fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ይህም መጻፍ የሊቀ ሊቃውንት መምህር ሳህሉ አደመ የሰዋሰው ብርሀን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሊቃውንት እና የመነኮስ መጻህፍት ትርጓሜ መምህር የተጻፈ የተብራራ መጻፍ በቅናሽ ዋጋ ስለ ጾም የሚና
+3
ይህም መጻፍ የሊቀ ሊቃውንት መምህር ሳህሉ አደመ የሰዋሰው ብርሀን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሊቃውንት እና የመነኮስ መጻህፍት ትርጓሜ መምህር የተጻፈ የተብራራ መጻፍ በቅናሽ ዋጋ ስለ ጾም የሚናገር መጽሀፉን የምትፈልጉ በዚህ አካውንት / 0932532529 ያገኝሉ

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ ብሔረ ነነዌ ዘሠረቀ። ከመ ማኅቶት ዘይሰድድ ጽልመተ ኃጢአት ጽፉቀ። በምሳር አቡሁ አመ ክሣዶ ነፈቀ። ቀዊሞ ተርእየ በእገሪሁ እስከ በደሙ ተጠምቀ። ወበድነ ሥጋሁ ውስጥ ምድር ኢወድቀ"። ትርጉም፦ ጭፍቅ ያለ የኃጢአት ጨለማን እንደ መብራት የሚያርቅ፤ በነነዌ አገር የወጣ ለኾነ ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባል ፤ በመጥረቢያ አባቱ አንገቱን በቈረጠው ጊዜ በደሙ እስኪጠመቅ ድረስ በእግሮቹ ቆሞ ታየ፤ የሥጋው በድንም በምድር ውስጥ አልወደቀም። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሚያዝያ 26። @Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሚያዝያ ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን በአባቱ እጅ በመጥረብያ አንገቱን ተመቶ ሰማዕትነት ለተቀበለ፤ አባቱን ከዐረፈ በኋላ ለፈወሰው ለጠራቢ ልጅ ለቅዱስ ዮሐንስ ለዕረፍት ለዕረፍቱ በዓልና ለሱሴ ልጅ ሱስንዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ከቅዱሳን ስብስጥራስ፣ ከአባ ሠርጋና፣ ከይድራስ ከምስክርነታቸው መታሰቢያና ከሱስንዮስ ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበሉ ከአንድ ሺህ አንድ መቶ ዘጠኝ ሰማዕታት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ ወልደ ጸራቢ"። ትርጉም፦ የጠራቢ ልጅ ለሚኾን ለዮሐንስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ቅዱስ ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ከነነዌ አገር ነው አባቱ ጣዖትን የሚጠርብና የሚያመልክ ነው። እናቱ ግን ክርስቲያናዊት ናት ልጅ በአጣችም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ለመነች ጌታም ልመናዋን ተቀብሎ ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት ስሙንም በሥውር ዮሐንስ ብላ ጠራችው። ስምንት ዓመትም በሆነው ጊዜ የጠረበውን ጣዖት እየሸጠለት አባቱን ያገለግል ነበር። ❤ በአንዲት ዕለትም ጣዖቱን ሊሸጥ ሲሔድ የእግዚአብሔር መልአክ ተገናኘውና "ጣዖት የሰይጣን ማደሪያ እንደሆነ ነገረው ጣዖቱንም ከእጁ እንዲጥለው አዘዘው በክብር ባለቤት በክርስቶስ ማመን አስተማረው" ወደ አባቱም በተመለሰም ጊዜ "ሰማይና ምድርን በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ ከፈጠረ ከክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም እኔ ለሰው እጅ ሥራ አልሰግድም" አለው። አባቱም ሰምቶ በእሥር ቤት አሰረው እናቱም መጥታ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ስም ደሙን ያፈስ ዘንድ አጸናችው። ❤ ከዚህም በኋላ በነገራቸው ሊሸነግሉት የአገር ሰዎች መጥተው "የአባትህ አምላኮች ለምን ተውክ" አሉት እርሱም "እኔ የሰው እጅ ለሰራቸው ጣዖቶች አልሰግድም እነርሱም የእርኵሳን አጋንንት ማደርያዎች ናቸውንና" አላቸው። አባቱም ይህንን በሰማ ጊዜ ምሳር አንስቶ አንገቱ ቆረጠው በድኑም አልወደቀም በደሙም እስከተጠመቀ ድረስ በእግሮቹ ቆመ እጅ። ❤ እናቱም በደሞ ተጠምቃ "አቤቱ የክብር ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የአቤል መስዋዕት በምድረ በዳ የተቀበልክ ይህንን መስዋዕት ከእኔ ተቀበል" አለች። በዚያ ጊዜ አባቱ ሰይጣን አደረበትና አበደ ሚስቱን ወደ ልጇ መቃብር ወስዳው ስለ እርሱ ጸለየች ቅዱስ ዮሐንስም በሌሊት ወደ እርሱ መጥቶ አባቱ በጦር ወጋው ሰይጣኑም ከእርሱ ወጣ ከዚህ በኋላ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመነና በስሙ ተጠመቀ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር አሜን። + + + ❤ ቅዱስ ሱስንዮስ፦ ይህም ከሀዲው ከዲዮቅልጥያኖስ ወዳጁ ነበረ የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጠለትና ሰማዕት እንደሚሆን ነገረው ይህም ነገር በልብ አደረ። ❤ከዚህም በኋላ አምልኮ ጣዖትን እንዲያስፋፋና እንዲያድሱ ከሹመት ደብዳቤ ጋራ ንጉሡ ወደ ኒቆድምያ ላከው ቅዱሱም አይቶ እጅግ አዘነ ወደ እርሱ አንድ ቄስ አምትቶ ክርስትናንን ተምሮ ተጠመቀ። ከዚህ በኋላ ወደ አንጾኪያ ተመለሰ ፍጥረቱ ልዩ የሆነ ልጅ ወልዳ እቱን አገኛት ከዚህ በፊት ሴት ልጅ ወልዳ ገድላ ደሙን ጠጥታለች ሰይጣን አድሮባታልና በወፍና ከይሲ አምሳልም ይገለጣል በአገር ውስጥም ልጅ በሚወለድ ጊዜ ወደርሱ ወርዳ በሥራይም ገድላ ደሙን ትጠጣለች። ❤ ቅዱስ ሱስንዮስም ይህን በአየ ጊዜ ጦሩን አንስቶ ከልጅዋ ጋራ እኅቱን ገደላት ልጅዋ የሰይጣን ልጅ ነውና ሁለተኛም ሥራየኞች ሲሆኑ ባሏንና የባሏን አባቱን ገደላቸው እነርሱ በሥራያቸው ሰውን እያሳመሙ ይድላሉና። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ኒቆድምያ ተመለሰ ወደዚያ ወደ አጠመቀው ቄስ ደርሶ ያደረገውን ሁሉ ነገረው። ወደ አገሩ አንጾኪያም በተመለሰም ጊዜ ከእርሱ የሆነውን አባቱ ሱሲ አወቀ መገደሉንም ወዶ ከንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት። ያንጊዜም ቅዱስ ሱስንዮስ ወደ ጣዖታት ቤት ሒዶ ወደ ሲዖል ይወልዱ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዘዘቸው ያን ጊዜም ምድር አፋን ከፍታ ዋጠቻቸው። አባቱ ዳግመኛ በንጉሡ ዘንድ ከሰሰው ታላቅ ሥቃይም ያሰቃዩት ዘንድ ንጉሥ አዘዘ በብረት ዘንጎችም ደበደቡት፣ በመንኰራኵር አበራዩት፣ በመዶሻም ቀጥቅጠው ሁለተኛ ደግሞ እህል በሚያበራዩበት መሳርያ አበራዩት፣ ከዚያም በከተማ ውስጥ ጎተቱት የክብር ባለቤት ጌታችንም ያጸናውና በስቃዩም ውስጥ ያስታግሰዋል ከቊስሉም የሚፈውሰውን መልአኩንም ልኮ ያለምንም ጉዳት አነሳው ብዙ ሰዎችም አይተው በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በእርሱ ምክንያት ሰማዕት ሆኑ። ንጉሡም ከማሠቃየት በደከመ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። በሥቃዩም ወራት በሰማዕትነት የሞቱት ቊጥራቸው አንድ ሺህ አንድ መቶ ዘጠኝ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ 26 ስንክሳር። + + + ❤ የለዕቱ ምስባክ፦ "አኀዝከኒ እዴየ ዘየማን። በምክረ ዚአከ ዘየማን። ወምስለ ስብሐት ተወአፍከኒ"። መዝ 72፥23-24። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፌ 5፥1-15፣ 1ኛ ዮሐ 3፥7-13 እና የሐዋ ሥራ 17፥16- 21። የሚነበበው ወንጌል ማር 13፥9-14። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን። @Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሚያዝያ ፳፬ (24) ቀን። ❤ እንኳን ለቅዱስ ኤስድሮስ ባልንጀራ ለቅዱስ ፃና ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለእስክንድርያ ስልሳ አምስተኛ ሊቀ ጳጳሳት ብዙ ተዓምራት ላደረገ ለአባ ስንትዮ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡት፦ ደብረ ሲና ከከበረችበት ከአባ ይድራ መታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያስትፈን። + + + ❤ ቅዱስ ፃና፦ ይህም እንዲህ ነው ባልንጀራው ከኤስድሮስ ጋራ ከአሠቃዩት በኋላ ባልጀራው ኤስድሮስ በሰማዕትነት ሞተ። ቅዱስ ፃናም በእሥር ቤት ቀረ ከአገረ ፈርማ መኰንንም ታሠረ በእርሱም ፈንታ ሌላ መኰንን ተሾመ። ያንን መኰንንም የክብር ባለቤት የሆነ የኢየሱስ ክርስቶስ ስም የሚጠራ ክርስቲያንን ሁሉ እንዳያስቀር ከሀዲው ንጉሥ አዘዘው። ስለ ቅዱስ ፃናም እርሱ ከጭፍሮች ውስጥ እንደሆነ ጽኑዕ ሥቃይም እንዳሠቃዩትና ከአላማውም እንዳልተመለሰ በነገሩ ጊዜ የከበረች ራሱን ይቆርጡት ዘንድ አዘዘና ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ❤ የቅዱስ ፃና እናቱም ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት በሆነ ጊዜ አስቀድማ እንዳየች አሁንም ብርሃናውያን መላእክትን የቅዱስ ፃናን ነፍስ ሲያሳርጓት አይታ ለሰው ነገረች። ምዕመናንም ሥጋውን ወስደው ገንዘው ሰምኑድ በሚባል አገር ከባልንጀራው ከኤስድሮስ ሥጋ ጋር አኖሩት። በውስጥዋም እስከ ዛሬ በዓል ይደረግላቸዋል። ወደ እርሳቸው በእምነት ለሚመጣም ታላላቅ ድንቆች ተአምራቶች ይታያል። በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። + + + ❤ አባ ስንትዩ፦ ይህም ከታናሽነቱ ጀምሮ መንፈሳዊ ነው። በአስቄጥስም ገዳም በአባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን በበጎ ሥራ በገድል ተጠምዶ አድጎ በዚያው ገዳም አበምኔት ሁኖ ተሾመ። ከዚህም በኋላም ሕዝቡና ኤጲስቆጶሳቱ መርጠውት በእስክንድርያ አገር ላይ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት። ነገር ግን በዘመኑ ሁሉ ከእስላሞች ነገሥታት ታላቅ ችግርና ኀዘን ደረሰበት። ይኸውም በእርሱ ዘንድ ምንም ምን ያልኖረውን ሊሰጣቸው የሌለውን ብዙ ገንዘብ ይሰጣቸው ዘንድ ፈልገው ይዘውታልና። እግዚአብሔር በእጆቹ ብዙ ድንቆች ተአምራቶችን አደረገ ብዙዎችን ጭንቅ ከሆነ ደዌያቸው አድኖቸዋልና ከሰዎችም ላይ ሰይጣናትና አስወጥቷልና በአገረ መርዩጥ ላይ በጸሎቱ ዝናምን አዝንሞአልና። እርሱም ዝናምን ከማጣት የተነሣ ወንዞቻቸው ጉድጓዶቻቸው ሁሉ ደርቀው ከረኃብና ከውኃ ጥም የተነሣ ለሞት ተቃርበው በታላቅ ረኃብ ሦስት ዓመት ኑረዋልና። ❤ በሰማዕት ቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን በዓልን ሊያከብር ወደርሳቸው በደረሰ ጊዜ የዚያች አገር ሰዎች ወደ ርሱ ተሰብስበው ውኃ በማጣት እንደ ተቸገሩ ነገሩት እርሱሙ ፈጽሞ አጽናናቸው። የቅዳሴውንም ሥርዓት ከፈጸመ በኋላ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ወዲያውኑ ታላቅ ነጐድጓዶችና ኩሬዎች ሁሉ ሞሉ የተክል ቦታዎች ሁሉ ረኩ። ረኃብ በሆነባቸው በእነዚህ ሦስት ዓመት እንደመላ ኖረ። ❤ አራተኛውም በአስቄጥስ አረቦች በተሰበሰቡ ጊዜ በዚያ የሚኖሩትን መነኰሳት ይገድሉአቸው ዘንድ ከበቡአቸው ይህም አባት መስቀሉን ይዞ ወደእርሳቸው ወጣ መስቀሉንም በአዩ ጊዜ ወደኋላቸው ተመልሰው ሸሹ በማንም ላይ ከቶ ጉዳት አላደረሱም። ደግሞ በትምርቱ ከአገሩና ከመንጋው ውስጥ ክህደትንና ኑፋቄን አስወገደ በዚያን ጊዜ ስለእኛ መከራ የተቀበለው ትብስእት ብቻውን ነው አምላክ አይደለም የሚሉ ነበሩና። ❤ ይህም አባት ስንትዩ በከበረ በታላቁ ጾም ወራት መልክትን ጽፎ ለአገሩ ሁሉ ላከ በውስጥዋም እንዲህ የሚል እያስተማረ "ስለእኛ መከራ የተቀበለ እግዚአብሔር ቃል በሥጋ ነው ከተዋሕዶ በፊት ሁለት የነበሩ በተዋሕዶ አንድ ባሕርይ ስለሆነ አንዲት ሰዓት ወይም የዐይን ጥቅሻ ያህል ከቶ አልተለያዩም በመከራ ጊዜ ወይም በሞት ከመለኮቱ ያልተለየ እርሱ አካላዊ ቃል በሥጋው ስለ እኛ መከራን ተቀበለ"። ይቺም መልእክት በአገሩ ሁሉ በአነበቡአት ጊዜ የክርስቲያን ወገኖች ታላቅ ደስታ ደስ አላቸው እሊያ የሳቱትም ተመልሰው ንስሓ ገቡ። ሁለኛም ደግሞ ምላሳቸውን መቆረጥ የሚገባቸው የተሳሳቱ የመለኮት ባሕርይ ሞተች የሚሉ ሰዎች ተገለጡ እሊህም የብልንያ አገር ሰዎችና ኤጲስቆጶሳቸውም ነው። ❤ ይህም አባት ይህን የእብደትና የስንፍና ነገር በሰማ ጊዜ እጅግ አዝኖ መልእክትን በውስጡ እንዲህ ጻፈ "እግዚአብሔር ባሕርዩ አትመረመርም የማትዳሠሥ የማትታመም ናት እግዚአብሔር ቃል ከእኛ ነሥቶ ያለ መለያየትና ያለ መቀላቀል ከመለኮቱ አዋሐደው ከሰውነቱ ባህርይ በቀር ሕማምን አታስገባም" ሁለተኛም በውስጥዋ እንዲህ አለ "እኛ መከራ ከሚቀበል ከሥጋው እግዚአብሔር ቃልን አንለየውም በመከራውም በሥራው ሁሉ አንድ እንደሆነ እናምናለን እንጂ ሁለተኛም መለኮቱ በባሕርዩ የማይታመም የማይሞት እንደሆነ ከመለኮት ሳይለይ ስለእኛ መከራ ተቀብሎ ሞተ እንጂ"። የመልእክቱም ደብዳቤዎች ወደእነዚህ ሰዎች ደርሰው በአነበቡአቸው ጊዜ ከስሕተታቸው ተመልሰው በእውተኛዪቱ በቀናች ሃይኖት አመኑ። ኤጲስቆጶሳቸውም ጋራ ወደዚህ አባት ወደ ሊቀ ጳጳሳት ስንትዩ ፊት ቀርበው የቀናውን እምነት ተቀብለው አመኑ ታላቅ ስሕተታቸውንና በደላቸውንም ይተውላቸው ዘንድ ለመኑት እርሱም ስሕተታቸውን እያመኑ በኤጲስቆጶሳቱ ሁሉ በካህናቱ በሕዝቡም ፊት እንዲሰግዱ አዘዛቸው እንዳዘዛቸው አደረጉ በደላቸውንም ተወላቸው። ❤ ይህም አባት አብያተ ክርስቲያናትን ስለማነፅ የስደተኞችንም ቦታዎች ስለማዘጋጀት ብዙ የሚአስብ ነው ከዚህ የሚተርፈውንም ለድኆችና ለምስኪኖች ይሰጣል። መልካም ጉዞንም በመጓዝ እግዚአብሔርን አገለገለው ሚያዝያ24 በሰላምም ዐረፈ። የሹመቱም ዘመን ዐሥራ አምስት ዓመት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ በአባት ስንትዩ ጸሎት ለዘላለሙ ይማረን አሜን። ምንጭ፦ የሚያዝያ 24 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወወሀብኮሙ ትእምርተ ለእለ ይፈርሁከ። ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት። ወይድኀኑ ፍቁራኒከ"። መዝ 59፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 12፥1-12፣ 2ኛ ጴጥ 3፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥27-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 21፥28-33። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዲዮስቆሮስ ወይም የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የበዓለ ሃምሳ ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን @eotcw

Repost from ያሬዳውያን
🌺መዝሙር ዘኒቆዲሞስ🌺 (በ፭/ር) ሖረ ኀቤሁ ዘስሙ ኒቆዲሞስ ወይቤሎ ለኢየሱስ ረቢ ሊቅ ንሕነ ነአምን ብከ ከመ እምኀበ አብ መጻእከ ከመ ትኩን መምህረ እጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ አንሥአኒ በትንሣኤከ። ትርጉም፦ ስሙ ኒቆዲሞስ የሚባል ሰው ወደኢየሱስ ሄዶ መምህር ታላቅ መምህር ሆነህ ታስተምረን ዘንድ ከአብ ዘንድ እንደመጣህ እኛ እናምንብሃለን አንተ የአንበሳ ደቦል ክርስቶስ ሸምቀህ ትነሣለህ (ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሠ መቃብር አድረህ ትነሣለህ) በትንሣኤህ አንሣኝ። የዕለቱ ምንባባት፦ #ሮሜ ፯፥፩ - ፲፪፤ #፩ዮሐ ፬፥፲፰ - ፍ፤ #ግብ ፭፥፴፬ - ፍ፤ የዕለቱ ወንጌል፦ ዮሐ ፫፥፩ - ፲፪ ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ ማርያም፤ የዕለቱ ምስባክ፦ ሐወፅከኒ ሌሊተ ወፈተንኮ ለልብየ፤ አመከርከኒ ወኢተረክበ ዓመፃ በላዕሌየ፤ ከመ ኢይንብብ አፉየ ግብረ እጓለ እመሕያው። መዝ ፲፮፥፫ ትርጉም፦ በሌሊት ጎበኘኸኝ ልቤንም ፈተንኸው፤ ፈተንኸኝ ዓመፅ አልተገኘብኝም፤ የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር። ምሥጢር፦ በሌሊት ጠላቴን ከእጄ ላይ ጠለህ ይገድለው ይሆን አይሆን ብለህ መረመርኸኝ። ብትመረምረኝ በእጄ መግደል በቃሌ መበደል በልቡናዬ ቂም በቀል አልተገኘብኝም። ሰው ሰውኛውን ነገር እንዳልናገር። አንድም ግብረ እደ እጓለ እመሕያው ይላል ሰው በቃሉ ፈክሮ ዘምሮ የሚያደርገውን እንዳላደርግ። ጠላትህ ዕገሌን አግኝቸው ነበር አንተ አግኝተኸው ቢሆን ምንታደርገው ነበር? ይለዋል። የመቼውን! የዘነጋሁትን! አግኝቼውማ ቢሆን አብልቼ አጠጥቼ በሰደድሁት ነበር ይለዋል ቢያገኘው ላይተወው። እሱ ግን ከአንድ ሁለት ጊዜ አግኝቶ ትቶታልና።

+ + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ዘሠርዓ ለአብርሃም። ወመሐለ ለይስሐቅ። ወአቀመ ስምዐ ለያዕቆብ"። መዝ 104፥9 ወይም መዝ 16፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ፊል 2፥5-12፣ 1ኛ ጴጥ1-10 እና የሐዋ ሥራ 3፥12-17 እና የሐዋ ሥራ 3፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 27፥62-ፍ.ም ወይም ዮሐ 3፥1-12። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን ለጻድቁ ለታላቁ ንጉሥ የክርስቶስ መስቀል ላገኘችው ለንግሥት ለቅድስት ዕሌኒ ልጅ ለቅዱስ ቈስጠንጢኖስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለአርእስተ አበው ለቅዱሳን ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለበዓላቸው መታሰቢያ በሰላም አደረሰ። + + + ❤ "ሰላም ለቈስጠንጢኖስ ለነገሥት ርእስ፤ ዘከለሎ እምሰማይ ሞገስ፤ እምኵሎሙ ነገሥት ይትሌዓል ቀርኑ፤ ዘከደነ ስፍሐ ዓለም ሃይማኖተ ሥኑ፤ ዘአስተጋብአ ጳጳሳተ ጽድቅ ሃይማኖተ እለ ሠርዑ ወወሰኑ፤ ማዕከለ ሁከቶሙ ለዕልዋን ዘአንሐለ ጥቅመ፤ ኵሎ ዓለም በሃይማኖት ዘከሠተ ጸጋ ብርሃነ ዘኮነ ለኵሉ ዘሥጋ ወቦቱ ተሐደሰ ለመርዓት ሕጋ"። ትርጉም፦ የሙሽሪት (ቤተ ክርስቲያኒቱ) ሕጓ ዐዲስ የኾነበት፤ ለሥጋዊ ለደማዊ ብርሃንን የኾነ የወልድ መስቀሉን በጸጋ የገለጠ፤ ዓለሙን ኸሉ በሃይማኖት የሸለመ (የጠለፈ)፤ የክፉዎችን የሁከት ማዕበል እንደ ግንብ ያፈረሰ፤ ሃይማኖትን የወሰኑና የደነገጉ የእውነት ጳጳሳትን የሰበሰበ፤ የሃይማኖቱ ደም ግባት የዓለምን ስፋት የሸፈነ፤ ከኹሉም ነገሥታት ይልቅ ሥልጣኑ ከፍ ከፍ ያለ፤ ከሰማይ ሞገስ የጋረደው ለኾነ ለነገሥታት አለቃ ለቈስጠንጢኖስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቈስጠንጢኖስ፦ የዚህ ቅዱስ የአባቱ ስም ቊንስጣ የእናቱም ስም ቅድስት ዕሌኒ ነው። ቊንስጣም በራንጥያ ለሚባል አገር ንጉሥ ነው። መክስምያኖስም በሮሜ በአንጾኪያ በግብጽ ላይ ነግሦ ነበር። ❤ ይህም ቊንስጣ አረማዊ ነበር፤ ግን በጎ ሥራ ያለው እውነትን የሚወድ በልቡናውም ይቅርታና ርኅራኄን የተመላ ክፉት የሌለበት ነበር። ወደ ሮሐ ከተማ በሔደ ጊዜ ቅድስት ዕሌኒን አይቶ ሚስት ልትሆነው አገባት እርሷም ክርስቲያናዊት ናት። ንጉሥ ቈስጠንጢኖስንም ፀንሳ ወለደችው ስሙንም ቈስጠንጢኖስ ብላ ጠራችው ይህም ዝንጉርጒር ማለት ነው። ❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ቊንስጣ ዕሌኒን በዚያም ትቷት ወደ በራጥያ ከተማ ተመለሰ። እርሷም ልጇን እያሳደገች በዚያው ኖረች የክርስትናን ትምህርት አስተማረችው ይቅርታንና ርኅራኄን በክርስቲያን ወገኖች ላይ እንዲያደርግ በልቡናው ትዘራበት ነበር። እርሷ ክርስቲያን ስትሆን የክርስትና ጥምቀትን ታጠምቀው ዘንድ አልደፈረችም መንፈሳዊ ዕውቀትን ሁሉ ለማስተማር አሳደገችው ዳግመኛም ለመንግሥት ልጆች የሚገባውንም ሁሉ። ❤ ከዚያም በኋላ ወደ አባቱ ሰደደችው አባቱም በአየው ጊዜ ደስ ተሰኘበት ዕውቀትን የተመላ ሁኖ አግኝቶታልና በበታቹም መስፍን አድርጎ ሹሞ በመንግሥቱ ሥራ ላይ ሁሉ ሥልጣን ሰጠው። ❤ ከሁለት ዓመትም በኋላ አባቱ ዐረፈ ቈስጠንጢኖስም መንግሥቱን ሁሉ ተረከበ የቀና ፍርድንም የሚፈርድ ሆነ ከእርሱ በፊት የነበሩ ነገሥታት የጫኑባቸውን ጽኑ አገዛዝ ከሰዎች ላይ አስወገደ። አሕዛብም ሁሉ ታዘዙለት ወደዱትም የአገዛዙ ቅንነትና የፍርዱ ትክክለኛነት በአገሮች ሁሉ እስቲሰማ ተገዙለት። ❤ የሮሜ ሰዎች ታላላቆች መልክትን ወደርሱ ላኩ ከከሀዲ መክስምያኖስ ጽኑ አገዛዝ እንዲያድናቸው እየለመኑ እርሱ አሠቃይቷቸው ነበርና። መልእክታቸውንም በአነበበ ጊዜ ስለ ደረሰባቸው መከራ እጅግ አዘነ ያድናቸውም ዘንድ ምን እንደሚያደርግ በዐደባባይ ተቀምጦ እያሰበ ሲያዝን እንሆ ከቀኑ በስድስት ሰዓት በቀትር ጊዜ ኅብሩ እንደ ከዋክብት የሆነ መስቀል ታየው በላዩም በዮናኒ ቋንቋ "ኒኮስጣጣን" የሚል ጽሑፍ አለ ትርጓሜውም በዚህ ጠላትህን ድል ታደርጋለህ ማለት ነው። የመስቀሉም ብሔር የፀሐይን ብርሃን ሲሸፍነው በአየ ጊዜ አደነቀ። በላዩ ስለተጻፈውም አስቦ ለጭፍሮቹ አለቆችና ለመንግሥቱ ታላላቅ ባለሥልጣኖች አሳያቸው። እርሱም ቢሆኑ ይህ መስቀል ስለምን እንደተገለጠ አላወቁም። ❤ በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ለቈስጠንጢኖስ በራእይ ተገልጦ እንዲህ አለው "በቀኑ እኩሌታ በቀትር በአየኸው በዚያ መስቀል አምሳል ላንተ ምልክት አድርግ በርሱም ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" አለው። ከእንቅልፉም በነቃ ጊዜ ልቡ ጸና የወርቅ መስቀልም አሠርቶ በነገሠበት ዘውድ ላይ አደረገው መኳንንቱንና ወታደሮቹን ጭፍሮቹን ሁሉ መስቀል ሠርተው በጦር መሣሪያቸው ላይ ያደርጉ ዘንድ አዘዛቸው እርሱም እንዳዘዛቸው አደረጉ። ❤ ይህም የሆነው በበራንጥያ በነገሠ በሰባተኛ ዓመት ነው። የሮሜን ሰዎች ከሥቃያቸው ሊያድናቸው ሥራዊቱን ሰብስቦ ተነሥቶ ወጣ። መክስምያኖስም ሰምቶ በታላቅ ወንዝ ላይም ታላቅ ድልድይ ሠርቶ ወደ ቈስጠንጢኖስም ተሻግሮ ከእርሱ ጋር ተዋጋ። የመስቀሉም ምልክት ቀድሞ በታየ ጊዜ የመክስምያኖስ ሠራዊት ድል ይሆኑ ነበር የቈስጠንጢኖስ ሠራዊት ከመክስምያኖስ ሠራዊት ብዙ ሰው ገደሉ። የቀሩትም ሸሽተው ሲሔዱ ከመክስምያኖስ ጋር ሊሻገሩትና ወደ ወሜ ሊገቡ ድልድይ ላይ ወጡ ድልድዩም ፈርሶ ፈርዖን ከሠራዊቱ ጋራ እንደ ሠጠመ እንዲሁ መክስምያኖስ ከሠራዊቱ ጋራ ሠጠመ። ❤ ቈስጠንጢኖስም ወደ ሮሜ ከተማ ሲገባ የሮሜ ሰዎች ከካህናት ጋራ መብራቶች ይዘው በዕንቊ የተሸለሙ አክሊሎችን ደፍተው እምቢልታ እየነፋ ተቀበሉት የተማሩ ሊቃውንትም የከበረ መስቀልን ሲያመሰግኑት የአገራችን መዳኛ ይሉት ነበር ለከበረ መስቀልም ሰባት ቀን በዓል አደረጉ። ❤ ቈስጠንጢኖስም ዳግመኛ በሮሜ ነገሠ ከሀዲዎች የሆኑ መክስምያኖስና ዲዮቅልጥያኖስ ስለ ክብር ባለቤት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ያሠሩሯቸውን እሥረኞች ሁሉንም ፈታቸው ደግሞ የጣዖታት ቤቶች ይዘጉ አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ ብሎ ዓዋጅ አስነገረ። ዳግመኛም ክርስቲያኖችን እንዲያከብሯቸው እንዲ እንዳያዋርዷቸው የጣዖታቱንም ገንዘብና ምድራቸውን በአረማውያን ላይ እንዲሾሙ አደረገ። ዳግመኛም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዘዙ ማንም ሰው በሰሙነ ሕማማት ሥራ እንዳይሠራ አዘዘ። ❤ በነገሠ በዐሥራ አንድ ዓመት በሮሜ ሊቀ ጳጳሳት በሶል ጴጥሮስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ። ሠራዊቱም ሁሉ ይህም የከበረ መስቀል ከተገለጠለት በኋላ በአራት ዓመት ነው። ❤ ከዚህ በኋላም በእርሱ ርዳታና ድል ያገኘበትን የሚያድን ስለ ሆነ ስለ ጌታችን መስቀል ትመረም ዘንድ እናቱ ቅድስት ዕሌኒን ወደ ኢየሩሳሌም ላካት። እርሷም ዓመፀኞች አይሁድ ቀብረው ከደፈኑት ቦታ አወጣችው። ❤ በዘመኑ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት ጳጳሳት የአንድነት ስብሰባ በኒቅያ ስለ አርዮስ ተደረገ። ለክርስቲያኖች መመሪያ በበጎ አሠራር ክርስቲያናዊት ሥርዓት ተሠራች። ❤ ከዚህም በኋላ በበራንጥያ ታላቅ ከተማ ሊሠራ አሰበ እንደ አሰበውም ታላቅ ከተማ ሠርቶ በስሙ ቊስጥንጥንያ ብሎ ጠራት። በውስጧም አምላክን በወለደች በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በአግያና በሶፍያም ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሠራ መንፈሳዊ በሆነ በመልካም ጌጥ ሁሉ አስጌጣት በውስጥዋ ከሐዋርያት የብዙዎቹን ዓፅም ከሰማዕታትና ከቅዱሳን ጻድቃን ሥጋቸውን ስለሚሰበስብ። ❤ የክብር ባለቤት ጌታችንን ደስ አሰኝቶ መልካም ተጋድሎውን ከፈጸመ በኋላ በኒቆምድያ ከተማ ጥቂት ታሞ መጋቢት28 ዐረፈ።ገንዘውም በወርቅ ሣጥን አድርገው ተሸክመው ወደ ከቊስጥንጥንያ አደረሱት የጳጳሳት አለቆችና ካህናቱ ከሁሉ ሕዝብ ጋር ወጥተው ተቀበሉት በብዙ ጸሎት በመዘመርና በማኅሌት በምስጋና ወደ ከበሩ ሐዋርያት ቤተ መቅደስ አስገብተው በክብር አኖሩት። የቅዱስ ቈስጠንጢኖስም በረከቱ ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት28 ስንክሳር።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለአባ መቃሪ ዘእግዚአብሔር ነባሪ፤ መምህረ ሕግ ምስለ መላእክት ዘውግ"። ትርጉም፦ ከመላእክት ጋር የሚወጋገን የሕግ መምህር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለኾነ ለአባ መቃሪ ሰላምታ ይገባል። https://t.me/eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለአባ መቃሪ ዘእግዚአብሔር ነባሪ፤ መምህረ ሕግ ምስለ መላእክት ዘውግ"። ትርጉም፦ ከመላእክት ጋር የሚወጋገን የሕግ መምህር፤ የእግዚአብሔር አገልጋይ ለኾነ ለአባ መቃሪ ሰላምታ ይገባል።

photo content
+1

❤ ነፍሱ ወደ ሰማይ መላእክት ሲያሳርጓት ሰይጣናት እየተከተሉ "መቃሪ ሆይ አሸነፍከን አሸነፍከን" እያሉ ሲጮኹ አባ መቃርስ "እስከ ዛሬ ገና ነኝ በጌታዬ በቀኙ ልቁም በግራው አላወኩምና" ብሎ በትሕትና መለሰላቸው፡፡ ወደ ገነትም ሲገባ "መቃሪ ሆይ አሸነፍከን ብለው በታላቅ ድምፅ ጮኹ" እርሱም "የክብር ባለቤት ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመስገን ስሙም ይባረክ ከእጃችሁ ያዳነኝ" አላቸው ፡፡ ከአባታችን ከአባ መቃርስ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን፡፡ በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፡- የመጋቢት27 ስንክሳር እና ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ። + + + ❤ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና፦ ሀገራቸው ጣና ዘጌ ነው። በዋሻ ውስጥ አርባ ዘመን ሙሉ ዘግተው ሲኖሩ መና ከሰማይ እየወረደላቸው ውሃም በዋሻ ውስጥ ፈልቆላቸው ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን መልአክ መጥቶ ምን ቢጋደሉ የጌታችንን ስጋውን በልተው ደሙን ካልጠጡ እንደማይድኑ ነገራቸው። በመልአኩም ትዕዛዝ መሰረት ከዋሻው ወጥተው ሊቆርቡ ቤተ ክርስቲያን ገቡ በቅዳሴም ላይ ሳሉ አንድ ድንቅ ምስጢር ተመለከቱ ይህም በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ካህኑ "ሀበነ" ሲል ጌታችን በዕለተ አርብ እንተ ተሰቀለ ሆኖ ደሙ ሲፈስ የካህኑ እጅ በደም ተነክሮ በመንበሩ ቆሞ ቢያዩት በድንጋጤ ሳይቀሳቀሱ አርባ ዓመት ተኝተዋል ይህም በሰው አቆጣጠር በጌታችን ዘንድ ግን ምን ያይህል ጊዜ እንደ ሆነ እራሱ ባለቤቱ ያውቀዋል። በመጨረሻም ጻድቁ በዐረፉ ጊዜ መቃብራቸውን አራዊት ቆፍረውላቸው መነኮሳቱ ገንዘው ቀብረዋቸዋል። ታቦታቸው በጣና ይገኝል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት። + + + ❤ "ሰላም ለመቃርዮስ ዘዐቢይ ዝክሩ። እስመ ዐቀበ መርዔቶ ለእንጦንዮስ በበትሩ። እምነ ፩ዱ ፩ዱ እንበለ ያሕጽሩ። ሶበ ዕሩየ ደቂቁ ምግባራተ ጽድቅ ገብሩ። መዳልወ አልባብ ተሰምየት እስከ ዮም ደብሩ። ትርጉም፦ የእንጦንዮስ መንጐች በበትሩ ጠብቋልና መታሰቢያው ታላቅ ለኾነ ለመቃርዮስ ሰላምታ ይገባል፤ አንዱ ከአንዱ ሳያጐድሉ ልጆቹ ተካክለው የጽድቅ ሥራዎችን ሠሩ ጊዜ ደብሩ እስከ ዛሬ ድረስ የልቡናዎች ሚዛን በመባል ተጠራች። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 27። https://t.me/eotcw

ያስተምረኝና ይመራኝ ዘንድ ተነሥቼ ወደርሱ ልሂድ የረከሱ ሰይጣናት የመከሩትን ምክራቸውን እገለብጥ ዘንድ እርሱ ዕውቀትንና ማስተዋልን ይሰጠኛልና" አለ ፡፡ ❤ ቅዱስ መቃርዮስም ተነስቶ ከጸለየ በኋላ ወደ ቅዱስ እንጦንዮስ ጉዞ ጀመረ ከቅዱሱ አረጋዊ ከእንጦንስ ጋር በተገናኘ ጊዜ በታላቅ ፍሰሐ ተቀበለው፡፡ ቅዱስ መቃርስ ልጅ በአባቱ ፊት እንደሚሆን ሀሳቡን ሁሉ ገለጠለት፤ ምንም ነገር አልደበቀውም፡፡ ቅዱስ እንጦንዮስም የቅዱስ መቃርስን ራሱን ሳመው፤ እንዲህም አለው "ልጄ መቃርስ ሆይ እንደ ስምህ ትርጓሜ ብፁዕ ትባል ዘንድ አለህ፤ እግዚአብሔር አምላኬ የአንተን ግብር ከብዙ ዘመን አስቀድሞ ገልጦልኛልና ወደ እኔ እንደምትመጣ ነግሮኝ ነበር፡፡ ስለዚህም ወደ እኔ መምጣትህን ስጠብቅ ኖርሁ፤ ስለ ደህንነትህም የማስብ ሆንሁ" አለው፡፡ ቅዱስ አረጋዊ እንጦንስ በብዙ ነገር እየተናገረ ለምንኩስና ግብር እንደሚገባ መከረው አጽናናው፤ የሰይጣናትን ጾርም እንዴት እንደ ሆነ ገልጦ አስረዳው፤ እርሱ በክፉ ህሊና በስውርና በገሃድ እስከ ሞት ድረስ አጽንተው እንደሚዋጉት ነገረው፡፡ "ቢታገሉህም እስከ ሞት ድረስ ፈጽሞ የምትታገስ ሁን" አለው፡፡ ቅዱስ መቃርስ ከእርሱ ጋር ይኖር ዘንድ ለመነው እርሱ ግን አልፈቀደለትም፤ እንዲህ አለው "ከእኛ እያንዳንዱ እግዚአብሔር በወሰነለት ቦታ በትዕግሥትና በአርምሞ ይኑር" አለው፡፡ ቅዱስ መቃርስ እንጦንስ በነበረበት ጊዜ የምንኩስናን የአኗኗር ሥርዓት ተማረ፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡ ለአባ ሰራጰዮን እንዲህ አለው "በቅዱስ እንጦንስ ዘንድ በነበርኩበት ጊዜ ሁሉ ሌሊት ፈጽሞ ተኝቶ አይቼው አላውቅም ትዕግሥቱና ገድሉ ሁሉ የሚደንቅ ነበር" አለው፡፡ አባ መቃርስም በምንኩስና ሥርዓት ተጠምዶ እየተጋደለ ብዙ ቀን ኖረ ያ ኪሩብም በግልጽ ይጎበኘው ነበር። ❤ ቅዱስ መቃርስ በሌሊትም በጸሎት ጊዜ ቁሞ ሳለ ጌታችን ጆሮውን ከፍቶለት ሰይጣናትን ሲማከሩ ሰማቸው እንዲህም አሉ "ይህን ሰው በዚህ በረሀ እንዲኖር ብንተወው የብዙ ብዙ ወገኖችን ይመራቸዋል፡፡ እነርሱም በዚህ በረሀ ውስጥ ነዋሪዎች ሆነው የሰማያውያን አገር ያደርጉታል፡፡ እነርሱ ለዘለዓለም ጸንቶ በሚኖር ሕይወት ይተማመናሉና፡፡እኛንም በሚቀጣ ጸሎታቸው ቀጥተው አሰቃይተው ያሳድዱናልና ከዚህ ቦታ ልናሳድደው እስኪ እንችል እንደሆነ ኑ ዛሬ በእርሱ ላይ እንሰብሰብ” ሲሉ ሰማቸው፡፡ አባ መቃርስም ይህን በሰማ ጊዜ ልቡ ጸና በሰይጣናት ላይም ተበረታታ የሰይጣናት ምክራቸውን እስከሚሰማ ጆሮውን የከፈተለት እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ድካማቸውንም አወቀ፡፡ ❤ ከዚህ በኋላ ይዋጉት ዘንድ ሰይጣናት በእርሱ ላይ ተሰበሰቡ በደጁም እሳትን እያነደዱ ከእሳቱ እያነሱ ወደ በዓቱ ይጨምሩ ጀመር፡፡ ያቺ እሳት ግን በጸሎቱ የምትጠፋ ሆነች፡፡ እንስሳዊ በሆነ ሥራ በፈቲው ጦር ተዋጉት በዚህም ታገሰ፡፡ ትካዜን፣ ዓለማዊ ክብር መውደድን፣ ትዕቢትን፣ መመካትን፣ ታካችነትን፣ ስድብን፣ ሃይማኖት ማጣትን፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተስፋ መቁረጥን በልቡ አሳደሩበት፡፡ ከዚህም ሁሉ በሚበዛ ተዋጉት የከበረ አባ እንጦንዮስ እንደነገረው ከሰይጣናቱ ፈተና በኋላ ዳግመኛ ወደ አባት እንጦንዮስ ተነሥቶ ሄደ ፡፡ ❤ ወደ ቅዱስ አባት በቀረበ ጊዜ በምድር ላይ ሰገደለት በፍጥነትም ቀና አድርጎ ሳመው ፊቱ እንደ በሽተኛ ፊት ተለውጦ አይቶታልና ይኸውም ሰይጣናት አብዝተው ስለተዋጉት ነው፡፡ ከዚያም ጸሎት አድርገው በአንድነት ተቀመጡ አባት እንጦንዮስ ደስታ በተመላ ቃል "ልጄ መቃርስ በደኀና አለህን" አለው ቅዱስ መቃሪስ "እነሆ ከእኔ የሆነውን ሁሉ እግዚአብሔር ቀድሞ ገልጦለሃል" ብሎ መለሰለት፡፡ እርሱም ያን ጊዜ አስተማረው አጽናናውም እንዲህም ብሎ መከረው "መንፈሳዊ ጥበብን ለሚሹ ለብዙ ወገኖች መምህራን እንድንሆን ይቺውም ምንኩስና ናት ከጠላታችን በላያችን የሚመጣብንን መከራ ሁሉ ልንታገስ ለእኛ የሚገባ ነው ልጄ መቃርስ ሆይ ውሀ ለመቅዳት ስትሄድ እግዚአብሔር የነገረህን ያንን አስብ" አለው ፡፡ ❤ ቅዱስ መቃርስም ሰምቶ እጅግ አደነቀ፡፡ የተሰወሩ ሥራዎቹ ለከበረ አባት ለእንጦንዮስ የተገለጡለት እንደሆኑ አወቀ፡፡ በእርሱ ዘንድም እየተማረና በረከትንም እየተቀበለ ብዙ ቀኖች ኖረ፡፡ ከዚያም የከበረች አስኬማን ያለብሰው ዘንድ ፈለገ አባ እንጦንዮስም በላዩ ጸለየ እርሷን አስኬማይቱን አለበሰው በትሩን ሰጠውና ዐረፈ ስለዚህም የከበረ እንጦንዮስ አባት ተባለ፡፡ ❤ የከበረ አባ መቃርስም ወደ ቦታው ተመልሶ በአስቄጥስ ገዳም ተቀመጠ ዜናውም በአራቱ ማእዘን ተሰማ እግዚአብሔርም በእጆቹ አስደናቂዎች ተአምራትን አደረገ ከተአምራቱ አንዱ ይህ ነው፡፡ በአገረ አውሲም ትንሣኤ ሙታንን አላምንም የሚል ባሕታዊ ተነስቶ ነበርና አባ መቃርስ ሄዶ ቢያስተምረው "የሞተ ሰው ከመቃብር ካላስነሳህ እኔ አላምንም" ብሎ መለሰለት፤ ያን ጊዜ አባ መቃርስ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸልዮ አንድ ሙት አስነሥቷል፤ በዚህ ጊዜ ያ የሳተው ባሕታዊና ያሳታቸው ሁሉ ተመልሰዋል፡፡ ያን ከሞት ያነሣውን ሰው የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ ልብሰ ምንኩስናን ካለበሰው በኋላ ሰባት ዓመት ኑሮ ተመልሶ አርፏል፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ የከበረ አባ መቃርስ ተመልሶ ከእርሱ አስቀድሞ በዚያ በረሀ ውስጥ ሰው እንዳለ ያይ ዘንድ ወደ በረሀው ውስጥ ዘልቆ ገባ ዕራቁታቸውን የሆኑ ሁለት ሰዎችን አይቶ ፈራ የሰይጣን ምትኃት መስሎታልና "እልቦት ቦሪቦን" ብሎ ጸለየ ይህም "አቡነ ዘበሰማያት" ማለት ነው እነርሱም "በስሙ ጠርተው መቃሪ ሆይ አትፍራ" አሉት እርሱም በበረሀ የሚኖሩ ቅዱሳን እንደሆኑ አውቆ ወደ እርሳቸው ቀርቦ እጅ ነሳቸው፡፡ እነርሱም በዓለም ስላሉ ሰዎች ስለ ሥራቸውም ጠየቁት እርሱም "በቸርነቱ እግዚአብሔር በሁሉም ላይ አለ" ብሎ መለሰላቸው፡፡ እርሱም ደግሞ "የክረምት ቅዝቃዜ ይቀዘቅዛቸው እንደሆነ የበጋውም ትኩሳት ያላልባቸው እንደሆነ" ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም "በዚህ በረሀ እግዚአብሔር አርባ ዓመት ጠብቆናል የክረምት ቅዝቃዜ ሳይቀዘቅዘን የበጋ ትኩሳት ሳያላልበን ኖርን" ብለው መለሱለት ደግሞ "እንደ እናንተ መሆን እንዴት እችላለሁ" አላቸው፡፡ እነርሱም "ወደ በዓትህ ተመልሰህ ስለ ኃጢአትህ አልቅስ አንተም እንደእኛ ትሆናለህ" አሉት ፡፡ ከእነርሱም በረከትን ተቀብሎ ወደቦታው ተመለሰ፡፡ ❤ ወደ አስቄጥስ ገዳም ተመለሰ ከእርሱ ዘንድ መነኰሳት በበዙ ጊዜ ጉድጓድ ቆፍረው መታጠቢያ ሰሩለት፡፡ ሊታጠብ በወረደ ጊዜ ሊገድሉት ሰይጣናት በላዩ አፈረሱበት፡፡ መነኰሳቱም መጥተው አወጡት፡፡ በመጨረሻም እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም መከራ ሊያሳርፈው በወደደ ጊዜ ሁልጊዜ የሚጎበኘውን ኪሩብን ወደእርሱ ላለ፡፡ አርሱም "እኔ ወደ አንተ መጥቼ እወስድሀለሁና ተዘጋጅ” አለው፡፡ ከዚያ በኋላ አባ እንጦንስና የቅዱሳንን አንድነት ማኀበር ሰማያውያን የሆኑ የመላእክትም ሠራዊት ተገለጡለትና በመዓዛ ገነት በይባቤ መላአክት ነፍሱን መጋቢት 27 ቀን 397ዓ.ም በ97 ዓመቱ በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ፡፡

እነርሱም በሕይወታቸው ፍጹም ሰማያውያን መላእክትን ይመስላሉ" አለው፡፡ ❤ አረጋዊው ካህን አብርሃም ከራዕዩ በነቃ ጊዜ ሚስቱ ሣራ እርሱን እያስታመመች አብራው ነበረችና ያየውን ነገር ሁሉ ነገራት፡፡ በነጋም ጊዜ ከበሽታው ድኖ ወደ ቤታቸው በደስታ ተመለሱ፡፡ ከዚያም በኋላ መልአኩ እንደተናገረው ሣራ ፀነሰች፡፡ መቃርዮስ በግብጽ ሃገር መኑፍ በሚባል አውራጃ ጁቢር በሚባል ቦታ በ300 ዓ.ም ተወለደ፤ የስሙ ትርጓሜም ብፁዕ ማለት ነው፡፡ እርሱም በእግዚአብሔር ጸጋ የተሞላና የተወደደ ልጅ ሆነ፡፡ ❤ መቃርዮስም ባደገ ጊዜ የእግዚአብሔር ጸጋ ስላደረበት ለወላጆቹ ይታዘዝና ያገለግል፣ በወላጆቹ ትዕዛዝ ምጽዋትንም በየቀኑ ይመጸውት ስለነበር በጣም ይደሰቱ ነበር፡፡ ወላጆቹን በሁሉም ነገር እያገዛቸው በማንኛውም መንገድ እግዚአብሔርን ያገለግል ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታ በጥሩ ሥነ ምግባር ቀስ በቀስ እያደገና እየጠነከረ በመምጣት ወላጆቹን ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ይንከባከባቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔርም አብዝቶ ባረካቸው፤ ከብቶቻቸውና እርሻቸው በሚያስደንቅ ሁኔታ እየበዛ ቤታቸው በተትረፈረፈ ሀብት ተሞላ፡፡ ❤ ወጣቱ መቃርዮስ በመንፈሳዊ ሕይወቱ አርአያ በመሆን በሰዎች ዘንድ በጣም የሚወደድ ሆነ፡፡ የእግዚአብሔር ጸጋ በላዩ እንዳለበት በግልጽ እስኪታወቅ ድረስ ፊቱ ያበራ ነበር፡፡ የአገሩ ካህናት ይህን በተመለከቱ ጊዜ ወደ ጳጳሱ ወሰዱትና አናጉንስጢስ እንዲሆን አደረጉት፡፡ እናትና አባቱ ግን በዚህ ደስተኛ አልነበሩም ነገር ግን "የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" አሉ እድሜው ከፍ አያለ ሲመጣ እናትና አባቱ ሊያጋቡትም አሰቡ እርሱ ግን አይሻም ነበር፡፡ ፈቃዳቸውን ይፈጽም ዘንድ ግድ ብለው አጋቡት፡፡ ወደ ሙሽራይቱም በገባ ጊዜ ራሱን እንደታመመ ሰው አደረገ እንዲህም ሁኖ ብዙ ቀን ኖረ፡፡ አባቱን "ተወኝ ወደ ገዳም ልሒድ ከበሽታዬ ጥቂት ጤና ባገኝ" አለው፡፡ እግዚአብሔር ወደ ሚወደው ሥራ ይመራው ዘንድ ሁል ጊዜ በጾምና በጸሎት ሁኖ ይለምነው ነበር፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ በረሀ ሄደ፡፡ ከበረሀውም በገባ ጊዜ ራእይን አየ፡፡ ስድስት ክንፍ ያለው ኪሩብ እጅና እግሩን ይዞ ወደ ተራራ ላይ እንደሚያወጣውና የአስቄጥንስን በረሀ ምሥራቋን ምዕራቧን የዚያችን በረሀ አራት ማዕዘንዋን አሳይቶ "እነሆ ይቺን በረሀ መላዋን ላንተና ለልጆችህ ርስት አድርጎ እግዚአብሔር ሰጥቶሃል" አለው፡፡ ከሦስት ቀን በኋላ መቃርዮስ ባየው ራእይ እየተገረመ ከአስቄጥስ በረሃ ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ያቺ ሚስት ትሆነው ዘንድ ብለው ያመጡለት ብላቴና በጽኑ ታማ አገኛት፡፡ ጥቂት ቆይታም ወዲያው በድንግልናዋ እንዳለች በሰላም ዐረፈች፡፡ የክብር ባለቤት እግዚአብሔርንም አመሰገነው፡፡ እርሱም "መቃርዮስ ሆይ ከእንግዲህ ወዲህ ለነፍስህ ድኀነት በሚሆን ትጋት በመትጋት መንፈሳዊ ፍሬን ለማፍራት ታጠቅ አንተም እንዲህ ትወሰዳለህና" እያለ ራሱን ይገስጽ ጀመር፡፡ ❤ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እናት አባቱ ዐረፉ፡፡ የተውለትንም ገንዘብ በሙሉ ለድሆችና ለጦም አዳሪዎች ሰጠ፡፡ የሳሱይር ሰዎች ግን ዕውነተኛነቱንና ቅድስናውን አይተው ቅስና አሾሙት፡፡ ከከተማውም ውጭ ቤት ሰሩለት፡፡ ሥጋውንና ደሙን ይቀበሉ ዘንድ ወደርሱ ይሄዱ ነበር ፡፡ በዚያች አገርም አንዲት ድንግል ብላቴና ነበረች፡፡ ከአንድ ጐልማሳ ጋርም አመንዝራ ፀነሰች፡፡ ጐልማሳውም "አባትሽ ድንግልናሽን ማን አጠፋው ብሎ ሲጠይቅሽ መቃርስ የሚባለው ባሕታዊ ቄስ እርሱ ስለ ደፈረኝ ነው በይው" ብሎ መከራት ጽንሷም በታወቀ ጊዜ አባቷ "ይህን አሳፋሪ ሥራ በአንቺ ላይ የሰራብሽ ማነው ብሎ ጠየቃት" እርሷም "በአንዲት ቀን መቃርስ ወደሚባለው ቄስ ሄጄ ሳለሁ በኃይል ይዞኝ ከእኔ ጋር ተኛ ስለዚህ ከእርሱ ፀነስኩ" ብላ መለሰችለት፡፡ ወላጆቿና ቤተሰቦቿም በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቆጡ ከብዙ ሰዎችም ጋራ ወደ ቅዱስ መቃርስ ሄደው ይዘው ከበዓቱ አወጡት እርሱ ግን ምን እንደሆነ አላወቀም ለመሞት እስኪቃረብም አጽንተው ደበደቡት እርሱም "ኃጢአቴ ምንድናት እናንተ ያለ ርኀራሄ ትደበድቡኛላችሁና" እያለ ይጠይቃቸው ነበር ፡፡ ከዚህ በኋላ በፍሕም የጠቆሩ ገሎችን በአንገቱ ላይ በገመድ አንጠልጥለው ወዲያና ወዲህ እየጎተቱ የልጃችንን ድንግልና ያጠፋ ይህ ነው እያሉ እንደ እብድ በላዩ ይጮኩ ጀመር፡፡ ❤ በዚያን ጊዜ መላእክት ከሩቅ አገር መጡና በሚታወቁ ደጋግ ምዕመናን ሰዎች አንጻር ተገልጠው እነዚያ ክፉ ሰዎች ከሚያደርሱበት ድብደባና ነቀፋ የተነሣ ሊሞት እንደቀረበ ባዩት ጊዜ የሚያሰቃዩትን ሰዎች "ይህ ተጋዳይ ምን አደረገ" አሏቸው፡፡ እነርሱም በልጃቸው ላይ የኃፍረትን ሥራ እንደ ሰራ አድርገው መልሰው ነገሩአቸው ፡፡ እነዚያ መላእክትም "ይህ ነገር ሐሰት ነው እኛ ይህን ሰው ከታናሽነቱ ጀምሮ እስከዚች ቀን እናውቀዋለን እርሱ የተመረጠ ጻድቅ ሰው ነውና" አሏቸው፡፡ የታሰረበትን ፈትተው ከላዩ ገሎችን ጣሉ፤ ከድካሙም አበረቱት፡፡ የልጅቷ አባት ግን "ፈጽሞ አይሆንም፤ እስክትወልድ ድረስ ቀለቧን እንደሚችልና ከወለደች በኋላም ለልጁ ማሳደጊያ ገንዘብ እንደሚሰጥ ዋስ ካላቀረበ በስተቀር አንለቀውም" አለ፡፡ እጅ ሥራውን የሚሸጥለት አንድ ሰው መጣ ለልጅቷም በየጊዜው ምግቧን ሊሰጣት ዋስ ሆነው ከዚያ በኋላ አሰናብተው ወደ በዓቱ ተመልሶ ገባ ከዚያች ቀን ጀምሮ ራሱን ለራሱ "መቃርስ ሆይ እነሆ እንግዲህ ባለ ሚስትና ባል ልጅ ሆነሃልና ሌሊትና ቀን መሥራት ይገባሃ" እያለ ያቺ ሴት ሴት ልጅ የምትወልድበት ጊዜ እስኪደርስ ድረስ ቅርጫቶችን እየሠራ ለዚያ ወዳጅ ለሆነውና ለሚገለግለው ወንድም ይሰጠውና ያም ሰው ለዚያች ሐሰተኛ ልጅ እየሰጠ ኖረ፡፡ ❤ ያቺ ሴት ልጅ የምትወልድበትም ቀን ሲደርስ እጅግ አስጨነቃት በታላቅ ስቃይም ውስጥ አራት ቀኖች፣ ያህል ኖረች ለሞትም ተቃረበች እናቷም "ከአንቺ የሆነው ምንድነው የተሠራ ሥራ አለና ንገሪኝ" አለቻት፡፡ እርሷም "በእግዚአብሔር አገልጋይ ላይ ዋሽቻለሁና ያመነዘርኩት ከዕገሌ ጐልማሳ ጋር ሲሆን በእውነት ሞት ይገባኛል" አለቻት ፡፡ አባትና እናቷም በሰሙ ጊዜ ደንግጠው እጅግ አዘኑ የአገሩ ሰዎችም ሁሉም ተሰበሰቡ በእርሱ ላይ የሠሩትን በደል ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ ቅዱስ መቃርስ ሄደው ለመኑት ያን ጊዜ በበረሃ ያየውን ራእይ አስታወሰ ይቅር አላቸው ቀድሶም ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ክንፉ ስድስት የሆነ ኪሩብ ደግሞ ተገለጠለት ትርጓሜው የልብ ሚዛን ወደተባለ ወደ አስቄጥስ ገዳም እጁን ይዞ መርቶ አደረሰው ቅዱስ መቃርስ ያንን ኪሩብ "ጌታዬ ሆይ በውስጡ የምኖርበትን ቦታ ወስንልኝ" አለው፡፡ ያ ኪሩብም "አልወስንልህም የእግዚአብሔርንም ትእዛዝ አትተላለፍ እነሆ ይህ ገዳም ሁለመናው ላንተ ተሰጥቷልና ወደ ፈለግህበት ሂደህ ተቀመጥ" ብሎ መለሰለት፡፡ ቅዱስ መቃርስም የቅዱሳን ሮማውያን ወንድማማቾዎችና የመኪሲሞስና የዱማቴዎስ ቦታ ወደ ሆነው ከውስጠኛው በረሀ ገብቶ ኖረ፡፡ እነርሱ ወደ እርሱ በመጡ ጊዜ ከእርሱ አቅራቢያ ኑረዋልና ከዕረፍታቸው በኋላ ግን ሂዶ በዚያ ቦታ እንዲኖር የእግዚአብሔር መልአክ አዘዘው፡፡ የከበረ አባት መቃርስም ታናሽ በዓት ሠራ፡፡ በውስጥዋም ሆኖ ያለማቋረጥ በጾም በጸሎት በስግደትም በመትጋት ታላቅ ተጋድሎን ተጋደለ፡፡ ሰይጣናትም ተገልጠው የሚመጡበትና በቀንም በሌሊትም በግላጭ የሚዋጉት ሆኑ በጾምና በጸሎት ሲጋደል ሰይጣናት እየተዋጉት ዕረፈትን ስለ አላገኘ ከሶስት ዓመት በኋላ በልቡ አሰበ "በአለም ውስጥ ሳለሁ የቅዱስ አባ እንጦንዮስን ዜና ሰምቻለሁ የምንኩስናን ሥርዓት

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለቅዱስ ዐፄ ገላውዴዎስ አንገቱን በመሰየፍስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ በገዳም ለሚፈጸም ተጋድሎ ፋና ለሆነ ለአስቄጥስ ገዳም ለሚኖሩ መነኰሳት ሁሉ አባት ለሆኑ ለከበሩ አባት ለታላቁ አባ መቃርስ ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለኢዮጵያውያኑ ጻድቃን ማኅሌተ ጽጌን ለደረሱት ለአባ ጽጌ ድንግልና ለአቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና ለመታሰቢያ በዓላቸው በሰላም አደረሰን፡፡ + + + ❤ ንጉሥ ቅዱስ ዐፄ ገላውዴዎስ፦ ይህ ቅዱስ በተግሣጽ በምክር በፈሪሀ እግዚአብሔር አደገ አባቱ ንጉሥ ልብነ ድንግል ሃይማኖቱ የቀና ነበርና በዘመኑም የእስላም ወገን የሆነ ስሙ ግራኝ የሚባል ተነሥቶ አብያተ ክርስቲያናትን አጠፋ። ከንጉሥ ልብነ ድንግል ጋር ጦርነት ገጠመ ንጉሡም ወግቶ መመለስ ቢሳነው አርበኞች ሠራዊትን እስከሚሰበስብ ከእርሱ ሸሸ በስደትም እያለ በድንገት ታሞ ሞተ። ❤ ይህም ዐመፀኛ የኢትዮጵያን አገሮች እያጠፋ ዐሥራ አምስት ዓመት ያህል ኖረ። ከኢትዮጵያም ሕዝቦች በመመካትም ማርኮ ከቀናች ሃይማኖት አውጥቶ የእርሱ ሃይማኖት ተከታዮች አደረጋቸው በመመካትም እንዲህ አለ "አገሮችን ሁሉ ግዛቶቼ ስለአደረግኋቸው ከእንግዲህ የሚቃወመኝ የለም"። ❤ ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ይህን ቅዱስ ገላውዴዎስን አስነሣ ከግራኝ ታላላቅ መኳንቶቹ ጋር ጦርነት ገጠማቸው ድልም አድርጎ አሳደዳቸው። ግራኝም በሰማ ጊዜ ተቆጣ ከቱርክ አርበኞች ጋርና ከአእላፍ ፈረሰኞች ጋር መጥቶ ንጉሡም ገጠመው ጌታችንም ግራኝን በንጉሥ ገላውዴዎስ እጅ ጣለው ገደለውም። ግራኝን በመፍራት የተበተኑ ሁሉ ከተማረኩበትም ሁሉ ተመለሱ የፈረሱ አብያተ ክርስቲያናትም ተመልሰው ታነፁ የክቡር ባለቤት የሆነ የክርስቶስ ሃይማኖት ተቃናች። ❤ ከዚህም በኋላ ከእስላሞች ወገን አንዱ ከብዙ አርበኞች ሠራዊት ጋር መጣ በመድኃኒታችን ስቅለት በዓል ከጥቂት ሰዎች ጋራ ተቀምጦ ሳለ በድንገት ንጉሡን ተገናኘው ሰዎቹም "የጦር መኰንኖች እስቲሰበሰቡ ፈቀቅ እንበል" አሉት። እርሱ ግን የክርስቲያኖችን መማረክና የአብያተ ክርስቲያናትን አላይም ብሎ እምቢ" አለ እንዲህም እያለ ወደ ውጊያው መካከል ገብቶ በርትቶ ሲዋጋ የኋላ ኋላ እስላሞች ሁሉም ከበቡት ተረባረቡበት ነፍሱንም በጐራዴም ጨፈጨፋት በብዙ ጦሮችም ወጉት ከፈረሱም ጣሉት የከበረች አንገቱንም ቆረጡት ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት27 ስንክሳር። + + + ❤ ታላቁ መቃርስ፣ መቃርዮስ መቃሪ፣ መቃራ፦ ይህም የከበረ አባት በግብጽ ደቡብ መኑፍ ከሚባል አውራጃ ሳሱይር ከሚባል መንደር ከሚኖሩ ከተወደዱ ደጋግ ክርስቲያኖች የተገኘ ታላቅ አባት ነው፡፡ ወላጆቹ በደጋጎቹ በቀደሙት በአብርሃምና በሣራ ስም የአባቱ ስም አብርሃም የእናቱ ስም ሣራ ተብለው ይጠሩ ነበር፡፡ አባቱም በፈሪሃ እግዚአብሔር ሆኖ ንጽሕናውን ቅድስናውን ጠብቆ ሁል ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን በትጋት በማገልገል ጸንቶ የሚኖር ካህን ነበር፡፡ እናቱም እንደ ኤልሳቤጥና እንደ ሣራ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጸንታ የምትኖር ነበረች፡፡ ❤ እግዚአብሔርም በላያቸው በረከቱን አሳድሮ በሥራቸው ሁሉ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡ እነርሱም ለድሆች የሚመጸውቱ ለሰው ሁሉ የሚራሩ ነበሩ፡፡ የመጀመሪያ ልጃቸው ሴት ነበረች ባደገች ጊዜም እግዚአብሔር ጎበኛትና ዐረፈች፡፡ ይህ ደግ ካህን አብርሃም እግዚአብሔርን የሚወድ ነበር፡፡ ቅድስት የሆነች ሣራ ንጽሕናን የምትወድ ነበረችና ልጃቸው ከሞተች በኋላ ባልና ሚስቱ በመመካከር ተወስነው አልጋ ለይተው በጾም፣ በጸሎት፣ ምጽዋትን በመስጠትና በሽተኞችን በመንከባከብ በታላቅ ትሩፋት መኖር ጀመሩ፡፡ በዚህ የተቀደሰ ሕይወታቸውም ሰው ሁሉ በጣም ይወዳቸው ነበር፡፡ ነገር ግን የመልካም ነገር ጠላት የሆነው ዲያብሎስ በእንዲህ ዓይነት ሕይወት እየኖሩ ማየት አላስቻለውም፡፡ በመሆኑም እንደ ልማዱ በቅናት ተነሣባቸውና የእርሱ ማደሪያ በሆኑ ክፉ ሰዎች አማካኝነት በእነርሱ ላይ ከባድ ፈተና አመጣባቸው፡፡ በመጨረሻም ሀብታቸው ሁሉ ጠፍቶ በድህነት መኖር ጀመሩ፡፡ ቅድስት የሆነች የዚህ የተቀደሰ ካህን አብርሃም ሚስት ሣራ የሆነውን ነገር ሁሉ ባየች ጊዜ በፍርሃት ሆና ነፍሳቸውን ለማዳን ዘመዶቻቸውንና አገራቸውን ለቅቀው መሄድ እንዳለባቸው ለባሏ ነገረችው፡፡ ነገር ግን የመቃርዮስ አባት አብርሃም ስለ ተከሰተው ነገር ሁሉ በጣም ተጨነቀና "በእኔ ላይ የሆነው ይህ ነገር ምንድን ነው" አለ፡፡ በመሸም ጊዜ ተኝቶ እያለ አረጋዊው አባት አበ ብዙኃን አብርሃም የሚያንጸባርቅና የሚያበራ ልብስ እንደ ተጎናጸፈ በህልም ታየው እርሱም ወደ መቃርዮስ አባት አብርሃም ተጠጋና እንዲህ አለው፦ "አይዞህ አትፍራ እኔ ያዕቆብን የወለደው የይስሐቅ አባት አብርሃም ነኝ፤ ስለዚህ የምነግርህን አድምጠኝ፤ የሚስትህን ቃል ከመስማት ወደ ኋላ አትበል፡፡ ይህን ቦታ ትለቅ ዘንድ እግዚአብሔር ፈቅዷልና በጁቢር ተቀመጥ፤ ጌታ እግዚአብሔር አልተውህም እባርክሃለሁ ይላልና፡፡ እኔ እግዚአብሔር እንደ ነገረኝ አገሬን በመተው በከነዓን ምድር ተቀመጥኩ፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ወንድ ልጅን እሰጥሃለሁ፣ ስሙም በትውልድ የታወቀ ይሆናል፣ እኔ በማሳየው ቦታ ያገለግሉኝ ዘንድ ብዙ የመንፈስ ልጆችን ይወልዳል" አረጋዊው ካህን ይህን በሰማ ጊዜ በታላቅ ሁኔታ አደነቀ፣ ነገር ግን ነገሮቹ አሳማኝ ስለ ነበር ተደሰተ፡፡ ❤ ጠዋትም በሆነ ጊዜ ሚስቱን ጠራትና ያየውንና የሰማውን ሁሉንም ነገር ነገራት ወዲያውም እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ነገር ለማድረግ ሁለቱም ተስማሙ ከዚያም በምሥጢር ለጊዜው የሚያስፈልጋቸውን ጥቂት ነገር ብቻ በመያዝ የቀራቸውን ንብረትና አገራቸውን በመተው በህልም እንደ ታዘዙት ወደ ጁባር ሄደው ተቀመጡ፡፡ በጁባር በሚኖሩበት ጊዜም የበለጠ የእግዚአብሔርን ሕግ በመጠበቅ መኖር የዘወትር ሕይወታቸው ነበር፡፡ የዚያች ከተማ ካህንም የአረጋዊው ካህን የአብርሃምን ምግባሩን በተመለከተ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ከእነርሱ ጋር እንዲያገለግል ጠየቀው ፡፡ እርሱ ግን አልተስማማም፤ ምክንያቱም ከሌላ ቦታ የመጣ ካህን እንዲሁ ማገልገል አይችልም ነበርና፡፡ አብርሃም በዚያ ቦታ ጥቂት እንደቆየ ራሱን በማረጋጋት መሬት በመያዝ ቀድሞ ይሠራ እንደነበር እርሻ ማረስ ጀመረ፡፡ ❤ እንዲያ እየኖረ እያለም በድንገት ታመመ፤ በዚያን ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ውሰዱኝ አላቸው ፡፡ በዚያም ይድን ዘንድ ከቤተ ክርስቲያኑ ግቢ መሬቱ ላይ በእምነት ተኛ፡፡ ሌሊትም በሆነ ጊዜ በሕማሙ ምክንያት እንቅልፍ አልወስደው ብሎ ነበርና በድንገት ቀና ሲል የእግዚአብሔር መልአክ ከፊቱ ለፊቱ በመቅደሱ ቆሞ ተመለከተ፡፡ መልአኩም "ተነስና ወደዚህ ና" በማለት ሦስት ጊዜ በመደጋገም ጠራው። ነገር ግን ለመልአኩ "ጌታዬ ከሕመሜ የተነሣ እውነት እልሃለሁ መነሣት አልችልም፣ እባክህ እለምንሃለሁ" አለው፡፡ መልአኩም ወደ እርሱ ተጠግቶ ዳሰሰውና "እግዚአብሔር እንድትድን አዝዟልና ተነስ ቁም" አለው፡፡ አብርሃም ወዲያው ተነስቶ ቆመ፤ መልአኩም "ወደ ቤትህ ሂድ፤ ሚስትህንም ባወቅኻት ጊዜ ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልድልሃለች ፡፡እርሱም ለአንተና ለሚስትህ ደስታ የሚሆንና ብዙ መንፈሳውያን ልጆችን የሚወልድ እጅግ የታወቀ ታላቅ መንፈሳዊ አባት ይሆናል፤ በዚህም የተነሣ ስሙ በዓለም ሁሉ ይነገራል፡፡ ብዙዎችን ሰዎች እንደመላእክት ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ወደ እርሱ ያመጣቸዋል፡፡

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ሰላም ለእለ ረከብዋ በኀሢሥ። አመ ለአለ ኀቤሃ እንዘ ይእቲ ነአስ። ትቤ ከመዝ በመንፈስ ቅዱስ። አንሰ ተሐጸይኩ ለሰማያዊ ክርሰቶስ። ተሰጥወተ ቃላ ሰሚዖ አንከረ ንጉሥ"። ትርጉም፦ ታናሽ ስትኾን ወደ ርሷ በላከ ጊዜ በመፈለግ ያገኟት ለኾነች ለኤውጰራክስያ (ኢዮጰራቅስያ) ሰላምታ ይገባል፤ በመንፈስ ቅዱስ እኔስ ለሰማያዊው ክርስቶስ ታጭቻለኊ ያለችውን ቃሏን ሰምቶ ንጉሥ አደነቀ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመጋቢት 26። https://t.me/eotcw

photo content
+1

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ መጋቢት ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ የመዛሙርቱን እግር ላጠበበትና፣ የሐዲስ ኪዳንን የቊርባን ሥርዓት ለመሰረተበት (ለጥንት ጸሎተ ሐሙስ) ና ለከበረችና ለተመሰገነች ለድንግሊቱ ከዘጠኛ ዓመቷ ጀምሮ ስትጋደል ለኖረች፤ ዐቢይ ጾም ምን ሳትባለ ትጾም ለነበረች ለቅድስት ኢዮጰራቅስያ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከቅድስት ኢዮጰራቅስያ ጓደኛ (ከመጋቢዋ) ና ከእመ ምኔቷ ከዕረፍታቸው መታሰቢያና ቅዱስ ፍርፍርዮስ ከመታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ እንዲህም አላቸው "እናንተም ለባልንጀሮቻችሁ እንዲሁ አድርጉ"። + + + ❤ ደግሞ የሐዲስ ኪዳንን የቊርባን ሥርዓት አሳያቸው። አሁንም በዚች ዕለት የክብር ባለቤት ጌታችንን ለአይሁድ ይሁዳ አሳልፎ ሰጠው። ነቢያት ትንቢት እንደተናገሩ የሽያጩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበለ። ይቅርታው ቸርነቱ ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለኤውጳራክስያ (ኢዮጰራቅስያ) ድንግል ቅድስት ዘኀየለት ጸብአ ከመ ወራዙት ዘኀደረ ላዕሌሃ ጸጋ አሶት። ትርጉም፦ ተአምራትን የሚያደርግ ጸጋ በላይዋ ያደረ እንደ ጐልማሶች በሰልፍ የበረታች ድንግል ለምትኾን ለቅድስት ኤውጳራክስያ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ቅድስት ኢዮጰራቅስያ፦ ይችም የተቀደሰች ብላቴና የንጉሥ አኖሬዎስ ዘመዱ ለሆነ በሮሜ ከተማ ከቤተ መንግሥት የአንድ ታላቅ መኰንን ልጅ ናት። የሚሞትበትም ቀን በደረሰ ጊዜ እርሷን ልጁን ለንጉሥ አኖሬዎስ ይጠብቃት ዘንድ አደራ ሰጠው። አባቷም ካረፈ በኋላ ለአንድ ታላቅ መኰንን ልጅ ንጉሥ አኖሬዎስ አጫት። ❤ በዚያም ወራት እናቷ የመሬቷን ግብር ልትቀበል ባሏ የተወላትን የአትክልት ቦታዎቿም ያፈሩትን ይችንም ቅድስት ብላቴናዋን ከእርሷ ጋር ወሰደቻት። ዕድሜዋ ዘጠኝ ዓመት ሁኖ ሳለ አስከትላት ወደ ግብጽ ሔደች። ❤ ወደ ግብጽ አገርም በደረሱ ጊዜ ሥራቸውን እስከሚፈጽሙ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ኖሩ። በዚያ ገዳም ውስጥ የሚኖሩ ደናግል ለገድል የተጸመዱ ናቸው። የሥጋ መብልን፣ ቅባትም ቢሆን ጣፋጭ ፍሬዎችንም ምንም ምን አይበሉም፣ ወይንም ቢሆን ከቶ አይቀምሱም ያለ ምንጣፍም በምድር ላይ ይተኛሉ። ኢዮጰራቅስያም በዚያ ገዳም ውስጥ መኖርን ወደደች ገዳሙን ከምታገለግል መጋቢዋ ጋር ተፋቅራለችና። መጋቢዋም "አንቺ ከዚህ ገዳም ወጥተሽ ተመልሰሽ እጮኛሽን ላትፈልጊ ቃል ግቢልኝ" አለቻት ኢዮጰራቅስያም በዚህ ነገር ቃል ገባችላት። ❤ እናቷ ሥራዋን በፈጸመች ጊዜ ወደ አገርዋ ልትመለስ ወደደች ልጅዋ ግን "እኔ የዚህን ኃላፊውን ዓለም ሙሽርነት ስለማልሻ ራሴን ለክብር ባለቤት ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማያዊ ሙሽራ ሰጥቻለሁ" ብላ ከእርሷ ጋር መመለስን አይሆንም አለች። ብላቴናዋ ከእርሷ ጋር እንደማትመለስ በተረዳች ጊዜ ገንዘቧን ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች መጽውታ ከልጅዋ ጋር በዚያ ገዳም ብዙ ዘመን ኑራ ከዚያ በኋላ ዐረፈችና በዚያው ቀበሯት። ❤ ንጉሥ አኖሬዎስም የኢዮጰራቅስያ እናቷ እንደሞተች ሰምቶ ለአጫት ያጋባት ዘንድ ኢዮጰራቅስያን እንዲያመጧት መልእክተኞችን ላከ። ቅድስቲቱም "ንጉሥ ሆይ ዕወቅ የክብር ባለቤት ለሆነ ለሰማያዊ ሙሽራ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ እኔ ራሴን ሰጥቻለሁና" ብላ ወደ ንጉሥ ላከች። ንጉሥ አኖሬዎስም መልእክቷን በሰማ ጊዜ አደነቀ ስለርሷም አለቀሰ እርሷ በዕድሜዋ ታናሽ ብላቴና ናትና። ❤ ይህቺ የከበረች ኢዮጰራቅስያ ግን ታላቅ ተጋድሎን ታጋደለች ለመንፈሳዊ ሥራ እጅግ የተጠመደች ሆነች በየሁለት ቀን ሁለት ሁለት ቀን እያከፈለች መጾም ከዚያም በሦስት ቀን ሦስት ሦስት ቀን ትጾም ጀመር ከዚያም በየሰባት ቀን ሰባት ሰባት ቀን የምትጾም ሆነች። በተለየች በከበረች አርባ ጾም ምንም ምን የምትበላ አልሆነችም። ❤ ሰይጣንም በእርሷ ላይ ቀንቶ አስጨናቂ በሆነ አመታት እግርዋን መታት ብዙ ቀኖችም በሕማም ኖረች ከዚያም እግዚአብሔር ራርቶላት ከደዌዋ አዳናት በሽተኞችንም ታድናቸው ዘንድ በሽተኞችን የምትፈስበትን ሀብት ሰጣት። ❤ ለእመ ምኔቷና ለእኅቶቿ ደናግል በመታዘዝ ታገለግላቸው ነበር በእኅቶች ደናግል ሁሉ ዘንድ የተወደደች ናት። ❤ በአንዲት ዕለትም እመ ምኔቷ አክሊላትንና አዳራሾችን እንደ አዘጋጁ ራእይን አየች እርሷም እያደነቀች "ከልጆቼ ለማን ይሆን ይህ የሚገባት" ስትል "እሊህ አክሊላትና አዳራሾች የተዘጋጁላት ለልጅሽ ለኢዮጰራቅስያ ነው እርሷም ወዲህ ትመጣለች" አሏት። ይህንንም ራእይ ለደናግሎች ነገራቻቸው እግዚአብሔርም በዚህ ዓለም መከራ ሊያሳርፋት እስከ ወደደበት ቀን ለኢዮጰራቅስያ እንዳይነግሯት አዘዘቻቸው። ❤ ከዚህ በኋላ በሆድ ዝማ ሕማም ጥቂት ታመመች ሁሉም ደናግል ከእመ ምኔቷ ጋር ወደ እርሷ ተሰበሰቡ ያቺ ቃል ኪዳን ያስገባቻት የምትወዳት መጋቢዋም መጣች። በእግዚአብሔርም ዘንድእንድታስባቸው ለመኑዋት እርሷም በጸሎታቸው እንዲያስቧት ለመነቻቸው ከዚያም መጋቢት 26 ቀን ዐረፈች። የተቀደሰችና የተባረከች እርሷን እኅታቸውን አጥተዋታልና ደናግሉ እጅግ አዝነው አለቀሱ። ❤ ከዚህም በኋላ የምትወዳት የገዳሙ መጋቢ የነበረችው ዐረፈች። ከእርስዋም በኋላ እመ ምኔቷ ጥቂት ቀን ታመመች ደናግሎቹንም ሰብስባ "በላያችሁ የምትሾሙትን እመ ምኔት ምረጡ ስለ እኔ ኢዮጰራቅስያ ለምናለችና እኔ ወደ ጌታዬ ኢየሱስ እሔዳለሁ አሁን ግን ደጁን በላዬ ዘግታችሁ ሒዱ" አለቻቸው እነርሱም እንዘዘቻቸው አደረጉ። በማግሥቱም ማለድ ብለው ሲደርሱ ዐርፋ አገኟት። የእሊህም የከበሩ እናቶች በረከታቸው ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት 26 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ተሐፅበኒ እምበረድ እጸዓዱ (ወእጻዓዱ)። ታሰምዐኒ ትፍሥሕተ ወኃሤት። ወይትፌሥሑ አዕፅምተ ጻድቃን"። መዝ 50፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ 11፥20-30፣ 1ኛ ዮሐ 3፥18-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 4፥24-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 26፥14-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ወይም የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/eotcw