fa
Feedback
Ethiopian Public Service University

Ethiopian Public Service University

رفتن به کانال در Telegram

ፐብሊክ አገልግሎት ልህቀት በተግባር ተኮር እውቀት

نمایش بیشتر

📈 تحلیل کانال تلگرام Ethiopian Public Service University

کانال Ethiopian Public Service University (@epsutelegram) در بخش زبانی امهری بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 12 734 مشترک است و جایگاه 15 756 را در دسته آموزش و رتبه 2 642 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 12 734 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 11 ژوئیه, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 106 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 3 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 34.72% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 16.17% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 4 419 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 2 058 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 27 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
ፐብሊክ አገልግሎት ልህቀት በተግባር ተኮር እውቀት

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 12 ژوئیه, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته آموزش تبدیل کرده‌اند.

12 734
مشترکین
+324 ساعت
+207 روز
+10630 روز
آرشیو پست ها
የኢፐሰዩ ካውንስል የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት የመደበኛና የሪፎርም ስራዎችን አፈጻጸም ገመገመ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል የዩኒቨርሲቲውን የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት የመደበኛና የሪፎርም ስራዎች እና ቁልፍ የውጤት አመላካችን (KPIs) አፈጻጸም ግምገማ እና በቀጣይ ሶስት ወራት የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የውይይት መርሀ ግብር መጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም በህዳሴ አዳራሽ አካሄደ፡፡ በዕለቱም የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚው አቶ ተፈሪ ጊሼ የ3ኛው ሩብ ዓመት የሪፎርም፣ የመደበኛ እና ቁልፍ የውጤት አመላካች (KPIs) የአፈጻጸም ሪፖርትን አቅርበዋል፡፡ በመቀጠልም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ በቀጣይ ሶስት ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው ሊከናወኑ የሚገቡ የሪፎርም፣ የመደበኛ እና ቁልፍ የውጤት አመላካቾች ከማስፈጸሚያ ስልታቸው እና ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳቸው ጋር ለካውንስሉ አቅርበዋል፡፡ ዶ/ር ንጉስ ታደሰ ይህን ዝርዝር መረሃግብር ማዘጋጀትና ማቅረብ ያስፈለገበትን ዓላማ ሲገልጹ እስከ ቀጣይ ሰኔ 30 ድረስ መደበኛም ሆኑ የሪፎርም ሥራዎችን በተቀናጀ ሁኔታ ለማጠናቀቅና ወደ ቀጣይ ስራዎች ለመግባት ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ንጉስ ታደሰ ባቀረቡት ዝርዝር መርሃ ግብር፣ በቀጣይ የሚፈጸሙትን ስራዎች በሶስቱም ዘርፎች እና በስልጠና ኢንስቲትዩት ለይተው ያመላከቱ ሲሆን፣ ይዘቱም የተጀመረውን የለውጥ ስትራቴጂክ እቅድ አጠናቆ ማስጸደቅ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር ሪፎርም ሙሉ በሙሉ ወደስራ ማስገባት፣ የተግባር እና የራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ማስፈጸሚያ ስትራቴጂክ ሰነዶችን ማጠናቀቅ እና ወደስራ ማስገባ፣ ለዩኒቨርሲቲው ገቢ ማሳደጊያ የሚውሉ አዳዲስ ኢንተርፕራዞችን ማቋቋም የሚሉ እና ሌሎችም ዋና ዋና ጉዳዮች ተካተዋል፤ ለእያንዳንዱ ተግባር የማስፈጸሚያ ስልት ተቀምጦለታል፡፡ ከዚያም የካውንስሉ አባላት በቀረበው ሪፖርትና በቀጣይ ሶስት ወራት ዝርዝር የስራ መርሀግብር ላይ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ያቀረቡ ሲሆን፣ የዘርፍ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እና የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ፣ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ ማጠቃለያ ተሰጥቷል፡፡ Visit our website: http://www.epsu.edu.et/ Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram Follow us on LinkedIn: https://www.linkedin.com/.../ethiopian-public.../about/ Subscribe to our YouTube channel: https://www.youtube.com/@EPSUyt

photo content
+3

በኢፐሰዩ መጋቢት 12 ቀን የተጀመረው የማህበረሰብ አገልግሎት መርሀ ግብር ተጠናቀቀ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተሳትፎ የኢንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በየካ እና በለሚኩራ ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከመጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ሲደርግ የቆየውን የማህበረሰብ ድጋፍ አገልግሎት ተጠናቀቀ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የምርምር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ምትኩ አዲሱ በመዝጊያ ስነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በአካባቢው ከሚገኙ ተቋማት ጋር የተቀናጀ የማህበረሰብ አገልግሎትን የመስጠት ተግባሩን በቀጣይነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቁመው፣ ይህ ተግባር ከዩኒቨርሲቲው ተቀዳሚ ተግባራት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህ ተግባር ላይ ለተሳተፉ አካላትም ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ወደፊትም ተሳትፎአቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል፡፡ የማህበረሰብ ተሳትፎ የኢንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ዋርካው ለገሰ በበኩላቸው የማህበረሰብ አገልግሎቱ፣ ለዩኒቨርሲቲው በተሰጡት ቁልፍ የውጤት አመላካቾች መሰረት የተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የማህበረሰብ አገልግሎቱ በየካ እና በለሚኩራ ክፍለከተማ ከሚገኙት ከሮፋም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ከጊብሰን አካዳሚ፣ ከሂልሳይድ አካዳሚ፣ ከሳፋሪ አካዳሚ እና ከደጃዝማች ወንድይራድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለተጠሩ 25 የትምህርት አመራሮች የአንድ ቀን የአስተዳደር እና የትምህርት አመራር የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዶ/ር ዘውዴ ዛኬ አማካኝነት፣ ከአምስቱ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 50 መምህራን የትምህርት እቅድ እና ዝግጅት፣ የትምህር ክፍል አስተዳደር እና የዲሲፕሊን የግምገማ ቴክኒኮች ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን ስልጠና ደግሞ በዶ/ር አስማማው ገብረ እግዚአብሔር እና በአቶ አበበ ተስፋ አማካኝነት ተሰጥቷል፡፡ ከየትምህርት ቤቶቹ ለተጠሩ 300 የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችም የሂሳብ ትምህርት ማጠናከሪ ትምህርት (tutorial) ለአስር ቀናት በአቶ ሹመቴ አበጀ፣ በአቶ ንጉሴ ማሞ፣ በአቶ ፈየራ አስፋው እና በአቶ ኢሳያስ ሽፈራው አማካኝነት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ከዚህም ሌላ በአእምሮ ጤና እና አደንዛዥ ዕጽ አላግባብ መጠቀም የሚያስከትለውን ጉዳት መሰረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና፣ ከየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እና ከለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ለተጠሩ 50 ወጣቶች፣ እንዲሁም በዩኒቨርሲቲው ዙሪያ ለሚገኙ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች በዶ/ር ብስራት ተክሌ አማካኝነት የተሰጠ ሲሆን፣ የመንገድ ደህንነት እና የትራፊክ አደጋን አስከፊነት የተመለከተ የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለ50 የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በዶ/ር በለጠ እጅጉ እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በመጡ ባለሙያ ተሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ/ም በተካሄደው የመዝጊያ ስነስርዓት ላይ፣ ከየካ እና ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች ከመጡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የጎዳና ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡ Visit our website: http://www.epsu.edu.et/ Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram Follow us on LinkedIn: https://www.linkedin.com/.../ethiopian-public.../about/ Subscribe to our YouTube channel: https://www.youtube.com/@EPSUyt

photo content
+3

በኢፐሰዩ የመምህራን ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ተካሄደ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ( ኢፐሰዩ) የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ማህበር ሥራ አስፈጻሚዎች ምርጫ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር ፕሬዚደንት፣ የውጪና የህዝብ ግንኙነት ተጠሪ እንዲሁም የማህበሩ ተወካይ በተገኙበት ዛሬ መጋቢት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በህዳሴ አዳራሽ ተካሄደ፡፡ በተደረገው ምርጫም ዶ/ር ወይንሸት መንግስቱ የማህበሩ ፕሬዚደንት ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ አቶ አብደላ ሁሴን ዋና ጸሐፊ፣ ዶ/ር መርጊቱ ደበላ የሥርዓተ-ጾታ እና ምክትል ዋና ጸሐፊ ፣ ዶ/ር መስፍን ስዩም የህዝብ ግንኙነት፣ ዶ/ር ይመር መሀመድ ኦዲተር እና ዶ/ር ወንድአፈራሁ ሙሉጌታ የትምህርት ስልጠናና ምርምር አሰተባባሪ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ በምርጫ ሥነ ስርዓቱ መክፈቻ ላይም የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንት ዶ/ር አማኑኤል ኩሲያ እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው የመምህራን ማህበርን ለመመስረት በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው፣ የማህበሩ ምስረታው እውን ሊሆን በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ አክለውም ማህበሩ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ መምህራን አንድነት በመፍጠር እና በመደራጀት የመምህራንን መብትና ጥቅም ከማስከበሩም በተጨማሪ፣ በመምህራን ላይ የሚመጡ ጫናዎችን አስቀድሞ ለመከላከል እንደሚያግዝ አመልክተው፣ የማህበሩ ምስረታም ዩኒቨርሲቲው በለውጥ ሂደት ላይ እያለ እውን ሊሆን መቻሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር ፕሬዚደንት በበኩላቸው ለማህበሩ መመስረት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንትና አመራር ላበረከቱት አሰተዋጽኦና ድጋፍ አመስግነው፣ ያለውን መነሳሳት አድንቀዋል፡፡ አያይዘውም የማህበሩ የምስረታ ሂደትና ዓላማ እንዲሁም ማህበሩ ከምስረታው ጀምሮ እያከናወቸው ያሉ ተግባራትን ለመምህራኑ አጋርተዋል፡፡ በምርጫው ላይ የተሳተፉ መምህራን በሰጡት አስተያየት የማህበሩ መመስረት እንደ መምህርም ሆነ እንደተቋም የሚኖረው ሚና እጅግ ከፍተኛ መሆኑን እና ማህበሩን በመምራት ላይ ያሉትን አመራሮች እያደረጉ ላለው አስተዋጽኦ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የተመረጡት ሥራ አስፈጻሚዎች ማህበሩን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል ቃለ መሀል ፈጽመዋል፡፡ Visit our website: http://www.epsu.edu.et/ Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram Subscribe to our YouTube channel: https://www.youtube.com/@EPSUyt

photo content
+3

ኢፐሰዩ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ጋር የማማከር ውል ስምምነት ተፈራረመ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ (ኢፐሰዩ) ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ ጋር የ10ኛዉ አዲስ አበባ ከተማ መዋቅራዊ ፕላን አፈጻጸም ዉጤታማነት እና ተጽዕኖ ግምገማ እና በ2025 በአዲስ አበባ ያለዉን ድህነት ግምገማ በሚሉ ሁለት ፕሮጀክቶች ላይ የማማከር አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን የስምምነት ውል መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ/ም በቢሮው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረመ፡፡ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው በዚህ የፊርማ ስነስርዓት የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ምትኩ አዲሱ ከመስተዳድሩ የፕላንና ልማት ቢሮ የስፓሻል ፕላን አፈጻጸም ክትትልና ቁጥጥር ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ መዓዛ መንግስቱ እና የፕላንና ልማት ቢሮ የከተማ ጥናት መረጃና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸዉ ኃይሌ ጋር ውሎቹን ተፈራርመዋል፡፡ በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ዶ/ር ምትኩ አዲሱ እንደተናገሩት ቢሮው እነዚህን ትልልቅ ሁለት ፕሮጀክቶችን ለማሰራት በዩኒቨርሲቲያችን ላይ ላሳደረው እምነት አመስግነው፣ ዩኒቨርሲቲው የካበተ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎችን ተጠቅሞ በስምምነቱ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ፕሮጀክቱን አጠናቆ እንደሚያስረክብ አረጋግጠዋል፡፡ Visit our website: http://www.epsu.edu.et/ Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram Follow us on LinkedIn: https://www.linkedin.com/.../ethiopian-public.../about/ Subscribe to our YouTube channel: https://www.youtube.com/@EPSUyt

ማስታወቂያ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም ክፍያ ለረጅም ጊዜ ሳይሻሻል በመቆየቱ፣ አሁን ካለው የገበያ ሁኔታና ለትምህርት ጥራት ከሚያስፈልገው ወጪ ጋር የማይመጣጠን ሆኖ ቆይቷል። በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠትና አስፈላጊው የትምህርት ግብዐቶችን ለማቅረብ እንዲችል የክፍያ ማሻሻያ ጥናት አድርጎ በዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የክፍያ ማሻሻያው የጸደቀ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ዩኒቨርሲቲው በተማሪዎች ላይ ሊያርፍ የሚችለውን የኢኮኖሚ ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ማሻሻያው በዚህ የ2018 ዓ.ም ሁለተኛ መንፈቀ ዓመት ተግባራዊ እንደማይሆን እየገለጽን፤ አዲሱ የክፍያ ተመን ከሚቀጥለው አካዳሚክ ዓመት ( መስከረም 2019 ዓ.ም) ጀምሮ ሥራ ላይ የሚውል መሆኑን እናስታውቃለን። የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ

photo content
+6

በኢፐሰዩ የኮምቲዩቲንግ እና ዲጂታላይዜሽን ኮሌጅ የመጀሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች የዳሰሳ ጥናት ግምገማ ተካሄደ፡፡ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ(ኢፐሰዩ) የኮምቲዩቲንግ እና ዲጂታላይዜሽን ኮሌጅ (College of Computing and Digitalization) ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው አዲስ ተክዕኮ መሰረት፣ ሊከፈቱ በታቀዱት አምስት የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ ያካሄደውን የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ግምገማ መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ/ም አካሄደ፡፡ የፍላጎት ዳሰሳ የተደረገባቸው የትምህርት ፕሮግራሞችም ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ፣ /Software Engineering/ ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ /Computer Science/ ዳታ ሳይንስ፣ / Data Science ኢንፎርሜሽን ሲስተም፣ /Information Systems/ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ /Information Technology/ ሲሆኑ፣ የዳሰሳ ጥናቱን ያካሄዱት ባለሙያዎች የጥናት ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ የኮሌጁ ዲን አቶ አለባቸው ጭጬ በግምገማው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፣ በእያንዳንዱ የትምህርት ፕሮግራም የተካሄደው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በተናጠል በጥልቀት ተገምግሞ አስተያየት የተሰጠበት መሆኑን ጠቁመው፤ በዚህ መድረክ የሚካሄደው ግምገማ ጥናቱ በተሰጠው አስተያየት መሰረት መስተካከሉን የማረጋገጥ ስራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቀጥሎም በአምስቱም የትምህርት ፕሮግራሞች ላይ የተካሄደው የፍላጎት ዳሰሳ ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ Visit our website: http://www.epsu.edu.et/ Follow our Facebook page: https://web.facebook.com/EPSUfb Follow our Telegram Channel: https://t.me/epsutelegram Subscribe to our YouTube channel: https://www.youtube.com/@EPSUyt

AFD Expertise Delegation Visits EPSU to Strengthen Ties and Define Collaborative Roles in Public Service Reform (March 19, 2026 ; E.P.S.U.) A key expertise delegation from the Agence Française de Développement (AFD) visited the Ethiopian Public Service University (EPSU) today to strengthen bilateral ties and define collaborative roles in supporting Ethiopia's national public service reform agenda. The AFD team, led by Lauriane Thibaud, Task Team Leader for Public Administration Reform at AFD, and Hiwotee Salvat from the AFD Addis Ababa office, was warmly received at the university by Dr. Amanuel Kussia, Vice President for Academic Affairs; Dr. Dereje Teklemariam, Director of International Collaboration and Partnership; and Dr. Azeb Assefa, Dean of the Training Institute. The visit aimed to provide the AFD delegation with a comprehensive understanding of EPSU's unique mandate as the only university in the country specifically tasked with building capacity across the entire public sector. Through specialized education, demand-driven training, policy-oriented research, and consultancy services, EPSU continues to play a pivotal role in shaping Ethiopia's civil service. Discussions held on campus focused on identifying synergies to further support the ongoing reform efforts of the Civil Service Commission. During the meeting, EPSU leadership proudly reflected on the historic partnership with France. Historical records indicate that the French government was a founding partner in the establishment of the Institute of Leadership and Good Governance in 2010 and has remained a steadfast supporter ever since. This enduring collaboration is formalized through institutional links with prestigious French institutions, including the French National School of Administration (ENA) and the School of Magistrates in France. The EPSU team noted that France's long-term vision and consistent commitment have been instrumental in developing generations of Ethiopian public sector leaders, and expressed enthusiasm for building upon this strong legacy. Building on this foundation, EPSU presented six key areas for potential future partnership: Trainers' Capacity Building to create a multiplier effect across the public service, A Digitalization and Incubation Centre to pilot innovative service delivery models, A Public Sector Innovation and Reform Centre to serve as a policy think tank, A Leadership Excellence Centre dedicated to executive-level development, Support for EPSU's own institutional capacity building as the university transitions to autonomy, Positioning EPSU as a national hub for supporting applied universities across the country. Following the productive discussions, the delegation was briefed on EPSU's ongoing transformation toward producing competent public servants through technology-driven, innovative, and modern programs. The university leadership showcased its commitment to delivering quality education, research, and community engagement services that contribute to a dynamic and accountable public sector. The visit represents a significant step in defining and advancing the collaborative framework between EPSU and AFD. Both sides expressed a shared commitment to deepening their partnership, with the AFD delegation acknowledging EPSU's strategic position in the future of Ethiopian public sector governance and conveying strong enthusiasm for supporting national reform efforts. The EPSU leadership, in turn, reaffirmed its dedication to translating the discussed areas of collaboration into concrete initiatives, ensuring that the partnership continues to yield meaningful outcomes for the modernization of Ethiopia's public service.

+9