cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Business Law and news

The aim of this channel is making business related news and laws easily available.

نمایش بیشتر
أثيوبيا10 586زبان مشخص نشده استقانونی7 918
پست‌های تبلیغاتی
230
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-430 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

👉የግንባታ ሥራ  ውል አፈጻጸም ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑ ዋና ዋና  ባለድርሻ አካላት፡ ➡️የስራው ባለ ቤት/Client or Employer/ *⃣ግለሰብ ወይም ማህበር ወይም ድርጅት ወይም የመንግስት ተቋም ሊሆን የሚችል ሲሆን የሥራው ባለቤት ከመሆኑ አንጻር ሥራውን ለማከናወን የሚችል ሥራ ተቋራጭና አማካሪ መሃንዲስ መቅጠር እና ለግንባታ ሥራው የሚያስፈልገውን የገንዘብ ሀብት የሚያዘጋጅና ዋጋ የመክፈል ሃላፊነት ያለበት አካል ነው፡፡ ➡️ሥራ ተቋራጭ:- *⃣ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ለሥራው አስፈላጊ የሆኑትን ግብዓቶች በሙሉ በሟሟላት የግንባታ ሥራውን  በተባለው ጊዜና በተቀመጠው የጥራት ደረጃ ለመስራት ተዋውሎ የሚሰራ ነው፡፡ ➡️መሃንዲስ(አማካሪ):- *⃣ይህ ባለድርሻ አካል ከባለቤት ጋር በፈጸመው ውል ስምምነት መሰረት ውለታውን እንዲያስተዳድር የሚቀጠር ነው፡፡ምንም እንኳን አማካሪ መሃንዲሱን የሚቀጥረውና ክፍያ የሚፈጸምለት በአሰሪው ቢሆንም፤ አማካሪው ውሉን በማስተዳደር ሂደት ውስጥ በቅን ልቡና በፍጹም ፍትሃዊነት ለሁለቱም የሚሰራ ነው፡፡ ➡️የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅቶች (Insurance Companies):- *⃣አንድ ሥራ ተቋራጭ በጨረታ ለመሳተፍ፣ ወደውል ለመግባት፣ ክፍያዎች ለማግኘትና በሌሎች አሰሪው ድርጅት ለደህንነቱ መጠበቂያ ከስራ ተቋራጩ እንዲቀርብለት የሚጠይቀውን የመተማመኛ የመድን ዋስትናዎች ለሥራ ተቋራጩ የሚያቀርብ አካል ነው። *⃣ከዚህ በተጨማሪ ሥራ ተቋራጩ በአጠቃላይ ለንብረቱ፣ ለገንዘቡ፣ ለስራውና ለሰራተኞቹ ደህንነት የሚጠይቃቸውን የመድን ዋስትናዎችንም (for Contractor’s all risks) የሚያቀርብ ይሆናል። *⃣አንድ የመድን ዋስትና ሰጪ ድርጅት አይነቱ ተለይቶ ለታወቀ ጉዳይ ለሥራ ተቋራጩ የመድን ሽፋን ሰጠ ማለት በአሰሪው ድርጅትና በሥራ ተቋራጩ በኩል ሊኖር የሚችለውን የአደጋ ስጋት ለመሸከም ሃላፊነት የሚቀበል ይሆናል ማለት ነው። *⃣ለወደፊት ስለግንባታ ፕሮጀክቶች የመድን ዋስትናዎች (Construction Insurances) በተብራራ ሁኔታ በምናቀርበው ጽሁፍ የምናየው ይሆናል፡፡ ➡️ባንኮች:- *⃣ለስራ ተቋራጩም ይሁን ለስራው ባለቤት ለፕሮጀክቱ ማከናወኛ የገንዘብ ፍላጎቶችን በማመቻቸት የሚሰሩ ናቸው፡፡ ባንኮች እንደ የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ የባንክ ዋስትናም በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡  ➡️አቅራቢዎች (Suppliers):- *⃣እነዚህ ባለድርሻ አካላት ለግንባታ ሥራ ከመጀመሪያ እስከ ሥራው ፍጻሜ የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ዓይነት የግንባታ ሥራ ግብዓቶችን፣ ማሽነሪዎችን ወይም የግንባታ ሥራ ቁሳቁሶችን በሽያጭና በኪራይ  የሚያቀርቡ ናቸው፡፡ ➡️ፈቃድ ሰጪ አካላት (Permitting bodies):- *⃣ለግንባታ ሥራው የግንባታ ቦታ በመፍቀድ፣ የግንባታ ፈቃድ በመስጠት፣ የግብዓት ማውጫ ካባዎችን ፣የማምረቻ የማከማቻና የቆሻሻ ማስወገጃ ቦታ ፈቃድ በመስጠት የሚሰሩ ናቸው፡፡ ➡️የመሰረታዊ አገልግሎቶች አቅራቢ ተቋማት (Public):- *⃣ለግንባታ ሥራው እንደ ውሃ፣መብራት፣ስልክ የመሳሰሉ ለግንባታ ሥራዎች የመሰረታዊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ አካላት ናቸው፡፡ @etconp
نمایش همه...
Repost from etrade.gov.et
የነጋዴ ግዴታዎች ምንድን ናቸው? ================ አዲስ አበባ 21/01/2015ዓ.ም (ንቀትሚ) 1. የንግድ ዕቃዎቹንና የአገልግሎቶቹን ታክስ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ሌሎች ሕጋዊና ክፍያዎችን ያካተተ የዋጋ ዝርዝር በንግድ ቤቱ በግልፅ በሚታይ ቦታ የማመልከት ወይም በንግድ ዕቃዎቹ ላይ መለጠፍ (አንቀፅ 15)፤ 2. በሚሸጣቸው የንግድ ዕቃዎች ላይ መግለጫ የመለጠፍ ወይም በተለየ ወረቀት ላይ ጽፎ ለሸማቹ መስጠት (አንቀፅ 16)፤ 3. መግለጫው የዕቃውን ስም፣ የተሠራበትን ሀገር፣ ክብደቱን፣ ብዛቱን፣ ጥራቱን፣ ይዘቱን፣ አጠቃቀሙን፣ የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜ …ወዘተ ያካትታል፤ (አንቀፅ 16/2 ሀ-ኀ) ለነጋዴ የተከለከሉ ድርጊቶች (አንቀጽ 22) 1. የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ስላላቸው ጥራት ወይም መጠን ወይም ብዛት ወይም ተቀባይነት ወይም ምንጭ ወይም ባህርይ ወይም ውሁድ ወይም ጥቅም የተሳሳተ መረጃ መስጠት(22/1)፤ 2. የንግድ ዕቃዎች ስለአዲስነታቸው ወይም ስለሞዴላቸው ወይም አገልግሎታቸው የቀነሰ ወይም የተለወጡ ወይም እንደገና የተሠሩ ወይም በአምራቹ እንዲሰበሰቡ የተባሉ ወይም ያገለገሉ ስለመሆናቸው በትክክል አለመግለጽ(22/2)፤ 3. የሌላውን ነጋዴ የንግድ ዕቃዎች በአሳሳች ሁኔታ መግለፅ(22/3)፤ 4. የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶችን በማስታወቂያ እንደተነገረላቸው አለመሸጥ ወይም ማስታወቂያው የመጠን ውሱንነት መኖሩን ካልገለፀ በስተቀር ሸማቾች በሚፈልጉት መጠን ልክ አለመሸጥ (22/4)፤ 5. ስለዋጋ ቅናሽ ሀሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ ማስተላለፍ(22/5) 6. የሸማቹን መብት የሚጠብቅ ባልሆነ ምክንያት የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን አልሸጥም ማለት(22/12)፤ 7. የንግድ ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን በንግድ መደብሩ ውስጥ ከተለጠፈው ዋጋ አስበልጦ መሸጥ(22/14)፤ 8. ከሽያጭ ጋር በተያያዘ የተገባ የዋስትና ግዴታን አለመወጣት(22/7)፤ 9. የንግድ ዕቃ የሚያስፈልገው ጥገና ወይም የሚተኩ ክፍሎች እንደማያስፈልጉት አድርጎ ማቅረብ(22/8) 10. የንግድ ዕቃዎች የተሠሩበትን ሀገር አሳስቶ መግለጽ(22/15)፤ 11. በሸማቾች መካከል ተገቢ ያልሆነ አድልዎ መፈጸም(22/16)፤ 12. ማንኛውንም አገልግሎት የመስጠት ሥራን በንግድ ሥራው ከሚታወቀው ደረጃ በታች ወይም ባልተሟላ ሁኔታ መስጠት922/9)፤ 13. በግብይት ወቅት ማንኛውንም የማጭበርበር ወይም የማደናገር ተግባር መፈፀም(22/11)፤ 14. ደረጃ የሚያስፈልጋቸውን የንግድ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ያለደረጃ ማህተም ለሽያጭ ማቅረብ (22/13)፤ 15. አንድን የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ለመሸጥ ሸማቹ ያልፈለገውን ሌላ የንግድ ዕቃ አብሮ እንዲገዛ ማስገደድ(22/17)፤ 16. ሕገ ወጥ በሆነ ማንኛውም የመለኪያ መሣሪያ መጠቀም(22/18)፤ 17. ለሰው ጤናና ደህንነት አደገኛ የሆነ፣ ምንጩ ያልታወቀ፣ የጥራት ደረጃው የወረደ፣ ወይም የተመረዘ፣ አገልግሎት ጊዜያቸው ያለፈ ወይም ከባዕድ ነገሮች ጋር የተደባለቁ የንግድ ዕቃዎችን ለሽያጭ ማቅረብ ወይም መሸጥ(22/10)፤ 18. አንድ ሸማች አንድን የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት በመግዛቱ ወይም የገንዘብ መዋጮ በማድረጉ እና በሸማቹ አሻሻጭነት ከእሱ ቀጥሎ ሌሎች ሸማቾች የንግድ ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን የሚገዙ ወይም የገንዘብ መዋጮ የሚያደርጉ ከሆነ ወይም በሽያጭ ስልቱ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ በሸማቾቹ ቁጥር ልክ ተጨማሪ የገንዘብ ወይም የዓይነት ጥቅም እንደሚያገኝ የሚገልጽ ፒራሚዳዊ የሽያጭ ስልት ተግባራዊ ማድረግ(22/6)፤ • ከላይ ከተጠቀሱት መብቶች ውስጥ ያልተከበረ ካለ ግብይቱን በፈጸሙበት አካባቢ ለመገኝ ንግድ ቢሮ ወይም ለፖሊስ በማቅረብ በሕግ ምላሽ እንዲሰጥዎ ያድርጉ፡፡ • በአዲስ አበባ እና ድሬዳዋ ከተማ በተፈጸመ ግብይት በሸማቹ ላይ ለደረሰ ጉዳት የካሳ ትያቄ በፍትህ ሚኒስቴር የንግድ ውድድና የሸማቾች ጥበቃ ዳኝነት ችሎት ማቅረብ ይቻላል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን:- Email: [email protected] [email protected] facebook:- Ethiopianministryof tradeandregionalitegration For trade license : www.etrade.gov.et website: www.motri.gov.et telegram channel :https://t.me/motri_gov_et https://t.me/etrade_gov_et https://www.youtube.com/@ethiopian_ministry_of_trade
نمایش همه...
Ministry of Trade and Regional Integration-Ethiopia

An Official Channel of Ministry of Trade and Regional Integration. ይህ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒሰቴር ኦፊሴላዊ ቻናል ነው።

Photo unavailableShow in Telegram
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፉን የወጭ ንግድ ገቢው ለማሳደግ እየተሰራ ነው፡፡ ================================= ነሐሴ 17/2015 ዓ.ም (ኢሚ) በተለያዩ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሀገራዊ ችግሮች ምክንያት የታቀደውን ያህል የወጭ ንግድ ገቢ እየተመዘገበበት ያልሆነውን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ በመደገፍ፣ በማስተዋወቅና ጥራት ላይ አተኩሮ በመስራት ዓለም አቀፋዊ ተቀባይነትና ተመራጭነቱን በማሻሻል በሀገራዊ የወጭ ንግድ ገቢው የተሻ ድርሻ እንዲኖረው ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የወጪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዘሪሁን አበበ ገልፀዋል ፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ባለፉት አምስት ዓመታት ከጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ዘርፍ በወጪ ንግድ ገቢ ከ152.9 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወደ 148.5 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዝቅ ያለ ሲሆን በመጠን ከ19.9 ሺ ቶን ወደ 31.3 ሺ ቶን ማደጉን አቶ ዘሪሁን አበበ ገልፀዋል ፡፡ ከጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለወጪ ንግድ ገቢ ዝቅ ማለት እንደ ምክንያት ያነሱት ከአጋዋ ገበያ መጣትና የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት እንዲሁም የሀገር ውስጥ በየአካባቢ የሚነሱ ግጭቶች መሆናቸው ጠቁመዋል፡፡ ወደ ውጪ ገበያ ከሚላኩ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ውጤቶች ውስጥ በዋናነት ያለቀለት ልብስ ትልቁን ድርሻ ይኖረዋል ያሉት ስራ አስፈፃሚ ከተላኩ ምርቶች 88 በመቶ ድርሻ እንዳለው አስረድተዋል። ጨርቃጨርቅ፣ ክር እና ባህላዊ አልባሳት አነስተኛ ድርሻ ሲኖራቸው እንደ ቅደም ተከተላቸው 6 በመቶ፣ 3 በመቶ እና 3 በመቶ ድርሻ እንዳላቸው አቶ ዘሪሁን አበበ አስታውቀዋል ። ባለፉት አምስት ዓመታት የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፍ መዳረሻ ሀገራት በዋናነት የአሜሪካ ገበያ 63 በመቶ፣ የአውሮፓ ገበያ 23 በመቶ፣ እስያ 9.1 በመቶ፣ ላቲን አሜሪካ 2.5 በመቶ፣ አፍሪካ 2.4 በመቶ የዘርፉ የምርት መዳረሻ መሆናቸውን ገልፀዋል። እነዚህን ወሳኝ መዳረሻዎች መጠቀም ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል ያሉት አቶ ዘሪሁን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ዘርፉን ለመደገፍና ለማስተዋወቅ ያለውን የገበያ አማራጭ በማጤን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የምርቶችን ጥራትንና መጠንን በመሳደግ የማስተዋወቅና የገበያ ላይ ተፈላጊነት ለማምጣት እየሰራ መሆኑ አስታውቀዋል፡፡ https://linktr.ee/fdremoi?subscribe
نمایش همه...
qajeelfamoota Baankii yeroo garagaraa bahan
نمایش همه...