fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ገብርዔል ነው https://t.me/Eotcw

በሀዘን በመከራ ዘማሪ ምህረተአብ አሰፋ https://t.me/Eotcw

አብሰራ ገብርኤል https://t.me/Eotcw

ገብርኤል ወዜናዊ ጥበብ ዘማሪ ይገረም ደጀኔ https://t.me/Eotcw

​​#ቅዱስ_ገብርኤል እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!! በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡ በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡ ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡ መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡ መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡ እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡ ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡ አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡ Join https://t.me/Eotcw

በነገው #ሐምሌ 17ቀን በቅዳሴ ጊዜ

+1
❣እስመ ለዓለም ይትባረክ ።አቡን በ፬ ኲ ጥቡዕ ልቡ ለህፃን https://t.me/Eotcw

❣ኢየሉጣ ወለደት@Memhir_sirak

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌱🌱🌱🌱🌱🌱 ሥርዓተ ማህሌት ዘ ሐምሌ ገብርኤል ☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘ #ስቡዕ_ከተባለ_በኃላ @EOTCW ❣መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለአቁያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን: አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን: ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን: ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ እብን: ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡ @EOTCW ❣ዚቅ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ: አንቃዕዲዎ ሰማየ: ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ: ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር: እጼውዓከ እግዚእየ: ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር: እጼውዓከ እግዚእየ: ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ። @EOTCW ❣ነግሥ ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል: ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል: ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል: አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል: እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡ @EOTCW ❣ዚቅ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል: ወብሥራት ለገብርኤል: ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። @EOTCW ❣ዘጣዕሙ፦ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣእሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ:ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ:እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡ @EOTCW ❣ዚቅ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ኀደረ ላዕሌሃ: ወአዘዘ ደመና በላዕሉ። @EOTCW ❣መልክአ ቂርቆስ ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን: ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን: ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን: ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን: ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡ @EOTCW ❣ዚቅ ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ: ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ: መላእክት ይትዋነይዋ: ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ: ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን: እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር። @EOTCW ❣ወረብ "ኢየሉጣ ወለደት"/፪/ ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት/፪/ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ/፪/ @EOTCW ❣መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ: እንተ ተመትረ እምጒንዱ: ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ: ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ: ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ። @EOTCW ❣ዚቅ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ: ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት: ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት። @EOTCW ❣ወረብ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ/፪/ ድምጻ "ለጽሕርት"/፪/ ከመ ነጎድጓደ ክረምት/፪/ @EOTCW ❣መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ: ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ: ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ: መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ: ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ። @EOTCW ❣ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ኢትፍርሂ እም ንፈጽም ገድለነ። @EOTCW ❣ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት/፪/ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም/፪/ @EOTCW ❣መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ: ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ: በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስዕለትከ መብረቅ: አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ: ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ። @EOTCW ❣ዚቅ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት: ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር: ጽዋዓ ሕይወት ወሀቦሙ: መገቦሙ ወመርሆሙ: እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡ @EOTCW ❣ወረብ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት/፪/ ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ/፪/ @EOTCW ❣መልክዐ ቂርቆስ ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ: እለ ሥዑላን በነድ: አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ: ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ: ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡ @EOTCW ❣ዚቅ በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም: ወኢብድብድ በሰብእ: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ: ወኢአባረ እክል: ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን: ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ: ወልደ አንጌቤናይት፡፡ @EOTCW ❣ወረብ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ/፪/ ባርካ ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን/፪/ @EOTCW ❣መልክዐ ኢየሉጣ ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ: ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ: ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ: ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ: ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ። @EOTCW ❣ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሰላማዊት: ሰላም ለኪ: ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ: ኢየሉጣ እምነ: ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ: ሰአሊ ለነ አስተምሕሪ ለነ: ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡ @EOTCW ❣መልክዐ ገብርኤል ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ: ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ: ገብርኤል ዉኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ: አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ: ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ። @EOTCW ❣ዚቅ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት: ወበላሕኮሙ እምእሳት: አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ: እምዕለት እኪት። @EOTCW ❣ወረብ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት/፪/ እግዚኦ አድኅነነ "ሃሌ ሉያ"/፪/ እም ዕለት እኪት/፪/ @EOTCW ❤️ምልጣን፦ ይቤላ ሕፃን ለእሙ: ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት: ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ ❤️አመላለስ: ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ/፪/ @EOTCW ❤️ወረብ ይቤላ ሕፃን ለእሙ "ኢትፍርሂ እም"/፪/ ነበልባለ እሳት/፪/ ዘአድኃኖሙ "ለአናንያ"/፪/ ወአዛርያ ወሚሳኤል/፪/ @EOTCW ❤️እስመ ለዓለም ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ: አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ: በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም: ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ ዕቶን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: አኃዘ ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሀባ ቅድመ መኮንን: አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን: ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ: እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ: አእኰትዎ ወሰብሕዎ: ወባረክዎ ለአብ፡፡ @EOTCW ❤️አመላለስ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፪/ አእኮትዎ ወሰብሕዎ/፬ @Eotcw ❤️ወረብ ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ/፪/ እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ እምዝ ዳግመ/፪/ https://t.me/Eotcw #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

ዋይዜማ እስመ ተለዓለ https://t.me/Eotcw

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ስርአተ ዋዜማ ዘሀምሌ ቅዱስ ገብርኤል ❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️ ☘ዋዜማ በ1- ሃሌ ሉያ እስመ ተለዓለ ዕበየ ስብሐቲከ መልዕልተ ሰማያት፤እምአፈ ደቂቅ ወሕጻናት አስተዳሎከ ስብሐት፤ ባረካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ በዛቲ መካን፤ኢይምፃአ ሞተ ላህም ወኢብድብድ በሰብእ፤ባረካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ በዛቲ መካን፤ ኢይኩን ሕፀተ ማይ ወኢአባረ አክል፤ባረካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፤ በዛቲ መካን፤ ቂርቆስ ሕፃን አንጌቤናይ፤ወልደ አንጌቤናይት @EOTCW @EOTCW ☘አመላለስ፦ ቂርቆስ ሕፃን አንጌቤናይ/2/ አንጌቤናይ ወልደ አንጌቤናይት/4/ @EOTCW @EOTCW ☘ለእግዚአብሔር ምድር በምላህ፦ ሰአል ለነ ሕፃን ቅዱሱ ለእግዚአብሔር ሰአል ለነ ሕፃን @EOTCW @EOTCW ☘እግዚአብሔር ነግሰ፦ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ ደምፃ ለጽሕርት ከመ ነጎድጓደ ክረምት፤ኢፈርሕዎ ለሞት ቅዱሳን @EOTCW @EOTCW ☘ይትባረክ፦ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ ወስምዖሙ አጥፍዑ ኃይለ እሳት ወቦዑ መንግሥተ ሰማያት @EOTCW @EOTCW ☘ስቡውኒ፦ ቂርቆስ ሕፃን አንጌቤናይ ወልደ አንጌቤናይት አጽምዑ መንግስተ ወኮኑ ሰማዕት ሕፃን ወእሙ @EOTCW @EOTCW ☘ሰላም፦ እንዘ ሕፃን አዕበዮ እግዚአብሔር ፣ወፈነዎ ብሔረ ጽልመት፤ ኢያውዓዮ ውኂዘ እሳት፤ለሕጻን ሀቦ ሞገሰ፤ሖረ ወገብዓ በሰላም https://t.me/Eotcw #ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ

መላው ተከታዮቻችን ለሐምሌ ፲፱ የቅዱስ ገብርኤል (የቅዱስ ቂርቆስ ) ሥርዓተ ዋዜማ እና ሥርዓተ ማኅሌት ቀድመ ለመልቀቅ እንዲመች ብለን የሐምሌ ፲፮ ፲፯ ፲፰ ፲፱ ስንክሳሮች ስለ ለቀቅን የእለቱ እየተመለሳችሁ እንድታነቡ ስንል እንጠይቃለን። እናም የሐምሌ ዑራኤል ዋዜማ እና ሥርዓተ ማኅሌት እየተዘጋጀ ስለሆነ በቅርቡ የምናካፍሎት ይሆናል ።

photo content