fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሐምሌ ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያን ጻድቃን ለአባቶቻችን ለአቡነ አፍቅረነ እግዚእ ለልደት በዓልና ለአቡነ እፍረተ ጊዮርጊስ ለዕረፍት በዓል በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ አፍቅረነ እግዚእ፦ እኚህ ጻድቅ እጅግ ከከበሩት ከሳባቱ ከዋክብት የሀገራችንን ቅዱሳን ውስጥ አንዱ ናቸው። ትውልዳቸው ትግራይ አክሱም ሲሆን አባታቸው ገብረ ኢየሱስ እናታቸው አፎምያ የተባሉ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው። ልደታቸው ሐምሌ 19 ሲሆን ዕረፍታቸው ጥር 19 ቀን ነው። በገዳማዊ ሕይወታቸው በእጅጉ ይታወቃሉ። በንጉሥ ዓምደ ጽዮን ዘመን የነበሩ ሲሆን ደራሲና ፈላስፋም ናቸው። ❤ ጻድቁ ደራ ፎገራ ውስጥ ባለ አራት ዓምድ አስደናቂ ገድል አላቸው። ደራ ፎገራ ተነስተው በጣና አድርገው ፈላሾችንና ቅማንቶችን በሚገባ በማስተማርና በማጥመቅ ብዙ ሐዋርያው አገልግሎት ፈጽመዋል፡ ጻድቁ በወጣትነታቸው ወደ ጣና ባሕር ሄደው መሐመላ፣ ምፅሌና፣ አይፋር በተባሉና በሌሎችም አገሮች ወንጌልን ካስተማሩ በኋላ ወደ ትግራይ ሔደው በዚያ ገዳማቸውን መሠረቱና በዚያው ዐረፉ። ከጌታችን ጋር አብረው ማኅበር የጠጡ 3 ሺህ ቅዱሳን አክሱም አካባቢ ባለው በአቡነ አፍቅረነ እግዚእ ገዳም ይከብራሉ። ነገር ግን ዛሬ ላይ በገዳማቸው ላይ የጻድቁ በዓል መከበር እየቀረ የእነዚህ 3ሺህ ቅዱሳን ማኅበርተኞች በዓል ነው በድምቀት የሚገበረው። ❤ አቡነ አፍቅረነ እግዚእ ዛሬ ግሸን ላይ በክብር ተቀምጦ አገራችንን ከመዓት እየጠበቀ ያለው የጌታችን ቅዱስ መስቀል ካመጡት የአቡነ መድኃኒነ እግዚእ ልጆች ውስጥ አንዱ ናቸው። አቡነ ሳሙኤል ዘደብረ ዋሊ አቡነ ያሳይና አፍቅረነ እግዚእ እነዚህ ሦስቱ ቅዱሳን ወደ ጣና አብረው ከመጡና አብረው የተወሰነ ጊዜ ከቆዩ በኋላ አቡነ ሳሙኤል ወደ ዋልድባ ሲሄዱ አቡነ ያሳይ ማንዳባን ገዳምን አቀኑ፡፡ አቡነ አፍቅረነ እግዚእ ደግሞ ጌታችን ባዘዛቸው መሰረት ጣና ውስጥ በስማቸው የተሰራውን ገዳም አቅንተዋል። + + + ❤ አቡነ እፍረተ ጊዮርጊስ፦ ኢትዮጵያዊ ታላቅ መምህር ሲሆኑ ትውልዳቸው ጎጃም ዋሸራ ጽላሎ ነው። በአህያና በበቅሎ ተጭነው ሲሄዱ እንስሶቹ በሰው አንደበት ያናግሯቸው ነበር። ከተወለዱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ ጫማ አድርገው አያውቁም። ጻድቁ ዋሸራ በምትገኘው፡አስደናቂዋ "መንክር ኃይላ" ሥዕል ሥር እየጸለዩ ሳለ በዚያው ዐርፈዋል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

photo content

የእግዚአብሔርን ክብር ታይ ዘንድ አለህ" አለው ይህንንም ብሎ ዕውሩን ጠራውና "ዐይኖችህ ቢገለጡ ያዳነህን ታመልከዋለህን?" አለው ዕውሩም "አዎን አምናለሁ" አለ ቅዱስ በጥላን በዕውሩ ላይ ረጅም ጸሎትን ጸለየ እጆቹንም በዕውሩ ዐይኖች ላይ አኑሮ "እንድታይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እመን" አለው ወዲያውኑም ዐይኖቹ ተገለጡ። አባቱም ይህን ድንቅ ሥራ በአየ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ከዕውሩ ጋር አመነ ቅዱስ በጥላንም ወደ ቄሱ ወሰደጃቸውና የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ከዚህም በኋላ ባሮቻቸውን ነፃ አወጡ ገንዘባቸውንም ለድኆችና ለችግረኞች አከፋፈሉ። ❤ ቅዱስ በጥላንም ጥበብ ያደርግ ነበር። ያለ ዋጋም ሰዎችን ያድናቸው ነበር። ነገር ግን ክብር ይግባውና በክርስቶስ እንዲያምኑ ይሻ ነበር። ስለዚህም ጥበበኞች ሰዎች በእርሱ ላይ ተነሡ ወደ ንጉሥም ሒደው ከቄሱ ጋራና ከአዳነውም ዕውር ጋራ በጌታችንም ከአመኑ ከብዙዎች ጋራ ከሰሱት። ወደ ንጉሡም በቀረቡ ጊዜ ንጉሡ ተቆጥቶ "ለአማልክት ሠዉ" አላቸው ባልታዘዙለትም ጊዜ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጠ። የሰማዕታት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ። ❤ ከዚህም በኋላ ቅዱስ በጥላንንም የጸና ሥቃይን አሠቃየው። ከእርሱም ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ በእጁም ብዙ ሰዎች ክብር ይግባውና በጌታችን አመኑ። በሰማዕነትም ዐረፉ። ንጉሡም አይቶ በበጥላን ላይ ተቆጣ። ለአንበሳም አስጣለው አንበሳውም እግሩን ላሰው እንጂ ክፉ አላደረገበትም። ሁለተኛም ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ በዚህም ምስክርነቱን ሐምሌ 19 ቀን ፈጽሞ በመንግሥተ ሰማያት አክሊልን ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በቅዱስ በጥላንና ከእርሱ ጋራ በሰማዕትነት በዐረፉ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱሳን ሰማዕታት ስማቸው ሱርስ፣ ኅርማን ያኑፋ ስንጣንያ የሚባሉ የእስና አገር ሰዎች የሆኑ፦ የሰማዕትነታቸው ምክንያትም እንዲህ ነው መኰንኑ አርያኖስ ወደ እስና ከተማ ሦስት ጊዜ ደረሰ። በመጀመሪያ የተባረከች መስተጋድልት የሆነች ዳላዢን ገደላት። ስማቸውን አስቀድመን የጠራናቸው አራቱን ልጆቿንም ገደላቸው። የሰማዕነታቸውም ፍጻሜ ግንቦት ሰባት ቀን ሆነ። ሁለተኛም ስማቸው አውሳፍዮስ ታማን ኅርማን ባኮስ የሚባል አራቱን መኳንንት ገደላቸው። የሰማዕታቸውም ፍጻሜ ሰኔ ሰባት ቀን ሆነ። ሦስተኛም ጊዜ በቤቷ ውስጥ በዐልጋዋ ላይ ተኝታ የነበረችውን አሮጊት የአርያኖስ ወታደሮች ስለ እነዚህ ቅዱሳን ከጠየቷት በኋላ ገደሏት። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ከክርስቲያን ወገን ያገኙትን ሁሉ እንዲገድሉ የተክል ማጠጫ በተባለች በከተማዋ ምዕራብም መግደልን እንዳያቋርጡ አዘዘ ወደ ከበረ አባት ወደ ባሕታዊ ይስሐቅም እስኪደርሱ ድረስ በመንገድ ብዙ ሕዝብን አገኙ። ያን ጊዜም ጠባቂያቸው እንዲህ እያለ ያጽናናቸውና ያረጋጋቸው ነበር "ወደ ሰማያዊት መንግሥት እንድትገቡ ጸንታችሁ ታገሡ"። እንዲህም ሲወስዷቸው መኰንኑ ደረሰ በአዩትም ጊዜ ሁሉም በአንድ ቃል "እኛ ክርስቲያን ነን" እያሉ በግልጽ ጮኹ መኰንኑም ሁሉንም እንደበግ ያርዷቸው ዘንድ አዘዘ። ጭፍሮች ግን በላያቸው በሰይፎች አጋና ተጫወቱ። በዚችም በሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ ቀን የእስናን ከተማ ሰዎች ከታናሾቻቸው እስከ ታላቆቻቸው ሴቶችንና ወንዶችን ጨረሷቸው። የመላእክት ሠራዊትም ነፍሶቻቸውን ይቀበሉ የብርሃን አክሊሎችንም ያቀዳጁአቸው ነበር። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ከዚያ ወደ እስዋን ከተማ ሔደ ሁለተኛም ወደ እስና ከተማ ተመለሶ ሦስት ገበሬዎችን የእርሻ ዕቃቸውን ተሸክመው አገኘ። በመኰንኑም በአዩት ጊዜ "እኛ ክርስቲያን ነን" ብለው በግልጥ ጮኹ መኰንኑም ሰምቶ ይገድሏቸው ዘንድ አዘዘ በእርሻ መሣሪያቸውም ገደሏቸው የእነዚህም ስማቸው ሱሩፋስ፣ አንጣኪዮስ፣ ስሐድራ ይባላል የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ መስከረም ዐሥራ አንድ ቀን ነው። ❤ ይህንንም ቅዱስ አባት ኤጲስቆጶስ ይስሐቅን መኰንኑ አሥሮ ለጣዖት እንዲሠዋ አስገደደው። እምቢ ባለውም ጊዜ ወደ እሳት እንዲወረውሩት አዘዘ የሰማዕትነቱም ፍጻሜ ታኅሣሥ ዐሥራ አራት ቀን ነው ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ገንዘው ቀበሩት። የስደቱ ወራትም ከአለፈ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው በስሙ አከበሩዋት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአገረ እስና ሰማዕትነት ሁሉ በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 19 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለከ ሰማዕት በጥላን። ዘሀገረ ትእማዳን። በእንተ ኢየሱስ ዘሞትከ በሰይፈ ኀፂን። ምስለ ዕውር ዘፈወስኮ ወምስለ መምህርከ ካህን። እንዘ ክዋኔከ ከመ ኤር ወስን"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ19። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወአፅዐንከ ሰብአ ዲበ አርእስቲነ። አኅለፍከነ ማእከለ እሳት ወማይ። ወአውጻእከነ ውስተ ዕረፍት"። መዝ65፥12-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ18፥1-12። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ይትኀፈሩ ኵሎሙ እለ ይሰግዱ ለግልፎ። ወእለ ይትሜክሑ በአማልክቲሆሙ። ወይሰግዱ ሎቱ ኵሎሙ መላእቲሁ"። መዝ 96፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ11፥25-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ ነው። መልካም የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሐምሌ ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን ለመጋቢ ሐዲስ ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ወደ ፈላ ውሃ ውስጥ በጣሏቸው ጊዜ ከእግዚአብሔር ተልኮ የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ አድርጎ ላደነበት ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል፣ ትዕማዳን ከምትባል ከተማ ብልህ ለሆነ ለሰማዕቱ ለቅዱስ በጥላን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለቅዱሳን ሰማዕታት ስማቸው ሱርስ፣ ኅርማን ያኑፋ ስንጣንያ የሚባሉ የእስና አገር ሰዎች ለሆኑ ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለዕረፍቻው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከአባ አቃራቦን፣ ከመቃርስና ከስካ አገር ሰው ከሆነ ከሙሴ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ"። ትርጉም፦ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ እናቱን እናቴ ከእሳተ ነበልባሉ የተነሣ አትፍሪ፤ አናንያን፣ አዛርያን፣ ሚሳኤልን ያዳነ እርሱ እኛን ያድናል አላት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ "ሰላም ለገብርኤል መልአከ ሰላም"። ትርጉም፦ የሰላም መልአክ ለኾነ ለቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ይገባል"። + + + ❤ "ሰላም ለቂርቆስ ወሬዛ በመንፈስ በልደት ንዑስ፤ ንጹሕ ከመ ዕጣን ወፍሡሕ ከመ ወይን"። ትርጉም፦ በልደተ ሥጋ ታናሽ በመንፈስ ጎልማሳ፤ እንደ ዕጣን ንጹሕ እንደ ወይንም አስደሳች ለኾነ ለቅዱስ ቂርቆስ ሰላምታ ይገባል። ሊቀ አባ ጊዮርጊስ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣን ቅዱስ ገብርኤል እንዳዳናቸው፦ ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ አገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው። ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም "መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ" አለችው። ❤ ሕፃኑም ቅዱስ ቂርቆስ ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና "አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ" አለው። ሕፃኑም መልሶ "አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና" አለው። እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑም በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም "ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ" አለችው። "ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት" አለችው ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ ሐምሌ 19 ቀን በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጎትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በመላእኩ በቅዱስ ገብርኤል፣ በቅዱስ ቂርቆስና በእናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ትዕማዳን ከምትባል ከተማ ብልህ የሆነ ሰማዕቱ ቅዱስ በጥላን፦ የዚህም ቅዱስ አባቱ አረማዊ ነበረ ስሙም አውጢኪዮስ ነበር እናቱ ግን አማኝ ነበረች ስሟም ኤልያና ነበር። በአደረገ ጊዜም አባቱ ጥበብን ሁሉ አስተማረው እጅግም አዋቂ ሆነ። ❤ በበጥላን ቤት አቅራቢያም አንድ ቄስ ይኖር ነበር። በጥላንም በፊቱ ሲያልፍ መልኩንና ዕውቀቱን ብልህነቱንና አስተዋይነቱንም ይመለከት ነበር ከሀዲ ስለ መሆኑም ስለርሱ ያዝን ነበር። ቄሱም በጥላን መንገድ መርቶ ወደ ቀናች ሃይማኖት ያስገባው ዘንድ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመነው። ስለ በጥላንም ልመናውን በአዘወተረ ጊዜ በጥላን በእርሱ እጅ ያምን ዘንድ እንዳለው ጌታችን በራእይ ገለጠለት ቄሱም ደስ አለው ሁልጊዜም በፊቱ ሲያልፍ በጥላንን ያነጋግረውና ሰላምታ የሚሰጠው ነበር። ስለዚህም በመካከላቸው ፍቅር ጸና። ❤ ከዚህም በኋላ በጥላን ወደ ቄሱ ቤት ይገባና ስለ ሃይማኖት ይነጋገር ነበር። ቄሱም ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ምን ያህል ክብር እንዳላት ለሚያምኑበትም ሁሉ ዕውቀትና ማስተዋል እንደሚሰጣቸው ድንቆችና ታላላቅ ተአምራቶች እንደሚደረግላቸው ታላቅ ፈውስም እንደሚያደርጉ ገለጠለት። በጥላንም ክብር ይግባውና በክርስቶስ የሚያምኑ ተአምራትን እንደሚያደርጉ ይህን በሰማ ጊዜም እጅግ ደስ ብሎት በዚያ ቄስ ትምህርት በጌታ አመነ ቄሱም ሁል ጊዜ የሃይማኖት ትምህርት ያስተምረው ጀመር። ❤ በአንዲትም ዕለት ቅዱስ በጥላን በከተማው አደባባዮች ሲያልፍ እባብ የነደፈውን አንድ ሰው ሲጨነቅ አየው እባቡም በርሱ ዘንድ ቆሞ ነበር በልቡም "የመምህሬን ቃል ልፈትን ክብር ይግባውና በክርስቶስ ከአመንክ በስሙ ታምራት ታደርጋለህ ብሎኛልና" አለ። እባቡ ወደ ነከሰውም ሰው ቀርቦ ኃይሉን ይገልጽለት ዘንድ እባቡንም ይገድለው ዘንድ ሰውዬውን ያድነው ዘንድ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ረጅም ጸሎትን ጸለየ ያን ጊዜም ሰውዬው ያለ ምንም ጉዳት ድኖ በጤና ተነሣ ከይሲውም ወደቀ ወዲያውም ሞተ። የበጥላንም ሃይማኖት ተጨመረለት። ❤ ከዚህም በኋላ በጥላን ወደ ቄሱ ሒዶ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀ ሁል ጊዜም ወደ ቄሱ እየመጣ ይማር ነበር። በአንዲት ቀንም ያድነው ዘንድ አንድ ዕውር መጣ። የቅዱስ በጥላም አባትም ባየው ጊዜ ዕውሩን ከውጭ መልሶ ሰደደው በጥላንም አባቱን "ማነው የፈለገኝ?" ብሎ ጠየቀው አባቱም "ልታድነው የማትችል አንድ ዕውር ነው" አለው። እርሱም አባቱን "

ሙ ለነፋሳት እመዛግብቲሆሙ"። መዝ134፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥ 47-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ የዕረፍት በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነው ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ለነበረው ለጌታችን ወንድም ለሚባለው ለሐዋርያው ለቅዱስ ያዕቆብ ለዕረፍት በዓል፣ ከቁልዝም ከተማ ለሆነ በከሀዲው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለ ለቅዱስ አትናቴዎስ ለዕረፍት በዓል፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከእንዱራናና ከጦቢያ፣ ከኤስድሮስ ማኅበር ከዘጠኙሽህ ጭፍሮችና ከመኰንኑ ከእንድራኒቆስና ከሠራዊቱ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። ❤ "ሰላም ለያቆብ እኁሁ ለእግዚእነ በሥጋ ዘቀደመ ተሠይሞ ውስተ አብያተ ክርስቲያና ወተጰጰሰ እምኀበ ሐዋርያት"። ትርጉም፦ ከሐዋርያት ጵጵስናን የተቀበለ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ መሾሙ የቀደመ በሥጋ ዝምድና የጌታችን ወንድም ለኾነ ለያዕቆብ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ፦ ይህም የጠራቢው የዮሴፍ ልጅ ነው። እርሱም ከልጆቹ ሁሉ የሚያንስ ነበር። እርሱም ንጹሕ ድንግል ነበር ከጌታችን ጋራ አደገ ስለዚህም ክብር ይግባውና የጌታችን ወንድም ተባለ። ከጌታችን ዕርገትም በኋላ ሐዋርያት በኢየሩሳሌም አገር ላይ ኤጲስቆጶስ አድርገው ሾሙት። ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተምሮ ብዙዎችን ወደ ቀናች ሃይማኖት መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው። እግዚአብሔርም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ። ❤ በአንዲት ዕለትም በጎዳና ሲጓዝ አንድ ሽማግለሸ አገኘ። ቅዱስ ያዕቆብም "ሽማግሌ ሆይ በቤትህ ታሳድረኛለህን?" አለው። አረጋዊውም "እሺ እንዳልክ ይሁን" አለ በአንድነትም ሲጓዙ ጋኔን ያደረበት ሰው አገኘው በአየውም ጊዜ "የክርስቶስ ሐዋርያ ሆይ እኔ ካንተ ጋር ምን አለኝ ልታጠፋኝ መጣህን" ብሎ ጮኸ። ሐዋርያውም "በናዝሬቱ ኢየሱስ ስም ተዘጋ ከሰውዬውም ውጣ" አለው። ወዲያውም ያ ጋኔን ከሰውዬው ላይ ወጣ። ❤ ያ ሽማግሌም ይህን ድንቅ ተአምር አይቶ ደነገጠ ከሐዋርያው እግር በታችም ወድቆ እንዲህ አለው "ወደ ቤቴ ልትገባ አይገባኝም ነገር ግን እድን ዘንድ ቤተ ሰቦቼም ሁሉ ይድኑ ዘንድ ምን ላድርግ" አለ ያን ጊዜም ሐዋርያው "አቤቱ ጌታዬ ሆይ መንገዴን አሳምረህልኛልና አመሰግንሃለሁ" ብሎ ጌታችንን አመሰገነው። ወደ ሽማግሌዎች ተመልሶ የድኅነትን ነገር ነገረው ከብር ይግባውና ስለጌታችን ሰው መሆን ስለ መከራው ስለ ሞቱና ስለ መነሣቱ አስተማረው። ❤ ከዚህም በኋላ ያ ሽማግሌ ሐዋርያውን ወደ ቤቱ አስገባው ቤተ ሰቦቹም ሁሉ ወደርሱ ተሰበሰቡ ቅዱስ ያዕቆብም አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው። ሥጋውንና ደሙንም አቀበላቸው። ❤ የከተማው ሰዎችም በሰሙ ጊዜ በሽተኞችን ሁሉ ወደርሱ አመጡ ሁሉንም አዳናቸው ለእነርሱም ሃይማኖትን አስተምሮ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸው። ቀሳውስትንና ዲያቆናትንም ሾመላቸው ያንን ሽማግሌም ኤጲስቆጶስ አድርጎ ሾመው ክብር ይግባውና የጌታችንንም ወንጌል ሰጣቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ያስተምር ዘንድ ወደ ሌሎች አገሮች ወጥቶ ሔደ። አንዲትም መካን ሴት ነበረች እግዚአብሔር ልጅን ይሰጣት ዘንድ ስርሷ እንዲጸልይላት ቅዱስ ያዕቆብን ለመነችው። እርሱም ጸለየላትና ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ያዕቆብ ብላ ጠራችው ልጅዋንም ተሸክማ ወደ ሐዋርያው መጥታ ሰላምታ አቀረበችለት ከልጅዋም ጋር ከእርሱ ተባረከች። ❤ ከዚህም በኋላ በአንዲት ቀን ብዙዎች አይሁድ ወደርሱ ተሰበሰቡ ስለ ጌታ ስለ ኢየሱስም የማን ልጅ እንደሆነ ይነግራቸው ዘንድ ጠየቁት እነርሱ እርሱ ጌታች የዮሴፍ ልጅ እንደሆነ እርሱም ወንድሙ እንደሆነ እንዲነግራቸው አስበው ነበርና። ቅዱስ ያዕቆብም በሦስተኛ ደርብ ላይ ወጥቶ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነም ከአብ ጋራም ትክክል እንደሆነ ይገልጽላቸው ጀመረ። ❤ ይህንንም በሰሙ ጊዜ እጅግ ተቈጡ ከደርቡ ላይ አውርደው የጸና ግርፍትን ገረፉት ከእነርሱም ውሰጥ የልብስ ማጠብያ የእንጨት ገበታ የያዘ አንድ ሰው መጣ በዚያ እንጨትም ቅዱስ ያዕቆብን ራሱ ላይ መታው ያን ጊዜም ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ። ❤ ስለርሱ ወይን እንዳልጠጣ ደም ከለው ወገን እንዳልበላ በራሱም ላይ ምላጭ እንዳልወጣ በውሽባ ቤት እንዳልታጠበ ሁለት ልብስን እንዳለበሰ ሁል ጊዜም እንደሚቆምና እንደሚሰግድ ተጽፏል። ከመቆም ብዙ የነሳ እግሮቹ አብጠው ነበር። ከዚህም በኋላ ዐረፈና በቤተ መቅደሱ ጎን ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱስ አትናቴዎስ፦ ይህም ቅዱስ ከነገሥታት ወገን ነበረ በሃይማኖቱም የጸና ነበረ። እኒህ ከሐዲያን ነገሥታት ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ የጣዖታትን አምልኮ በዓወጁ ጊዜ ይህን አትናቴዎስን ለግብጽ አገር ገዥ አድርገው ሾሙት አብያተ ክርስቲያናትንም እንዲአፈርስ አዘዙት።እርሱ ግን ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ ሒዶ በረከትን ተቀበለ እርሱም ክርስቲያን እንደሆነ ነገረው በእርሱም ደስ አለው። ንጉሡም በሰማ ጊዜ ይዞ ይመረምረው ዘንድ ሌላ መኰንን ላከ። ❤ መኰንኑም በደረሰ ጊዜ ተገናኘውና "የአማልክትን ፍቅር ለምን ተውክ" አለው። አትናቴዎስም እንዲህ ብሎ መለሰለት "እኔ ከታናሽነቴ ጀምሬ ክብር ይግባውና የክርስቶስ ነኝ የቀናች ሃይማኖቴንም አልተውም"። መኰንኑም "የንጉሥን ትዕዛዝ የሚለውጥ ሁሉ ቅጣት እንዲአገኘውና በጽኑ ሥቃይ እንዲሠቃይ አታውቅምን" አለው። ቅዱስ አትናቴዎስም እንዲህ አለው "አንተ ሰነፍ በአንተ ላይና በንጉሥህ ላይ ቸር ሕይወት ሰጭ እግዚአብሔርን በሚጠላ በአባትህ ሠይጣን ላይ የሚመጣው የዘላለም ሥቃይን እስከምታይ ጥቂት ታገሥ" አለው። ❤ መኰንኑም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ራሱንም በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። ቅዱስ አትናቴዎስም ነፍሱን ከቅዱሳኑ ጋራ እንዲያሳርፍ ከቤተ ክርስቲያንም መከራን እንዲያርቅ የሮምንና የአኲስምን የክርስቲያን መንግሥት እንዲአጸና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ጸሎቱም በፈጸመ ጊዜ በክር ብሎ ሰገደ ጭፍሮችም ራሱን በሰይፍ ቆረጡ። ምእመናንም ሥጋውን ወስደው ቀበሩት። ከመቃብሩም ቁጥር የሌላቸው ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋ ይሁን እኛንም በቅዱስ አትናቴዎስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 18 ስንክሳር + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4 ወይም መዝ 25፥4 ። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 13፥52-ፍ.ም ወይም ማር 6፥1-14። + + + ❤ "ሰላም ለያዕቆብ በኀበ ማርያም ዘተሐፅነ። ዕጓለ ማውታ እምእሙ እስመ ውእቱ ኮነ። ወዝንቱ ጻድቅ እኅወ እግዚእነ። ኢያብአ ውስተ አፉሁ ሥጋ ወወይነ ወኢገብረ ሎቱ ክልኤተ ክዳነ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ18። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ያዐርግ ደመናተ እምአጽናፈ ምድር። ወገብረ መብረቅ ለጊዜ ዝናም። ዘያወጽኦ

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፯ (17) ቀን። ❤ እንኳን ለየዋሁ ነቢይ ለዮናስ ከዓሣ ዐንበሪ ሆድ ውስጥ ለወጣበት ቀን መታሰቢያ በዓልና ለቅድስት አውፎምያ ሰማዕትነት ለተቀበለችበት ለዕረፍቷ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቅዱሳን ኤስድሮስና ከሰማዕቱ ቤዱል፣ ከዘካርያስና ከአውልያን ከዐይነ ፀሐይ ከመታሰቢያቸው ከቅዱስ ሰማዕት ከዮስጦስም ዐፅሙ ከተገኘበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ቅድስት አውፎምያ፦ ይቺም ቅድስት በርሴፎስ የሚባል ከዲዮቅልጥያኖስ መኳንንቶች አንዱ አሠቃያት። የታሠሩ ሰማዕታት በሚያልፉ ጊዜ በአንገታቸው የሚከብዱ ሰንሰለቶች ነበሩ። እንደ ውሾችም ይጎትቷቸው ነበር። ግፋቸውንም ባየች ጊዜ ይቺ ቅድስት አለቀሰች ልቡናዋም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ፍቅር ተቃጠለ ዲዮቅልጥያኖስንና የረከሱ አማልክቶቹንም ረገመች። ያንንም መኰንን እንዲህ ብላ ዘለፈችው። "ርኅራኄ የሌለህ ልብህ እንደ ደንጊያ የሆነ ለእኒህ ቅዱሳን ሰዎች አትራራምን ፈጣሪያቸውስ እንዲያጠፋህ አትፈራንምን"። ❤ መኰንኑም ሰምቶ ወደርሱ ያቀርቡአት ዘንድ አዘዘ። ስለ ሃይማኖቷም ጠየቃት እርሷም ክርስቲያን እንደሆነች በፊቱ አመነች። በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ በግርፋትና በስቅላት ታላቅ ሥቃይን አሠቃያት። ❤ ከዚህ በኋላ በእሳት ምድጃ ውስጥ ጨመሩዋት ነገር ግን ከሥቃዩ የተነሣ ምንም ጉዳት አልደረሰባትም። በዚያን ጊዜሜ በእሳቱ መካከል ቆማ ጸለየች ፊቷንና መላ ሥጋዋንም በመስቀል ምልክት አማተባ ነፍሷን በእግዚአብሔር እጅ ሰጠች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት አውፎምያ በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 17 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ዕብል ለአውፎምያ ኅሪት። ክበደ ሰናስል ነጺራ በክሣደ ሰማዕት። ወሶበ ነደ ልባ በአምላካዊ ቅንዓት። መቅሠፍት ኢያፍርሃ ወኢያደንገፃ ስቅለት። ወለኪፎታ ኢክህለ እሳት"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ17። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ወአይቴ እጎይይ እምቅድመ ገጽከ። እመኒ ዐረጉ ውስተ ሰማይ ህየኒ አንተ። ወእመኒ ወረድኩ ውስተ ቀላይ ህየኒ ሀሎከ"። መዝ138፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥38-43። የሚቀደሰው ቅዳሴ የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ዕድሜ ልካቸውን እናትና አባታቸውን እንኳን ባለመናገር ዘረኝነትን ከሀገራችን ላጠፉ ለታለቁ አባት ለአባታችን ለአቡነ ዳንኤል ዘቦረና ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ አቡነ ዳንኤል ዘቦረና፦ እኚህ ጻድቅ አባት አንድ ትልቅ ግብር አላቸው፤ ይኸውም ዕድሜ ልካቸውን እናትና አባታቸውን እንኳን ባለመናገር ዘረኝነትን ከሀገራችን ያጠፋ ታላቅ ጻድቅ አባት ናቸው። ግድ ብለው አጥብቀው ሲይዟቸው "እናቴ አክሱም አለች፤ አባቴም ልጇ ነው" በማለት ዘረኝነትን በዘመናቸው አጥፍተዋል። ❤ ቦረና ሳይንት ባለው ገዳማቸው ውስጥ የሚገኘውን ባለ፡ሦስት ዓምድ ገድላቸውን ደርቡሾች ከጠባቂው በትንሽ ገንዘብ ገዝተው ወስደውታል። እርሱም በመቅሰፍት ተመቶ ሞቷል። ጻድቁ በሀገራችን ከ 250 በላይ አብያተ ክርስቲናትን አሠርተዋል። መካነ መቃብራቸው በጋስጫ ይገኛል"። ምንጭ መዝገበ፦ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤ ❤ ሐምሌ ፲፮ (16) ቀን። ❤ እንኳን ለቅዱስ አባት ወንጌሉ ዘወርቅ ለተባለ ልክ እንደ ገብረ ክርስቶስ በእናት አባቱ ቤት እንደ ነዳይ ሆኖ ለተጋደለ ለአባ ዮሐንስ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ ወንጌሉ ዘወርቅ የተባለው ቅዱስ አባት አባ ዮሐንስ፦ ይህም ቅዱስ ከሮሜ አገር ነበር አባቱም አጥራብዮስ የሚባል ባለጠጋ ነው። የእናቱም ስም ብዱራ ይባላል። እንዲማርም ለመምህር ሰጡት ቅዱሳት መጻሕፍትንም ተማረ። ❤ ከዚህም በኋላ ገበታው የወርቅ የሆነ ወንጌልን ያሠራለት ዘንድ አባቱን ለመነው አባቱም እንደፈለገው አሠራለት ሁል ጊዜም ያነበው ነበር። በሚያነብ ጊዜም አባቱና እናቱ ደስ ይላቸው ነበር። ❤ በዚያም ወራት ወደ ኢየሩሳሌም የሚጓዝ መነኵሴ ወደ እነርሱ መጣ በእነርሱም ዘንድ አደረ ከቅዱስ ዮሐንስም ጋራ ተነጋግሮ የምንኵስናን ሥራ አመሰገለት ይህን ዓለም እስከ ናቀና እንደ እርሱ መነኰስ ይሆን ዘንድ እስከ ወደደ ድረስ ልቡን ማረከው። ያን ጊዜም ያ መነኰስ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘ ሁለተኛም ተመልሶ እንደ ልማዱ በእነርሱ ዘንድ አደረ። ቅዱስ ዮሐንስም መነኵሴው ወደ ገዳም ይወስደው ዘንድ ፈለገ መነኵሴውም "አባትህን እፈራዋለሁ ልወስድህ አይቻለኝም" አለው። ቅዱስ ዮሐንስም ከእርሱ ጋራ እንዲወስደውና ነፍሱን እንዲያድን አማለው። ❤ ከዚህም በኋላ በስውር ወሰደው በመርከብም ተጭነው ያ መነኰስ ወደሚኖርበት ገዳም ደረሱ የገዳሙም አበ ምኔት የወጣቱን ዮሐንስን መልኩን አይቶ አደነቀ። ቅዱስ ዮሐንስም የምንኵስናን ልብስ ያለብሰው ዘንድ አበ ምኔቱን ለመነው አበ ምኔቱም "ልጄ ሆይ የምንኵስና ሕግ እጅግ ጭንቅ ናት እኮ" አለው። አብዝቶም በለመነውና ግድ ባለው ጊዜ ራሱን ላጭቶ አመነኰሰው። ❤ ከዚህም በኋላ ከጾም ከትጋትና ከኀዘን የተነሣ ሥጋው ደርቆ አጥንቶቹ እስከ ሚታዩ ድረስ በብዙ ተጋድሎ ተጸመደ። አም ምኔቱም "ልጄ ሆይ ለሰውነትህ እዘን ድካምህንም ቀንስ መነኰሳቱም ሁሉ እንደሚሠሩት ሥራ" እያለ ያጽናናውና ይመክረው ነበር። ❤ በዚህ ተጋድሎም ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ "ከእነርሱ በረከትን ትቀበል ዘንድ ከመሞትህ በፊት ወደ አባትህና እናትህ ሒድ" የሚል ራእይ አየ። ይህንንም ራእይ በሦስት ሌሊቶች ውስጥ አየ ለአበ ምኔቱም እንዴት እንዳየ ነገረው አበ ምኔቱም "ይህ ራእይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለ ሆነ ልትሔድ ይገባሃል" አለው። ❤ ከገዳሙም በወጣ ጊዜ አንድ ምስኪን ሰው ጨርቅ ለብሶ አገኘ። የእርሱንም ልብስ ሰጥቶት ጨርቁን ወሰደ። ወደ አባቱ ቤትም በደረሰ ጊዜ በትንሽ ጎጆ ውስጥ በአባቱ ደጅ በጾም በጸሎትና በስግደት እየተጋደለ ባሮች ከአባቱ ማዕድ የሚጥሉለትን ፍርፋሪ እየተመገበ ሰባት ዓመት ኖረ። እናቱም በአንጻሩ ስታልፍ የሚከረፋ ሽታው ያስጨንቃት ነበር። ❤ ዕረፍቱም በቀረበ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ "ከሰባት ቀን በኋላ ከዚህ ዓለም ትወጣለህ" ብሎ ነገረው። ያን ጊዜም ወደ እናቱ ልኮ ልምናውን ልትሰማ ወደ እርሱ መጣች ልጅዋም እንደሆነ ፈጥኖ አልነገራትም ነገር ግን በዚያች በታናሽ ማደሪያ ውስጥ በላዩ ባለ ጨርቅ እንድትቀብረው የለበሰውንም ጨርቅ እንዳትለውጥ አማላት። ከዚህም በኋላ ያንን የወርቅ ወንጌል ሰጣት። እንዲህም አላት "ይህን መጽሐፍ አንብቡ እኔንም አስቡኝ"። ❤ አባቱም በመጣ ጊዜ ያንን የወርቅ ወንጌል አሳየችው ለልጁ ያሠራለት ወንጌል እንደሆነ አወቀ። አባቱና እናቱም ወደ እርሱ ሔደው ስለ ልጃቸው ጠየቁት እርሱም "ከዚህ ጨርቅና ከዚህ ትንሽ ማደሪያዬ ውስጥ በቀር በሌላ እንዳትቀብሩኝ ማሉልኝ" አላቸው። በአማላቸውም ጊዜ እርሱ ልጃቸው እንደሆነ ገራቸው ያን ጊዜም ጮኹ መሪር ልቅሶንም አለቀሱ የሮሜ ከተማ ሽማግሎዎችና ሕዝቡ ሁሉ ተሰበሰቡ ሰባቱ ቀንም ሲፈጸም ቅዱስ ዮሐንስ ሐምሌ 16 ቀን ዐረፈ። ❤ እናቱም መሐላዋን ረስታ አስቀድማ ለሠርጉ ያዘጋጀቻቸውን ያማሩ ልብሶች አውጥታ ገነዘች። በዚያችም ጊዜ ታመመች አባቱ ግን መሐላውን አስታውሶ እነዚያን ያማሩ ልብሶች አስወገደ በጨርቆቹም ገነዙት በዚያ በትንሹ ማድሪያም ውስጥ ቀበሩት ከሥጋውም በሽተኞች የሚፈወሱበት ታላቅ ድኅነት ተገኘ። ❤ ከዚህም በኋላ በስሙ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሐምሌ 16 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ ዘወንጌል ወርቅ ንዋዩ። ዘአግበረ ሎቱ አቡሁ እምነ ዕበዩ። ወበተጋድሎ ማሰነ ወተወለጠ ራእዩ። እስከ ሰእኑ ጠይቆተ ገጹ ኪያሁ ዘአርእዩ። ወእስከ ሰአልዎ ያውሕድ እምብዙኅ ሥቃዩ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሐምሌ16። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ከመ ነኪር ኮንክዎሙ ለአኃውየ። ወነግድ ለደቂቀ አቡየ ወእምየ። እስመ ቅንዓተ ቤትከ በልዐኒ"። መዝ68፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ማር 8፥34-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

photo content

photo content