በተሰራው የተቀናጀ የመልሶ ጥገና ስራ አግልግሎቱ ተመልሶለቿዋል፡፡ ተመሳሳይ ስራዎችን በማከናወን በተቀሩ ታቅደው በተቀሩ ሌሎች ቦታዎችም ህብረተሰብ ዳግም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት በስፍራዎቹ ተሰማርተው የተለያዩ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ የስራ መሪዎችና በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን ተቋቁመው ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
نمایش همه...
👍 2 2
Photo unavailableShow in Telegram
ለመላዉ የእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቻችን እንኳን ለ1445ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
نمایش همه...
👍 2 2
Photo unavailableShow in Telegram
#እናስታውስዎ! የመጨረሻውና 10ኛ ዙር ነፃ የስራ ዘመቻ ነገ ቅዳሜ ሰኔ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ከዋናውን መስሪያ ቤት እስከ አገልግሎት መስጫ ማዕከሎቻችን ድረስ ዘጠነኛው ዙር ነጻ የስራ ዘመቻ መርሃ-ግብር ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም ክቡራን ደንበኞቻችን በተጠቀሰው ቀንና ቦታ በመገኘት አገልግሎት ማግኝት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
نمایش همه...
👍 15🏆 3 2👏 1
የፓወር ሴክተሩ ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት መሆኑ ተገለፀ ***************** ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ከብክለት የፀዳ የግሪን ኢነርጂ ፍላጎት አሁን ላይ ዋነኛ የኢኮኖሚ መሰረት እየሆነ መምጣቱን የኃይል አቅራቢ ተቋማቱ የኃይል ሽያጭ ታሪፍን ለማሻሻል ያቀረቡትን ምክረ-ሃሳብ አስመልክቶ ባለድርሻ አካላት ገለፁ፡፡ በመድረኩ ላይ ተገኝተው ሃሳብ እና አስተያየታቸውን የሰጡት ባለ ድርሻ የኃይል አቅራቢ ተቋማቱ አሁን ያለውን የኃይል ፍላጎት ሊመጥን የሚችል በቴክኖሎጂ የታገዘ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራት እና በቂ የሆነ የግብዓት አቅርቦት አቅም መገንባት ላይ በሰፊው መስራት እንደሚጠበቅባቸው ጠቁመዋል፡፡ ባለ ድርሻ አካላቱ አክለውም የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሁሉንም ተገልጋይ ትኩረት የሚስብ የኃይል አማራጭ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በቀጣይ አገልግሎቱን ለማስፋት እና የተጠቃሚውን ፍላጎት ማርካት ላይ መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በስፋት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ያለው የኃይል አቅርቦት ሂደት በቂ ያልሆነ እና መቆራረጥ የበዛበት በመሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች በተደጋጋሚ የኃይል መቆራረጥ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ እና አዲስ ኃይል ጠያቂ ባለሃብቶች ለመስተናገድ እየተቸገሩ መሆኑን አመላክተዋል፡፡ ከባለድርሻ አካላቱ በኩል ከመድረኩ ለተነሱ ሃሳብ እና አስተያየቶች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ሽፈላው ተሊላ ምላሽ እና ማብራሪያ ሰተዋል፡፡ እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚው ምላሽ እና ማብራሪያ፤የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ከማዘመን እና የተገልጋዩን እርካታ ከመጨመር አኳያ በርካታ ሪፎርሞች መደረጋቸውን አውስተው አገልግሎቱን ከማዘመን አኳያ ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን መተግበር፤ስማርት ቆጣሪዎችን የመቀየር እና ደንበኞች መረጃዎችን በቀላሉ ሊያገኙ የሚችሉበት የሞባይል መተግበሪያ በማበልፀግ ጥቅም ላይ የማዋል ስራዎች በሰፊው መከናወኑን ገልፀዋል፡፡ ተቋሙ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትን ከማስፋት አኳያ ከግሪድ ውጪ ያሉ የገጠሩን ማህበረሰብ የኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ 12 የሚሆኑ የሶላር ሚኒ ጊሪድ ፕሮጀክቶችን አጠናቆ ለአገልግሎት ያበቃ መሆኑን እና 1 መቶ አምስት የሚሆኑ የሶላር ሚኒ ጊሪድ ፕሮጀክቶችን ደግሞ በትግበራ ላይ እንዳሉ ዋና ስራ አስፈፃሚው አስረድተዋል፡፡ ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም፤ በተቋሙ መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሰውን ስርቆት እና ውድመት ብሎም የውስጥ አሰራር ክፍተቶችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ የኤሌክትሪክ መሰረተልማቶች ለህዝቡ አገልግሎት የሚሰጡ እና ህዝቡ ዘንድ ያሉ በመሆኑ ህብረተሰቡ የራሱን ድርሻ መወጣት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ የውስጥ አሰራር ክፍተቶችን አስመልክቶ ዘርፉ የሚፈልገውን የሙያ ስነ-ምግባር እና ክህሎት የተላበሰ የሰው ኃይል ለመፍጠር ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በጋራ በመሆን ስልጠናዎችን እየሰተጠ እንደሚገኝ እና በቀጣይ የባለሙያውን የምርምር ክህሎት ለማዳበር የሚያስችል የቴክኖሎጂ ልህቀት ማዕከል እየተገነባ እንደሚገኝ ዋና ስራ አስፈፃሚው ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በመጨረሻም የተቋሙን ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስመልክቶ ግንዛቤ የፈጠሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው ሴክተሩን ይበልጥ በማሻሻል የግሉን ባለሃብት ለመጋበዝ በሚያስችል መልኩ አዲስ የውስጥ አሰራር ሂደት አስጠንቶ ለትግበራ መቃረቡን ጠቁመዋል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
نمایش همه...
2
ምላሽ እና ማብራሪያዎች
نمایش همه...
አስተያየት.docx0.18 KB
ቀደም ሲል ስራ ላይ የዋለው የታሪፍ ማሻሻያ የህብረተሰቡን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነት ማሳደጉን ተገለፀ ከሁለት ዓመት በፊት የተሻሻለው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ታሪፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማስፋት ማስቻሉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፋይናንሻል ማናጅመንት ዳይሬክተር እና የታሪፍ ማሻሻያ ጥናት ቡድን አባል አቶ አለማየሁ መንግስቱ ገለፁ፡፡ ዳይሬክተሩ ይሔን ያሉት ከደንበኛው እና ከባለድርሻ አካላቱ ጋር እየተደረገ ባለው የታሪፍ ማሻሻያ ምክረ-ሃሳብ እና ግብዓት ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ነው፡፡ እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ቀደም ሲል ከ2010 እስከ 2014 ዓ.ም ድረስ ለአራት ዓመታት የተተገበረው የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማሻሻያ በወቅቱ የነበረውን የኃይል ተጠቃሚ ቁጥር በእጅጉ በማሳደግ ተጨማሪ 1 ሺህ 347 የገጠር ከተሞችን የኤሌክትሪክ ተደራሽ ማድረግ ያስቻለ መሆኑን አብራርተዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አክለውም ኃይል አመንጪ ተቋሙ በቀጣይ የሚጠበቀውን ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ፍላጎት ለማርካት ተጨማሪ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን ቀርፆ እየሰራ ቢሆንም የተቋሙ የፋይናንስ አቅም ውስን በመሆኑ የባለድርሻ አካላቱን የጋራ ተሳትፎ ጠይቋል ብለዋል፡፡ በመሆኑም አሁን ያለውን የኤሌክትሪክነ አገልግሎት ሽፋን አሁን ካለበት በአማካይ 55 ፐርሰንት ወደ 74 ፐርሰንት ለማሳደግ እንዲያስችል የህብረተሰቡን እና የባለድርሻ አካላቱን አስተያየት ግብዓትነት መሰረት ያደረገ የታሪፍ ማሻሻያ ምክረ-ሃሳብ ላይ የጋራ ምክክር ማድረግ አስፈልጓል ሲሉ ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡ የህብረተተሰቡን የቀጥታ ተሳትፎ መሰረት ያደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ምክረ-ሃሳብ፤ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፋይናንስ አቋም የሚያጠናክር፤ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንዲሁም የኃይል ማመንጫ እና ማሰራጫ መስመር ግንባታዎችን የሚያፋጥን ብሎም የተቋማቱን የብድር ጫና ለመቀነስ ዕድል የሚሰጥ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ #የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
نمایش همه...
👍 6