fa
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

رفتن به کانال در Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

نمایش بیشتر
1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
#የሰላም_እናት ዘማሪ ዲን ኤፍሬም ፀጋዬ የሰላም እናት የመዳኒዓለም እመቤታችን ማርያም ግቢ ከቤታችችን ከልባችን ውዳሴ አለን ለአንቺ ድንግል እናታችን #አዝ ፀንተን እንኖራለን ግቢ ከቤታችን የያዕቆብ መሰላል ድንግል ድልድያችን አማልጂን ከልጅሽ ይፈር ጠላታችን ዳዊትም ነግሮናል አንቺ ነሽ ተስፋችን የብርሃን እናቱ ያለበሺን ግርማ ሞገስ ሆኖን ድንግል ወጣን ከጨለማ ስለዚህ ማርያም ሆይ እናገንሻለን ምልጃሽን ተማምነን ስምሽን እንጠራለን #አዝ ጠቢቡ እንዳለሽ ነይ እርግብዬ እመቤቴ ማርያም አንቺው ነሽ ተስፋዬ ፅንሱ የዘለለው ስምሽ ሲጠራ ለካ ስላለ ነው ጌታ ከአንቺ ጋራ ከፍ ከፍ ያለ ነው ክብርሽ ከፍጥረት የጌታዬ እናት መሰረተ ህይወት ትውልድ ይህን አምኖ ያመስግን አንቺን አንቺ ነሽ ምክንያቱ ከሞት እንዲድን #አዝ እሙ ለማስያስ ድንግል መፅናኛዬ የማህፀኑ ስግደት ሆኗል መማርያዬ ህይወት ያለሽ ሰማይ የጌታ ዙፋኑ ምልጃሽ ያው ነው ዛሬም አንቺን ለታመኑ መላዕክት በመንጦላይት የሚያመሰግኗት ክብሯ የገነነው እመቤታችን ናት እፁብ ነው የድንግል እረዳትነቷ የዳነ ይዘምር በአማላጅነቷ #አዝ አዳም ስለዳነ በማህፀንሽ ፍሬ ብፅይት ይላል ፍጥረት ደርሷልና ዛሬ እኔም እንደ ያሬድ እንደ ሊቁ አባቴ ማርያም ማርያም ስልሽ ጠግባለሁ እናቴ ክብርሽን ልናገር ቃላቶች ቢያጥሩኝ ዝመምታን መርጬ እፁብ ነሽ አልኩኝ አከብርሻለሁኝ በኤፍሬም ውዳሴ ቆሜ በማለዳ በሕርያቆስ ቅዳሴ https://t.me/Eotcw

#የያረድ_ዉብ_ዜማ የያረድ ዉብ ዜማ ድንግል እመቤቴ ስጦታዬ ነሺ /2/ በምን አንደበቴ እንዴትስ ባለ ቃል ማርያም ልበልሽ/2/ ምድርና ሰማዩ ተአምርሺን ይንገሩ  ፍጥረታት በሙሉ ስለ አንቺ ይመስክሩ  ተነግሮ የማያልቅ ድንቅ ነው ስራሽ  ድንግል ሆይ እናቴ አምሳያም የለሺ  ማርያም ድንግል እረዳቴ የምትደርሺልኝ ነይ ስልሽ በጭንቀተ  ታምርሺንም በአይነ አይቻለሁ  ጽዮን ሆይ ስልሽ ድንግል ሆይ እጠግባለሁ  #አዝ የእግዚአብሄር ጥበቡ በአንቺ ተገለጠ  የአዳም ዘር በሙሉ ከሞት አመለጠ  የመዳን ምክንያት ማርያም አንቺ ነሽ ለፍጥረቱ ሁሉ መሰላል የሆንሺ ነገን ባላውቅ እኔን ቢያስፈራኚ  አንቺ ካለሺኝ በፍጹም አልወድቅም  በፊትሺም እንድቆም ለምስጋና  ማርያም ልበልሽ በትህትና  #አዝ ትውልዱ በሙሉ ለምስጋና ይቁም  ባንቺ ስለሆነ የቀረለት መርገም  አዳም ከነልጁ በሰማይ በምድር  ማርያም ማርያም ይበል ተአምርሺን ይናገር  ጨለማው ከፊቴ ተገፈፈ  ማርያም በምልጃሽ ልቤ አረፈ  ከጎኔ ነይ ስልሺ እጽናናለሁ  እሳት ገደሉን ሁሉንም አልፈዋለሁ  https://t.me/Eotcw

​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። #ሰኔ_20_እና_21 👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል። የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው። ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ። ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር። ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል። የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች። ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን! Join https://t.me/Eotcw

በሰኔ 21 ቀን በቅዳሴ ጊዜ #መልዕክታት ኤፊ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥4-11 እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። #ምስባክ መዝ ፵፭ ቊ፬-፭ ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል ። እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሀወክ። ወይረድአ እግዚአብሔር ፍጽመ። #ትርጉም ልዑል ማደሪያውን ቀደሰ ፣ እግዚአብሔር በመካከልዋ ነው አትናወጥም፣ እግዚአብሔር ፈጥኖ ይረዳታል። #ወንጌል ማቴ16፥13-20። #ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእ(የጌታ ቅዳሴ)

photo content

photo content

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለቤተ ክርስቲያን ቅድስት ማኅደረ ስብሐት ምዕዋደ መላእክት እመ ኵሉ ሕዝብ። ሰላም ለኪ ቤተ ክርስቲያን እምየ ዘትጼንዊ መጽርየ ብኪ ጸናዕኩ እምከርሠ እምየ ቤተ ክርስቲያን አክሊለ ርእስየ ሰላም ለኪ። በሐኪ በሐኪ ቤተ ክርስቲያን እምነ ግበሪ ሰላመ ማእከሌነ እምኀይለ ጸላኢ ወፀር ዕቀቢ ኪያነ ትንብልናኪ የሀሉ ምስሌነ፤ ሰላም ለኪ"። ትርጉም፦ የሕዝብ ኹሉ እናት የመላእክት መዘዋወሪያ (ቦታ) የምስጋና ማደሪያ ለኾነችው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ይገባል። እንደ ቀጋ የምትሸትቺ ቤተ ክርስቲያን እናቴ ሰላምታ ለአንቺ ይገባል፤ ከእናቴ ማሕፀን ዠምሮ በአንቺ ጸናኍ፤ የራሴ አክሊል የምትኾኒ ቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ለአንቺ ይገባሻል። ሰላምታ የተገባሽ እናታች ቤተ ክርስቲያን ሰላም ሰላም እንልሻለን በመኻከላችን ሰላምን አድርጊ፤ ከፍጹም ጠላት እኛን ጠብቂ፤ ልመናሽም ከእኛ ጋራ ይኹን። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። https://t.me/Eotcw

+9
፩ኛ ወረብ እግዚአብሔር ውእቱ https://t.me/Eotcw

⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️ሥርዓተ ማኅሌት ዘሰኔ ሕንፀተ ቤታ"ሰኔ ፳፩" @eotcw @eotcw የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ) ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል። ⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️ @eotcw @eotcw መልክዐ ሥላሴ ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል: ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣኅል: እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል: ተፈጸመ ተስፋ አበው #በማርያም_ድንግል: ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል። ዚቅ በዕንቊ ሰንፔር ትትሐነጽ ወበመረግድ: ሃሌ ሉያ ለአብ: ሐጹር የዓውዳ: ትበርህ እምከዋክብት: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ: #ጽዮን ቅድስት ቤተክርስቲያን: ደብተራ ፍጽምት። ነግሥ ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክጣዕሙ: ለወልድኪ አምሳለ ደሙ: መሠረተ ሕይወት #ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ: ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ: እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ። ዚቅ እግዚአብሔር ውእቱ ብርሃንኪ ለዓለም: ወመሠረትኪ ለትውልደ ትውልድ: ኢየኀልቅ ብዝኃ ሰላምኪ: ወነገሥት ይትቀነዩ ለኪ: ያመጽኡ አምኃኪ እምርኁቅ ብሔር። ወረብ እግዚአብሔር ውእቱ ብርሃንኪ ለዓለም እግዚአብሔር/፪/ "ወመሠረትኪ"/፪/ እግዚአብሔር/፪/ ⛪️⛪️⛪️⛪️⛪⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️️ ⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️⛪️️@EOTCW መልክዐ ማርያም ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ: እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ: #ማርያም_ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ: ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ: ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ። ዚቅ በሐ በልዋ ተሳለምዋ: ዕግትዋ #ለጽዮን ወሕቀፍዋ: ደዩ ልበክሙ ውስተ ኃይላ: እንተ ተሐንጸት በስሙ: ወተቀደሰት በደሙ: ወተአትበት በዕጸ መስቀሉ: ጌሡ ኃቤሃ እስመ ሃይለ እግዚአብሔር ላዕሌሃ። @eotcw ወረብ "በሐ በልዋ"/፪/ ተሳለምዋ/፪/ ዕግትዋ ለጽዮን ወሕቀፍዋ ደዩ ልበክሙ ውስተ ሃይላ ለቤተክርስቲያን/፪/ መልክዐ ማርያም ሰላም ለሥዕርተ ርእስኪ ዘተንዕደ ጽፍሮሁ: ለአቡኪ በከናፍሪሁ: #ማርያም_ድንግል ለእግዚአብሔር ጽርሑ: ለገብርኪ እግዝእትየ እትኅድግኒ እላሁ: ከመ ኢይበሉኒ ፀር አይቴኑመ ምክሁ። @eotcw ዚቅ ወሀለወት አሐቲ #ድንግል ጽርሐ ቅድሳቱ ይእቲ ለልዑል: መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል: ወሥዕርታ ሜላት ፍቱል: ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል። ወረብ ወሀለወት አሐቲ "#ድንግል"/፪/ አሐቲ ድንግል/፪/ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል/፬/ @eotcw መልክዐ ማርያም ሰላም ለእስትንፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት: ከመ መዓዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት: #ማርያም_ድንግል ቤተ ቅድሳት: ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት: በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት። ዚቅ ገነይነ ለኪ ኦ ወለተ ዳዊት: ጽርሐ ቅድሳቱ ለወልድ: ዘወርቅ ማኅፈድ: ወሡራሬሃ ዘመረግድ። ወረብ "ጽርሐ ቅድሳቱ #ማርያም"/፪/ ዘወርቅ ማኅፈድ/፪/ ወሡራሬሃ ዘመረግድ ዘወርቅ ማኅፈድ/፪/ መልክዐ ማርያም ሰላም ለገቦኪ ዘሐመልማለ ወርቅ ክዳኑ: በከመ ዳዊት ይዜኑ: #ማርያም_ድንግል ለያዕቆብ ሞገሰ ስኑ: በልኒ እግዝእትየ አፈቅረከ አኮኑ: እንዘ ረዳኢትከ አነ ዘይክለከ መኑ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ አዳም ሕንፄሃ: ሐመልማለ ወርቅ ገበዋቲሃ: #ጽዮንሃ አምኁ ኪያሃ። ወረብ ሕንፄሃ "አዳም"/፪/ ሕንፄሃ ለቤተክርስቲያን/፪/ "ሐመልማለ ወርቅ"/፪/ ገበዋቲሃ ሐመልማለ ወርቅ/፪/ መልክዐ ማርያም ሰላም ለማኅጸንኪ ለእግዚአብሔር ማኅፈዱ: ዘሐነጸኪ የማነ ዕዱ: #ማርያም_ድንግል ምዕዝት ዘእምናርዱ: ኀቤኪ ያንቀዓዱ ለረኪበ ኲሉ መፍቅዱ: ምስለ ካልኡ ዓይንየ አሐዱ። ዚቅ ሃሌ ሃሌ ሉያ: ለቤተክርስቲያን ልዑል ሐነፃ: በጽድቁ ሐወፃ: እምነ ፀሐይ ይበርህ ገፃ። ወረብ ሃሌ ሃሌ ሉያ ለቤተክርስቲያን/፪/ ሐነፃ ልዑል ለቤተክርስቲያን/፪/ መልክዐ ማርያም በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ: ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ: ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ: #ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ: ዘጸገየ ማኅጸንኪ አፈወ ነባቤ። ዚቅ ኢይትአጸው አናቅጽኪ: ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ: ሠናይት ሰላማዊት: እንተ ናፈቅራ በጽድቅ: መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል። ወረብ ኢይትአጸው አናቅጽኪ ክቡራት ዕንቊ መሠረትኪ/፪/ ሠናይት ሰላማዊት "እንተ ናፈቅራ"/፪/ በጽድቅ/፪/ @eotcw ማኅሌተ ጽጌ በሠላስ አዕባን ገጸ ሥላሴሁ ለአምሮ: ሐኒጾ ቤትኪ #ድንግል ድኅረ ፈጸመ ሣርሮ: አመ ወረደ ለበዓል ምስሌኪ በአማኅብሮ: እንዘ ይብል ቃለ ለዘምሮ ልዑል ቀደሰ ማኅደሮ: ደናግል ለጽጌኪ ዘበጣ ከበሮ። ዚቅ በሥላሴሁ ሐነጸ ጥቅማ: #ቤተ_ማርያም ሰመየ ስማ: በሥላሴሁ ሐነጸ ጥቅማ። ወረብ በሥላሴሁ "ሐነጸ"/፪/ ጥቅማ #ለማርያም/፪/ ሰመየ ስማ #ቤተ_ማርያም/፪/ ምልጣን ተቀደሲ ወንስዒ ሃይለ ኦ ቤተ እግዚአብሔር: እስመ ናሁ ንጉሥኪ በጽሐ ዘያበርህ ለኪ በሃይሉ: ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት: ሐነጻ ወልድ ለዛቲ ቤት: ወፈጸማ መንፈስ ቅዱስ። @eotcw እስመ ለዓለም አመ ትትሐነጽ ኢየሩሳሌም: በዕንቊ ሰንፔር ወበከርከዴን በዕንቊ ክቡር: ዓረፋቲሃኒ ወማኅፈዲሃኒ በወርቅ ንጹሕ: ወመርህባሰ ለኢየሩሳሌም ዘቢረሌ: በዕንቊ አጶሮግዮን ወበዕንቊ ሦፎር ትትገበር: እንዘ ይብሉ በኲሉ ፍናዊሃ ሃሌ ሉያ: ይሴብሕዎ እንዘ ይብሉ: ይትባረክ እግዚአብሔር ዘአልዓላ ለጽዮን እምኲሉ ዓለማት። @eotcw ቅንዋት አመ ትትሐነጽ ኢየሩሳሌም በዕጸ መስቀሉ ክቡር: ወአመ ትትቄደስ በዕደዊሁ ለልዑል: ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን ትዌድሶ join and share the link https://t.me/Eotcw

+1
ማርያም ዋይዜማ። https://t.me/Eotcw

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ሥርዓተ ዋዜማ ዘሰኔ ሕንፀተ ቤታ #ለማርያም "ሰኔ ፳፩" 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 @eotcw ያሬዳውያን ዋዜማ ሃሌ ሉያ ሐነጽዋ ወሣረርዋ ለቤተክርስቲያን: ከመ ትኩን አርአያ ዘበሰማያት: ወከመ ትኩን ምሥተስራየ ኃጢአት: ዳዊትኒ ይቤ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም። @Eotcw @Eotcw ምልጣን ወከመ ትኩን ምሥተስራየ ኃጢአት: ዳዊትኒ ይቤ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም: ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም። አመላለስ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም/፪/ ዛቲ ይእቲ ምዕራፍየ ለዓለም/፬/ @Eotcw በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ እንተ ተሐንጸት በስሙ: ወተቀደሰት በደሙ: እንተ ተሐንጸት በስሙ። እግዚአብሔር ነግሠ አመ የሐንፃ እግዚአብሔር ለጽዮን: ወይቄድሳ ለኢየሩሳሌም: ኢየሱስ ክርስቶስ ምስለ መላእክቲሁ ዖደ: በደሙ ቀደሳ: በዕጸ መስቀሉ ዓተባ። @eotcw ይትባረክ ተለዓለ ቃሎሙ ለእለ ይሴብሑኪ: ኢይትዓጸው አናቅጽኪ። ሰላም ሐነጽዋ ለቤተክርስቲያን: ወሣረርዋ በመንፈስ ቅዱስ: ከመ ትኩን አርአያ ዘበሰማያት: ከመ ታድኅነነ እምዕቶነ እሳት: ተሀበነ ፍሥሐ ጽድቅ: ወሰላመ በዲበ ሰላም: ዘይክል ኲሎ ወአልቦ ዘይሰዓኖ። @eotcw አመላለስ ተሀበነ ፍሥሐ ጽድቅ ወሰላመ በዲበ ሰላም/፪/ ዘይክል ኲሎ ወአልቦ ዘይሰዓኖ/፬/ @EOTCW join and share ማህሌታውያን

photo content

photo content

❤ እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኞች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል ስለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሁኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው። እርሷን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እንድትወልደው ላደረገ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእርሷ በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ከምስር አገር የሆነ ሰማዕቱ ቅዱስ ጢሞቴዎስ፦ ይህም ቅዱስ አስቀድሞ ከእንዴናው ገዥ ከአርያኖስ ጭፍራዎች ውስጥ ነበር ሰው ሁሉ ጣዖታትን እንዲያመልክ የሚያዝ የዲዮቅልጥያኖስ የመልእክት ደብዳቤ በተነበበ ጊዜ ይህም ቅዱስ ከሕዝቡ መካከል ተነሥቶ የንጉሡን ደብዳቤ ወስዶ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ የከሀዲውን ንጉሥ የመልክት ደብዳቤ ቀደደ። ❤ መኰንኑም ድፍረቱን አይቶ ወደርሱ ገሥግሦ ሔደና የራሱን ጠጉር ይዞ አንሥቶ በምድር ላይ ጣለው ታላቅ ድብደባም እንዲደበድቡት አዘዘ ሁለተኛም ሁለመናው እስቲደቅ እንዲደቁሱት አዘዘ እርሱም "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እርዳኝ" እያለ ይጮኽ ነበር። ጌታችንም ትዕግሥቱን አይቶ መልአኩን ልኮ ከሥቃዩ አድኖ ጤነኛ አደረገው ወደ መኰንኑም ቀርቦ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከአንዱ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለምና አንተ ከሀዲ እፈር" አለው። ያን ጊዜም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው በመጋዝም መግዞ ሰቀለው ከዚያም በኋላ ሥጋው እንደ ሰም ቀልጦ እንደ ውኃ እስቲፈስ በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰለው ከከተማ ውጪም ጣሉት። ❤ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለምንም ጉዳት አንሥቶ ጤነኛ አደረገው። ወደ መኰንኑም ተመልሶ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለምና አንተ ከሀዲ እፈር" ብሎ ጮኸ። ይህንንም ድንቅ ተአምር አይተው ቁጥር የሌላቸው ብዙ አሕዛብ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ። ❤ መኰንኑም ማሠቃየቱ በሰለቸው ጊዜ ሰኔ 21 ቀን ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ። የድል አድራጊነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በድል አድራጊ ሰማዕት በቅዱስ ጢሞቴዎስ አማላጅነት ይማረን በረከቱ ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የእስክንድር አራተኛ ሊቀ ጳጳሳት አባ ከላድያኖስ፦ ይህም ቅዱስ በወንጌላዊው ቅዱስ ማርቆስ እጅ የክርስትና ጥምቀትን ተጠምቀ እርሱም ዲቁናን ሾመው ደግሞም ቅስና ሾመው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርትና ሕግ ጠንቅቆ ተማረ። ❤ አባ ሜልዮስ በዐረፈ ጊዜ ይህን አባት መርጠው በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ዐሥራ አንድ ዓመት ያህል በቀናች ሃይማኖት እያጸናቸው በትምህርት በምክር ሁሉ እንደሚገባ የክርስቶስን መንጋዎች ጠበቀ። ልዑል እግዚአብሔርም አገልግሎ ሰኔ 21 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ከላድያኖስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 21 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወንሰግድ ውስተ መካነ ኀበ ቆመ እግረ እግዚእነ። ተንሥእ እግዚኦ ውስተ ዕረፍትከ። አንተ ወታቦተ መቅደስከ"። መዝ131፥7-8። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ1፥39-57። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል። እግዚአብሔር ውስተ ማእከላ ኢትትሀወክ። ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ"። መዝ 44፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት ኤፊ 2፥13-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 2፥4-11 እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ16፥13-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፳፩ (21) ቀን። ❤ እንኳን ለአዳም ለዘር ሁሉ ድኅነት ለተደረገባት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በስሟ የተሰራችው የመጀመርያ ቤተ ክርስቲያን በልጇ በወዳጇ እጅ ለተቀደሰችበት ለከበረችበት ዓመታዊ በዓሏና በዓለም ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን መታነጽ መታሰቢያ ታላቅ በዓል፣ እመቤታችን ለቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ለተገለጠችለትና ሥዕሏን እንዲያሠራላት ለነገረችውና ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ላደረገች፣ ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ በመሸታ ቤት ባረድዋት በአንዲት ሴት ላይ ላደረገው ተአምር መታሰቢያ በዓል፣ ለምስር አገር ለሆነ ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ለእስክድርያ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ ለአባ ከላድያኖስ ለዕረፍት በሰላም በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ሜሮን ከተገኘችበትና የአስታፍን ዐፅም ከተገኘችበት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ፦ ሃሌ ሉያ "ተቀደሲ ወንሥኢ ኃይለ ኦ ቤተ እግዚአብሔር እስመ ናሁ ንጉሥኪ በጽሐ ዘያበርህ ለኪ በኃይሉ ለዛቲ ቤት ሣረራ አብ ቀዲሙ ለዛቲ ቤት ሐነፃ ወልድ ለዛቲ ቤት ወፈፀማ መንፈስ ቅዱስ። ትርጉም፡- የእግዚአብሔር ሆይ ቤተ ሆይ ተቀደሺ (ተከበሪ) ኃይልንም ውሰጂ (አድርጊ) እነሆ በኃይ የሚበራልሽ ንጉሥሽ ደረሰ፤ ይኽቺን ቤት አብ አስቀድሞ መሠረታት፤ ይኽቺንም ቤት ወልድ አነጻት (ሠራት) ፈጸማት (ጨረሳት)። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ በዚች ዕለት የአዳምና የዘሩ ድኅነት የተደረገባት አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታላቁ በዓል መታሰቢያና በዓለም ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መታነፅ መታሰቢያ ነው። ከሁሉ አስቀድሞ ያቺ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያት ዘመን ብቻዋን ታነፀች። ❤ ይኸውም ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ በአሕዛብ ውስጥ በሰበኩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሰዎች ቤቶች በቀር ቅዱስ ቊርባንን የሚቀበሉበት ቤተ ክርስቲያንም አልነበራቸውም ነበር። ስለዚህም ወደ ቅዱሳን ጴጥሮስና ወደ ሐዋርያት ሁሉ ስለ ቤተ ክርስቲያን መታነፅ ጉዳይ እየለመኑ መልእክትን ላኩ። ሐዋርያትም እንዲ ብለው መለሱላቸው "ክብር ይግባውና ያለ ጌታችን ፈቃድ እኛ ምንም ምን አንሠራም። ነገር ግን የምንሠራውን እስኪያስረዳን ድረስ ወደ እግዚአብሔር እየጸለዩና እየማለዱ አንድ ሱባኤ ይጾሙ ዘንድ ወደ ሃይማኖት የተመለሱ አሕዛብን እዘዙአቸው" እንዲህም አዘዙአቸው። ❤ በሱባኤውም ፍጻሜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጾላቸው ሐዋርያትም ሁሉ ከየአገሮች ሁሉ እስከ ፊልጵስዩስ በደመና ሰበሰባቸው ከእርሳቸውም ጋር ቅዱሳን ጳውሎስና በርባስ ነበሩ ጌታችንም ባረካቸው እንዲህም ብሎ ነገራቸው "ይቺ ዕለት በእናቴ በማርያም ስም በአራቱ ማእዘነ ዓለም አብያተ ክርስቲናት እንዲታነፁ የፈቀድኩባት ናት"። ይህንንም ብሎ በከተማዋ በስተ ምሥራቅ በኵል አወጣቸው የቤተ ክርስቲያኒቱም ቦታና መሠረቷን ወሰነላቸው ከእርሳቸውም ጋራ የእግዚአብሔር ኃይል ነበረ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕንፃዋ እስከ ተፈጸመ ድረስ ሦስቱ ደንጊያዎች በሐዋርያት እጆች ውስጥ ይለመልሙ ነበር ጌታችንም ንዋየ ቅዱሳቷን አልባሳትዋንና መሠዊያዋን አዘጋጀ። ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን እጁን በቅዱስ ጴጥሮስ ራስ ላይ ጭኖ በአራቱ ማዕዘነ ዓለም ውስጥ "አርሳይሮስ" ብሎ ሾመው ይህም ሊቀ ጳጳሳት ማለት ነው "ለሐዋርያት አለቃ ለቅዱስ ጴጥሮስ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የጳጳሳት አለቃ ይሆን ዘንድ ይገባዋል ይገባዋል ይገባዋል" እያሉ ሰማያውያን መላእክትና ምድራውያን ሰዎች ሦስት ጊዜ አሰምተው ተናገሩ። ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን የቊርባኑን ቅዳሴ ሥርዓት ያከናውኑ ዘንድ ለሕዝቡም ሥጋውን ደሙን ያቀብሏቸው ዘንድ አዘዛቸው እንዲህም የሚል አለ ራሱ መድኃኒታችን ቀድሶ ሥጋውንና ደሙን ለሐዋርያት አቀበላቸው። እንዲህም አላቸው "በዚች ቀን የእጃቸውን ሥራ እንዳይሠሩ ሕዝቡን ሁሉ እዘዙአቸው ይኸውም በሰኔ ወር ሃያ አንድ ቀን ነው"። ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ከእርሳቸው ዘንድ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ። ከዚያች ቀን ጀምሮ አባቶቻችን ሐዋርያት በዓለሙ ሁሉ ውስጥ አምላክን በወለደች በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን የሚያንሳንፁ ሆኑ። + + + ❤ በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በአባ ባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት። ❤ ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ፤ ባለጸጋውም "ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው" አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ ልጆቹም ፈሩ ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና ዕንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት። ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዒሊ ሰጠው። ❤ እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛም ሰው እጅ ወስዶታልና። እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ ያንንም ሠሌዳ አገኘው ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው። ❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳችው እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው። ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ ጠበል አፈለቀ በውስጥዋም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ። እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ዘር በሃያ አንድ ቀን ነው። ❤ በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው። ቅዱስ ባስልዮስም "ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ" አላት በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት እርሷ የረከሰች ስትሆን ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

photo content

❤ ከዚያም በኋላ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴር ሠራዊቱን ሁሉ ሰበሰበና ወጥቶ ሰማርያን ከበባት፡፡ በሰማርያም ታላቅ ራብ ሆኖ ነበር፤ እነሆም፥ የአህያ ራስ በአምሳ ብር፥ የርግብም ኩስ የጎሞር ስምንተኛ የሚሆን በአምስት ብር እስኪሸጥ ድረስ በሀገራቸው የሶርያ ሰዎች ሰፍረው ተቀመጡ፡፡ በዚህም ጊዜ እናት ልጇን ቀቅላ እስክትበላ ድረስ እጅግ አሠቃቂ ታላቅ ርሃብ ሆነ፡፡ ይህም ክፉ የርሃብ ዘመን በነቢዩ ኤልሳዕ ጸሎት በአንዲት ቀን ተለውጦ የጥጋብ ዘመን ሆኗል፡፡ 2ኛ ነገ 6፥8-33፣ 7፥1-20፡፡ ኤልሳዕም በዘመኑ ትንቢትን እየተናገረ እጅግ ታላላቅ ተአምራን እያደረገ እግዚአብሔርንም ሕዝቡንም ሲያገለግል ከኖረ በኋላ ሰኔ 20 ቀን ዐርፏል፡፡ ከሞተም በኋላ ዐፅሙ የሞተን ሰው አሥነቷል፡፡ 2ኛ ነገ 13፡21፡፡ ይኸውም የሞአብ ሰዎች አገራቸውን ከበው ሳለ አንድ ሰው ሞቶ ሊቀብሩት ሲወስዱት አደጋ ጣዮች አዩአቸው፡፡ እነርሱም ደንግጠው ሬሳውን በአልሳዕ መቃብር ላይ ጣሉት፡፡ በዚህም ጊዜ ሬሳው የአልሳዕ ዐፅም በነካው ጊዜ አፈፍ ብሎ ከሞት ተነሥቶ በእግሮቹ ቆሟል፡፡ ❤ ይህም ነቢይ በአራት ነገሥታት ዘመን ትንቢት ተናገረ እሊህም ኢዮራም፣ አካዝያስ ኢዩና ዮአስ ናቸው የትንቢትም ዘመን ከሃምሳ ዓመት በላይ ነው። ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም ከመምጣቱ አስቀድሞ ትንቢት ተናገረ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ በቅዱስ ኤሌሳዕ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 20 ስንክሳርና መዝገበ ቅዱሳን። + + + ❤ "ሰላም ለኤልሳዕ እምኀበ ኤልያስ ዘሰአለ። ካዕበተ መንፈስ ቅዱስ አመ ሰማየ ተለዓለ። ወበዝንቱ ረኪቦ ዐቢየ ኃይለ። ክልኤተ ጊዜ አንሥኦ ሙታን ክህለ። ወክልኤተ ጊዜ ፈለገ ከፈለ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 20። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ሰኔ ፳ (20) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ ነቢይ ለየሳፋጥ ልጅ ለኤልሳዕ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለአቡነ ዘርዐ ሃይማኖት ዘሳይንት በዓለ ለዕረፍት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕት አርጣልስ፣ ከሚናስና ከዘቡፍር ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ታላቁ ነቢይ ቅዱስ ኤልሳዕ፦ የዚህም ነቢይ መጠራቱ እንዲህ ኾነ ኤልያስ አልፎ ሲሔድ የሳፋጥ ልጅ ኤልሳዕን በፊቱ ዐሥራ ሁለት ጥማድ አስጠምዶ ሲያሳርስ አገኘው እርሱም በነዚያ የተሾመ ነበር ኤልያስም ሔዶ መጎናጸፊያውን በላዩ ጣለበት። ኤልሳዕም ጥማዱን ትቶ ኤልያስን ተከተለው ኤልሳም "አባቴ እወድሃለሁ አንተንም እከተላለሁ" አለው ኤልያስም "ብላቴናዬ አድርጌሃለሁና ተመለስ" አለው። እርሱም ኤልያስን ከመከተል ተመለሰ ዐሥራ ሁለቱንም ጥማድ በሬዎች ወስዶ አረደ በላመ ፈጅ ጋኖችም ቀቅሎ ለሕዝቡ አቀረበላቸው እነርሱም በሉ ኤልያስንም ተከተሎት ሔደ ብላቴናውም ሆነ። ብዙ ዘመናትም ሲያገለግለው ኖረ። ❤ ኤልያስም በሚያርግበት ጊዜ ኤልሳዕን "ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ሳልወጣ አደርግልህ ዘንድ የምትሻውን ለምነኝ" አለው ኤልሳዕም "በአንተ ያደረ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ ዕጥፍ ሁኖ ይደርብኝ" አለው። ኤልያስ ኤልሳን "ድንቅ ነገርን ለመንከኝ ነገር ግን ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ብታየኝ ይደርብህ ከአንተ ተለይቼ ወደ ሰማይ ስወጣ ባታየኝ ግን አይሆንልህም" አለው። ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሔዱ የእሳት ፈረስና እሳት ሠረገላ መጣ ወደ መካከላቸውም ገብቶ አራራቃቸው ኤልያስም በመነዋወጥና በጥቅል ነፋስ እንደዚህ ወደ ሰማይ ዐረገ። ❤ ኤልሳዕም አይቶ "የእስራኤል ኃይላቸውና ጽንዓታቸው አባ አባ ብሎ ጮኸ። ከዚህ በኋላም ዳግመኛ አላየውም ልብሶቹንም ከሁለት አድርጎ ከፈላቸው። ኤልያስም ለኤልሳዕ መጠምጠሚያውን ጣለለት በኤልሳዕ ራስ ላይም ወረደ ኤልሳዕም ተመልሶ በዮርዳኖስ ባሕር ዳር ቆመ። በራሱ ላይ የወረደች የኤልያስንም መጠምጠሚያ ይዞ ውኃውን መታባት ውኃውም አልተከፈለም "የኤልያስ ፈጣሪ ወዴት ነው ይህስ እንዴት ነው" አለ ከዚህ በኋላም ውኃውን መታው ውኃውም ተከፍሎ ወዲያና ወዲህ ቆመ ኤልሳዕም ተሻገረ። በዚህም ኤልሳዕ የመንፈስ ቅዱስን ሀብት በዕጥፍ እንደተቀበለ ታወቀ። ኤልያስ የወንዙን ውኃ አንድ ጊዜ ከፈለ ኤልያስ አንድ ምውት አስነሣ ኤልሳዕ ግን ሁለት ምውት አስነሣ። ❤ ከዚህም በኋላ ኤልሳዕ ወደ ኢያሪኮ ሲገባ የሀገሪቱ ሰዎች ውኃቸውን ሲጠጡት ሴቶቹ እንደሚመክኑ ነገሩት፡፡ እርሱም "ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ" ብሎ ወደ ምንጩ ውሃ ሄዶ ጨውን ጨመረው፡፡ ውሃውም ጣፋጭ ሆነ፣ እርሱን ሲጠጡ የሚመክኑትም ሴቶች ወላዶች ሆኑ፡፡ ወደ ቤቴልም በወጣ ጊዜ ከከተማው ሲወጡ ታናናሽ ልጆችን አገኘ፡፡ እነርሱም "አንተ ራሰ በራ ውጣ" እያሉ ሲዘባበቱበት የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ቢረግማቸው ወዲያው ሁለት ድቦች ከዱር ወጥተው አርባ ሁለት ልጆችን ገደሉ፡፡ ❤ ኤልሳዕ ሌላው የሚታወቅበት ነገር የመበለቲቷን ቤት በበረከት በመሙላቱ ነው፡፡ ሴቲቱ ወደ ኤልሳዕ መጥታ "የምታውቀው የእግዚአብሔር ሰው የሆነው ባሌ ስለሞተ አሁን ባለዕዳ ሁለቱን ልጆቼን ወስዶ በባርነት ሊገዛቸው" አለችው፡፡ እርሱም በቤቷ ምን እንዳለ ጠየቃት፡፡ "ለእኔ ለባሪያህ ከዘይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አንዳች የለኝም" አለችው፡፡ እርሱም ከጐረቤቶቿ ባዶ ማድጋዎችን ተውሳ እንድታመጣ ነግሯት ማድጋዎቹን ሁሉ በጸሎቱ በተአምራት በዘይት ሞልቶላታል፡፡ እርሷም ዘይቱን ሸጣ ለባለ ዕዳው ከፈለች፡፡ የተረፈውንም ከልጆቿ ጋር ተመገበች፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ መካን ስለነበረችው ስለሱነማዊቷ ሴት ግያዝ ነግሮት ኤልሳዕ ካስጠራት በኋላ "በሚመጣው ዓመት በዚህ ወራት ወንድ ልጅ ትታቀፊአለሽ" ብለ ከነገራት በኋላ በዓመቱ ፀንሳ ወልዳለች፡፡ ልጁም ካደገ በኋላ ከአባቱ ጋር ወደ አዝመራ ወጥቶ ሳለ ታመመና በእናቱ እቅፍ እያለ ሞተ፡፡ በሞተም ጊዜ በእግዚአብሔር ሰው በነቢዩ አልጋ ላይ አስተኝታው በሩንም ዘግታበት ወጣች፡፡ ሎሌዋን ይዛ አህያዋን ጭና የእግዚአብሔርም ሰው ኤልሳዕ ወዳለበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣችና የልጇን መሞት ነገረችው፡፡ ኤልሳዕም ሄዶ የሞተውን ልጇን ከሞት አስነሣላትና "ልጅሽን አንሥተሽ ውሰጂ" አላት፡፡ እርሷም ለኤልሳዕ ከሰገደችለት በኋላ ልጇን ወሰደች፡፡ ❤ ነቢዩ ኤልሳዕ የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንን በዮርዳኖስ ውኃ እንዲጠመቅ ካደረገው በኋላ ከለምጹ ፈውሶታል፡፡ ንዕማንም ከለምጹ ከዳነ በኋላ ለኤልሳዕ ወርቅና ብር ልብስም ሊሰጠው ሲል አልሳዕ በሕያው እግዚአብሔር ስም ምሎ አልቀበልም አለው፡፡ ንዕማንም "እነሆ ከእስራኤል ዘንድ በቀር በምድር ሁሉ አምላክ እንደሌለ አወቅሁ" ብሎ ከመሰከረ በኋላ ሁለት የበቅሎ ጭነት አፈር ወስዶ ወደ ሀገሩ ሶርያ ሄደ፡፡ ❤ ደቀ መዝሙሩ ግያዝ ግን ንዕማንን በመንገድ ተከትሎ "ሁለት ጎልማሶች ከተራራማው ከኤፍሬም አገር ወደ እኔ መጥተዋልና አንድ መክሊት ብርና ሁለት መለወጫ ልብስ ትሰጣቸው ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጌታዬ ላከኝ" በማለት በኤልሳዕ ስም ዋሽቶ ተቀበለ፡፡ ኤልሳዕም ግያዝ በሥውር ያደረገውን ዐውቆ አዘነ፡፡ ወደ እርሱም ተመልሶ በመጣ ጊዜ "ግያዝ ሆይ፥ ከወዴት መጣህ?" አለው፡፡ እርሱም "እኔ ባሪያህ ወዴትም አልሄድሁም" አለ፡፡ ኤልሳዕም "ያ ሰው ከሰረገላው ወርዶ ሊቀበልህ በተመለሰ ጊዜ ልቤ ከአንተ ጋር አልሄደምን?" ብሎ ያደረገውን እንዳወቀበት ከነገረው በኋላ "እንግዲህስ የንዕማን ለምጽ በአንተ ላይ ለዘላለምም በዘርህ ላይ ይጣበቃል" አለው፡፡ ግያዝም እንደ በረዶ ለምጻም ሆኖ ከእርሱ ዘንድ ወጣ፡፡ ከዚህም ሌላ ኤልሳዕ ውኃ ውስጥ የወደቀውን የብረቱን ምሳር በውኃው ላይ ዕንጨቱን ጥሎ የሰመጠውን ብረት ተንሳፎ እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ ❤ የሶርያ ንጉሥ ከእስራኤል ጋር ለመዋጋት በዱር ሰፍሮና ተደብቆ ሳለ የእግዚአብሔር ሰው ኤልሳዕ "ሶርያውያን በዚያ ተደብቀዋልና በዚያ ስፍራ እንዳታልፍ ተጠንቀቅ" ብሎ ወደ እስራኤል ንጉሥ ላከ፡፡ የእስራኤልም ንጉሥ በዚያ ባለመሄድ ራሱን አዳነ፡፡ የሶርያም ንጉሥ ባሪያዎቹን ጠርቶ "ከእኛ ዘንድ ከእስራኤል ንጉሥ ጋር የተወዳጀ እንዳለ ንገሩኝ?" አላቸው፡፡ ከባሪያዎቹም አንዱ "ጌታዬ ሆይ በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውን በእስራኤል ዘንድ ያለ ነቢይ ኤልሳዕ ለእስራኤል ንጉሥ ይነግረዋል" አለው፡፡ የሶርያ ንጉሥ ኤልሳዕ ያለው በዶታይን እንደሆነ ሲነግሩት የዶታይንን ከተማ ከበባት፡፡ የኤልሳዕ ሎሌ ማለዳ ተነሥቶ የከበባቸውን ጭፍራና ፈረሶቻቸውን ሲመለከት እጅግ ፈራ፡፡ ኤልሳዕም "ከእኛ ጋር ያሉት ከእነርሱ ጋር ካሉት ይበልጣሉና አትፍራ" አለው፡፡ "አቤቱ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን እባክህ ግለጥ" ብሎ በመጸለይ የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፡፡ ❤ ኤልሳዕም በጸሎቱ ሁሉንም ዕውር አደረጋቸው፡፡ ወደ ሰማርያም እየመራቸው ከወሰዳቸው በኋላ ዳግመኛ ያዩ ዘንድ ጸለየና ሁሉም ማየት ቻሉ፡፡ የእስራኤልም ንጉሥ ባያቸው ጊዜ አልሳዕን "አባቴ ሆይ?" ባለው ሰዓት እንዳይገድላቸው ይልቁንም አብልቶ አጠጥቶ እንዲልካቸው ነገረው፡፡ እነርሱም በልተው ጠጥተው ሲያበቁ ወደ ጌታቸው ሄዱ፡፡