ሰዋስው ☘☘☘☘
رفتن به کانال در Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
نمایش بیشتر1 161
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
1 161
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ሥርዓተ ዋዜማ ዘዓውደ ዓመት
☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘☘
ብጹዕ አንተ ዮሐንስ፤ ዘሀለወከ ታእምር፤ ወተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር፤ ጸሊ በእንቲአነ፤ ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ፤ እንሣእ በረከተከ።
❣አመላለስ፦
ባርከኒ ባርከኒ/፪/
እንሣእ በረከተከ እንሣእ በረከተከ /፬/
@EOTCWW
@EOTCWW
❣በ፭ ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
ይቤ ዮሐንስ ዓለምኒ ለልየ ርኢኩ፤ ወአነ ሰማዕቱ፤ ወውእቱ በባሕር ሣረራ አንሰ ኢየአምሮ፤ ዳዕሙ ከመ ያእምርዎ ፳ኤል አንሰ መጻእኩ።
@EOTCW
@EOTCWW
እግዚአብሔር ነግሠ
ጸርሐ ዮሐንስ ወይቤ ድኅረ እምነቢያት እምቅድመ ምጽአተ ወልድ ቤዛ ኃጢአቶሙ አጥምቅ በማይ አንሰ ተፈኖኩ።
@EOTCW
@EOTCW
❣ምልጣን
ጸርሐ ዮሐንስ ወይቤ፤ ድኅረ እምነቢያት እምቅድመ ምጽአተ ወልድ ቤዛ ኃጢአቶሙ አጥምቅ በማይ፤ አንሰ ተፈኖኩ።
@EOTCW
@EOTCWW
በ፭ እግዚኦ ጸራሕኩ ኀቤከ
እምከርሠ እሙ አእመረ ወአጽምዕ ቃለ ስዕለትየ፤ እምከርሠ እሙ አእመረ ሰገደ ወአንፈርዓፀ።
@EOTCW
❣ምልጣን
እምከርሠ እሙ አእመረ ሰገደ ወአንፈርዓፀ፤ ሰገደ ወአንፈርዓፀ፤ እምከርሠ እሙ አእመረ፤ ሰገደ ወአንፈርዓፀ።
@EOTCW
@EOTCW
❣ይትባረክ
ጸርሐት ቤተ ክርስቲያን ኀበ ዮሐንስ ወትቤሎ አንተኑ ክርስቶስ ወይቤላ አንሰ ኢኮንኩ ኪያሁ።
@EOTCW
@EOTCW
❣ሰላም
በ፬: ዘመጠነዝ ትርሢተ ክብር፤ ፈሪሃ ልዑል ትሕትና ወፍቅር፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ዘመላእክት ይሰግዱ ሎቱ፤ ኃይለ ልዑላን ኪያሁ ይሴብሑ፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ዘምስለ እግዚኡ ኪዳነ ዘአቀመ ወብዙኃነ አሕዛበ አእመነ፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ውስተ ሐቌሁ ቅናቱ ዘአዲም፤ ንብረቱ ገዳም ወኲሉ ነገሩ በሰላም፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ እግዚኡ ዘከመ ከለሎ፤ ዮም በምድር ተዝካሩ በሰማያት በላዕሉ፤ ርእዩ ዕበዮ ለዮሐንስ ይቤሎ መድኃኒነ ለዮሐንስ፤ ዕውራን ይሬእዩ ወጽሙማን ይሰምዑ፤ እለ ለምጽ ይነጽሑ፤ እለ መጽኡ ኀቤየ።
@EOTCW
አመላለስ፦
ውስተ ሐቌሁ ቅናቱ ዓዲም/፪/
ንብረቱ ገዳም ወነገሩኒ ሰላም/፬/
https://t.me/Eotcw
# Join & share
1 161
ርሱማ በኋላ እንግዲህ ስዎችን ማን ያጽናናቸዋል"። ደቀ መዝሙሩ ያሰበውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ በንጹሕ አንደበቱ እንዲህ ብሎ መለሰለት። "ልጄ ዮሐንስ ሆይ የቶባል ልጅ አባ በርሱማ ብሎ ስሜን የሚጠራኝን ሁሉ ከእሳቸው እንደማልርቅ ዕወቅ እኔ እነሆኝ ብዬ የክብር ባለቤት ከሆነ ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ የሚሻውን ሁሉ እፈጽምለታለሁ"።
❤ ከዚህም በኋላ ወደ ግራው ተመልክቶ እነሆ ፈለጉብን ተመራመሩን ከክፋ ሥራ ምንም ምን በእኛ ላይ አላገኙም አለ። ከዚህም በኋላ ደግሞ ደቀ መዝሙሩ አብርሃምን "ቢላዋ ወይም መቊረጭት ስጠኝ" አለው መቁረጫውንም ተቀብሎ ምላሱን ቆርጦ ጣላትና እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ምንድነው የሚለውን መዝሙር እስከ መጨረሻው ይዘምር ጀመር።
❤ ከዚህም በኋላ አዳኝ በሆነ መስቀል ምልክት ፊቱን አማተበ ነፍሱንም በእግዚአብሔር እጅ ሰጠ ብርሃናውያን መላእክትም የከበረች ንጽሕት ነፍሱን ተድላ ደስታ ወደ ሚገኝባት ገነት አሳረጓት።
❤ መነኰሳቱም ከበግ ጸጒር በተሠራ ንጽሕ በሆነ በነጭ ባና ገነዙት ተሸክመውም ወስደው ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት። ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰማንያኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ መጣ ከእርሱ ጋርም ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስትና ዲያቆናት የምስር አገር ታላላቆችና ብዙ የክርስቲያን ወገኖች በአንድነት ሁነው በመዘመርና በማመስገን በታላቅ ክብር ሥጋውን ገንዘው ቀበሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ በርሱማ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የምስር አገር ኤጲስቆጶስ አባ ያዕቆብ፦ ይህም ተጋዳይ የሆነ አባት ገና በታናሽነቱ የምንኵስናን ልብስ ይለብስ ዘንድ ነፍሱ ወደደች። ከሀገሩም ወጥቶ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደና በአባ ዮሐንስ ሐጺር በዓት ውስጥ ኖረ በዚያም ጽኑዕ በሆነ ገድል ብዙ ዘመናት ተጠምዶ ኖረ።
❤ ከዚህም በኋላ በአባ ዮሐንስ ሐጺር ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊቀ ዲያቆናት አድርገው ሾሙት የደግነቱ፣ የትሩፋቱና የቅድስናውም ዜና ተሰማ። በእግዚአብሔርም ፈቃድ በምስር አገር ላይ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። በሹመቱ ወንበርም በተቀመጠ ጊዜ ጾምን ጸሎትን ጨመረ ስለ ሹመቱም ተጋድሎውንና አገልግሎቱን ከቀድሞው አበዛ እንጂ ቸልል አላለም። ሕዝቡንም ሁልጊዜ ያስተምራቸዋል መጻሕፍትንም ያነብላቸዋል ከእነርሱ ሥውር የሆነውንም ይተረጒምላቸዋል።
❤ ኃጢአትን በመሥራት የሚኖሩትን ይገሥጻቸዋል፤ በንስሐ እስከሚመለሱም ሥጋውንና ደሙን ከመቀበል ያርቃቸዋል። በጎ ተጋድሎውንም በፈጸመ ጊዜ ጥቂት ታመመ መንጋዎቹንም ጠርቶ በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ አዘዛቸው ደግሞ ካህናቱን ጠርቶ በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ ቸለል እንዳይሉ አዘዛቸው። ሁለተኛም "ሥጋውንና ደሙን ለማክበር በንጽሕና እግዚአብሔርን በመፍራት ሁናችሁ ካላገለገላችሁ ከደማችሁ ንጹሕ ነኝ" አላቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ፊቱንና ደረቱን በመስቀል ምልክት አማተበ እጆቹንም ዘረጋ ዐይኖቹንም ራሱ ከደነና ጳጒሜን 5 ቀን በሰላም ዐረፈ በአማሩ ልብሶችም ገነዙት ታላቅ ልቅሶንም አልቅሰው በክብር በምስጋና በማወደስ ቀበሩት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ያዕቆብ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጳጒሜን 5 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለበርሱማ ትርሲተ ዓለም ዘገደፈ። እስከ ኢያጥረየ አሐደ ዐጽፈ። ወዲበ ዝኒ ወሰከ ፃማ ተጋድሎ ትሩፈ። ከመ ያጽምዕ አመ ደኃሪ ምስለ ቅዱሳን ምዕራፈ። ማዕከለ ሥጋሁ ወምድር ኢገብራ መንጸፈ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጳጒሜን 5።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ላዕለ ተኵላ ወከይሲ ትፄዐን። ወትከይድ አንበሳ ወከይሴ። እስመ ብየ ተወከለ አድኅኖ"። መዝ 90፥13-14። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥32-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥1-17 ወይም ማር16፥15-19። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የነቢዩ ቅዱስ አሞጽና የአባ በርሱማ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጳጒሜን ፭ (5) ቀን።
❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ለሆነው ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ አሞጽ ለዕረፍት በዓልና እናትና አባቱ የተውለትን ንብረት በመተው ከዓለም ለወጣ (ወደ ገዳም ለገባ) ከልብስ ተራቁቶ ለሚኖር በጸሎቱ ታላቁን አስፈሪ ዘንዶ ለማዳ እንስሳ ላደረገ ለታላቁ አባት ለብርቱ ልጅ አባ በርሱማ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን፡፡ በተጨማሪ በዚች ቀንከሚታሰቡ፦ ከንጽሕ ከድግል አባት ከምስር አገር ኤጲስቆጶስ ከአባ ያዕቆብ ዕረፍትና ከታላቁ አባት ከአባ መግደር ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ይደርብን።
+ + +
❤ "ሰአሉ ለነ ነቢያት ስኩራነ መንፈስ ምሉኣን ሞገስ አቅርንተ ሥሉስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ የሥላሴ ነጋሪቶች (ዐዋጅ፡ነጋሪዎች) የምትኾኑ ክብርን የተመላችኊ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኛችኊ ነቢያት ለምኑልን ለእኛ አማልዱን። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ላይ።
❤ ነቢዩ ቅዱስ አሞጽ፦ ይህም ዕውነተኛ ነቢይ በእስራኤል ነገሥታት በኢዮአስና በኦዝያ ዘመን አስተማረ የእስራኤልንም ልጆች የእስራኤልንና የይሁዳንም ነገሥታት ይገሥጻቸው ነበር።
❤ ስለ ክብር ባለቤት ስለ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራ ስለመቀበሉ በዚያችም ቀን ስለ ፀሐይ መጨለም ከዚያም በኋላ እስራኤልን ስለሚደርስባቸው መከራ ኀዘን ልቅሶ ረድኤትም እንደሚአጡ የእግዚአብሔርንም ቃል መስማትን ከማጣት የተነሣ እንደሚራቡና እንደ ሚጠሙ። በሀገሩ ሁሉ በአሕዛብም መካከል እንደሚበተኑ አሕዛብም እንደ አጃ ሸክሽከው እንደሚአጓልቧቸው ትንቢትን ተናገረ ትንቢቱም በላያቸው ተፈጸመ።
❤ ስለኃጢአታቸውና ስለ ክፉ ሥራቸው ስለ ዘለፋቸው እነርሱ እንደ ገደሉት ተናገረ። የትንቢቱም ዘመን ከጌታችን ሥጋዌ በፊት በስምንት መቶ ዓመት ነው። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቅ ነቢይ በቅዱስ አሞጽ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ አባ በርሱማ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ በምስር አገር እጅግ ባለጸጎች ነበሩ እነርሱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ መጻተኞችንም በፍቅር የሚቀበሏቸው በእግዚአብሔርም በሕጉ ሁሉ ጸንተው የሚኖሩ ናቸው።
❤ ይህን ቡሩክ በርሱማን በወለዱት ጊዜ በፈሪሀ እግዚአብሔር የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትንም ሁሉ በማስተማር አሳደጉት። ከዚህም በኋላ ወላጆቹ አረፉ የእናቱም ወንድም ወላጆቹ የተውለትን ገንዘብ ሁሉንም ወሰደ አባ በርሱማም አባትና እናቱ የተውለትን ገንዘብ የእናቱ ወንድም እንደ ወሰደ አይቶ የዓለምን ኃላፊነት አሰበ። እንዲህም አለ "መድኃኒታችን "ነፍሱን ሊያድን የሚወድ ይጣላት ስለእኔም ሰውነቱን የጣላት ያገኛታል" ብሏል"። "ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን በሰጠ ነበር። የሰው ልጅ በአባቱ ጌትነት ከመላእክቶቹ ጋር ይመጣ ዘንድ አለውና ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ይከፍለዋል"።
❤ ይህንንም ብሎ ከዓለም ወጣ በበጋ ቃጠሎ፣ በክረምት ቅዝቃዜ ልብስ ሳይለብስ በአምስት ኮረብታዎች ላይ ኖረ። ወገቡንም በማቅ መታጠቂያ ይታጠቃል በልቡም እንዲህ ይላል "በርሱማ ሆይ በሚያስፈራ ዕውነተኛ ፈራጅ ፊት ትቆም ዘንድ አለህ እኮን"። ሁልጊዜም በጾም በጸሎት በስግደት በቀንና በሌሊት ይተጋ ነበር። በሚመገቡም ጊዜ በውኃ የራሰ ደረቅ ቂጣ ይመገባል ቆዳውም ከአጥንቱ ጋር ተጣበቀ።
❤ ከዚያም ቦታ ሊሸሽ ወደደ ከንቱ የሆነ የሰውን ምስጋና ፈርቷልና በምስር ወዳለት የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተ ክርስቲያን ደረሰ በዚያም በጾም በጸሎት በስጊድ እየተጋደለ ሃያ አምስት ዓመት ኖረ። በዚያችም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በዋሻ ውስጥ ታላቅ ዘንዶ አለ ዘንዶውንም ከመፍራት የተነሣ ሰው መብራትን ማብራት የማይችል ነው። እግዚአብሔርም የዚህን ቅዱስ የአባ በርሱማን ደግነቱን ሊገልጥና በእጆቹም ድንቆች ተአምራትን ለማድረግ በወደደ ጊዜ አባ በርሱማ ወደዚያች ዋሻ ገባ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ብሎ ጸለየ "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እባቡን ጊንጡን እንረግጥ ዘንድ በጠላት ኃይል ላይ ሁሉ ሥልጣንን የሰጠኸን አንተ ነህ። አሁንም በዚች ዋሻ ውስጥ በሚኖር ከይሲ ላይ ታሠለጥነኝ ዘንድ እለምንሃለሁ ላንተም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ"።
❤ ከዚህም በኋላ ራሱን በመስቀል ምልክት አማተበ እንዲህም እያለ ዘመረ "በተኲላና በእባብ ላይ ትጫማለህ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ"። ከዚህም በኋላ ያንን ዘንዶ በእጁ ይዞ እንዲህ አለው "ከእንግዲህ ገራም ሁን ታጠፋ ዘንድ ሥልጣን አይኑርህ ኃይልም ቢሆን በማንም ላይ ከሰው ወገን በአንዱ ላይ ክፉ ሥራ አታደርግ የሚሉህን ሰምተህ የምትታዘዝ ሁን እንጂ" በዚያን ጊዜም አንበሶች ለነቢዩ ዳንኤል እንደተገዙ ያ ዘንዶ ከአባ በርሱማ እግሮች በታች ተገዢ ሆነ።
❤ ከዚህም በኋላ አባ በርሱማ በመራብ በመጠማት ተጋድሎውን ጨመረ በየሁለት ቀን፣ በየሦስት ቀን፣ በየሰባት ቀን እያከፈለ ብርሃን በላዩ እስቲወጣ ያለ ማቋረጥ የሚጾም ሆነ። ለጸሎት በሚቆም ጊዜ ከይሲው ከርሱ ይርቃል በሚቀመጥም ጊዜ ሲጠራው ወደርሱ ይመጣል።
❤ በዚችም ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የውኃ ጒድጓድ አለች ወደርሷ በመውረድ ሁል ጊዜ ከማታ እስከ ንጋት ከውስጧ ገብቶ ያድራል በክረምትም በበጋም እንደዚህ ያደርጋል መላዋን ሌሊትም በውስጥዋ እየጸለየ ያድራል። የሚመገበውም የደረቀና የሻገተ ቂጣ ሲሆን የሚጠጣውም የከረፋ ውኃ ነው።
❤ የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን አዘውትሮ ያነባል ይልቁንም የዳዊትን መዝሙር አባቶችም ሥጋቸውን ለማድከም ያደረጓቸውን ትኀርምቶች በማንበብ ስለዚህ ትኀርምትን ንጽሕናን ወደደ ለሰዎችም እንዲህ እያለ ጠቃሚ ሥራዎችን ያስተምራል "ያለ ልብ ንጽሕና በቀር አንዱ እንኳን የእግዚአብሔር መንግሥት ማየት አይችልም ኃጢአት ሁሉ ከንስሓ በኋላ ይሠረያልና"። ለክርስቲያን ወገኖችም እንዲህ ያስተምራቸዋል ከእግዚአብሔርም ተአምራት የማድረግ ሀብት ተሰጠው ከገድሉም ለሰው የገለጥነው ጥቂቱን ነው።
❤ የዚህም አባት አርአያው የሚያምር መልኩም በብርሃን ያሸበረቀ ገጽታው ደስ የሚል ነው። ጥሪት በማጣቱም ደስ ይልዋልና። ከዓለማዊ ልብስ የተራቆተ ዓለምን ከማግኘትም የራቀ ነው። ቀድሞ ከቤቱ ከወጣ ጀምሮ የቀይ ግምጃ ጨርቅ በማገልደም ሥጋውን ይሸፍናል በክረምትም በበጋም የቀን ሐሩርን የሌሊት ቊርን ይታገሣል በጐኑና በምድር መካከል ምንጣፍ አላደረገም ወደ ሕይወት አገር ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት የሚያደርስ ተጋድሎን እንደዚህ ተጋደለ።
❤ ከክፉዎች ሰዎችና ከክፉዎች አጋንንት ብዙ ጊዜ ኀዘን ፈተና አግኝቶታል ከዚህም ሁሉ ጋር በዚህ ጭንቅ በሆነ ሥራ የረዳው እግዘሐአብሔርን ፈጽሞ ያመሰግነዋል። ይህንን በጎ የገድል ጒዞ በተጓዘ ጊዜ ሰዎት ዜናውን ሰሙ ሽማግሎችም ጐልማሶችም ከእነርሱ በጽነት የተሰነካከለ ወይም ከጠላት ሰይጣን ፈተና ያገኘው ወይም የመንፈስ ደዌ ያገኘው ሁሉ መሪና አጽናኝ ይሆናቸው ዘንድ ተመኝተውት ፈለጉት ከእርሱ ፈውስ ያገኙ ዘንድ መጡ።
❤ ይህ የከበረ አባ በርሱማ በዚህ የጽና ተጋድሎ ሠላሳ ዓመታትን በፈጸመ ጊዜ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ከዚህ በኋላ ጳጒሜን አምስት በዚች ቀን በሺህ ሠላሳ ሦስት ዓመተ ሰማዕታት በሰላም በፍቅር አንድነት አረፈ።
❤ ከዚህ አስቀድሞ ደቀ መዝሙሩ ቀሲስ ዮሐንስ በልቡ እንዲህ አለ "ከአባታችን በ
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 18:23-ፍ፡ም፡ "ወበእንተዝ ትመስል መንግሥተ ሰማያት" - "ስለዚህ፥መንግሥተ፡ሰማያት፡ባሮቹን፡ሊቈጣጠር፡የወደደን፡ንጉሥ፡ትመስላለች። መቈጣጠርም፡በጀመረ፡ጊዜ፥እልፍ፡መክሊት፡ዕዳ፡ያለበትን፡አንድ፡ሰው፡ወደ፡እርሱ፡አመጡ። የሚከፍለውም፡ቢያጣ፥እርሱና፡ሚስቱ፡ልጆቹም፡ያለውም፡ዅሉ፡እንዲሸጥና፡ዕዳው፡እንዲከፈል፡ጌታው፡አዘዘ። ስለዚህ፥ባሪያው፡ወድቆ፡ሰገደለትና፦ጌታ፡ሆይ፥ታገሠኝ፥ሁሉንም፡እከፍልሃለሁ፡አለው። የዚያም፡ባሪያ፡ጌታ፡ዐዘነለትና፡ለቀቀው፥ዕዳውንም፡ተወለት። ነገር፡ግን፥ያ፡ባሪያ፡ወጥቶ፡ከባልንጀራዎቹ፡ከባሮቹ፡መቶ፡ዲናር፡ዕዳ፡ያለበትን፡አንዱን፡አገኘና፦ዕዳህን፡ክፈለኝ፡ብሎ፡ያዘና፡ዐነቀው። ስለዚህ፥ባልንጀራው፡ባሪያ፡ወድቆ፦ታገሠኝ፥ሁሉንም፡እከፍልሃለሁ፡ብሎ፡ለመነው። እርሱም፡አልወደደም፥ግን፡ሄዶ፡ዕዳውን፡እስኪከፍል፡ድረስ፡በወህኒ፡አኖረው። ባልንጀራዎቹ፡የሆኑ፡ባሪያዎችም፡ያደረገውን፡አይተው፡እጅግ፡ዐዘኑ፥መጥተውም፡የሆነውን፡ሁሉ፡ለጌታቸው፡ገለጡ። ከዚያ፡ወዲያ፡ጌታው፡ጠርቶ፦አንተ፡ክፉ፡ባሪያ፥ስለ፡ለመንኸኝ፡ያን፡ዕዳ፡ሁሉ፡ተውኹልህ፤ እኔ፡እንደ፡ማርኩህ፡ባልንጀራህ፡የሆነውን፡ያን፡ባሪያ፡ልትምረው፡ለአንተስ፡አይገባህምን? አለው። ጌታውም፡ተቈጣና፡ዕዳውን፡ሁሉ፡እስኪከፍለው፡ድረስ፡ለሚሣቅዩት፡አሳልፎ፡ሰጠው። ከእናንተ፡እያንዳንዱ፡ወንድሙን፡ከልቡ፡ይቅር፡ካላለ፥እንዲሁ፡ደግሞ፡የሰማዩ፡አባቴ፡ያደርግባችኋል።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
04/13/2014 ዓ.ም (፬/፲፫/፳፻፲፬ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ክላእ ልሳነከ እምእኩይ።
ወከናፍሪከኒ ከመ ኢይንብባ ጕሕሉተ።
ተገሐሥ እምእኩይ ወግበር ሠናየ መዝ.33÷13
🕯 ትርጉም
አንደበትህን ከክፉ ከልክል።
ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 17:22-31 "ወይቤሎሙ ለአርዳዒሁ" - "ለደቀ፡መዛሙርቱም፡እንዲህ፡አለ፦ከሰው፡ልጅ፡ቀኖች፡አንዱን፡ልታዩ፡የምትመኙበት፡ወራት፡ይመጣል፡አታዩትምም። እነርሱም፦እንሆ፥በዚህ፥ወይም፦እንሆ፥በዚያ፡ይሏችኋል፤ አትሂዱ፡አትከተሏቸውም። መብረቅ፡በርቆ፡ከሰማይ፡በታች፡ካለ፡ካንድ፡አገር፡ከሰማይ፡በታች፡ወዳለው፡ወደ፡ሌላ፡አገር፡እንደሚያበራ፥የሰው፡ልጅ፡በቀኑ፡እንዲህ፡ይሆናል። አስቀድሞ፡ግን፡ብዙ፡መከራ፡እንዲቀበል፥ከዚህም፡ትውልድ፡እንዲጣል፡ይገባዋል።በኖኅ፡ዘመንም፡እንደ፡ሆነ፥በሰው፡ልጅ፡ዘመን፡ደግሞ፡እንዲሁ፡ይሆናል። ኖኅ፡ወደ፡መርከብ፡እስከገባበት፡ቀን፡ድረስ፥ይበሉና፡ይጠጡ፡ያገቡና፡ይጋቡም፡ነበር፥የጥፋት፡ውሃም፡መጣ፡ሁሉንም፡አጠፋ። እንዲሁ፡በሎጥ፡ዘመን፡እንደ፡ሆነ፤ይበሉ፡ይጠጡም፡ይገዙም፡ይሸጡም፡ይተክሉም፡ቤትም፡ይሠሩ፡ነበር፤ ሎጥ፡ከሰዶም፡በወጣበት፡ቀን፡ግን፡ከሰማይ፡እሳትና፡ዲን፡ዘነበ፡ሁሉንም፡አጠፋ። የሰው፡ልጅ፡በሚገለጥበት፡ቀን፡እንዲሁ፡ይሆናል። በዚያም፡ቀን፡በሰገነት፡ያለ፡በቤቱ፡ያለውን፡ዕቃ፡ሊወስድ፡አይውረድ፥እንዲሁም፡በእርሻ፡ያለ፡ወደ፡ኋላው፡አይመለስ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
04/13/2014 ዓ.ም (፬/፲፫/፳፻፲፬ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእግዚአብሔር ምድር በምልዓ።
ዓለምኒ ወኲሎሙ እለ ይነብሩ ውስቴታ።
ወውእቱ በባሕር ሣረራ። መዝ.23÷1
🕯 ትርጉም
ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት።
ዓለምም በእርሷም የሚኖሩ ዅሉ።
እርሱ በባሕሮች መሥርቷታልና።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
