ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
#ለጣዖት_አንሰግድም
ለጣዖት አንሰግድም ብለው
ሶስቱ ህፃናት እምቢ አሉ
የምናመልከው አምላክ
ከእሣት ያወጣል እያሉ
#አዝ
በንጉሱ ቁጣ ልባቸው ሳይርድ
አንዳችም ሣይፈሩ በእሣቱ መንደድ
በእምነት በርትተው መከራን ታገሱ
የታመኑት ጌታ ፈረደ ለነሱ
#አዝ
በመካከል ታየ ከእነሱ ጋር
መላኩ ገብርኤል ታዞ ከእግዚአብሔር
በእሳቱ መካከል ምስጋናን ጀመሩ
ስቡህኒ ብለው ለስሙ ዘመሩ
#አዝ
የእሳቱን ነበልባል ውሀ እያደረገ
የእግዚአብሔር መላክ ነብሳቱን ታደገ
አንዳች ሳይነኩ ከእሳቱ ወጡ
የእግዚአብሔርን ክብር ለዓለም ገለጡ
#አዝ
ተመላልሰው ታዩ በእሳቱ መሀል
ከራሳቸው ፀጉር አንዲቶአ ሳትጎል
የከለዳውያን የእሳት ምድጃቸው
ህፃናቱን ትቶ እነሱን በላቸው
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ ሰላም ለአርጌንዮስ ወቢልፍዮስ፤ ወአርሶፎኒስ ወጴጥሮስ ወአስኪርዮን ሰማዕታተ ወልድ እለ ኀመይዎሙ ኀበ ኅርወተ ጒንድ፤ ወእለ ሰቀልዎሙ፡ቊልቊሊተ ዘስምዕ ፍኖተ እለ ፈጸመ ሩጸተ"። ትርጉም፦ የምስክርነት መንገድን ሮጠው የጨረሱ በተበሳ (በፍልፍል) ግንድ ላይ አስረው የቊልቊሊት (ዘቅዝቀው) የሰቀሏቸው የወልድ ሰማዕታት ለኾኑ ለአርጌንዮስ፤ ለቢልፍዮስና አርሶፎኒስ፤ ለጴጥሮስና አስኪርዮን ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ እንኳን ዘመነ አስተምሮ ለሚታሰብበት ሰንበት (እሑድ) ቀን እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን። እንደ ቤተ ክርስቲያኖች አስተምሮ ከሰኔ 18 እስከ ሰኔ 25 አስተምሮ ይባላል።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ "ናክብር ሰንበቶ በጽድቅ ወኢንኅድግ ሥርዓቶ ለዘውእቱ ባሕቲቱ ሃሌ ሉያ ጻድቅ ውእቱ ጽድቅ ይኴንን በመንግሥቱ ሃሌ ሉያ ይገብር ነግሀ እንተ ጸብሐት የሀበነ ምሕረቶ ወንሕነኒ ርቱዓ ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ሃሌ ሉያ አምላክነሰ አምላክ አድኅኖ ይክል ኵሎ ወአልቦ ዘይሰዓኖ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ጽድቅ ቃሉ ወእሙን ነገሩ። ትርጉም፦ ብቻውን ቅድመ ዓለም ለነበረ ዛሬም ላለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም ለሚኖር ምስጋና ይገባል፤ መልካም ሥራ በመሥራት በእውነት ሰንበቱን እናክብር፤ ሥርዓቱንም አንተው፤ እርሱ ጻድቅ ነው፤ በመንግሥቱ እውነትን ይፈርዳል፤ ቅድመ ዓለም ለነበረ ዛሬም ላለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም ለሚኖር አምላካችን የሚሳነው ነገር የሌለ ሁሉን ማድረግ የሚችል አዳኝ አምላክ ነው፤ ቅድመ ዓለም ለነበረ ዛሬም ላለ ወደፊትም ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም የሚኖር አምላካችን ቃሉ የታመነ ነው፤ ነገሩም እውነት ነው። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "አንተሰ እግዚኦ መሐሪ ወመስተሣህል። ርኁቀ መዓት ወብዙኀ ምሕረት ወጻድቅ። ነጽር ላዕሌየ ወተሣሃለኒ"። መዝ 85፥15-16። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 5፥12-ፍ.ም፣ 3ኛ ዮሐ 1፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 16፥1-14። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 22፥1-23። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም በዓለ ዕለተ ሰንበትና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ ከዚህ በኋላ በዚያች ቀንና በዚያች ሌሊት በሥጋው ላይ እሳትን አነደዱ እሳቱም በላዩ እየነደደ ምንም ምን አልነካውም ወስደውም በገበያ ውስጥ ጣሉት ከዚያም አንሥተው በባሕር ውስጥ ጣሉት በእግዚአብሔርም ፈቃድ ወደ ደሴቱ ወደብ ዳር ደረሰ እናቱም ጠብቃው ነበርና ወስዳ ገነዘችው ለጥቂት ወራትም በቤቷ ውስጥ ሸሸገችው።
❤ ከዚህም በኋላ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠሩለት ሥጋውንም በውጧ አኖሩ ከእርሱም ታላላቅና ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ በሐዲስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ለዘላለም ትኑር አሜን።
+ + +
❤ አባ ብሶይ አኖብ፦ የስሙ ትርጓሜውም የጠራ ወርቅ ማለት ነው። ይህም ቅዱስ ከድምያጥ አውራጃ ስሟ ባኖስ ከሚባል አገር ከአቅራብ መኰንን ከቆጵርያኖስ ጭፍሮች ውስጥ ከከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ልጆች ወገን ነበር በዚህም ቅዱስ በመኰንኑ ዘንድ ነገር ሠሩበት። ቅዱሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በፊቱ ታመነ።
❤ ወደ እንዴናውም ወሰዱት በመኰንኑ አርያኖስ ፊት ቁሞ በጌታችን ታመነ አርያኖስም በእርሱ ላይ ተቆጣ "ለአማልክትም ሠዋ" አለው። አልታዘዘለትም ሥቃዩንም አልፈራም መኰንኑም ወስዶ ጽኑዕ ሥቃይ አሠቃየው ከዚያም ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ ወደሚገድሉበት ቦታም ሊወስዱት አወጡት ብዙ ሕዝብም ይከተሉት ነበር እነሆ ከዚያም የአርያኖስ መኰንን አንበሶች ነበሩ። የሚጠብቃቸውም ሰው ነበር እነርሱም በብረት ሰንሰለት ታሥረው ነበር ከእነርሱም አንዱ አንበሳ የብረት ሰንሰለቱን በጥሶ ሩጦ ወደ ቅዱስ ደረሰ። የእግዚአብሔርም መልአክ ቅዱሱን በአንበሳው ጀርባ ላይ አወጣውና ዐይነ ፀሐይ ወደሚባል አገር እስከሚያደርሰው በረረበት ቅዱሱ ግን ዐይኑን ሸፍኖ ስለ ነበር ውዴት እንዳለ አላወቀም በዚያም ራሱን በሰይፍ ቆረጡት የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ብሶይ አኖብ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 19 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለጻድቃን እለ በቋዓት"። ትርጉም፦ በቋዓት ያሉ ለኾኑ ጻድቃን ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለአርሶፎኒስ ወለጴጥሮስ አምሳሉ። ለአስኪርዮን ወአርጌንዮስ ወቢልፍዮስ አብያጸ እሉ፡፡ በእንተ ኢየሱስ ክርስቶስ አመ ተጋደሉ። እንዘ ርኁባን ወጽሙዓን ተቀትሉ፡፡ እንበለ ይብልዑ እክለ ወማየ ያጥልሉ"። ትርጉም፦ ለአርሶፎኒስና ለአምሳያው ለጴጥሮስ የእሊኽም ባልንጀሮች ለኾኑ ለእኒኽ ለአስኪርዮን ለአርጌንዮስና ቢልፍዮስ ሰላምታ ይገባል፤ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በተጋደሉ ጊዜ የተራቡና የተጠሙ ሲኾኑ ተገደሉ እኽልን ሳይበሉና ጥሩ ውሃንም ሳይጠጡ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ19።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፲፱ (19) ቀን።
❤ እንኳን ለሰማዕቱ ሐዲስ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ለአባ ብሶይ አኖብ ሰማዕትነት ለተቀበሉት ለዕረፍታቸው በዓልና ለአምስት ጭፍሮች እሊህም ለአርሶፎኒስ፣ ለጴጥሮስ፣ ለአስኪርዮን ለአርጌንዮስ ለቢልፍዮስ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከደብረ ቋዓት ቅዱሳን አባቶቻችን ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ አምስቱ ጭፍሮች፦ እሊህም ስማቸው አርሶፎኒስ፣ ጴጥሮስ፣ አስኪርዮስ፣ አርጌንዮስና ቢልፍዮስ ነው። በዲዮስጲልዮስ ቅጽር ውስጥ ይኖሩ ነበር። መኰንኑም ለጣዖታት እንዲሠው በአስገደዳቸው ጊዜ "እኛስ የንጉሣችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ትእዛዝ እንፈጽማለን ለእርሱም እንሰዋለን" አሉት መኰንኑም ሰምቶ ተቆጣ በአንድ ቤት ውስጥም እንዲዘጉባቸውና እስከ ሁለት ቀን ያህል ውኃ እንዳይሰጧቸው አዘዘ።
❤ ከዚህም በኋላ እንዲያመጧቸው አዘዘ በፊቱም በቆሙ ጊዜ "ለአማልክት ሠዉ" አላቸው እነርሱም በአንድ ቃል "እኛስ ለፈጣሪያችን ለክርስቶስ እንሠዋለን ለረከሱ አጋንንትን ግን አንሠዋም" አሉት። አንገታቸውንም አሥረው ወደ ሌላ አገር ይወስዱአቸው ዘንድ አዘዘ። አርጌንዮስም ወንድሞቹን "እኔ እውነትን እነግራችኋለሁ የእግዚአብሔር መልአክ አምስታችንንም በስማችን ሲጠራን ሸምቼዋለሁና" አላቸው።
❤ ዳክስ ወደሚባል መኰንንም በአደረሷቸው ጊዜ መኰንኑ አስቀድሞ አርሶፎኒስን ወስዶ "ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ በአለውም ጊዜ በፈረስ ጅራት ላይ አሥረው በከተማ ውስጥ እንዲጎትቱትና እንዲአዞሩት አዘዘ። በመለሱትም ጊዜ በውሽባ ቤት ማንደጃ ውስጥ ፊቱን እንዲአጠወልጉት አዘዘ ሁለተኛም እስከ ሚጨነቅ ድረስ በሠረገላ ውስጥ አሥረው ቊልቊል ሰቀሉት ሃይማኖቱንም ጠብቆ ክብር ይግባውና ለጌታችን ነፍሱ ሰጠ።
❤ ሁለተኛም ጴጥሮስን አቀረቡት ዳክስም "ለአማልክት ሠዋ" አለው ትእዛዙንም ባልተቀበለው ጊዜ እንዲአሠቃዩትና እንጨት ተክለው ዘቅዝቀው እንዲሰቅሉት አዘዘ ሁለተኛም ምድሩን ቆፍረው ከትከሻው በታች ቀብረው በቅሎዎችን በላዩ እንዲነዱበት አዘዘ ይህንንም እግዚአብሔር እየረዳው ታገሠ ከጉድጓድም በአወጡት ጊዜ ከሥቃዩ ብዛት የተነሣ ሥጋው ጠወለገ መናገርም ተሣነው በግንድ ውስጥም አሥረው ጣሉት።
❤ ከዚህም በኋላ አርጌንዮስን አቀረቡት ዳክስም "ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ ያሠቃዩት ዘንድ አዘዘ ያለ መብልና መጠጥም በተበሳ ግንድ ውስጥ አሥረው ዘቅዝቀው ሰቀሉት።
❤ ዳግመኛም አስኪርዮንን አቀረቡት ዳክስም "ለራስህ እዘን በክፉ አሟሟትም እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ" አለው እምቢ ባለውም ጊዜ እንዲሰነጥቁት አዘዘ ወታደሮችም ተረከቡትና በጽኑ ሥቃይ አሠቃዩት በትዕግሥቱም በአሸነፋቸው ጊዜ ለመኰንኑ ነገሩት በረኃብና በጽም ይሞት ዘንድ በግንድ ውስጥ አሥረው በባዶ ቤት እንዲዘጉበት አዘዘ እንዲሁም አደረጉበት።
❤ ደግመው ዲያቆን ቢፍዮስን አቀረቡት መኰንን ዳክስሞ "እንዳትሞት ለአማልክት ሠዋ" አለው ባልሰማውም ጊዜ እስከሚገድሉት ድረስ እንዲአሠቃዩት አዘዘ ሥጋውን ሠነጣጥቀው በከተማው አደባባይ ጎተቱት እንጨት ተክለውም ቊልቊል ሰቀሉት በአንገቱም ከባድ ደንጊያ አንጠለጠሉ ከሃይማኖቱም ባልተናወጸ ጊዜ በረኃብና በጽምዕ እንዲሞት በግንድ ውስጥ አሥረው በላዩ መዝጊያ ሠርተው ዘጉበት። በየዕለቱም ወንድሞች ምእመናን ከውጭ ሆነው ይጎበኙት ነበር ጳሔን የተባለው የሰኔ ወር በባተ በሠላሳ ጴጥሮስ ነፍሱን ሰጠ። እርሱንም አውጥተው ደጁን በሌሎቹ ላይ ዘጉ።
❤ የከበረ አርጌንዮስም ከአምስት ቀን በኋላ ዐረፈ እርሱን አውጥተው በቀሩት ላይ ደጁን ዘጉ። ብፁዕ አስኪርዮንም ከዐሥራ ሁለት ቀን በኋላ ዐረፈ። እርሱንም አውጥተው በቅዱስ ቢልፍዮስ ላይ ደጃፍ ሠርተው ዘጉበት እርሱም የሚያርፍባት ቀን ስትደርስ ወንድሞቼ ታገሡኝ በዚች ሌሊት እወጣለሁና አላቸው። ከዐሥራ ዘጠኝ ቀን በኋላ በዚያች ልሊት ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእሊህ ገድለኞች ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሰማዕቱ ሐዲስ ቅዱስ ጊዮርጊስ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም መዛሕዝም ነው ትርጓሜውም ድንገተኛ ማለት ነው። እርሱም እስላም ነበር ከግብጽ ደቡብ ድምራ ከሚባል አገር ክርስቲያን ሴት አግብቶ ከእርሷም ሦስት ልጆችን ወለደ ከሦስቱም አንዱ ይህ ቅዱስ ነው። ከእናቱም ጋራ ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሔድ ነበር ቅዱስ ቁርባንንም ይቀበል ዘንድ እናቱን ለመናት እርሷም ማንም የክርስትናን ጥምቀት ሳይጠመቅና ንጹሕ ሳይሆን ቁርባን ሊቀበል አይችልም አለችው።
❤ ከዚህም በኋላም ከተረፈ መሥዋዕቱ ሰጠችው በጎረሳትም ጊዜ ጣዕሟ በአፉ ውስጥ እንደ ማር ሆነ "የዚች የቁራሿ ጣዕም በአፌ ውስጥ እንዲህ የሆነ የዋናው የቁርባኑ ኅብስት ጣዕም ምን ያህል ይሆን" ብሎ በልቡ አሰበ ከዚች ጊዜ ጀምሮ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ ወደደ።
❤ በአደገም ጊዜ ክርስቲያን ሴት አገባ ክርስቲያን ይሆን ዘንድ መፈለጉንም ነገራት እርሷም ወደሌላ አገር ሒዶ የክርስትናን ጥምቀት እንዲጠመቅ መከረችው እርሱም ወደ ሌላ አገር ሒዶ ተጠመቀ ስሙንም ለውጦ ጊዮርጊስ ተባለ። እስላሞችም በአዩት ጊዜ ይዘው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት ከዚያም አምልጦ ሳፍጥ ወደሚባል አገር ሸሸ በዚያም ሦስት ዓመት ኖረ። ወሬውም በተገለጠ ጊዜ ቀጡር ወደ ሚባል አገር ሒዶ የልዳዊው ሰማዕት የቅዱስ ጊዮርጊስን ቤተ ክርስቲያን እያገለገለ ኖረ።
❤ ከዚህ በኋላ ወደ አገሩ ድምራ ተመለሰ እስላሞችም ሰሙ ይዘውም ለመኰንኑ ሰጡት የመኰንኑም ሚስት ክርስቲያን ነበረች ለመኰንኑም "አታሠቃየው" አለችው መኰንኑም አሥሮ በወህኒ ቤት ዘጋበት። እስላሞችም ተሰብሰቡ የወህኒ ቤቱንም ደጅ ሰብረው ታላቅ ግርፋት ገረፉት አካላቱም ቈራርጠው በሕይወትና በሞት መካከል ጣሉት። ሲነጋም ክርስቲያኖች የሞተ መስሏቸዋልና ሊቀብሩት መጡ ነገር ግን በሕይወት አገኙት።
❤ ከዚህም በኋላ እስላሞች ተሰብስበው "ከዚህ ምክርህ ካልተመለስክ እኛ ጽኑ ሥቃይ አሠቃይተን እንገድልሃለን" አሉት የመዛሕዝም ልጅ የከበረ ጊዮርጊስም "ሰማይና ምድርን የፈጠረ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም የፈለጋችሁትን አድርጉ" አላቸው። እጅግም ተቆጡ በመርከብ ምሰሶ ላይም ሰቅለው ታላቅ ሥቃይን አሠቃዩት መኰንኑም ከስቅላት አውርደው በእሥር ቤት እንዲአሥሩት አዘዘ እንደዚሁም አደረጉ። ሚስቱም ታጽናናውና እንዲታገሥ ታደርገው ነበር ሰይጣንም እንዳያስተውና የደከመበትን ዋጋ እንዳያጣ በልቡ ወደ ክርስቶስ ያስብ ዘንድ ትመክረው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና አረጋጋው አበረታታውም ከሰማዕታትም ጋራ እንደ ተቈጠረ በማግሥቱም ራሱን በሰይፍ እንደሚቆርጡት ነገረው። በነጋም ጊዜ እስላሞች ወደ መኰንኑ ተሰብስበው ጊዮርጊስን ይሰጣቸው ዘንድ ፈለጉ መኰንኑም የወደዱትን ያደርጉበት ዘንድ እንዲሰጧቸው አዘዘ።
❤ ከዚህም በኋላ ከእሥር ቤት አወጡት ድምራ በምትባል አገር በከበረ የመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ራሱን በሰይፍ ሰኔ 19 ቀን ቆረጡ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ።

❤ ሰኔ ፲፰ (18) ቀን።
❤ እንኳን ለእስክንድርያ አርባ አምስተኛው ሊቀ ጳጳስ ለአባ ድምያኖስ ለዕረፍት በዓል መታሰቢያና ለሐዋርያው ፊሊጲስና ለአባታችን ለከፋሌ ባሕር ለአባ ኤዎስጣቴዎስ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰው፦ ከሰማዕቱ ቅዱስ ኤስድሮስ መታሰቢያው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ አባ ድምያኖስ፦ ይህም አባት ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ አምስተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ነው። በአስቄጥስ በአባ ዮሐንስ ሐጺር ገዳም ከታናሽነቱ ጀምሮ መነኰሰ ዐሥራ ሰባት ዓመት ያህልም እየተጋደለ ኑሮ ዲቁና ተሾመ። ከዚህም በኋላ በታርን ወደተባለ ገዳም ሔደ ይኸውም የአባቶች ገዳም ማለት ነው እርሱም በእስክንድርያ ምዕራብ ያለ ነው። እንደ ገዳመውያንም ገድል በውስጡ ተጠምዶ እየተጋደለ ኖረ።
❤ ከእርሱ አስቀድሞ የነበረው አባ ጴጥሮስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ በሊቀ ጵጵስናው ሥራ የሚረዳውና በሥራው ሁሉ የሚአማክረው ስለ ቤተ ክርስቲያን ጥበቃ አዋቂ ሰው ፈለገ ይህንንም አባ ድምያኖስን ሰዎች በበጎ ሥራ ሁሉና በዕውቀቱ ያመሰግኑታል። ስለዚህም ወደርሱ ወሰደውና በሊቀ ጵጵስናው ሥራ እየተራዳው ከእርሱ ጋራ እንዲቀመጥ አደረገው እርሱም ትእዛዙን ተቀብሎ ከእርሱ ጋር ተቀምጠ ሰዎችም ሁሉ ወደዱት።
❤ አባ ጴጥሮስም በዐረፈ ጊዜ ኤጲስቆጶሳትና አዋቂዎች ሊቃውንት በአንድ ምክር ተስማምተው በእስክንድርያ ከተማ ይህን አባ ድምያኖስን ሊቀ ጵጵስና ሾሙት ለአገልግሎትም ፅሙድ ሆነ በመልካም ሥራ ሁሉ ጸንቶ ኖረ። ሁሉጊዜም ድርሰቶችንና መልክቶችን እየጻፈ ወደ አገሩ ሁሉና ወደ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ይልክ ነበር።
❤ በአስቄጥስም ገዳም በአባ መቃርስ ደብር ከነጣቂው ከሀዲ ወገን የሆኑ አርሲሳን የሚሉአቸው መናፍቃን ነበሩ እነርሱም በሚቆርቡበት ቀን ሌሊት ወይን ይጠጣሉ በማግሥቱም ቅዱስ ቁርባንን ይቀበላሉ። እነርሱ ጌታችን በመጀመሪያ ኅብስቱን ከመፈተቱ በፊት በኋላም ኅብስቱን ከሰጣቸው በኋላ ሁለት ጊዜ ጽዋን እንደሰጣቸው በሉቃስ ወንጌል ተጽፎ ያለውን ምክንያት ያደርጋሉና። ይህም አባት አባ ድምያኖስ ስሕተታቸውን ገለጠላቸው የፊተኛው ጽዋ የአለፈው ኦሪት ፋሳካ ምሳሌ እንደ ሆነም አስረዳቸው አዲሱ የአባቶቻችን ሐዋርያት ቀኖና ሕግ ግን የመድኃኒታችንን ሥጋውንና ደሙን የሚቀበል ሁሉ ከመብልና ከመጠጥ ይጠበቅ ዘንድ ከቁርባንም አስቀድሞ ምንም ምን እንዳይቀምስ ያዝዛል። ከእርሳቸውም ውስጥ ከስሕተታቸው ተመልሰው ንስሐ የገቡና የታዘዙለት አሉ ያልተመለሱትን ግን አውግዞ ከምእመናን አንድነት ለይቶ አባረራቸው።
❤ በዚህ በአባ ድምያኖስ ዘመንም የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎድሮስ ዐረፈ። በእርሱ ፈንታም የሥላሴን ስም ፈጽሞ የማያወሳ አንድ እግዚአብሔር ብቻ ይላል እንጂ በልዩ ሦስትነት የማያምን መናፍቅ ሰው ተሾመ የከፋች ሃይማኖቱንም የምትገልጽ መልእክት ወደዚህ አባት ድምያኖስ ላከ። አባ ድምያኖስም በአነበባት ጊዜ እጅግ አዘነ በመልክቱ ውስጥ እግዚአብሔር አንድ ገጽ ብቻ እንደ ሆነ ያወሳል እንጂ የልዩ ሦስትነትን ስም የሚያወሳ አላገኘምና።
❤ ይህም አባት ድምያኖስ የሥላሴን በመለኮት አንድነታቸውን በገጽ በአካልና በግብር ሦስትነታቸውን ከቅዱሳን መጻሕፍትም ጠቅሶ ለዚህም መናፍቅ መልእክት ጻፈለት ደግሞም እንዲ አለው "ለእግዚአብሔር ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋራ የነበረ ጥንትና ፍጻሜ የሌለው አካላዊ ቃል አካላዊ ሕይወት አለው"። ይህችንም ምሥጢርንና ዕውቀትን የተመላች መልእክት ለአንጾኪያ ሊቀ ጵጵስና ወደ ተሾመ ወደዚያ መናፍቅ በደረሰች ጊዜ ትርጓሜዋን ያውቅ ዘንድ የልቡ ድንቁርና የአእምሮው ጉድለት አለቀቀውም። ነገር ግን በክህደቱ ጸና። አባ ድምያኖስም ከዚህ መናፍቅ አንድነት ተለየ ማኅበሩንም በቅዳሴና በጸሎት ጊዜ ይህ ከሀዲ እስኪሞት ድረስ ለሃያ ዓመት ስሙን እንዳይጠሩት አዘዛቸው።
❤ ይህም አባት ድምያኖስ በተግሣጾቹና በመልክቶቹ መንጋውን እየጠበቀ አርባ ሦስት ዓመታት ያህል ከኖረና ወደ በጎ እርጅና ከደረሰ እግዚአብሔርንም ከአገለገለ በኋላ ሰኔ 18 ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ድምያኖስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 18 ስንክሳር።
+ + +
❤ ሰላም ለሊቀ ጳጳሳት ድምያኖስ አቡነ። ለተልእኮ ምሥዋዕ ዘጽሐቀ ወዘአስተንተነ። ለእለ አመክነየ ሰብእ በፍስሐ ሐሙስ ዘኮነ። ገሠጾሙ ወአውገዞሙ ኢይትመጠዉ ቁርባነ። በኑኅ ሌሊት ሰትዮሙ ወይነ። ሊቀ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 18።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ሠርከ ወነግሀ ወመዓልተ እነግር። አየድዕ ወኢሰምዑኒ ቃልየ። አድኅና በሰላም ለነፍስየ እምእለ ይትቃረኑኒ"። መዝ 54፥17-18። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 2፥1-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 2፥9-14 እና የሐዋ ሥራ 17፥5-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥15-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ባስልዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የጾም ጊዜና በዓል ለሁላችን ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
+ + +
❤ "ሰላም ለአባ ገሪማ መድምመ ዘአርአየ ዲበ ዕፅ ዘአዕረገ ብዕራየ ወዲበ ዐውድ ዘአውረደ ሥርናየ"። ትርጉም፦ በዐውድማ ላይ ሥንዴን ያወረደ ወደ ዕንጨት ላይም በሬን ያወጣ፤ ድንቅ ነገርን ያሳየ ለኾነ ለአባ ገሪማ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ አባ ጰላሞንም እየጸለየ ቃሉ ወዳመለከተው ወደ አባ ለትጹን በዓት ደረሰ፡፡ አባ ጰላሞንም ባየው ጊዜ በደስታ ተቀብሎ ሰላምታ ሰጠው፡፡ ወደ ተራራውም ወጥተው ከጸለዩ በኋላ ተቀምጡ፡፡ አባ ጰላሞንም የመረረ ልቅሶን እያለቀሰ ሰይጣን በፈተናው እንደጣለው ለአባ ለትጹን ይነግረው ጀመረ፡፡ እንዲህም አለው፡- "በአንዲት ዕለት የእጅ ሥራዬን ለመሸጥ በግብፅ ገበያ መንገድ ስጓዝ ሰይጣን መጥቶ ልቤን አዘነጋት፤ መድኃኒት የሚሆነኝን የጌታዬ የኢየሱስ ክርስቶስን ስም እጠራ ዘንድ አልተወኝም፡፡ ዳግመኛም እንደ ንጉሥ ከተማ የታነፀች ውኃዎችና ተክሎች መልካም ዛፎችም ያሏት ከተማን አሳየኝ፡፡ የእጅ ሥራዬንም ልሸጥ ሳስብ ባሏ ብዙ ገንዘብ ትቶላት ሙቶ በምታዝን ሴት አምሳል ታየኝ፡፡ "የእጅ ሥራህን እኔ እገዛሃለሁ" ብለኝ ወደ አዳራሽ አስገባችኝ፡፡ እንቅቦቹንም ከላዬ አውርዳ አኖረች፣ እግሮቼንም አጠበች፣ አሽከሮቿንም ምግብ ያቀርቡ ዘንድ አዘዘቻቸው፡፡ ከእርሷ ጋርም እበላ ዘንድ ብዙ ማለደችኝ፣ በልተን ጠጥተን ሰከርን፡፡ ስንጨዋወትም አሽከሮቿ ሁሉም ወጡና ሁለታችን ብቻችንን ቀረን፡፡ ያንጊዜም ልቤ በዝሙት እሳት ተቃጠለ፡፡ እግዚአብሔርንም መላእክቶቹንም ቢሆን አላሰብኩም በእርግጥ ከእርሷ ጋር እንደሚተኛ ሆንኩ፡፡
❤ ከዚህ በኋላ በነቃሁ ጊዜ ብመለከት ምንም ነገር አላገኘሁም፡፡ ሴትም ቤትም ማዕድም አትክልትም ቢሆን አላገኘሁም፡፡ ነገር ግን ራሴን ከተራራው በታች አገኘሁት፡፡ ምንም እንዳልበላና እንዳልጠጣም ሰው ሆንኩ፡፡ እጅግም አለቀስኩ፡፡ ሰይጣንም በሩቁ ቆሞ "መጻተኛ ጰላሞን ሆይ ወዮልህ እንደወፍ ላጠምድህ በአንተ ላይ በርትቻለሁና…" እያለ ሲዘብትብኝ አየሁት፡፡ ነገሩንም ሰምቼ በመስቀል ምልክት በላዩ አማተብኩ፣ ከእኔም ሸሸ፡፡ "አሁንም አባቴ ለትጹን ሆይ በደሌን ይቅር ይለኝ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንልኝ በቅድስናህ ተማፅኛለሁ" አለው፡፡ ቅዱስ አባ ጰላሞንም "አይዞህ እግዚአብሔር ኃጢአትህን ይቅር እንደሚልህ አምናሁ" ብሎ አጽናናው፡፡ ከዚህም በኋላ ተነሥቶ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ጸለየ፡፡ ወደ እነርሱም እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡- "የታመናችሁ አገልጋዮቼ አትፍሩ ከእንግዲህ ወዲህ ጠላት በእናንተ ላይ አይበረታታም፡፡ ጰላሞንም የሠራውን ኃጢአት በራሱ በሰይጣን ላይ አደረግሁ፣ የጰላሞንን ኃጢአት ብቻ አይደለም ነገር ግን የሚፈትናቸውን ሰዎች ሁሉ ኃጢአታቸውን በሰይጣን በራሱ ላይ እመልሳለሁ"፡፡
❤ ከዚህም በኋላ አባ ጰላሞን ከአባ ለትጹን በረከትን ተቀብሎ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ በዓቱ ሄደ፡፡ ተጋድሎውንም ፈጽሞ በዚህች ዕለት በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፡- የሰኔ 17 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለአባ ለትጹን እስከ ፍጻሜ ዘክህለ። ከመ ያውጽእ እምደይን ብእሴ ህጉለ። ለለ መዋዕል ሰዱስ እንዘ ይበልዕ ቈጽለ። በትርሕምት ዐቢይ እምብዝኀ ተጋደለ ገድለ። በአምሳለ ዖፍ ኮነ ሥጋሁ ቀሊለ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 17።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ኀይልየኒ ወዝክርየኒ እግዚአብሔር። ወውእቱ ኮነኒ መድኃንየ። ቃለ ትፍሥሕት ውስተ አብያቲሆሙ ለጻድቃን"። መዝ 117፥14። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 17፥5-11።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አኮ ከመዝ ኃጥአንሰ አኮ ከመዝ። ዳዕሙ ከመ መሬት ዘይግሕፎ ነፋስ እምገጸ ምድር። ወበእንተዝ ኢይትነሥኡ ረሲዓን እምደይን"። መዝ 1፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 1፥1-10፣ ያዕ 5፥14-17 እና የሐዋ ሥራ 13፥44-49። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 6፥20-24። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ገሪማ ከሞት የተሰወሩበት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ሰኔ ፲፯ (17) ቀን።
❤ እንኳን ለታላቁ አባት እናቱን በዝሙት አስረግዞ ፅንሱንም መርዝ አጠጥቶ በማኅፀኗ የገደለውን ርጉም ሰው ከዘላለማዊው ሥቃይና ኩነኔ ለታደጉት ለአባ ለትጹንና ፍፁም መናኒ ለሆነ ለመጻተኛ ከሰው ጋር ተነጋግሮ ለማያውቀውና በተራራ ላይ ብቻውን በገድል ተጠምዶ ሲኖር የጌታችንን መከራ እያሰበ ቀንና ሌሊት ያለቅስ ለነበረው ለባሕታዊ አባ ጰላሞን ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሰማዕታት ከነአኮራን፣ ከበርተሎሜዎስ፣ ከእለስክንድርያ፣ ከእለስክንድሮስ፣ ከዮሴፍና ከጻድቂቱ አርሴማ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ አባ ለትጹን፦ ይህም አባት ከብህንሳ አገር ነበር ጎልማሳ በነበረ ጊዜም "ነፍሱን ስለ እኔ የጣላትም ያገኛታል ለዘላለም ሕይወትንም ይጠብቃታል" የሚለውን በቅዱስ ወንጌል ውስጥ የተጻፈውን የሕያው ንጉሥን ቃል ሰማ ወዲያውኑ ልቡ ስለ እግዚአብሔር ፍቅርና ስለ ዘላለማዊ ተድላ እንደ እሳት ነደደ። ቅዱስ ቁርባንንም ተቀብሎ እስዋሕት ወደ ሚባል ገዳም ሔደ በጾም በጸሎትና በስግደት ታላቅ ተጋድሎን ያለ ማቋረጥ ይጋደል ጀመር ሰባት ሰባት ቀንም ይጾም ነበር።
❤ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጸለትና የምንኲስና ልብስን ዘንድ ወደ አባ ኤስድሮስ እንዲሔድ አዘዘው እርሱም መልአኩ እንዳዘዘው ሔደ አባ ኤስድሮስም በልብሱና በአስኬማው ላይ አርባ ቀኖች ጸለየ ከዚያም በኋላ ልብሱንና አስኬማውን አለበሰው በገድል መጠመድን ጨመረ።
❤ ከዚያም መምህሩንም አስፈቅዶ ወጥቶ ብቻውን መጋደል ጀመረ፡፡ በአቅራቢያውም አንድ ገዳም ነበረና አንድ ቀን አበ ምኔቱ ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው፡፡ መነኰሳትም ዙሪያውን ከበውት ሲያለቅሱት አገኛቸው፡፡ እንዲሁም የሰይጣን ሠራዊትም አበ ምኔቱን ከበውት ደስ ሲሰኙ አያቸውና ደንግጦ "አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድነው?" ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው፡፡ እርሱም መነኰሳቱን ከእርሱ እንዲርቁ ካደረገ በኋላ የሠራውን በደሉን እንዲህ ብሎ ነገረው "እኔ ካሁን በፊት ማንም ያልሠራውን ኃጢአት ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ፡፡ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ ሀገር ሄድኩ፡፡ "ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል" ብዬ በድፍረት በቁርባን ላይ የምቀድስ ሆንኩ፡፡ ለጠላሁትም በቁርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ እሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል፡፡ ከእናቴም ጋራ ዓሥር ጊዜ ተኝቻለሁ፣ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆዷ ውስጥ ገደልኩት፡፡ ኃጢአቴ ብዙ ነውና ተነግሮ አያልቅም፡፡ ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም፡፡ ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና" ብሎ ለአባ ለትጹን ነገረው፡፡ ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ፤ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲያሠቃዩዋት አባ ለትጹን ተመለከታት፡፡
❤ በዚህም አባ ለትጹን የመረረ ልቅሶን አለቀሰ፡፡
ከዚህም በኋላ አባ ለትጹን "ስለ ወዳጆቹ ነፍሱን አሳልፎ የሚሰጥ ያለ ከሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" የሚለውን የቅዱስ ወንጌልን ቃል አስቦ ስለዚያ ኃጥእ ሰው ነፍስ ወደ ጌታችን እየለመነ አምስት ጊዜ እስከሚሞት ሰውነቱን ሊያሠቃያት ጀመረ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል መትቶ አስነሣውና እንዲህ አለው "ስለዚያ ኃጢአተኛ ነፍስ ነፍስህን አትግደል ምሕረት አይገባውምና፡፡ እግዚአብሔር እውነት ፈራጅ ስለሆነ በደሉ አይሠረይለትም"፡፡
❤ አባ ለትጹን ግን መሐሪ ይቅር ባይ ወደሆነ እግዚአብሔር ስለዚያ ኃጢአተኛ እየለመነ ራሱን ማሠቃየት አልተወም፡፡ ከዚህም በኋላ ራሱን በባሕር አስጥሞ ሞተ፡፡ ያን ጊዜም ጌታችን መጥቶ በባሕሩ ዳር ተቀመጠና ከባሕሩ ውስጥ አውጥቶ ከሞት ያድነው ዘንድ ሚካኤልን አዘዘው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም አባ ለትጹንን ከባሕሩ አውጥቶ ከሞት አድኖ ቤታችን ፊት አቆመው፡፡ ክብር ይግባውና ጌታችንም "የመጥኩህ ለትጹን ሆይ ኃጢአቱ እጅግ ብዙ ስለሆነ በደሉም ከኃጢአተኞች ሁሉ በደል ስለሚከፋ ምሕረት ስለማይገባው ስለዚያ ኃጢአተኛ ሰው ብዙ ጊዜ ነፍስህን ለምን ትገድላለህ?" አለው፡፡ አባ ለትጹንም "መሐሪና ይቅር ባይ ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ ያን ኃጢአተኛ ትምረው ዘንድ እለምንሃለሁ ያለዚያ ግን የእኔንም ነፍሴን ከእርሱ ጋራ ወደ ሥቃይ ውሰዳት" ብሎ ጌታችንን ለመነው፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን የዚያን ኃጥእ ነፍስ ያመጣት ዘንድ ቅዱስ ሚካኤልን አዘዘውና አመጣት፡፡ ጌታችንም በከበሩ እጆቹ ዳሰሳትና እንዳልተፈጠረች አደረጋት፡፡ ወዲያውም "ይህቺ ነፍስ አፈር ትሁን እንጂ ለሥቃይ ወይም ለሕይወት አትሁን" አለ፡፡ አባ ለትጹንም ስለይቅርታውና ስለቸርነቱ ገናናነት መድኃኒታችንን ፈጽሞ አመሰገነው፡፡
❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን አባ ለትጹንን "የመጥኩህ ለትጹን ሆይ በእውነት እነግርሃለሁ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ በስምህ መባ ለሚያስገባ ወይም የተራበ ለሚያበላ የተጠማ ለሚያጠጣ የተራቆተ ለሚያለብስ ገድልህን ለሚጽፍ እኔ የሁሉንም ኃጢአታቸውን ይቅር እላለሁ፣ ስማቸውንም በሕይወት መጽሐፍ እጽፋለሁ፣ በጎ ዋጋቸውንም እሰጣቸዋለሁ" የሚል ቃልኪዳን ሰጥቶት ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ አባ ለትጹንም እጅግ ደስ ብሎት ወደ በዓቱ በመመለስ ብዙ ከተጋደለ በኋላ ገድሉን ፈጽሞ ሰኔ 17 ቀን በሰላም ዐረፈ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ለትጹን ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትጉር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ባሕታዊ አባ ጰላሞን፦ ከተጋድሎው የተነሣ ሰይጣን እስከ ደከመ ድረስ በተራራ ላይ እግዚአብሔርን እያገለገለ በገድል ተጠምዶ ሲኖር ቀንና ሌሊት ያለቅስ ነበር፡፡ ከሰው ጋር ሳይነጋገር ብዙ ዘመን ከኖረ በኋላ ሰይጣን የሚያስቅ ነገርንና ጨዋታን እያመጣበት ይፈትነው ነበር፡፡ ነገር ግን አባ ጰላሞን የጌታችንን መከራ እያሰበ ይተክዝ ያለቅስ ነበር፡፡ ሰይጣንም በዚህ ተቆጥቶ አንበሳ ሚዳቋን እንደሚያድን አባ ጰላሞንን ያድነው ነበር፡፡ በአንዲት ቀንም አባ ጰላሞን የእጅ ሥራውን ሊሸጥ ተነሠቶ ወደ ገበያ ሲጓዝ ሰይጣን ጎዳናውን አሳተው፣ ልቡንም መሰጠው እንጂ የሚያደርገውን ያውቅ ዘንድ አልተወውም፡፡
❤ ከሰባት ቀኖች በኋላ አባ ጰላሞን ከረኀብና ከውኃ ጥም የተነሣ ከመሬት ላይ ወደቀ፤ ለሞትም የደረሰ ሆነ፡፡ ሰውን ወዳድ የሆነ ጌታችንም እንዲጠፋ አልተወውምና ሰይጣንን ከእርሱ አርቆ አሳደደው፡፡ አባ ጰላሞን በእርሱ ላይ የሆነውን ባወቀ ጊዜ ወደ ጌታን ጮኸ፡፡ ወዲያውም "ጰላሞን ሆይ አትፍራ ከእንግዲህ ወዲህ ጠላት በአንተ ላይ ክፉ ሊሠራ አይልችም፡፡ ነገር ግን ተነሥተህ ወደ ደቡብ ጥቂት ተጓዝ በዚያም በተራራው አጠገብ የሚኖር ስሙ ለትጹን የሚባል ሽማግሌ ጻድቅ ሰው ታገኛለህ፣ እርሱ ስለ ስሜ ብዙ መከራ የተቀበለ ነው፡፡ ያደረከውንም ሁሉ ሰይጣንም እንዴት እንዳሳተህ ንገረው፣ እርሱ ኃጢአትህ እስኪሠረይ ስለ አንተ ይጸልያልና" የሚል ቃልን ሰማ፡፡