fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ለሆነው ለሐዋርያው ቅዱስ በርቴሎሜዎስ እልዋህ በሚባል አገር አስተምሮ ብዙዎችን እግዚአብሔር ወደማወቅ ለመለሰበት ለመታሰቢያ በዓሉና ለቅዱስ ቴዎፍሎስ ከሚስቱ ጰጥሪቃ ከአምስት ወር ልጁም ከደማሊስ ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓልና ሩጻፋ በሚባል አገር ለሰማዕት ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን ለከበረችበት በዓል በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የዕለቱ ምልጣን ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ርዕዩ ዘከመ ባረከ እግዚእነ ዐሰርተ ወክልዔተ መሳይምተ ኀረየ ዐሰርተ ወክልዔተ ሐርያተ ሴሞሙ ኖሎተ ወረሰዮሙ አርድዕተ"። ትርጉም፦ ጌታችን ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያትን እንደባረከ እንደመረጠ እዩ ጠባቂዎችን አድርጎ ሾማቸው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሚስቱ ጰጥሪቃ የአምስት ወር ልጁ ደማሊስ፦ ይህ ቅዱስ እግዚአብሔርን በመፍራትና በአማረ አምልኮ ያደገ ነው ሰዎች ሒደው ቅዱስ ቴዎፍሎስ ክርስቲያን መሆኑን ለመኰንኑ ለአንቲጳጦስ ነገሩሩት መኰንኑም በዜውስ ጣዖት ቤት ሳለ ወደርሱ ያመጡት ዘንድ አዘዘ። ቅዱሱንም በአቀረቡት ጊዜ "አንተ ከወዴት ነህ? ሃይማኖትህስ ምንድን ነው?" አለው። እርሱም "የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስን ክርስቶስ የማምን ክርስቲያን ነኝ" አለ መኰንኑም "በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ለአማልክተሰ ሠዋ" አለው ቅዱሱም "ክብር ይግባውና ከጌታዬ ከኢየሱስ በቀር ለረከሱ አማልክት አልሠዋም" አለው። ❤ መኰንኑም የሆድ ዕቃው እስቲታይ ሰቅለው ይሠነጥቁት ዘንድ አዘዘ እርሱ ግን በጌታችን ኃይል ስለጠበቀ ምንም ምን አልደረሰበትም ሁለተኛም እሳትን አንድደው ከውስጡ እንዲጨምሩት አዘዘ ቅዱሱም በእሳት መካከል በጸለየ ጊዜ እሳቱ ተበተነ ምንም ምን ሳይነካው ከእሳት ውስጥ ወጣ። መኰንኑም ይህን አይቶ በረኃብ እንዲሞት አሥረው አጽንተው ይጠብቁት ዘንድ አዘዘ ከስምንት ቀንም በኋላ ሚስቱ ጰጥሪቃ ሕፃኗን ተሸክማ መጣች ምስክርም ሁኖ በክርስቶስ ስም ይሞት ዘንድ አጽናቸው። ❤ መኰንኑም ለቅዱስ ቴዎፍሎስ ምግብ የሰጠው እንዳለ ብሎ ሊመረምር ሔደ የእሥር ቤቱንም ደጅ በከፈተ ጊዜ ጣፋጭ የዕጣን መዓዛ ተቀበለው ቅዱስ ቴዎፍሎስንም በተነጠፈ መቀመጫ ላይ ተቀምጦ ሦስት መላእክት ማርና ወተት ሲመግቡት አገኘው በአየውም ጊዜ ደንግጦ ወደኋላው ተመለሰ። በማግሥቱም ቅዱስ ቴዎፍሎስን ወደ አደባባይ እንዲአመጡት አዘዘ እርሱም ሚስቱ ተከታትለው መጣ መኰንኑም "ዲዮስ ለሚባል አምላክ ሠዋ" አለው። ቅዱሱም "እኔ ዓለምን ሁሉ ለያዘ ለእውነተኛው አምላክ ለጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ለሌላ አልሠዋም" አለ። ❤ በዚያንም ጊዜ ለአንበሳ እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ አንበሳውም ሩጦ እግሮቹን ሳመ ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ አቈሰለው ተጋድሎውን በዚህ ፈጽሞ ነፍሱን ሰጠ ቅድስት ሚስቱ ጰጥሪቃም ሥጋውን አንሥታ ከሣጥን ጨመረች መኰንኑም እርሷንም ወደ አደባባይ አምጥተው ለአንበሳ እንዲሰጧት አዘዘ ሕፃኑም አንበሳውን በአየው ጊዜ ሣቀ የአምስት ወርም ልጅ ሲሆን "አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ አምናለሁ" ብሎ በአንበሳ አፍ ከእናቱ ጋር ተበላ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የሰማዕቱ ቅዱስ ሰርጊስ ቤተ ክርስቲያን የከበረችበት፦ ይህም ቅዱስ ሰርጊስ በሩጻፋ አገር በሰማዕትነት በአረፈ ጊዜ ምእመናን ሥጋውን ወስደው ገንዘው በእርሱ ዘንድ አኖሩት በፊቱም መብራቶችን አኖሩ የመከራውም ዘመን እስቲያልፍ በእነርሱ ዘንድ ተሠውሮ ኖረ። ከዚያም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያንን አነፁለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትንም ሰብስበው አከበሩዋት በዚች ቀን ኅዳር 19 ቀን ሥጋውንም በውስጧ አኖሩ ከእርሱም ድንቅ ተአምር ተገለጠ በእምነት ከእርሱ ለሚወስዱ ሁሉ በሽተኞችን የሚፈውሳቸው ሽታው እጅግ ጣፋች የሆነ የሽቱ ቅባት ከሥጋው የሚፈስ ሆኗልና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም እብል ሐዋርያ መስተጋድለ። በተወርዎ ባሕር ዕሙቅ እንዘ ሠቀ ጸጒር ጥብሉለ። በርተሎሜዎስ ገዳመ አመ ምስሌሆሙ ዔለ። በማየ ጸሎቱ ጽምዐ ነጋድያን አጥለለ። ወአንሥአ ዓዲ ዘሞቱ አግማለ"። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ሕጉ ለእግዚአብሔር ንጹሕ ወይመይጣ ለነፍስ። ስምዑ ለእግዚአብሔር እሙን ወያጠብብ ሕፃናተ። ኵነኔሁ ለእግዚአብሔር ርቱዕ ወያስተፌሥሕ ልበ"። መዝ18፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ማቴ10፥1-16። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ነው። መልካም ጾም ጊዜና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

photo content

በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ (ዘጸ3፡17)፣ (ሕዝ20፡12)፣ (ዘኁ15፡32-36)ፈሪሳውያን በነበራቸው የተሳሳተ አመለካከ
በእግዚአብሔር እና በህዝቡ መካከል ምልክት ነበረ ሰንበትን አለማክበር ግን ከባድ ቅጣት ያስከትል ነበር፡፡ (ዘጸ3፡17)፣ (ሕዝ20፡12)፣ (ዘኁ15፡32-36)ፈሪሳውያን በነበራቸው የተሳሳተ አመለካከት በሰንበት ቀን እንኳን መልካም ሥራን አይሰሩም ነበር፡፡ የዕለቱ መልዕክት ከአማን ዕይታ(93) 🙏ሰናይ ቀን🕊 🕊 ነገ መልካም ይሆናል ! መልካም ዕለተ ሰንበት

❣❣❣❣❣❣❣❣ የህዳር 19 መዝሙር፦ 💠💠💠💠💠💠💠💠 በ6 ሎቱ ስብሐት ወሎቱ አኮቴት፤ ለዘቀደሳ ለሠንበት፤ አልቦ አመ ኢሀሎ ወአልቦ አመ ኢሀሎ ፤ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር፤ ዘገብሮ በአርአያ ዚአሁ፤ ኩሉ ውስተ እዴሁ ውእቱ ይኮንን ሰማያት ወምድር፤ማ፦ገብረ በከመ ፈቀደ፤ አምላክ ወልደ እግዚአብሔር @EOTCW 🔹አመላለስ፦ 🍁🍁🍁 ኩሉ ውስተ እዴሁ ውእቱ ይኮንን ሰማያት ወምድር/2/ ገብረ በከመ ፈቀደ አምላክ ወልደ እግዚአብሔር/4/ @EOTCW 🌿🌿🌿🌿 ዘላይ ቤት፦ ገብረ በከመ ፈቀደ ገብረ በከመ ፤ /2/ አምላክ ወልደ እግዚአብሔር/4/ @EOTCW @EOTCW https://t.me/Eotcw # Join & share #

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዮሐ. 5:16-28፡ "ወበእንተ ዝንቱ ይሰድድዎ" - "ስለዚህም፡በሰንበት፡ይህን፡ስላደረገ፡አይሁድ፡ኢየሱስን፡ያሳድዱት፡ነበር፡ሊገድሉትም፡ይፈልጉ፡ነበር። ኢየሱስ፡ግን፦አባቴ፡እስከ፡ዛሬ፡ይሠራል፡እኔም፡ደግሞ፡እሠራለኹ፡ብሎ፡መለሰላቸው። እንግዲህ፡ሰንበትን፡ስለ፡ሻረ፡ብቻ፡አይደለም፥ነገር፡ግን፥ደግሞ፡ራሱን፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር፡አባቴ፡ነው፡ስለ፡አለ፥ስለዚህ፡አይሁድ፡ሊገድሉት፡አብዝተው፡ይፈልጉት፡ነበር። ስለዚህ፥ኢየሱስ፡መለሰ፥እንዲህም፡አላቸው፦እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥አብ፡ሲያደርግ፡ያየውን፡ነው፡እንጂ፡ወልድ፡ከራሱ፡ሊያደርግ፡ምንም፡አይችልም፤ያ፡የሚያደርገውን፡ዅሉ፡ወልድ፡ደግሞ፡ይህን፡እንዲሁ፡ያደርጋልና። አብ፡ወልድን፡ይወዳልና፥የሚያደርገውንም፡ዅሉ፡ያሳየዋል፤እናንተም፡ትደነቁ፡ዘንድ፡ከዚህ፡የሚበልጥ፡ሥራ፡ያሳየዋል። አብ፡ሙታንን፡እንደሚያነሣ፡ሕይወትም፡እንደሚሰጣቸው፥ እንዲሁ፡ወልድ፡ደግሞ፡ለሚወዳቸው፡ ሕይወትን፡ይሰጣቸዋል። ሰዎች፡ዅሉ፡አብን፡እንደሚያከብሩት፡ወልድን፡ያከብሩት፡ዘንድ፥ፍርድን፡ዅሉ፡ለወልድ፡ሰጠው፡እንጂ፡አብ፡ባንድ፡ሰው፡ስንኳ፡አይፈርድም።ወልድን፡የማያከብር፡የላከውን፡አብን፡አያከብርም። እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ቃሌን፡የሚሰማ፡የላከኝንም፡የሚያምን፡የዘለዓለም፡ሕይወት፡ አለው፥ከሞትም፡ወደ፡ሕይወት፡ተሻገረ፡እንጂ፡ወደ፡ፍርድ፡አይመጣም። እውነት፡እውነት፡እላችዃለኹ፥ሙታን፡የእግዚአብሔርን፡ልጅ፡ድምፅ፡የሚሰሙበት፡ሰዓት፡ይመጣል፡ ርሱም፡አኹን፡ነው፤የሚሰሙትም፡በሕይወት፡ይኖራሉ። አብ፡በራሱ፡ሕይወት፡እንዳለው፡እንዲሁ፡ደግሞ፡ለወልድ፡በራሱ፡ሕይወት፡እንዲኖረው፡ሰጥቶታልና። የሰው፡ልጅም፡ስለ፡ኾነ፡ይፈርድ፡ዘንድ፡ሥልጣን፡ሰጠው። በመቃብር፡ያሉቱ፡ዅሉ፡ድምፁን፡የሚሰሙበት፡ሰዓት፡ይመጣል።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.11 KB

18/3/2015 ዓ.ም (፲፰/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ኲሉ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር። በሰማይኒ ወበምድረኒ። በባሕርኒ ወበኲሉ ቀላያት፡፡ መዝ. 134÷6 🕯 ትርጉም በሰማይና በምድር። በባህርና በጥልቆች ሁሉ። እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በዕለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 10፥1-15 "ወጸውዖሙ ለ፲ወ፪ ሐዋርያት" -"ዐሥራ፡ሁለቱን፡ደቀ፡መዛሙርቱን፡ወደ፡እርሱ፡ጠርቶ፥እንዲያወጧቸው፡በርኩሳን፡መናፍስት፡ላይ፡ ደዌንና፡ሕማምንም፡ሁሉ፡እንዲፈውሱ፡ሥልጣን፡ሰጣቸው። የዐሥራ፡ሁለቱም፡ሐዋርያት፡ስም፡ይህ፡ነው፤መጀመሪያው፡ጴጥሮስ፡የተባለው፡ስምዖን፡ወንድሙ፡እንድርያስም፥የዘብዴዎስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ወንድሙ፡ዮሐንስም፥ ፊልጶስም፡በርተሎሜዎስም፥ቶማስም፡ቀራጩ፡ማቴዎስም፥የእልፍዮስ፡ልጅ፡ያዕቆብም፡ታዴዎስም፡ የተባለው፡ልብድዮስ፥ ቀነናዊውም፡ስምዖን፡ደግሞም፡አሳልፎ፡የሰጠው፡የአስቆሮቱ፡ይሁዳ። እነዚህን፡ዐሥራ፡ሁለቱን፡ኢየሱስ፡ላካቸው፥አዘዛቸውም፥እንዲህም፡አለ፦በአሕዛብ፡መንገድ፡አትሂዱ፥ወደሳምራውያንም፡ከተማ፡አትግቡ፤ ይልቅስ፡የእስራኤል፡ቤት፡ወደሚሆኑ፡ወደጠፉት፡በጎች፡ሂዱ፡እንጂ። ሄዳችኹም፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ቀርባለች፡ብላችሄ፡ስበኩ። ድውዮችን፡ፈውሱ፤ሙታንን፡አስነሡ፤ለምጻሞችን፡አንጹ፤አጋንንትን፡አውጡ፤በከንቱ፡ተቀበላችሁ፥በከንቱ፡ስጡ። ወርቅ፡ወይም፡ብር፡ወይም፡ናስ፡በመቀነታችሁ፥ወይም፡ለመንገድ፡ከረጢት፡ወይም፡ኹለት፡እጀ፡ጠባብ፡ወይም፡ጫማ፡ወይም፡በትር፡አታግኙ፤ለሠራተኛ፡ምግቡ፡ይገባዋልና። በምትገቡባትም፡በማናቸዪቱም፡ከተማ፡ወይም፡መንደር፥በዚያ፡የሚገባው፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡በጥንቃቄ፡ መርምሩ፤እስክትወጡም፡ድረስ፡በዚያ፡ተቀመጡ። ወደ፡ቤትም፡ስትገቡ፡ሰላምታ፡ስጡ፤ ቤቱም፡የሚገባው፡ቢሆን፡ሰላማችሁ፡ይድረስለት፤ባይገባው፡ግን፡ሰላማችሁ፡ይመለስላችሁ። ከማይቀበሏችሁም፡ቃላችሁንም፡ከማይሰሙ፡ሁሉ፥ከዚያ፡ቤት፡ወይም፡ከዚያች፡ከተማ፡ስትወጡ፡የእግራችሁን፡ትቢያ፡አራግፉ። እውነት፡እላችኋለሁ፥በፍርድ፡ቀን፡ከዚያች፡ከተማ፡ይልቅ፡ለሰዶምና፡ለገሞራ፡አገር፡ይቀልላቸዋል።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.54 KB

18/3/2015 ዓ.ም (፲፰/፫/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አጽናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ፡፡ መዝ. 18፥3 🕯 ትርጉም ነገር የለም፤ መናገርም የለም፤ ድምፃቸውም አይሰማም። ድምፃቸው በምድር ላይ ተሰማ። ቃላቸውም ሁሉ እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለኤላውትሮስ ሰማዕት ዘአበየ ሰጊድ ለአማልክት"። ትርጉም፦ ለአማልክት መስገድን እምቢ ላለው ለሰማዕት ኤላውትሮስ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

photo content
+1

❤ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለፊልጶስ ጽዑረ አባል በመቅሠፍት። ወለ ኤላውትሮስ ርጉዝ በብልሐ ኲናት። ምስለ እንትያ እባእ ኀበ ተርኅወ ገነት። ያሩጸኒ መዓዛሆሙ ወጼናሆሙ ዕፍረት። ለዝ ሐዋርያ ወለዝ ሰማዕት"። ትርጉም፦ በሾለ ጦር ለተወጋ ለኤውላትሮስና በግርፋት ሰውነቱ ተጨንቆ የተሠቃየ ለኾነ ለፊልጶስ ሰላምታ ይገባል፤ ከእንትያ ጋር ወደተከፈተ ገነት እገባ ዘንድ የዚኽ ሐዋርያና የዚኽ ሰማዕት ዕፍረት የሚባል መዐዛቸውና ሽቱዋቸው ያሩጠኝ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ)የኅዳር 18። https://t.me/Eotcw

photo content
+2

❤ ድንግል ዮናም የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነበትን ምክንያት እግዚአብሔር አዳምን ከፈጠረበት ጊዜ በመጀመር ልትነግራት ጀመረች አዳም እንደበደለና ከተድላ ገነት እንደ ወጣ በኖኅም ዘመን የጥፋት ውኃ መጥቶ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንደደመሰሰ የእግዚአብሔርን ሕግ የጠበቁ ስምነት ሰዎች ብቻ እንደ ቀሩ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ ሰዎች በምድር ላይ በበዙ ጊዜ እንደበደሉና ጣዖትን እንዳመለኩ እግዚአብሔርም ለአብርሃም እንደተገለጠለትና መርጦ ወዳጅ እንዳደረገው ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳንን እንዳጸና እስራኤልንም ከግብጽ አገር እንዳወጣቸው የሰውንም ወገን ጠላት ሰይጣንን ከማምለክ ለእርሱም ከመገዛት ያድነው ዘንድ የእግዚአብሔር ልጅ መምጣቱንና ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው መሆኑን ነቢያት እንደሰበኩ ነገረቻት። ❤ ሁለተኛም ስለ ከበረ ስሙ መከራ በመቀበል ለሚደክሙ ሰማያዊ ሀብት የዘላለም መንግሥትን እግዚአብሔር ስለ ሚሰጣቸው አስረዳቻት። አጥራስስም የዮናን ትምርቷን ሰምታ እጅግ ደስ አላት በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመነች። ❤ እሊህ ደናግልም ሌሊትና ቀን በተጋድሎ ተጠምደው በአንድነት ተቀመጡ የአጥራስስም አባቷ ይህን አያውቅም ከሌሊቶችም በአንዲቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዩት እናቱን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም አዩአት። እመቤታችንም ወደ ልጅዋ እግዚአብሔር እንደ ቁርባን አቀረበቻቸውና እርሱም ባረካቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ንጉሥ ወደ ጦርነት ሒዶ በተመለሰ ጊዜ ወደ ልጁ አጥራስስ ገብቶ "ልጄ ሆይ ወደ መሞሸሪያሽ ከመግባትሽ በፊት ለአምላክ አጵሎን ዕጣን ታሳርጊ ዘንድ ነዪ" አላት። አጥራስስ ድንግልም "አባቴ ሆይ ነፍስህና ሥጋህ በእጁ ውስጥ የሆነ የፈጠረህን በሰማይ ያለ አምላክን ትተህ ነፍስ የሌላቸው የረከሱ ጣዖታትን ለምን ታመልካለህ" ብላ መለሰችለት። ንጉሥም እንዲህ ያለ ነገር ከቶ ያልሰማውን ከልጁ አፍ በሰማ ጊዜ አደነቀ በልጁ ላይ ምን እንደደረሰ ልቧንም ማን እንደለወጠው ጠየቀ የፍላጽፍሮን ልጅ ድንግል ዮና የልጁን ልብ እንደ ለወጠች ነገሩት። ❤ ንጉሡም በእሳት ያቃጥሏቸው ዘንድ አዘዘ በወርቅና በብር በተጌጠ የግምጃ ልብሶችን እንደ ተሸለሙ አወጧቸው እነርሱ የነገሥታት ልጆች ስለሆኑ አላራቆቿቸውም ታላላቆችና ታናናሾች ሁሉም ሰዎች ስለ እሳቸው እያዘኑና እያለቀሱ ወጡ ነፍሳቸውንም እንዳያጠፉ ለንገሥ ይታዘዙ ዘንድ ለመኗቸው እነርሱ ግን ከበጎ ምክራቸው አልተመለሱም። ❤ በዚያንም ጊዜ ጉድጓድ ቆፈሩላቸውና በውስጡ እሳትን አነደዱ ነበልባሉም እጅግ ከፍ ከፍ አለ ያን ጊዜ አንዷ ከሁለተኛዋ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘው ወደ እሳት ውስጥ ተወረወሩ ፊታቸውንም ወደ ምሥራቅ መልሰው በመቆም ረጅም ጸሎትን ጸለዩ ከዚህም በኋላ ነፍሳቸውን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ እሳቱም እንደውኃ የቀዘቀዘ ሆነ ምእመናንም ሥጋቸውን አነሡ ተጠጋግተውም ልብሳቸውንም ቢሆን ወይም የራሳቸውን ጠጉር እሳት ምንም ምን ሳይነካቸው አገኟቸው ። የመከራውም ወራት እስቲፈጸም በታላቅ ክብር በአማረ ቦታ አኖርዋቸው ከዚህም በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸው ሥጋቸውን በውስጥዋ አኖሩ ከእርሳቸውም ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ደናግላን ሰማዕታት አጥራስስና ዮና ጸሎት ይማረን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የኅዳር 18 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "አልቦ ነገር ወአልቦ ነቢብ ዘኢተሰምዐ ቃሎሙ። ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ። ወእስከ አፅናፈ ዓለም በጽሐ ነቢቦሙ"። መዝ 18፥3-4 ወይም መዝ 145፥8-9። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 6፥4-17 ወይም ማቴ 10፥1-11። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ኵሉ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር። በሰማይኒ ወበምድርኒ። በባሕርኒ ወበኵሉ ቀላያት"። መዝ 134፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት ቈላ 1፥12-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 1፥13-21 እና የሐዋ ሥራ 19፥21-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 5፥16-28። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ወይም የቅዱስ አትናቴዎስ ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ፊሊጶስ የዕረፍትና የነቢያት (የገና) ጾም ጊዜ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። https://t.me/Eotcw

❤ በስመ አብ ወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ኅዳር ፲፰ (18) ቀን። ❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ለሆነው ለሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል፣ ከሮሜ አገር በንጉሥ እንድርያኖስ እጅ ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለቅዱስ ኤላውትሮስና ለእናቱ እንትያ ለዕረፍትና ለቅዱሳን ደናግል አጥራስስና ዮና ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከየዋህ ከቅዱስ አትናቴዎስ ከዕረፍቱ መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ በዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፮ "ስብሐት ወሎቱ አኰቴት ለዘቀደሳ ለሰንበት አልቦ አመ ኢሀሎ ወአልቦ አመ ኢሀሎ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ዘገብሮ ለሰብእ በአርአያ ዚአሁ ኵሉ ውስተ እዴሁ ውእቱ ይኴንን ሰማያተ ወምድረ ገብረ በከመ ፈቀደ አምላክ ወልደ እግዚአብሔር። ትርጉም፦ ሰንበትን ለቀደሳት፣ ላከበራት፣ ለለያት፣ ላጸናት ለእርሱ ክብርና ይገባል፣ እርሱ የሌለበትና የማይኖርበት ጊዜ የለም፣ እርሱ ያልነበረበት ጊዜ አልነበረም ሰውን በእርሱ አርአያና አምሳል የፈጠረው የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ሁሉ በእጁ ውስጥ ነው፣ ሰማይንና ምድርን ይገዛል፣ ያስተዳድራል እግዚአብሔር ልጅ እርሱ እንደ ፈቀደ ሁሉን አደረገ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ሐዋርያ ቅዱስ ፊሊጶስ፦ ቁጥሩ ከ12ቱ ሐዋርያት ውስጥ ነው በማቴ10፥3 ላይ እንደተጠቀሰው ከ12ቱ ሐዋርያት ውስጥ በ5ኛ ደረጃ ተጠቅሷል፡፡ ከገሊላ የተገኘ የቤተ ሳይዳ ሰው ሲሆን የግሪክ ሰዎችን ወደ ጌታችን ያቀረባቸው እርሱ ነው፡፡ ዮሐ12፥20-22፡፡ቅዱስ ፊሊጶስ ሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤልን "የናዝሬቱን ኢየሱስን አግኝተነዋል መጥተህ እይ…" በማለት ወስዶ ከጌታችን ጋር አገናኝቶታል፡፡ ዮሐ 1፡44-52፡፡ በኋላም ጌታችንን "አብን አሳየንና ይበቃናል" ብሎ የጠየቀውም ይኸው ሐዋርያ ፊሊጶስ ነው፡፡ ይህም ጥያቄው ለእኛ ለሁላችን መሠረታዊውን የክርስትና እውቀት እንድናገኝ ረድቶናል፡፡ ጌታችንም"እኔን ያየ አብን አይቷል፣ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ" በማለት ነው መልስ የሰጠው፡፡ ዮሐ14፥8-14፡፡ ❤ ሐዋርያው ቅዱስ ፊሊጶስ ወንጌልን ዞሮ በማስተማር ብዙዎች ጣዖት ማምለካቸውን ትተው በክርስቶስ እንዲያምኑ አድርጓል፡፡ ከጌታችን ዕርገት በኋላ ሐዋርያው ፍርግያ፣ ሰማርያና ጋዛ በሚባሉ አገሮች ወንጌልን ሰብኮ ብዙዎችን አሳምኖ አጥምቆአል፡፡ ሐዋርያው በመጨረሻ ወደ ታናሽዋ እስያ ሄዶ በሄራፖሊስ ከተማ ሲያስተምር ብዙዎችን በማሳመኑ ክፉዎች ይዘው አሠቃዩት፡፡ ከብዙ ሥቃይም በኋላ ጣዖት አምላኪዎች ኅዳር 18 ቊልቁል ሰቅለውት ሰማዕትነቱን ፈጽሞ የድል አክሊልን ተቀዳጅቷል፡፡ ክፉዎችም በግፍ ከገደሉት በኋላ ሥጋውን በእሳት ሊያቃጥሉት በወደዱ ጊዜ የታዘዘ መልአክ የሐዋርያውን ቅዱስ ሥጋ ከእጃቸው ነጥቆ ወሰደባቸውና ሰወረው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር በተመለከቱ ጊዜ ሁሉም በአንድ ድምፅ "ከቅዱስ ፊልጶስ አምላክ በቀር ሌላ አምላክ የለም"ብለው፡ጮኹ፡፡ ❤ አሠቀይተው ስለገደሉትም ተጸጽተው እጅግ አዘኑ፡፡ ክብር ይግባውና በጌታችን ካመኑ በኋላ የሐዋርያው የቅዱስ ፊሊጶስን ቅዱስ ሥጋውን ይሰጣቸው ዘንድ በጸሎት ለመኑ፡፡ ሰውን የሚወድ ቸር ይቅር ባይ ጌታችንም የቅዱስ ፊሊጶስን ቅዱስ ሥጋውን መልሶ ሰጣቸውና እጅግ ተደሰቱ፡፡ ከሐዋርያውም ቅዱስ ሥጋ ብዙ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራት ተፈጸሙላቸው፡፡ የሐዋርያውም መካነ መቃብሩ እስካሁንም ድረስ በዚህች ከተማ ይገኛል፡፡ ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስና ስንክሳር የኅዳር18። + + + ❤ ቅዱስ ኤላውትሮስና እናቱ ቅድስት እንትያ፦ ይህም ቅዱስ እግዚአብሔርን ከሚፈራ አንቂጦስ ከሚባል ኤጲስቆጶስ ዘንድ አደገ ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ዲቁና ተሾመ ደግሞ በዐሥራ ስምንት ዐመቱ ቅስና ተሾመ ከዚህም በኋላ በሃያ ዓመቱ አላሪቆስ ለሚባል አገር ጵጵስና ተሾመ። ❤ በዚያንም ወራት ንጉሥ እንድርያኖስ ወደ ሮሜ አገር መጣ ስለ ኤላውትሮስም ሰምቶ ወደርሱ ያመጣው ዘንድ ፊልቅስን አዘዘው ፊልቅስም በሔደ ጊዜ ቅዱሱን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ሲያስተምር አገኘው። ፊልቅስም ትምርቱን በሰማ ጊዜ አመነና በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቀ። ❤ ቅዱስ ኤላውትሮስንም ወደ ንጉሥ እንድርያኖስ በአደረሱት ጊዜ "ለአማልክት ሠዋ አንተ ነጻነት ያለህ ስትሆን ለተሰቀለ ሰው ለምን ትገዛለህ" አለው ። ኤላውትሮስም "ነጻነትማ ሰማይና ምድርን በፈጠረ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ነው" ንጉሡም መንኰራኩር ካለው የእሳት ማንደጃ ውስጥ ጨምረው እንዲአቃጥሉት አዘዘ በጨመሩትም ጊዜ እሳቱ ጠፋ መንኩራኩሩም ተቆራረጠ። ንጉሡም አይቶ አደነቀ የሚያደርገውንም አጥቶ ከወህኒ ቤት ጨመረው ርግብም ከገነት መብልን አምጥታለት በልቶ ጠገበ ። ቆሊሪቆስ የሚባለውም መኰንን አይቶ በቅዱስ ኤላውትሮስ አምላክ አምኖ በሰማዕትነት ሞተ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበለ። ❤ ከዚህም በኋላ ፈረሶችን አምጥተው በሠረገላ ላይ እንዲጠምዷቸው ቅዱስ ኤላውትሮስንም ከሠረገላው በታች አሥረው ሕዋሳቱ እስኪሰነጣጠቅ ፈረሶችን እንዲአስሮጡአቸው እንድርያኖስ አዘዘ። በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወረደ ከማሠሪያውም ፈትቶ ወደ ከፍተኛ ተራራ ወሰደው በዚያም እግዚአብሔርን እያመሰገነ ከአራዊት ጋር ተቀመጠ ። ❤ እንድርያኖስም አራዊትን ያድኑ ዘንድ ወታደሮቹን በአዘዘ ጊዜ በዚያ ተራራ ውስጥ ቅዱስ ኤላውትሮስን አግኝተው ከዚያ ወደ ንጉሥ እንድርያኖስ ወሰዱት። ንጉሡም ለአንበሳ እንዲሰጥ አዘዘ አንበሶችም የፊቱን ላብ ጠረጉለትና እግሮቹን ሳሙ ከዚህም በኋላ ተመልሰው ከአረማውያን መቶ ሃምሳ ሰው ገደሉ እንድርያኖስም አይቶ ቁጣን ተመላ ሁለት ወታደሮችን ከእንትያ እናቱ ጋር በጦር እንዲወጉት አዘዘ እርሷንም ብዙ ከአሠቃይዋት በኋላ የልጅዋን አንገት እንዳቀፈች ከእርሱ ጋር ወጓት ነፍሳቸውንም ኅዳር 18 ቀን በእግዚአብሔር እጅ ሰጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በቅዱስ ኤላውትሮስና በእናቱ ቅድስት እንትያ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ቅዱሳት ደናግል ሰማዕታት አጥራስስና ዮና፦ አጥራስስ ግን ጣዖታትን ለሚያመልክ ንጉሥ እንድርያኖስ ልጁ ናት እርሱም ከሰው ወገን ማንም እንዳያያት አዳራሽ ሠርቶ ለብቻዋ አኖራት እርሷ ግን ስለዚህ ዓለም ኃላፊነት የምታስብ ሆነች አውነተኛውንና የቀናውን መንገድ ይመራት ዘንድ በቀንና በሌሊት እግዚአብሔርን ትለምነው ነበር። "ወደ ፍላጽፍሮን ልጅ ወደ ድንግሊቱ ዮና ላኪ እርሷም የእግዚአብሔርን መንገድ ትመራሻለች" የሚላትን ራእይ አየች ከእንቅልፏም ስትነቃ በልቧ ደስ አላት ወደ ዮና ድንግልም ላከች እርሷም ፈጥና መጣች ለዮናም ሰላምታ ሰጠቻትና ከእግርዋ በታች ሰገደችላት የእግዚአብሔርንም ሃይማኖት ታሰተምራትና ትገልጥላት ዘንድ ለመነቻት።

፱ኛ ወረብ ዘካርያስ ርእየ @EOTCW

፰ኛ ወረብ ሙሴኒ ርእያ @EOTCW

፯ኛ ወረብ ለቅድስት ቤተክርስቲያን @EOTCW